ቲቪ ጥገና Tv maintenance , ቲቪ ቴክኒሻን ,Tv repair 🖥
Відкрити в Telegram
ይህ ቻናል በመቀላቀሎ የሚያገኝዋቸው ጥቅሞች ፩የኤሌክትሮኒክስ እውቀቶን ያዳብራሉ። ፪ቲቪ ፣ ሳተላይት ሪሲቨር ፣ ሞባይል ፣ ኮምፕዩተር ፣ ፍሪጅ እና የልብስ ማሺን ወዘተ ባለሙያዎችን የትም መሄድ ሳያስፈልጎ እዚህ ያገኛሉ። @Yilymj @newgroupmaintenance ለቲቪ መለዋወጫ Website : ysak-electronics.netlify.app
Показати більше2 915
Підписники
-224 години
-47 днів
-430 день
Архів дописів
#ዜና_እረፍት
በትላንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ አርባምንጭ 61 ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ሰላም ባስ ልክ ሀላባ መግቢያ በምትገኘው ወራቤ ከተማ ላይ እንደደረሰ ሹፌሩና ረዳቱን ጨምሮ ሁሉም ተሳፋሪዎች
.
.
ከባሱ ወርደው ሽንታቸውን ሸንተው ጉዟቸውን ቀጥለዋል:: 😂😂
@ysakelectronics @ysakelectronics
✅አንድን ስልክ ሰርቀነው ባለቤቱ እንዳይከተለን ከፈለግን ወይም በሌላ በማንኛውም ምክንያቶች የአንድን ስልክ #መከታተያ ማጥፋት ከፈለጋችሁ⬇️
1⃣. Setting ውስጥ ይግቡ...
2⃣. security and location የሚለው ውስጥ ይግቡና location የሚለውን ይምረጡ...
3⃣. ከላይ በኩል #ON እና #OFF ማድረጊያ ያገኛሉ፤ Off ያድርጉት።
4⃣. Location > Google Location History ውስጥ ይግቡ...
5⃣. Location history #Off ያድርጉ።
6⃣አሁን የስልኩ📱 ባለቤት እንደማያገኛችሁ እርግጠኞች ሁኑ።
⚠️ነገር ግን ኢትዩ-ቴሌኮም ባለቤቱን ከተባበረው በስልኩ Imei number (international mobile equipment identity) በጣም በቀላሉ ትገኛላችሁ።🤷♂😁
join us and #Share
@ysakelectronics
#አንድ ሴተኛ አዳሪ ግብር ክፈዪ ስትባል ምን ብትል ጥሩ ነው...😳
.
.
.
.
.
.
.
አልከፍልም_ከፈለጋቹ_አሽጉት😂😂
🎃
በአንድ ቀን እሰከ 20 የሚደርሱ
አዳዲስ በሳቅ የሚገሉ ቀልዶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው እስካሁን በጣም ብዙ ሰዎች እየገቡ ነው እናንተም ተቀላቀሉ ስንል በአክብሮት ነው ።
የይለፍ ቃልዎ ወይም 'ፓስወርድዎ' ምንድን ነው? እንገምት እስኪ. . .
123456 ይሆን? ወይስ 123456789?
