330
Підписники
-224 години
-87 днів
-1730 днів
Архів дописів
330
🔰 How To Root Your Android Device With Just One Click! 🔰
1. Install Kingo Android Root.
2. Enable USB Debugging (Setting > About > Developer Options)
3. Run The Kingo Android Root And Connect You Phone To Your Computer (Via USB).
4. After A Moment, The Former
Will Show A Connection To The Latter.
5. Click Root And Wait For Processing To Be Finish. All The Process Will All Take About Two Minutes.
🔶 If you Don't Like The Change You Can Go All The Way Back And Click Unroot 🔷
@simatechnology
330
10 ጠቃሚ የሆኑ አፖችን እነሆ!
@simatechnology
📍 #1 ትሩኮለር/True Caller/ ይህ አፕ ማንኛውም ሰዉ ወደ ሞባይላችን ሲደውል በሶሻል ሚድያ የተመዘገበው ስሙ ያሳየናል: ማለትም ስልኩ በሞባይላችን ባንመዘግበዉም የደዋዪ ስልክ ስም ለማወቅ ይጠቅመናል!
📍 #2 ሴክሪቲ 360 /360 Security/ ይህ ጸረ ቫይረስ ስልካችንን ከቫይረስ፣ ማል ዌር እና ትሮጃኖች በመከላከል ረገድ የተዋጣለት አፕ ነው። በዚህም ከስልካችን ቀርፋፋነት እስከ ሙሉ የኦፕሬቲንግ ሲስተም ብልሽት የሚያደርሱ የአንድሮይድ ቫይረሶችን አስቀድሞ በመከላከል ስልካችንን ከችግር ይጠብቅልናል።
📍 #3 ዋይፋይማፕ/WiFi Map/ በሆቴሎች ወይም በሌሎች ስፍራዎች የምናገኛቸው አብዛኞቹ ዋይ ፋይ ኔትወርኮች በይለፍ ቃል (password) የተዘጉ ናቸው። ይህም ማለት የዋይ ፋዩ ፓስወርድ ከሌለን ዋይ ፋዩን ለመጠቀም አንችልም ማለት ነው። ይህ አፕሊኬሽን በአለማችን የሚገኙትን በሆ ፋዮች ሁሉንም በሚባል መልኩ ፓስወርዳቸውን በቀላሉ ይነግረናል። ከእኛ የሚጠበው አፑን ከጫንን በኋላ ከሚመጣልን የአለም ከርታ ላይ ኢትዮጵያን፤ ከዚያም የምንፈልገውን ከተማ መምረጥ ሲሆን በከተማው ውስጥ ያሉትን ዋይ ፋይ ኔትወርኮችና ፓስወርዳቸውን ያመጣልናል። ዋይ ፋይ ኔትወርክ በአቅራቢያችሁ ኖሮ ፓስወርድ ለገደባችሁ ሁሉ ቀላል መፍትሄ ነው።
📍 #4 ዊስትል ፎን ፋይንደር/Whistle Phone Finder/ ለመሆኑ ቤት ውስጥ ወይም ስራ ቦታ ስልክዎን ያስቀመጡበት ቦታ ጠፍቶዎት ያውቃል? የሚያውቅ ከሆነ ፍለጋውንና ከሌሎች ስልክ ተውሶ ወደራስ ስልክ ለመደወል የሚደረገውን ድካም በደንብ ያውቁታል። ይሄንን አፕሊኬሽን ስልክዎት ላይ አስቀድመው ከጫኑ, ስልክዎን ያስቀመጡበት ቦታ ሲጠፋዎት ከእርስዎ የሚጠበቀው ማፏጨት ብቻ ነው። የፉጨትዎ ድምጽ አፕሊኬሽኑን በማንቃት ስልክዎ የመጥሪያ ደወል እንዲያሰማ በማድረግ ስልኩን በቀላሉ በድምጹ ተመርተው እንዲያገኙት ይረዳዎታል።
📍 #5 ኔክስትዶር/NextDoor/ ይህ ሞባይል አፕሊኬሽን ከጎረቤቶቻቸን ለማዉራት የሚጠቅመን አፕ ነው ይህንን አፕ ተጠቅመን ከጎረበቶቻቸን ጋር መረጃ ለመለዋወጥ እርዳታ ለመፈለግና ተመሳሳይ ስራዎች ለማደረግ ይጠቅማል! ይህንን ስራ ለመስራት ኢንተርኔት አያስፈልገዎም::
📍 #6 ኢንስታፔፐር/Instapaper/ ይህ ገራሚ አፕ በሞባይላችን የምናገኛቸው መረጃዎች ሴቭ ለማድረግና በፈለግነው ጊዜ ለማንበብ ወይም ለመመለከት ይጠቅመናል
📍 #7 ዪቱዪብኪድስ/YoutubeKids/ ይህ አፕ የዪቱብ አፕ በጎግል በራሱ የተሰራ ሲሆነ ለልጆች ተብሎ የተሰራ አፕ ነው:: በዚህ አፕ ለልጆች የሚሆኑ ሙዚቃ የትምህርት መረጃዎች ቪድዮዎች ወዘተ ይገኛሉ! ከ18 አመት ለሆኑ ይህንን አፕ ብጨንላቸው ተመራጭነው::
📍 #8 ለርንሲፕላስፕላስ/Learn C++/ ይህ አፕ ሲፕላስፕላስ ለመማር ለሚፈልጉ በጣም ምርጥ አፕ ነው! በሞባይልዎ ሁነው ሲፕላስፕላስ በመማር የተሻለ ፕሮግራመር ይሁኑ::
📍 #9 IDM download manager በኮምፒውተራችን ፋይሎችን በፍጥነት ዳውንሎድ ለማድረግ የምንጠቀምበት IDM, በቅርቡ ደግሞ ለአንድሮይድ ስልኮች የሚያገለግል አፕ ለቋል። IDM የስልካችን ብሮውዘር ዳውንሎድ ለማድረግ የሚወስድበትን ጊዜ በእጅጉ በመቀነስ የምንፈልገውን ፍይል በአጭር ጊዜ ያወርድልናል።
📍 #10 ዲስክዲገር/DiskDigger/ ዲስክዲገር ከስልካችን በስህተት ያጠፋናቸውን ፎቶዎች፣ ሙዚቃዎች፣ ቪዲዮዎችና ሌሎች ፋይሎቻችንን የስልኩን ጥልቅ ዳታ ስቶሬጅ በማሰስ ይመልስልናል። በጣም አስፈላጊ ፍይሎቻችንን በስህተት ወይም በሌላ ሰው delete ከተደረጉብን ዲስክዲገር አፕ መፍትሄያችን ይሆናል ማለት ነው።
@simatechnology
330
💻 ብዙ ጊዜ Delete አልሆን ያሉ Folderዎችን ማለትም permission የሚጠይቁትን ለምሳሌ window old ፋይሎችን ከኮምፕዩተራችን ላይ እንዴት አድርገን እንደምናጠፋ እናያለን..
━━━━━━━━━━━━━━
@simatechnology
━━━━━━━━━━━━━━━
🔰Stepዎችን በመከተል ማስተካከል ትችላላቹ......
