cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Ortholic + Cathodox = "Christian" = Catholic + Orthodox

Catholic & Orthodox, we are one in the name of GOD!

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
146
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ስለምን ማርያም ብለው አወጡላት ቢሉ:እነሆ በዚ አለም ከሚመገቡት ሁሉ ምግብ ለአፍ የሚጥም ለልብ የሚመጥን "ማር" ነው:በገነትም በህይወት የተዘጋጁ ጻድቃን ቅዱሳን "ያም" የሚባል ምግብ አላቸው :: ከዚ ሁሉ የበለጥሽ የከበርሽ ነሽ ሲሉ ስለዚህ "ማርያም" ብለው አወጡላት::የእመቤታችን ማርያም ስም ተነቦ ሳይተረጎም ይቀር ዘንድ አይገባምና:- ↪""ማ"" ማለት ማህደረ መለኮት: ↪""ር"" ማለት ርግብየ ይቤላ: ↪""ያ"" ማለት ያንቀዓዱ ኃቤኪ ኩሉ ፍጥረት: ↪""ም"" ማለት ምስሃል ወምስጋድ ወምስትሥራየ ኃጥያት ማለት ነው:: አንድም "ማርያም" ማለት ልዩ ከጣዖት:ክብርት እምፍጥረታት:ንጽህት እምሃጥያት:መልክ ከደም ግባት የተሰጣት ማለት ነው:ዳግመኛም "ማርያም" ማለት ተፈስሂ ቤተ ይሁዳ ወተሃሠዪ ቤተ እስራኤል ማለት ነው:: አንድም "ማርያም" ማለት መርህ ለመንግስተ ሰማያት ማለት ነው:ይህስ እንዴት ነው ቢሉ:እነሆ ዛሬ በዚህ አለም ለዕውር መሪ በትር እንዲሰጡት ሁሉ እርሱአም በፍቅሩአ: በጣዕመ ፍቅሩአ የሰውን ሁሉ ኃጥያት:ክፋት ፍቃ ከልጁአ ከወዳጁአ አስታርቃ ከገሃነመ እሳት አውጥታ መንግስተ ሰማያት የምታስገባ ስለሆነች ስለዚህ መርህ ለመንግስተ ሰማያት አሉአት::አንድም ማርያም ማለት ሰረገላ ፀሃይ ማለት ነው:አንድም ማርያም ማለት ተላኪተ እግዚአብሄር ወሰብእ ማለት ነው:አንድም ማርያም ማለት ውብህት(ስጥውት) ማለት ነው::
Показати все...
#ግንቦት1ልደታ ለማርያም ማለት⛪ #ጴጥርቃ_እና_ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር: #እነዚህም በእግዚአብሄር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ:እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የበቁ ባለጸጎች ነበሩ:ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ:አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን: #አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት:እርሱአም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚ ያለ ነገር እንኩአንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት: #እርሱዋም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም:ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው:: #እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው:ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሄር በምህረቱ አይቱአቹአል በሳህሉ መግቡአችሁአል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዱአ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹ የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው: #እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሱአም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች: #ከዛም ፀንሳ በ9 ወሩአ ሴት ልጅ ወለደች:ስሙአንም ሄሜን ብለው አወጡላት:ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኑአም ደርዲ ብለው ስም አወጡላት:ደርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት:ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት;ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት:ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት:ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደውን ሃናን ወለደች:: #ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆተረላቸውምና አልተፃፈም:ይህቺም ሃና በስራት በቅጣት አደገች:ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው(መጽሃፍ ቅዱስ ይገልጸዋል) ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቡአት:: #እነዚህ ቅዱሳን እያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ:ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ: #ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ:እያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው አትጣለኝ:አትናቀኝ:ፀሎተን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ:ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:ሃናም በበኩሉአ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው:ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች: #እንዲ ብለው ስይዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቹአ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኅኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች: #እንዲ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን:ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስለት ገቡ:: ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማላቹ ስእለታችሁን ይቀበልላቹ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላቹ ብሎ አሳረገላቸው: #ከዚያም በሁአላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም እለቱን ራእይ አይተው ነገር አግንተው አደሩ:ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት: #ወፍ የተባለው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:ነጭነቱ ንጽሃ ባህሪው ነው:ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ:የኢያቄምን ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው:7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህሪው:ምልአቱ:ስፍሃቱ:ርቀቱ:ልእልናው:ዕበዩ መንግስቱ ናቸው:ሃናም እኔም አየሁ አለችው:ምን አየሽ ቢላት:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው:: #ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት:ነጭነቱአ ንጽህናዋ:ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቱአ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሱአ ነው:ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው:: #እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን:ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም:ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7 ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ: #ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ዓለሙ ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሱአን ፀጉር የማያህል ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአቹሃል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ተፀነሰች(በኦሪት ስርአት እሁድ ዕለት ባል እና ሚስት መገናኘት ልማድ ነበርና): #እመቤታችን የተፀነሰች ዕለት አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ:ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት:የሃናም የአጎቱአ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቹአ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት: #እርሱአም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሃየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት:አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ህፃን ሰማይ ምድርን:እመቅ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኑአት ሰማሁአቸው እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሱአ ናት አላቸው በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ:: ↪""እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች::"" እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም የተወለደችበት እለት በአባት እናቱአ ቤት ፍስሃ ደስታ ተደረገበት ቤቱንም ብርሃን መላው በስምንተኛውም ቀን ""ማርያም"" ብለው አወጡላት::
Показати все...