💠Step 1⃣
🔅Folder/File ጋር Right Click አድርገን Properties የሚለውን ይምረጡ።
💠Step 2⃣
🔅ከዛም Security የሚለው ላይ Advanced የሚለውን ይንኩት።
💠Step 3⃣
🔅 Administration ከሚለው አጠገብ Change የምትለዋን ይጫኑ።
💠Step 4⃣
🔅ከዛም Advanced የሚለውን ይመርጣሉ።
💠Step 5⃣
🔅ከዛም Find Now የሚለውን ተጭነው ከሚመጡት ዝርዝር ውስጥ የኮምፒውተርዎን User Name ይመርጡ።
💠Step 6⃣
🔅መቀየሩን ካረጋገጡ በኋላ ሳጥኖቹ ላይ ✅ ያድርጋሉ።
💠Step 7⃣
🔅Apply የሚለውን መምረጥ
💠Step 8⃣
🔅Messages box ያመጣል ከዛም yes ይበሉ።
💠Step 9⃣
🔅Permission ሰጥቶ ከጨረሰ በኋላ OK ይበሉት።
💠Step 1⃣0⃣
🔅OK ብለው ሁሉንም window ፕሮግራሞችን ይዝጉት።
💠Step 1⃣1⃣
🔅መጨረሻ ላይ file ላይ አድርገውት Shift + Del ይንኩት ሙሉውን ያጠፋዋል።
━━━━━━━━━━━━━━━
📢: @simatechnology
━━━━━━━━━━━━━━━
330
🔍 ዛሬ የኮምፒዩተሮች በተለይም የlaptop ኮምፒዩተሮች CPU ሲያሜ ላይ ነው የምናወራው፡፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
@simatechnology
❖አብዛኞቻችን በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ ያለን እውቀት ውስን ነው፡፡
ለምሳሌ Core i3, Core i5 እና Core i7 CPU አይነቶች ስናይ እላያቸው ላይ ባለው ቁጥር ብልጫ ብቻ እናወዳድራለን፡፡ ከዛሬ በኃላ ግን በትክክለኛው ስያሜ እንገመግማለን፡፡
❖በኮምፒዩተሮቻችን CPU ላይ የምናየው ስሞች እላያቸው ላይ ፊደላት ይገኛሉ፡፡ እነሱ ለምን ተቀመጡ? እንዲሁ በዘፈቀድ የተቀመጠ ፊደላት ናቸውን?
እነዚህ ፊደላት ዝም ብለው የተቀመጡ አይደሉም የራሳቸው የሆን ትርጉም አላቸው፡፡
🖱የኮምፒዩተሮቻችን CPU ስም እነዚህም ፊደላት ከያዘ፡
“K” – Unlocked፡- ያልተቆለፈ CPU ይህ ማለት በቀላሉ Overclocked (የCPU አቅም ከነበረበተት መጠን መጨመር ‹በቀጣይ ዘገባዎች ላይ እናየዋለን›) የሚደረግ CPU ናቸው፡፡ እላያቸው ላይ “K” የሚል ፊደል የሌለበት የCPU አይነቶች የOverclock የመደረግ ሁኔታ አምብዛም ነው፡፡
ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-8600K
“H” – High Performance Graphics: - እነዚህ CPU ለኮምፒዩተር ጨዋታዎች(Gaming) እና ፎቶ እና ቪዲዮ ለማቀናበር ይመረጣሉ ማለትም ብዙ ሀይል ተጠቀሚ እና የተሻለ አቅም ያላቸው CPU ናቸው።
“Q” – Quad Core:- አራት Core ወይም አንድን ስራ ለአራት አካላት የሚከፋፈል CPU ናቸው፡፡
🖱በዚህም መሰረት “HQ” ሚል ፊደላት ካሉ በጣም ውድ እና ምርጥ ከሚባሉት CPU አይነቶች ወስጥ አንዱ ነው፡፡
ምሳሌ፡ Intel® Core™ i7-7700HQ
”M” – Mobile CPU:- በተንቀሳቃሽ(Portable) ኮምፒዩተሮች ላይ የምናገኘው ሲሆን በቀላሉ ለመቀዝቀዝ ትንሽ ሀይል ይጠቀማል፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጊዜ እንዲተኙ(Sleep mode capability) የደረጋል፡፡
“Y” - Extremely low Power
“U” – Ultra low Power
ከለይ ያሉት ሁለቱም የሚያመለክቱት ሀይል ቆጣቢ ወይም ዝቅተኛ አቅም ያላቸው CPU ናቸው፡፡
ምሳሌ፡ Intel® Core™ i5-7200U
Source ethio hackers
@simatechnology
330
የቻናላችን አባላት ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች | ለጥንቃቄ 🚸
@simatechnology
❗️በቴሌግራም Bitcoin የሚባል ነገር አትሞክሩ | ሰዓታችሁን አታባክኑ
❗️Telegram እና Facebook አካውንት በቀላሉ Hack አይደረግም
❗️Final Corrupt ያደረገ ሚሞሪ አይስተካከልም
❗️Wifi Password በስልክ App ሀክ ይደረጋል ብላችሁ አታስቡ
❗️የሚሞሪ ካርድን የመያዝ አቅም መጨመር አይቻልም | 2GB ወደ 4GB never
❗️ኢትዮጵያ ውስጥ ለጊዜው ነፃ ኢንተርኔት መጠቀም አይቻልም | ቴሌ አንዳንድ ኮንፊገሬሽኖችን Block አርጓቸዋል | ሲሰራ እናሳውቃለን
❗️ቴሌግራም ላይ ያሉ ያለምንም Description የሚለቀቁ አፖችን install አታድርጉ
❗️Online ብር መስራት የምትፈልጉ በመጀመሪያ Verified የሆነ Paypal Account ያስፈልጋችኋል | በWestern Union ምናምን የሚባለው Totally Scam🚸
❗️ብር እንከፍላለን የሚሉ ዌብሳይቶችን ሳታረጋግጡ ጊዜአችሁን አታባክኑ
❗️በቴሌ Package ሲስተም አትጠቀሙ | ከባድ የዘረፋ ሲስተም ነው
❗️በአሁን ሰዓት Bitcoin በቀላሉ ማግኘት አይቻልም | ቢትኮይን ከ Diamond በልጧል
❗️ያገኛችሁትን አፕ ሁሉ ስልካችሁ ላይ install አታድርጉ | Auto Rooter የሆኑ Malicious Applicationኖች እየተበራከቱ ነው!
❗️ይህንን ቻናል Leave አታድርጉ ይጠቅማችኋል😂😎
@simatechnology
330
የ8 አመቱ baby በጣም ተናዶ እያለ
አባት- baby እንካ ከሱቅ ለስላሳ አምጣልኝ
baby- coca ነው pepsi
dad- coca🙄🙄
baby- diet ወይስ normal
dad- normal🤔
baby- ጠርሙዝ ወይስ ቆርቆሮ
dad- ጠርሙዝ😏
baby- 500 ml ወይስ 1 litre
dad- ኡፍ ምናባክ ሆነካል? በቃ ውሃ ይዘህ ና 😠😠
baby- normal ወይስ mineral
dad- mineral
baby- ቀዝቃዛ ወይስ ከውጪ
dad- በመጥረጊያ አናትህን ሳልተረትረው ሂድ😠😠😠😡
baby- በእንጨት ወይስ ፕላስቲክ መጥረጊያ
dad- አቁም ማላገጥህን አንተ ትንሽ እንስሳ😬😬
baby- ላም ወይስ አሳማ
dad- ደደብ ሂድ ውጣልኝ አይንህን እንዳላየው🤕🤕
baby- አሁን ወይስ በኋላ
dad- አሁኑኑ🗣🗣🗣
baby- ገፍትረከኝ ወይስ እራሴ
dad- በጣም ተናዶ... እገልካለው👁👁
baby- በሽጉጥ ወይስ በቢላዋ
dad- ተኩሼ ነው የምገልክ አንተ የማትረባ
baby- ራሴን ወይስ ሆዴን
dad- በብስጭት ፌንት😡😈😈
baby- ሞተህ ነው ተኝተክ 😂😂😂😂😂😂😂😖
@simatechnology
330
ዋይፋይ_ምንድነው?
ገመድ አልባ አውታረመረብ ልክ እንደ ሞባይል ስልኮች ፣🖥 ቴሌቪዥኖች እና 🔊ራዲዮዎች ሁሉ የራዲዮ ሞገድን(radio waves) ይጠቀማል ፡፡ በእውነቱ በገመድ አልባ አውታረመረብ መካከል የሚደረግ ግንኙነት ብዙ የሚመስል ባለ ሁለት መንገድ የሬድዮ ግንኙነት ነው ፡፡
💻የኮምፒተር ገመድ አልባ አስማሚ ዳታን ወደ ሬዲዮ ምልክት ይተረጉመዋል እና አንቴናውን በመጠቀም ይተላለፋል ገመድ አልባ ራውተር ምልክቱን ተቀብሎ ይቀይረዋል ፡፡ ራውተሩ መረጃውን ወደ 🌐በይነመረብ ይልካል ።ይህ ሂደት እንዲሁ በተቃራኒው የበይነመረብ መረጃ ይቀበላል ፣ ወደ ሬዲዮ ምልክት ይተረጉመዋል እና ወደ ኮምፒተርው ሽቦ አልባ አስማሚ( wireless adapter) ይልካል።
ለ WiFi ግንኙነት ጥቅም ላይ የዋሉት 🔊ሬዲዮዎች ለ Walkie-talkies ፣ ለሞባይል ስልኮች እና ለሌሎች መሳሪያዎች አገልግሎት ከሚውሉ ራዲዮዎች ጋር በጣም ተመሳሳይ ናቸው ፡፡ እነሱ የሬዲዮ ሞገዶችን ማስተላለፍ እና መቀበል ይችላሉ ፣ የሬዲዮ ሞገድን ወደ 1 እና 0 መለወጥ ይችላሉ ፡፡ ግን የ WiFi ራዲዮዎች(WAVE) ከሌሎች 🔊ራዲዮዎች ጥቂት የማይታወቁ ልዩነቶች አሏቸው፡፡
🔑እነሱ በ 2.4 GHz ወይም 5 GHz ድግግሞሽ ይተላለፋሉ። ይህ ድግግሞሽ ለሞባይል ስልኮች ፣ ለ Walkie-talkies እና ለቴሌቪዥኖች ከሚያገለግሉት ድግግሞሽ በጣም ከፍ ያለ ነው ፡፡ ይህም ደግሞ ተጨማሪ ዳታን 💾እንዲይዝ ያስችለዋል።,
🔆ዋይፋይ መቼ ተፈለሰፈ?🔆
“#ዋይ ፋይ” የተፈጠረው እና #ለመጀመሪያ ጊዜ ለሸማቾች የተለቀቀው አንደ ኤሮፕያን አቆጣጠር 1997 ነዉ ፡፡ ይህን ተከትሎም በመሳሪያዎች መካከል ያለ ገመድ አልባ መረጃ ሽግግር #ሁለት_ሜጋ_ባይት_በሰከንድ እንዲኖር አስችሏል ፡፡ በ 1999 WiFi ለቤት አገልግሎት አስተዋወቀ።
🙏Join and Share🙏
━━━━━━━━━━━━━━━
📢: @simatechnology
━━━━━━━━━━━━━━━
330
ፌስቡክ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተቀናበሩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ከፕላትፎርሙ ለማስወገድ መዘጋጀቱን ገለጸ
°°°@simatechnology °°°
ግዙፉ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ፌስቡክ በሰው ሰራሽ አስተውሎት(artificial intelligence ) በመቀናበር እጅግ በተራቀቀ መልኩ ሰዎችን የሚያታልሉ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ከፕላትፎርሙ ለማስወገድ መዘጋጀቱን አስታወቀ
ረቂቅ አታላይ ተንቀሳቃሽ ምስሎች (Deepfakes video) በኮምፒውተር አማካኝነት አውነተኛ መስለው የሚዘጋጁ የቪዲዮ ቅንብሮች ናቸው፡፡
ፌስቡክ ኩባንያ በረቀቀ መልኩ የሚቀናበሩ ተንቀሳቃሽ ምስሎቹ እውነታን የሚያዛቡና በኢንዱስትሪው ላይ የጎላ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ መሆናቸውን ገልጿል፡፡
ምንም እንኳ አታላይ ቪዲዎቹ በበይነ-መረብ ላይ እምብዛም ያልተለመዱ ቢሆኑም በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፉ የመጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሶፍትዌሮች የሰዎችን ጥልቅ ማታለያ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለመስራት የሚውሉ ሲሆን ጥልቅ የማታለል ተግባሮች የሚፈጸሙት የፖሊቲከኞችን እና የታዋቂ ሰዎችን ቪዲዮ ትክክለኛ እንዲመስሉ የማዋሃድ፣ የመተካት ወይም ይዘቱን በከፍተኛ ደረጃ በመለወጥ የሚፈጸም ተግባር ነው፡፡
ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም “ሰዎችን ለማሳሳት በሚዲያ ውስጥ የተጠመዱ ሰዎች ፣መኖራቸውን ፌስቡክ ኩባንያ የግሎባል ፖሊሲ ማኔጅመንት ምክትል ፕሬዝዳንት ሞኒካ ባይከርት በመጦመሪያቸው አስፍረዋል፡፡
ምንጭ፡ ቢቢሲ/INSA
330
✳️ ለዛሬ አንድን ፍላሽ (Flash, Pen drive) ምንም ዓይነት #Software ሳንጠቀም እንዴት #ቡተብል (Bootable) ማረግ እንደምንችል እናያለን።
#መጀመርያ cmd (Command Prompt) መክፈት ይኖርቦታል ከዛ ቀጥሎ ያሉትን ስቴፖች ይከተሉ !
1.diskpart ብለው #ጽፈው Enter ይበሉት
2. በመቀጠል List disk ብለው #በመጻፍ Enterን ይጫኑ ።
3. Select disk number
ይሄኛው ስቴፕ ጥንቃቄ ይፈልጋል ከምናያቸው የ ዲስኮች ዝርዝር ውስጥ ለፍላሹ የተሰጠውን #ቁጥር በትክክል በመምረጥ Enterን ተጭነው ወደ ቀጣይ ስቴፕ ይሂዱ (እዚ ላይ ለፍላሹ የተሰጠውን ቁጥር ትተው ሌላ እንዳይመርጡ #ጥንቃቄ ይደረግ)
4. Clean ብለው #በመጻፍ Enter ይበሉት
5. Create partition primary ብለው #በመጻፍ አሁንም Enter
6. እንደገና Active ብለው #ይጽፉና Enter
7. format fs = ntfs quick ብለው በመጻፍ Enter
8. Assign ብለው በመጻፍ አሁንም Enter ይበሉት
በመቀጠል ኦፐሬቲንግ ሲስተምዎ ወዳለበት በመሄድ ወደ #ፍላሽዎ ይላኩት !