💙👰🏽💟👸🏽🛐 Enkuan aderesachu Beteseb😍 ye Lideta Maryam bereket yderbn😇
Показати все...
🌹🌱🕊🌹 #ማረን 🌹🌱🕊🌹 ማረን (3×) ጌታ ሆይ ማረን ምህረትህ ያሻናል ፈጥነህ ድረስልን ማረን(3×) ጌታ ሆይ ማረን ልጆህ ነንና ምህረትህ ላክልን(2×) ትዛዝህን ትተን ከመንገድህ ወጥተን በመረጥነው መንገድ ኮብልለን ተጉዘን ዛሬ ግን ቆመናል ዙርያችን ጨልሞ / ሀጥያት በወለደው ህይወታችን ታሞ/2× የኛ ከንቱ ምኞት ተራ ፍልስፍና ለመሆን ስንሞክር ጠቢባን ገናና ሄደናል ጌታችን ወደ ሞት ጎዳና / ፈጥነህ ድረስልን ጌታ ሆይ ቶሎ ና /2× የበረከት አምላክ ምድራችን ባርከሀል ከዘመናት ጥፋት እኛን ታድገሀል በአመጽ በትቢት ተፈታትነንሀል / ይቅር በለን ጌታ እጅግ በድለንሀል /2× ህዝብህን እየመራህ በድል አሻግረሀል የጭንቀት የፍርሀት ሰንሰለት ሰብረሀል ከባርነት ህይወት ነፃ አውጥተሀል ዛሬም ጌታ ማረን ሁሉም ይቻልሀል መፍትሔው አንተ ነህ ውዱ አምላካችን ጩኸታችን ስማ እሩህሩህ ጌታችን አንተኑ ነህና ፅኑ አለታችን ፈጥነህ ድረስልን መሀሪ ጌታችን http://t.me/YariedDessale
Показати все...
ጌታዬ ሁለመናዬ።

ስለ አንዲት፡ ቅድስት፡ ሐዋርያዊትና ኩላዊት ቤተ-ክርስቲያን ምንነትና ምን እንደምታስተምር በሚገባ ለማወቅ፣ በአጠቃላይም ስለ ቤተ/ያን ታሪክ፤ ሰለ ቅዱሳን-ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ፣ ስለመላዕክት፣ የር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስን አዳዲስ ት/ቶች፤ መንፈሳዊ ፊልሞች ሁሉ በቀላሉ ያገኙበታል፡፡ #ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡ “አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

“አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። (1ኛ ቆሮ 15:20-22) http://t.me/YariedDessale
Показати все...
ክርሰቶሰ ተንሥኦ እሙታን! በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን! አሰሮ ለሰይጣን ! አግዐዞ ለአዳም ! ሰላም ! እምይዕዜሰ! ኮነ ! ፍሥሐ ወሳላም ! "'ተሻግረናል"' ☦️
Показати все...