9.በመጨረሻም ልኮ ሲጨርስ ወደ #cmd በመመለስ Exit ብለው ይጻፉና Boot የሆነ ፍላሽ ባለቤት ሆኑ ማለት ነው ።
#መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ።
👇👇
╭─••─═•📱••••••••═─•📱•─╮
➙ @simatechnology
➙ @simatechnology
╰─••─═•📱••••••••═─•📱•─╯
330
💻በኮምፒውተራችን አዲስ ዊንዶው ምርት ከጫንን በኋላ እንዴት ደህንነቱን አስተማማኝ እናደርጋለን?🔐
@simatechnology
አዲስ ዊንዶውስ ምርቶችን /Windows/ (7፣ 8፣10) ወይም ሌላ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከጫንን በኋላ ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግና ለማሻሻል ከዚህ በታች የተቀመጡትን የደህንነት እርምጃዎች መተግበር ይመከራል፡፡
1. የዊንዶው ስርዓትን ማዘመን/up to date/ የቅርብ ጊዜ የደህንነት ማዘመኛዎች እና መጠገኛዎችን /updates and patches/ መጫን፡፡
2. ሶፍትዌሮችን ማዘመን /Update software/ ፕሮግራሞች እና መተግበሪያዎች ሁሉም ዓይነት የቅርብ ጊዜ ማዘመኛዎች እና የደህንነት መጠገኛዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የታወቁ ሶፍትዌሮች እንደ ጃቫ ፣ አዶቤ ፍላሽ ፣ አዶቤ ሾክዌቭ ፣ አዶቤ አክሮባት ሪደር የመሳሰሉት ጊዜ ያለፈባቸው ከሆኑ በአጥፊ ተልእኮ ላይ የተሰማሩ ተዋንያን ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎች በቀላሉ ለመድረስ ያስችላቸዋል።
3. መልሶ ማግኛ ስርዓት መፍጠር/Create a restore point/ ለዊንዶው ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች(OS) የደህንነት ማዘመኛዎች ከተጫነ ቀጣዩ እርምጃ በዊንዶውስ ውስጥ ወደ ነበረበት የመመለሻ ቦታ መፍጠር ነው። በኮምፒተር ላይ ችግርን ሊያስከትሉ የሚችሉ ወይም ስርዓቱ ላይ ማንኛቸውም ለውጦች ከማድረግዎ በፊት የመልሶ ማግኛ አማራጭን ተግባራዊ ማድረግ ይመከራል።
4. ፀረ-ቫይረስ መጫን Install antivirus product - አስተማማኝ የደህንነት መፍትሔ የሚሰጥ ማለትም ሪልታይም ቅኝት ፣ ራስ-ሰር ዝመና (Automatic update) እና ፋየርዎል ማካተት አለበት
5. ለባለብዙ ደረጃ የጥቃት መከላከያ ንቁ የደህንነት መፍትሄን መጫን/Install a proactive security solution for multi-layered protection
6. የምትክ ስርዓት መፍጠር /Back up your system/
7. መደበኛ አካውንት መጠቀም/ Use a standard user account/
8. የተጠቃሚ መለያ ቁጥጥርዎን ንቁ ማድረግ/Keep your User Account Control enabled/ - የተጠቃሚ መለያ ቁጥጥር በኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ያልተፈቀዱ ለውጦችን እንዳይኖሩ ያግዛል።
(INSA)
@simatechnology
330
@simatechnology
በሞባይል ስልካችን ከ2 እስከ 5 ከሚደርሱ ሰዎች ጋር በተመሳሳይ ሰዓት
ጥሪ ማድረግ እንደሚቻል ታቃላችሁ?|
አንድ እንድ ግዜ ከ2 ሰዎች በላይ በአንድ ግዜ በተመሳሳይ ሰዓት መደወል
ልንፈልግ እንችላለን።
ለምሳሌ ለስራ ወይም ለጫወታ ከጓደኞቻችን ወይም ከስራ ባልደረቦች ጋር
በተመሳሳይ ሰዓት በስልክ ማውራት ካለብን ለየእያንዳንዱ ሰው ከመደወል
ይልቅ በአንድ ጥሪ ሁሉንም ማግኘት የምንችልበት አገልግሎት ስልካችን ላይ
አለ።
ይህአገልግሎት ኮንፈረንስ ኮል ይባላል።
ኮንፈረንስ ጥሪ ለማድረግ፦
1ኛ- መጀመሪያ ወደ ሚፈልጉት ሰው ይደውሉና ስልኩ እስከሚነሳ መጠበቅ
2ኛ-በመጀመ የደወሉላቸው ሰው ስልኩ ሲያነሱ መስመር ላይ እንዲጠብቁ
ይንገሩ
3ኛ- ወደ ሁለተኛው ሰው ስልክ ይደውሉና እስከሚነሳ ይጠብቁ
4ኛ- የሁለተኛው ስልክ ሲነሳ እንደ ስልካችሁ አይነት በቀጥታ መርጅ
(Merge) የሚለውን ምርጫ ይጫኑ። ወይም ኦፕሽን(Option) ውስጥ
በመግባት ኮንፈረንስ(Conference) ወይም ጆይን(Join) የሚለውን
በመጫን የኮንፈረንስ ጥሪ ማደረግ ትችላላችሁ።
ተጨማሪ ሰዎችን ወደ ኮንፈረንስ ጥሪ ለማስገባት ከፈለጋችሁ ከተራ ቁጥር
2 እስከ 4 ያለውን መድገም ነው።
📱📱📱📱📱📱📱📱📱📱📱
330
📲 ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች
@simatechnology
▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃▃
1. #የስልክዎ ፍጥነት ከቀነሰ
#ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትዕዛዞችን ለማከናወን ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ፤ ባዕድ ሶፍትዌሮች #(ማልዌር) እያስቸገሩት ነው ማለት ነው።
እነዚህ #ማልዌር የተባሉት ቫይረሶች ዋነኛ ሥራቸው የስልክዎን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማዘግየት ሊሆን ስለሚችል፤ በአፋጣኝ #ማስወገድ ተገቢ ነው።
2. #ስልክዎ በጣም የሚግል ከሆነ
#ስልክዎት ከተለመደው ከፍ ባለ ሁኔታ #የሚግል ከሆነ፤ ችግር አለ ማለት ነው። በፍጥነት #እርምጃ ይውሰዱ አልያም #ባለሙያ ያማክሩ።
3. #የስልክዎ የባትሪ ኃይል ቶሎ የሚያልቅ ከሆነ
#ስልክዎ ከፍተኛ #ሙቀት አለው ማለት ደግሞ #የባትሪው ኃይል ቶሎ ቶሎ ያልቃል ማለት ነው።
#ምናልባት ስልክዎ አዳዲስ መተግበሪያዎችንና #ሶፍትዌሮችን ለማደስ በሚሞክርበት ወቅት የባትሪውን ኃይል #ሊጨርስ ይችላል። ነገር ግን ምክንያቱ #ይህ ካልሆነ ስልክዎ #ተጠልፎ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ አለብዎ።
4. #ወደ ማያውቁት ሰው መልዕክት ከተላከ ወይም ከማያውቁት ሰው መልዕክት ከደረስዎ
#ብዙ ጊዜ እርስዎ የማያውቋቸው #መልእክቶች የሚላኩት በዋትሳፕና በመሳሰሉ #መተግበሪያዎች በኩል ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ ወደ ጓደኛዎት አልያም ወደ #የማያውቁት ሰው ሊሆን ይችላል።
ወደ እርስዎ የሚላኩ #መልዕክቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ #ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ የሚሉ ማሳሰቢያዎች ይበዟቸዋል።
5. #ከበይነ መረብ የሚመጡ ድንገተኛ መልዕክቶች
ስልክዎን በመጠቀም በይነ መረብን #(ኢንትርኔት) በሚያስሱበት ወቅት #ወደ ሌላ ድረ-ገጽ #የሚያሸጋግሩ መልዕክቶች በተደጋጋሚ የሚመጡ ከሆነ #የስልክዎ መጠለፍ ነገር እውን ሊሆን ይችላል።
#መልዕክቱን ሲጫኑ በአንድ ጊዜ ወደ #ሁለትና ሦስት የድህ-ረገጾች አድራሻዎች የሚመራዎ ከሆነ በፍጥነት ይውጡ።
6. #አጠራጣሪ መተግበሪያዎችና ገንዘብ ነክ ጥያቄዎች
አንዳንድ ጊዜ እርስዎ #ያልገዙት ወይም ከበይነ መረብ #ያላወረዱት መተግበሪያ ስልክዎት ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ። ምናልባትም #የሞባይል ዳታ እና የጽሁፍ መልዕክት ላይ የዋጋ #ጭማሪም ሊያስተውሉ ይችላሉ።
የክሬዲት ካርድና የሞባይል ገንዘብ ማንቀሳቀሻ መንገዶችን የሚጠቀሙ ከሆነ ይህ ሁኔታ #ለጠላፊዎች ምቹ አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላልና ይጠንቀቁ።
#ስለዚህ የይለፍ ቃሎችንና #የግል መረጃዎችን ስልክዎት ላይ ባያስቀምጡ ይመረጣል፤ አልያም #በጠላፊዎች እንዳይገኝ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
7. #ያልተለመዱ ድምጾች
#የድምጽ ጥሪ በሚያደርጉበት ወቅት ያልተለመዱና ከዚህ በፊት ያልነበሩ ድምጾች #የሚሰማዎት ከሆን ምናልባት ስልክዎ #የጠላፊዎች ሰላባ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎም የስልክ ጥሪዎችዎ #እየተቀዱም ሊሆን ይችላል።
🏷 #መፍትሄዎች
━━━━━━
▫️የስልክ #ማጽጃዎችን ከታማኝ ምንጭ ማግኘት
▫️እርስዎ #የማያውቋቸውን #መተግበሪያዎች ከስልክዎ ማጥፋት
▫️ብዙ ሰው የሚጠቀማቸው #ነጻ የኢንተርኔት #አገልግሎቶችን አለመጠቀም
▫️ስልክዎን #በቀላሉ ሊታወቅ በማይችል #የይለፍ ቃል መዝጋት
▫️ከማይታወቁ #ምንጮች #መተግበሪያዎችን አለመጫን
▫️ስልክዎና በስልክዎ ላይ ያሉ #መተግበሪያዎችን ቶሎ ቶሎ #ማሳደስ (update)
▫️#የስልክ ክፍያዎንና #የዳታ አጠቃቀምዎን #ይቆጣጠሩ
#መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ።
━━━━━━━━━━━━━━━
Join @simatechnology
330
@simatechnology
🔆ዛሬ ጠቃሚ #የመጽሐፍ 📚 ድረ ገጾችን እንጠቁማችሁ👇👇👇
1⃣. http://gen.lib.rus.ec/
ይህ👆 ድረ-ገጽ ማንኛው አይነት መፅሀፍ ማውረድ የሚያስችሎት
ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠር መፅሀፎች አሉት በዉስጡ
ከሚግኙ መፅሀፎች መካከል👉 #የትምህርት መፅሀፎች፤ #የሳይኮሎጂ መፅሀፎች፤
#ፍልስፍና መፅሀፎች ፤ #የታሪክ መፅሀፎች ይገኙበታል፡፡
2⃣. http://sci-hub.org/
ይህ👆 ድህረ-ገጽ ከ64 ሚሊዮን በላይ #የጥናት ወረቀት
የሚገኝ ሰለሆነ በቀላሉ ማዉረድ ይቻለሉ ፡፡
✔️በዚህ👆 ድረ- ገጽ የተለያዩ መጻፎች በተለያ ምርጫ እና አይነት ያገኛሉ።
3⃣. https://bookboon.com/
ይህ👆 ድረገጽ ማንኛው አይነት የነጻ መጻፍ የሚያገኝበት
ሲሆን በየትኛዉም የክፍል ደረጃ 👨🎓 ላሉ #ተማሪዎች አንዲዉም
በማንኛው የስራ ሁኔታ ላይ ላሉ ሰዎች ጠቃሚ ድርገጽ ነው፡፡
4⃣. http://bookzz.org/
#ቡክዚ 👆 አለማችን ለይ ትልቅ የመጻሀፍ #ላይብረሪ ያለው ሲሆን በአማካኝ 2.6 #ሚሊዮን መጻሀፍ በ ድረገጹ ይገኛል።
5⃣. www.allitebooks.com/
ይህ 👆 ድረገጽ ብዙ የቴክኖሎጂ #መጽሀፍት ያሉት ሲሆን የፕሮግራሚንግ፤ ግራፊክስ ፤ የኮምፒተር አጠቃቀም እና
የተለዩ የትምህርት መጻሃፎች📚 ያገኛሉ፡፡
@simatechnology
330
#NANO
@simatechnology
ለሞባይል ስልክ ስክሪን ማጠንከሪያነት አገልግሎት ላይ የሚውለው ቴክኖሎጂ በተጠቃሚዎች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እንደሌለ ተገለጸ!‼️
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰
ሰሞኑን በሃገራችን በስፋት መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተው በብዛት ከቻይና ወደ ሃገር ውስጥ የሚገባ #የናኖ ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው (Nano coating machine) ለሞባይል ስልክ ማጠንከሪያነት አገልግሎት ላይ በመዋል ላይ ይገኛል፡፡ ይህንን ተከትሎ ከተገልጋዮች እና የተለያዩ ሚዲያ አካላት በደረሰ መረጃና በቀረበው ጥያቄ መሰረት ወደ ሃገር እየገባ ባለው የዚህ ቴክኖሎጂ መሳሪያ ከጨረራ አንጻር ጤና ላይ ሊያስከትል የሚችለው ጠንቅ መኖሩና አለመኖሩን ለማጣራት የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ በመገኘት በመጋዘን ውስጥ ከሚገኙ (Nano coating machine) መሳሪያዎች ውስጥ ናሙና በመውሰድ ባደረገው የቁጥጥር እና ምርመራ ሥራ መሳሪያው የኢትዮጵያ ጨረራ መካላከያ ካስቀመጠው ጉዳት ከሚያስከትሉ የጨረራ መጠን ልኬት በታች የሆነ እና በህዝብ እና በአካባቢ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት አለመኖሩን አረጋግጧል፡፡
አዮን ፈጣሪ ስላልሆኑ የጨረራ አይነቶች
አዮን ፈጣሪ ያልሆኑ የጨረራ አይነቶች በርካታ ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ልዕለ ሀምራዊ ሞገድ (UV Radiation) ይገኝበታል:: ይህ አዮን ፈጣሪ ያልሆነ የጨረራ አይነት በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች አማካይነት ለሰው ልጅ የተለያዩ ጥቅሞችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ለምሳሌም ጀርሞችን፣ ባክቴሪያዎችን፣ ፈንገሶችንና እና የመሳሰሉትን ለማምከን ይረዳል፡፡ በጤና ተቋማት፣ በምርምር ላቦራቶሪዎች ውስጥ፣ በጸጉር ማስተካከያ ቤቶች፣ በመኖሪያ ቤቶች ጌጣጌጦችን ከኢንፌክሽን ለመከላከል፣ የህጻናት መመገቢያዎችን ወዘተ ከተሀዋስያን ብክለት ለማከም በስፋት አገልግሎት በመስጠት ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡
በተመሳሳይ ይህ ሞገድ ለሞባይል ስልክ ማጠንከሪያነት በሚያገለግል የናኖ ቴክኖሎጂ ውጤት በሆነ መሳሪያ ውስጥ በፈሳሽ መልክ የሚገኝ ሲሆን ፈሳሹ የስልክ ስክሪንን ለማድረቅ ጥቅም ላይ ሲውል ሞገዱ ስራው ከሚሰራበት ሳጥን ሊያልፍም ሆነ አፈትልኮ የማይወጣበት ዲዛይን ስላለው በተጠቃሚው ላይ ሊያሳድር የሚችል ተጽዕኖ አለመኖሩ ተረጋግጧል፡፡ ሆኖም ግን አገልግሎቱን የሚሰጡት ሰራተኞች ከመሳሪያው ጋር በሚያያዘው ማንዋል መሰረት እንዲሰሩና የጥንቃቄ መርህን በመከተል ስራቸውን ማከናወን እንዳለባቸው ይመከራል፡፡
የዚህ ቴክኖሎጂ ሳይንሳዊ ፍተሻ የተካሄደው በሁለት መንግድ ሲሆን እነዚህም በመስክ በመገኘት የምልከታና የጨረራ መጠን ልኬት ስራ እና የላቦራቶሪ ፍተሸ ተግባራት ናቸው፡፡ በዚሁ መሰረትም የሁለቱም ፍተሻ ስራዎች ውጤት ቴክኖሎጂው በሰው ንብረትና አካባቢ ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ እንደሌለ ተረጋግጧል፡፡ ህብረተሰቡም በዚህ ቴክኖሎጂ ምክንያት የሚመጣ ችግር እንደሌለ እንዲገነዘብ መልዕክታችን ነው፡፡
(የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን)
🙏እባኮትን ይህን መረጃ ስልኮ ላይ ወዳሉ ግሩፖች እና ኮንታክቶች ይላኩ‼️
🚀ትኩስ ትኩስ መረጃዎች እንዲደርሶ አሁኑኑ ይቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@simatechnology
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
330
ነገ ወደ ህዋ የምትመጥቀው የኢትዮጵያ ሳተላይት ETRSS- 01‼️
@simatechnology
• የሳተላይቷ ጠቅላላ ከሸብደት 72 ኪሎ ግራም ሲሆን ነገ ታሕሳስ 10 ከማለዳው 12 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ከቻይና ዋና ከተማ ቤይጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የቻይና ሳተላይት ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ ትላካለች፡፡
• ሳተላይቷ በተወነጨፈች በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የህዋ ጥግ ላይ የምሕዋር ቦታዋን ትይዛለች፡፡
• በኢትዮጵያና ቻይና መንግስት በጀት የተገነባችው የመረጃና ኮሙኒኬሽን ሳተላይት የምትመጥቀው ከቻይና የጠፈር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነው።
• ሳተላይቷ ለግብርና፣ ለማዕድን፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ለመገናኛና ቴክኖሎጂ ለመሳሰሉት አገልግሎት መረጃ ለመስጠት ነው፡፡
• የሳተላይቷ የመረጃ መቀበያ እንጦጦ ላይ የተሰራ ሲሆን ከማምጠቅ ስራው ጀምሮ ቁጥጥሩ ሙሉ ለሙሉ እንጦጦ ላይ በኢትዮጵያውያን ይከናወናል።
• እንጦጦ የሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ ጣቢያ እንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና የምርምር ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገንብቶ ለአገልግትት ተዘጋጅቷል፡፡
• ጣቢያው የሳተላይቷን ደህንነት ክትትል የሚደረግበትና ከሳተላይቷ የሚገኙ መረጃዎች የሚሰበሰቡበት ነው፡፡
@simatechnology
330
🔰#ጉግል የክሮም 79 እትም ላይ የደህንነት ክፍተት መገኘቱን ተከትሎ ማዘመኛውን አስወገደ🔰
አዲስ አበባ ታህሳስ 7/2012፡- ጉግል ባቀረበው #የክሮም 79 ማዘመኛ /Chrome 79 update/ ላይ አደገኛ የሶፍትዌር ክፍተት መገኘቱን ተከትሎ ማዘመኛውን #ማስወገዱ ተጠቁሟል፡፡
ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ #ጉግል ከክሮም 79 እትም ማዘመኛ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ቅሬታዎችን እንደደረሰው ጠቁሟል፡፡ ተጠቃሚዎች በሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ያከናወኗቸው የሎግ-ኢን ዴታዎች /login data/ ክሮም 79ኝን በሚጭኑበት ወቅት እንደሚጠፉ ከቀረቡት ቅሬታዎች መካከል አንዱ ነው፡፡
#ጉግልም ችግሩ በአንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚዎች ላይ መከሰቱን ያረጋገጠ ሲሆን የተፈጠረውን አደገኛ የሶፍትዌር ክፍተት ለማስተካከል የሳምንት ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልጿል፡፡
የክሮም 79ኛ እትም በአለም አቀፍ ደረጃ ላሉ እና 50 በመቶ ለሚሆኑ የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች መለቀቁን #ጉግል ጠቅሷል፡፡
ከደህንነት ክፍትቱ ጋር በተያያዘ የተጠቃሚዎች መረጃ እንደሚሰረዝ እና መረጃዎቻቸውን ለማግኘት በሚያስቸግር መልኩ እንደሚሰወሩ ለጉግል ከቀረቡለት ቅሬታዎች መካከል ይገኛሉ፡፡
ጉግል ሰሞኑን ለክሮም መረጃ ማፈላለጊያ ማዘመኛ መልቀቁ ይታወቃል፡፡ ምንጭ፡ bbc
©INSA
@simatechnology
330
✳️ Whats is #Quantum_Computing ?