#በትኩረት_ያንብቡት!! 🌱🌱🌾🌾🌾🌾🌾🌹🌹🕊🕊🕊🕊🌹🕊🌱 ቀዳም ስዑር ማለት ምን ማለት ነው? የቀዳም ስዑር ቄጤማ ትርጉም?? በጭንቅላት የማሰሩ ትርጉምስ ለምን ይሆን?? . . . . 🌱🌱🌾🌾🌾🌾🌾🌹🌹🕊🕊🕊🕊🌹🕊🌱 አብይ ጾም ብዙ ጊዜ በበጋ መጨረሻ እና በፀደይ መጀመርያ ወቅቶች ላይ የሚያርፍ የቤተክርስቲያን ስርአተ አምልኮ የተከተለ ታላቅ ጾማችን ነው፡፡ በዚህ በአብይ ጾም ውስጥ ከሚደረጉት የስርአተ አምልኮ ክፍሎች አንዱ የሆነው "ቀዳም ስዑር" የስርአተ አምልኮ ክዋኔ ነው፡፡ •በዚህ የስርአተ አምልኮ ክዋኔ መጀመሪያ ከስሙ ትርጓሜ ስንነሳ፡፡ ቀዳም ስዑር ማለት የተሻረ ቅዳሜ ማለት ነው ይህንን ስያሜ የሚገኘው ደግሞ ክርስቶስ በዚህ እለት ሲኦል ድረስ ወርዶ የሰይጣን የሞት መግዣ በትር ቀምቶ በመስበር ለሲኦሎች እንኳን ሳይቀር ሀዋርያው ጳውሎስ እንደሚለው "ወንጌል የሰበከበት ቀን ስለሆነና ሞት የተሻረልን ቀን ስለሆነ ክርስቶስ ከሞተ በኃላ ስራውን ሳያቋርጥ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ነፃ ያወጣበትን ቀን እንደሆነ ስለምናስብ ነው፡፡ ይህ ቀን የትንሳኤን ተስፋ የምናከብርበት ነው፡፡ በዚህ ቀን ልክ አንደ ሆሳዕና ስርአተ አምልኮ እርጥብ እፅዋት በቤተ ክርስቲያን ከተባረከ በኃላ ይታደላል፡፡ ይህም ስርአተ አምልኮውን ልዩ እና ውብ የሚያደርገው ክፍል ነው፡፡ •በዚህ ስርአተ አምልኮ እርጥብ ቄጤማ የሚገኘው በበጋ መጨረሻ እንዲሁም በፀደይ ወራት መግቢያ አህፍሶ/ ጎሚት አበባ የምትበቅልበት ምልክት ነው፡፡ ምክንያቱም በዚህ የወቅት ልዩነቶች መካከል የወቅት መለያ የሆነው አጭር ዝናብ ይጥላል በዚህም ምክንያት በተለይ የገጠር ክፍሎች ላይ የሚበቅለው ቄጤማ ወይም በሌላ ስሙ ግጫ ብለን የምንጠቅሰው የሳር አይነት ይበቅላል፡፡ እንደየ ቦታው የዚህ ግጫ/ቄጤማ አበቃቀል ወይም ዝርያ ቢለያይም፡፡ በብዙ ቦታ የሚበቅለው እና ብዙዎች የሚጠቀሙበት የቄጤማ አይነት በአንድ በኩል ባለው ጎን ላይ ስለት ያለው ጫፍ መሆኑ እና የክርስቶስን መወጋት የሚያሳይ ነው፡፡ ይህንን ለስርአተ አምልኮ እንጠቀምበታለን፡፡ አጠቃቀሙ ልክ እንደ ዑደተ ሆሳዕና አይነት ዑደት ከተደረገ በኃላ ይህንን ቄጤማ ተባርኮ ከቀዳም ስዑር ቅዳሴ በኃላ ለምእመናኑ ይሰጣል፡፡ ይህንን የቀዳም ስዑር ቄጤማ ወይም ግጫ ምእመናኖች ጭንቅላታቸው ላይ በማሰር ለበረከት ይጠቀሙበታል፡፡ በጭንቅላት የማሰሩ ትርጉም "ክርስቶስ በተሰቀለበት ወቅት የእሾህ አክሊል ራሱ ላይ እንደተደረገ እና ክርስቶስ ባሳለፈው ስቃይ የትንሳኤ ብርሀን ተስፋ እንደሆነ እንዲሁም ይህ የክርስቶስን ስቃይ በማሰብ በህይወታችን ያለውን መስቀል በደስታ በመቀበል ወደ ትንሳኤ ተስፋ የሚያደርሰን የልጁን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ተካፋይ እንደሆንን የምናስብበት ነው፡፡ •ይህንን ግጫ/ቄጤማ ተጠቅሞ የመስቀል ምልክት ያላቸው ጌጦች ልክ እንደ ሆሳእና እለት ዘንባባ ሰርተው በግንባራቸው ላይ ያደርጋሉ፡፡ ይህም የመስቀሉ መስራት ለእኛ ክብራችን እና ኩራታችን እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ ሌላኛው የማክፈል የፆም ስነስርአት የሚጀመርበት ቀን ነው፡፡ እንደ ግዕዝ ስርአት በዚህ እለት ምዕመናን በካህናት ንፁህ ውሀ እና ህብስት ይዘው በመምጣት በመባረክ ከካህናት ጋር ይከፋፈላሉ፡፡ ለካህናት ቤትም እሱን በስጦታ መልክ ያቀርባሉ እሱ ደግሞ ከእያንዳንዱ አንድ እጅ በመውሰድ ለቤታቸው በረከት እንዲሁም ቤት ውስጥ ላሉት ምዕመናን ያደርሳሉ ቄጤማውም ከበረከቱ ጋር ባለው ትስስር እንደ ምስጢር ያለ ነው (sacrmental). •በግዕዝ ስርአተ አምልኮ መሠረት ቀዳም ስዑር ለምለም ቄጤማ ሲሰጥ ከተስፋ ጋር የተያያዘ ምልክት አለው ይህ የትንሳኤ ተስፋ ምልክት ከተለያዩ ከመፅሀፍ ቅዱስ አንፃር ስናየው ኖህ በመርከብ ውስጥ እያለ እርግቧን በላከበት ወቅት አፏ ላይ የወይራ ቅጠል ይዛ በመምጣት የጥፋት ውሀን መድረቅ እና ከዛ መውጣት አንደሚችሉ የሚያሳይ ልምላሜ ማምጣቷን ማሰብ እንችላለን፡፡ በሌላኛው ጎኑ ደግሞ ክርስቶስ በሞቱ ስራውን እንዳላቋረጠ ዘለአለማዊ ክህነቱን ከሞቱ ጋር እንዳላከተመ የምናስብበትም እለት ነው፡፡ በዚህም ይህ እውነተኛ የሆነውን የትንሳኤ ተስፋ ክርስቶስ ከአብ ዘንድ ተልኮ ልክ እንደ እርግቧ ሰላምን ሊሰጠን እንደሚችል ይህንን የምንመሰክርበት እለት ነው፡፡ በሌላ ጎን ይህንን ግጫ/ቄጤማ ወደ ምእመናኑ ቤት ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮች በታላቅ ክብር ከፀበል እና ከተለያዩ ቡራኬዎች ጋር ያደርሳሉ በዚህም ወቅት የተለያዩ ምዕመናን ቤት ይጎበኛሉ፡፡ ይህም ቤተክርስቲያን መምጣት ላልቻሉ ምእመናን የትንሳኤው ተስፋ በረከት ሁሌም ከእነሱ እንደማይለይ እና ከቤተክርስቲያን ያላቸውን ህብረት የሚያሳይ የስርአተ አምልኮ ክፍል ነው፡፡ በተለይ በዚህ የቀዳም ስዑር ስርአተ አምልኮ ቄጤማ/ግጫ ተክል ልክ እንደ ስርአተ ሆሳእና የበአሉ ድምቀት እና ትልቅ ትርጉም ያለው የክርስቲያኖች መገለጫ (symbolic representation) ከምንላቸው ነገሮች መካከል አንዱ ነው፡፡ በምልክት ወንጌሉን የምንገልፅባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ነው፡፡ በተወዳጁ በወጣት ሴሚናሪና #ዘማሪ_ራዕይ_ሳሙኤል (ጆሲ ደብረሰላም) የተዘጋጀ፡፡ እግዚአብሔር መንገድህን እና ህይወትሀን የቀና ያድርግልን፤ ፍቅር ከዚህም በላይ ከብዝቶና ጨማምሮ ይስጥሀ ወንደም ራዕይ ሳሙኤል!! ከዚህ በታች ያላውን ሊንክ በመጫንና #Join በማድረግ በቴሌግራም ቤተሰብ ይሁኑን፡፡ 👇👇👇👇👇 http://t.me/YariedDessale 👆👆👆👆👆👆👆 The Universal Catholic Church Teaching Channel.
Показати все...
ጌታዬ ሁለመናዬ።

ስለ አንዲት፡ ቅድስት፡ ሐዋርያዊትና ኩላዊት ቤተ-ክርስቲያን ምንነትና ምን እንደምታስተምር በሚገባ ለማወቅ፣ በአጠቃላይም ስለ ቤተ/ያን ታሪክ፤ ሰለ ቅዱሳን-ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ፣ ስለመላዕክት፣ የር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስን አዳዲስ ት/ቶች፤ መንፈሳዊ ፊልሞች ሁሉ በቀላሉ ያገኙበታል፡፡ #ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡ “አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

😭የተከፈለልን ዋጋ እንዲህ በቀላሉ የሚነገር አይደለም፡፡ 🎤እስኪ ሁላችንም #በአንድነት እየሱሴ እወድሀለሁ (2X) አባብዬ አፈቅርሀለሁ (2X) __________________________________________________ @catholicb
Показати все...
Sam~ Kip _2.gif3.62 KB