#Quantum_Computing ምንድነው ?
@simatechnology
Quantum Computer: #የQuantum_Mechanics ሀሳቦችን በመጠቀም አሁን ካሉት ኮምፒተሮች #በፍጥነትና በተሻለ መልኩ ስራውን ሚከውን #የኮምፒተር ዐይነት ነው !
#አሁን ዓለም ላይ ያሉት #ኮምፒተሮች በሙሉ ዳታዎችን ለማስቀመጥ ሆነ ለማስተላለፍ #Binary_Digit ተብሎ በሚጠራው የ 0 እና 1 ስብስብ የሆነው #Streams_of_Bits (ባጭሩ Bits) ተጠቅመው ነው. .. ስእሎች, ቪድዮዎች, ሙዚቃዎች ብሎም #ማንኛውም ኮምፒተሮች ላይ ያሉት #ዶክመንቶች በ #Bit መልኩ ነው ሚቀመጡት: !
#Quantum_Computeሮች በሌላ መልኩ #ዳታዎች ሚያስተላልፉትም ሆነ ሚያከማችሁት Bit ተጠቅመው ሳይሆን #Qubits በሚባሉት የ 0 እና 1 ስብስቦች #በመጠቀም ነው !
#Bit እና #Qubit ሚለያቸው፣ Bit ብለን #የጠራናቸው ወይ 0 ወይ 1 በመሆን ነው ሚቀመጡት ! #Qubits ሚባሉት ግን እንደ Bits ለየብቻ 1 እና 0 መሆን ይችላሉ ደግሞም በተመሳሳይ ቦታና ግዜ 1ም 0ም ሆነው መቀመጥ ይችላሉ፥ ይህ #Superposition ተብሎ ይጠራል ! አሁን በምንጠቀማቸው #ኮምፒተሮችና በQuantem Computers መሃል ያለው ትልቁ ልዩነትም ይሄኛው ነው !
#ለምሳሌ አንድ ካሲኖ (Casino) ውስጥ ገብታችሁ ከምታገኙት ኮምፒተርጋ #አንበሳና_ሰው (በBit ሲገለጽ Head=1 and Tail=0) ጨዋታ ብትጫወቱ የማሸነፍም የመሸነፍም እድላችሁ 50/50 ነው ሚሆነው። ኮምፒተሩ #Quantem_Computer ቢሆን ግን #የማሸነፍ እድላችሁ ዜሮ ይሆናል ምክንያቱም #Qubit 1ም 0ም መሆን ስለሚችል #አንበሳ ስትጥሉ ሰው, #ሰው ስትጥሉ ደሞ አንበሳ እየጣለ #ስለሚያሸንፋችሁ!
#አሁን በዋነኝነት #የIBM ሪሰርቸሮችን ጨምሮ ብዙ ኩባንያዎች #Quantum_Computing ላይ ተስፋ ሰጪ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም፥ #በሜዲካል፣ #ኬሚስትሪና #ኮምፒቲንጉ አለም ያበረክተዋል ተብሎ ከታሰበለት አላማ ብዙም እምርታ አላሳየም !
#Quantum_Computers በዚህኛው ትውልድ #ለገበያም ሆነ #ጥቅም ላይ ይውላሉ ተብሎ #ባይታሰብም፣ ለመጪው ትውልድ አሁን እየተጠቅምንባቸው ያሉት #ኮምፒተሮች ግን የሞባይል ስልክ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲጀመር #ብዙዎች ሲይዙት እንደነበር #ሰማኸኝ_በለው ( Nokia) ስልክ ታሪክ እንደሚሆኑ አትጠራጥሩ !
#መረጃዎችን ለወዳጅዎ ያጋሩ።
➖➖➖❇️ ❇️➖ ➖➖
@simatechnology
330
የስልካችን ፖስወረድ ወይም ፖተርን ብንረሳው እንዴት አድርገን ያለ ኢንተርኔት መክፈት እንችላለን ?
በ PATTERN ወይም Password የተዘጉ ስልኮች ካለ ምንም ኢንተርኔት እና ምንም መረጃ ሳናጠፋ እንዴት መመለስp እንደምንችል እናቀርባለን
ኣስፈላጊ ነገሮች:-
1 aroma file manager በ ሌላ ስልክ ማውረድ ኣለብን
2 ሚሞሪ ካርድ(ያወረድነውን app
የምንናስቀምጥበት)
3 የተዘጋው ስልክ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
Step1:- aroma file manager ካወረዳቹ ወደ ሚሞሪ ካርዱ ጫኑት እና ካርዱ ወደ ተዘጋው ስልክ ኣስገቡት
Step2:- ከዛ ስልኩ power off እናረገው እና የ recovery stock ወይም ስልካችን ካጠፋነው ቡሃላ የ power እና የ ድምፅ መጨመርያ ኣንድ ላይ ተጭነን እንቆያለን( እንደ የ ስልኩ ኣይነት ሊለያይ ይችላል)
Step3:- ወደ recovery mode ከገባን ቡሃላ የ ድምፅ መጫኞቹ ወደ ላይ እና ታች የ power መጫኛው ደሞ እንደ ok ሁነው ያገለግላሉ
Step4:- recovery mode ላይ install zip from sd card የሚለውን ላይ ok/power button እንጫን እና aroma file manager ያስቀመጥንበት folder ገብተን install እንለዋለን
Step5:- ከዛ aroma file manager ከከፈታቹ ቡሃላ ወደ nevigate የሚለውን ትወርዱ እና automount all devices on start የሚለውን ተጭናቹ ከዛ ዝጉት
Step 6:- step4 ላይ እንዳደረጋችሁት step6 ላይም ድገሙት
Step7:- aroma file manager እንደገና ሲከፈት ወደ data folder ከዛ system folder ትገቡ አና 'gesture.key' or 'password.key' የሚል ታገኛላቹ
Step8:- ከዛ ያገኛችሁት gesture.key or password.key ኣጥፉት ከዛ ስልካቹ reboot ኣድርጉት
Step9:- ስልኩ ሲከፈት የማትረሱትን pattern ወይም password በማስገባት መክፈት ትችላላቹ
@simatechnology
330
📌NanoTechnology
NanoTechnology ምንድነው?
Nano Technology ሌላ ተአምር ሳይሆንእየተጠቀምን የምንገኛቸውን ቴክኖሎጂዎች አሁን ካሉበት size እንዲያንሱ ለማድረግ መሞከር ነው።
ለምሳሌ ያክል የመጀመርያው ENIAC ኮምፒውተር አንድ ክፍል ይሞላ እንደነበር ሲነገር እንሰማለን! Transistors እና Integrated Circuit( IC ) ከተፈጠረ በኋላ ግን አሁን ያለውን መጠን ሊይዝ ችሏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲ ደሞ በ Nano Technology ከዚህ በጣም በብዙ እጥፍ አሳንሶ ለመስራት እየተቻለ ነው።
Nano ማለት የ ግሪክ ቃል ሲሆን "Dwarf" ወይም ድንክ ማለት ሲሆን በ ማትስ ቀመር ደሞ ከ Micro ቀጥሎ የሚገኝ የ አንድ አንድ Billion (10^-9) ነው።
በየትኛው ዘርፍ ላይ ይገኛል?
ይሄ ቴክኖሎጂ በጤናው ዘርፍ ትልቅ ዕምርታ እያሳየ ሲሆን እንዲሁም በ መኪና እና በ አውሮፕላን ኢንደስትሪ ላይ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል።
📲 ከሞባይል ጋር ምን አያያዘው?
አድማሱን እያሰፋ የሚገኘው ይሄ ቴክኖሎጂ ለስልኮችም ገጸ በረከት ይዞ እየመጣ ነው። ለስልክ ስክሪኖች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው።
✍ እንዴት ስልክ ላይ ይሰራል❓
✍🤭እንኳን ወደ silicon dioxide Sio2 አለም በሰላም መጣቹ።
እንዴት መሰላቹ መስታወት የሚሰራው ከ Sio2 ነው። በፈሳሽ መልክ የሚመጣው ይሄ element በስልኮቻችን ላይ ይቀቡና እንዲደርቁ ይደረጋል። ✍🖥ከደረቀ በኻላ ያለው ቅጥነት 100nm እንደሆነ ይነገራል ይሄም በአይናችን ለማየት አዳጋች ነው። እንግዲህ ይሄን ነው በየመንገዱ እና በየሱቁ እየለጠፉ ያሉት!
🔧 ያለው ጠቀሜታ 🔧
🔅እንደ ግላስ መለጠፉ በአይን ስለማይታይ የስልካችንን ውበት አይቀንሰውም።
🔅Scratchን እጅግ በጣም መቋቋም ይችላል። ይሄንንም መሞከር ይቻላል።
🔅WaterProof በመሆኑ ውሃ አያስገባም። 🔅እንዲውም ቆሻሻ አይይዝም።
🔅Uv Light መቋቋም ይችላል
🔅በጣም ለስላሳ በመሆኑ ተች ለማድረግ እንደ ግላስ አያስቸግርም!
❌❌ ችግሮቹ❗️❌❌
✍ እዚጋ ማየት ያለብን አንዳንድ ፔጆች Fake ነው የሚል ነገር ሲይፉ አያለው ምክንያት ሲጠየቁ የተሰበረባቸው ሰዎች አሉ የሚል ነው። ይሄ ቴክኖሎጂ የሚሰራው ለስልካችን Digitizer ወይም Touch ነው እንጂ ውስጥ ያለውን screen አያጠነክረውም። ስክሪን በባህሪው ፈሳሽ በመሆኑ ከከፍታ ቦታ ሲወድቅ የመፍሰስ ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ሌላኛው ደሞ ምናልባት አጭበርባሪዎች ተመሳሳይ fake ኬሚካል እየተጠቀሙ ሊሆን ይችላል። እኔ ለምሳሌ ተጠቃሚ ነኝ ስልኬን በተለያየ ነገር ተቹን በመምታት ቼክ አርጌው የስክሪኑ ጥንካሬ ጥሩ መሆኑን ተረድቻለሁ። እርግጥ ነው ምንም ነገር ገደብ ስላለው ከዛ ፎርስ በላይ ስንጠቀም ብረትም እንደሚጣመመው ይሄም ሊሰበር ይችላል።
✍ ሌላ ችግር ሰሞኑን በየሚዲያው እየሰማን ያለነው ካንሰር ያመጣል የሚለው ነው። ይሄ በጥናት ያልተረጋገጠ እና የጨረራ መስሪያ ቤት ጥናት አላደረኩም ያለ ሲሆን ምናልባት ጥናት አድርጎ ይፋ ቢያደርገው ካሉባልታ ወሬ ይታደገናል። የጨረራ መስሪያ ቤት " በየመንገዱ የስልክ ስክሪን ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ስላለው ፈሳሽ የሚያውቀው ነገር አለመኖሩን የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን አስታውቋል!
ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ፈሳሽ መፈተሽ እንዳለበት የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አወቀ ሺፈራው ገልፀው በፍተሻውም ወቅት በስልክ ገጽ ላይ የሚቀባው ፈሳሽ ጨረራ አለው ወይስ የለውም፤ የጨረራ ይዘቱ ምን ያህል ነው የሚለው ፍተሻ እንደሚደረግበት ለEBC ገልጸዋል ።" ይሄን ነው እንግዲህ የገለጸው።
🚫🚫NB፦ ይሄን ፕሮግራም ለመስራት ሳስብ ብዙ ድረገጾች ላይ የተለቀቁ ጽሁፎችን ለማንበብ ሞክሬያለው እንዲሁም ስልካቸውን ያሰሩ ሰዎችን ለመጠየቅ ሞክርያለው ይሄ ነው የሚባል ትልቅ ችግር አላነበብኩም አልሰማውም። ምናልባት ከኔ የተሻለ መረጃ ያለው ካለ ችግሮችን በማስረጃ አስደግፎ ሊነግረን ይችላል።
@simatechnology
330
🔰ተንኮል አዘል ድረ-ገጽ ምንድነው? እንዴት መለየት ይቻላል?🔰
@simatechnology
ተንኮል አዘል ድረ-ገጾች /malicious website/ የኮምፒውተር ተግባራትን ለማስተጓጎል፣የግል ኢንፎርሜሽኖችን ለመሰብሰብ፣ ተጠቃሚዎች አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዲገቡ ለማድረግ እንዲሁም በስርዓተ ኮምፒውተሩ ውስጥ ያሉ አጠቃላይ መረጃዎችን ለመድረስ /access/ እንዲያግዛቸው አጥፊ ሶፍትዌሮችን ለመጫን /install malware/ የሚሞክሩ ገጾች ናቸው፡፡
ተንኮል አዘል ድረ-ገፆች የጥቃት ምልክቶች፡
i. ድረ-ገፁ ሶፍትዌሮችን እንዲያወርዱ ፣ ፋይልን እንዲያስቀምጡ ወይም ፕሮግራም እንዲያካሂዱ/እንዲከፍቱ ይጠይቅዎታል::
ii. የክፍያ መጠየቂያ ደረሰኝ እንዲያወርዱ ይጠይቅዎታል፤
iii. ማንኛውም ድህረ-ገፅ ሲከፈቱ ወደ አደገኛ ወይም ጎጂ ድረ-ገፆች ይመርዎታል፤
iv. ድረ-ገፁ በትክክል አይሰራም ፣ ስህተቶችን እና ማስጠንቀቂያዎችን ያሳያል ፤
v. ድረ-ገፁን ከጎበኙ በኋላ ኮምፒተሮች ያልተለመዱ ባህሪዎችን ያሳያሉ ፤
vi. ተጠቃሚዎች ድረ-ገፁን በአሳሹ እና / ወይም በደህንነት ሶፍትዌሮች የታገደ መሆኑን ቅሬታ ያሰማሉ ፤
vii. ድረ-ገፁ በትራፊክ ጉልህ ለውጦች ሲኖሩት ወይም በፍለጋ ደረጃዎች መውረድ ሲታይበት፤
viii. ውድድር ወይም የነፃ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል ሊልዎ ይችላል፤እንዲሁም የዱቤ ካርድዎን ወይም የባንክ መረጃዎን እንዲያስገቡ የሚጠይቁ ነፃ ገንዘብ ወይም ቫውቸሮች ሊሰጡዎት ይችላሉ::
©INSA
--------------------//-------------------------
@simatechnology