ምናልባትም እርስዎን ጨምሮ ሚሊዮኖች የይለፍ ቃላቸው
123456 እንደሆነ በጥናት ተረጋግጧል።
የእንግሊዝ የመረጃ ደህንነት ተቋም በሠራው ጥናት መሰረት 123456 የበርካቶች የይለፍ ቃል ሲሆን፣ 123456789 እንዲሁም 1111111 'ፓስወርዳቸው' ያደረጉትንም "ቤቱ ይቁጠራቸው" ተብሏል።
ጥናቱ እንደሚያሳየው፣ በርካቶች እጅግ ሚስጥራዊ መሆን ለሚገባቸው መረጃዎቻቸው የይለፍ ቃል የሚያደርጉት በቀላሉ ሊገመት የሚችል ቁጥር ወይም ቃል ነው።
ማንም ሊገምተው የሚችል የይለፍ ቃል መጠቀም በቀላሉ ለኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች (ሀከርስ) ያጋልጣል።
በጥናቱ ይፋ እንደተደረገው መረጃቸው ከተመዘበረባቸው ግለሰቦች አብዛኞቹ የይለፍ ቃላቸው 123456 ሲሆን፣ ወደ 23 ሚሊየን ሰዎች የይለፍ ቃላቸው 123456 ነው።
የእንግሊዝ የመረጃ ደህንነት ተቋም፤ ሰዎች በቀላሉ ማስታወስ የሚችሉት ነገር ግን ሌላ ሰው ሊገምተው የማይችል የይለፍ ቃል በመጠቀም መረጃቸውን መጠበቅ አለባቸው ብሏል።
ብዙዎች አሽሊ፣ ማይክል፣ ዳንኤል፣ የሚሉ ስሞችን 'ፓስወርዳቸው' ከማድረጋቸው ባሻገር 'ሊቨርፑል' እና 'ቸልሲ' የይለፍ ቃላቸው የሚያደርጉም አሉ። የሙዚቃ ባንድ መጠሪያ እንዲሁም የራሳቸውን ስም የይለፍ ቃላቸው የሚያደርጉም ጥቂት አይደሉም።
የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች በተበራከቱበት በዚህ ዘመን የይለፍ ቃልን ማጠንከር አንዱ ራስን የመከላከያ መንገድ ነው ተብሏል።
ታዲያስ የይለፍ ቃልዎን ለመቀየር አላሰቡም?
@ysakelectronics
@ysakelectronics
❤️Xender ===> PC
🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅
✅አንድሮይድ ስልካችንን እንዴት በ Xender ተጠቅመን
ከላፕቶፓችን ጋር ማገናኘት እንችላለን?
1️⃣ Update የሆንዉን Xender ስልካችን ላይ እንጭናለን
2️⃣ Xender እንከፍታለን
3️⃣ Connect to PC የሚለዉን እንጫናለን
4️⃣ WI-Fi Hotspot የሚለዉን እንጫናለን
5️⃣ ወደላፕቶፓችን እንሄድና WI-Fi ከፍተን ስልካችን ላይ
በሚነግረን አድራሻ አይተን Connect እንላለን Xender
_AP6911 ሌላም ሊሆን ይችላል
6️⃣ Connect መሆኑን ከረጋገጥን በሁዋላ ማንኛዉንም
ኢንተርኔት የምንጠቀምበተን ብሮውዘር ከፍተን ስልካችን
ላይ የሚያሳየንን አይፒ “ http://192.168.43.1:334/
55/ ” አስገብተን Connect እንላለን / ሌላም IP ሊሆን
ይችላል /
7️⃣ ስልካችን ላይ Accpet እንላለን አበቃ።
ከዛማ ላፐቶፓችን ላይ ከስልካችን ላይ ያሉን
መተግበሪያዎች ጨምሮ ሁሉንም ፋይሎችን እንደ ፎቶ
ቪዲዮ ልክ ኢንተርኔት እምንጠቀም እስኪመስለን
እናገኛቸዋለን፡፡ ከፈለግን ላፐቶፓችን ላይ Backup
መውሰድ ፡ ኮፒ ማድረግ ወደስልካችን መጫን…. በዙነገር
እስቲ ሞክሩትና ኮሜንት ...
#ማሳሰቢያ ይህን ስንሰራ ሞባይል ዳታ መዝጋት
ይኖርብናል ፡ አለበለዚያ ወደ ላፕቶፓችን ሼር ስላሚሆን
ካርድ ይበላናል፡፡
🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅
@ysakelectronics
@ysakelectronics
ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት
መታየት ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ ሰዎች
ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም ደረጃ
ጥሩ የሚባል ነው፡፡ ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን
ተመራጭ የሆነ ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ
ወደ ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ
ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን
ሳይዝ ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ
ከፈለጉ ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር
ዲዛይን ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡
3. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ
(CPU), ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች
ሲሆኑ Corei5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን
ስራዎችን ለምሳሌ እንደ Photoshop, Archicad, AutoCadን
የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡
በተጨማሪም ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡
ግራፊክስ ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን
ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና
የዲዛይን እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ
ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን
የላፐቶፕ አይነት ነው፡፡
4 .ራም(RAM): ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ
RAM እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ
ላፕቶፖች በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር
ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ
በላይ ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
5. የሃርድ ድራይቭ አይነት፡ ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ
አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን
በሃገራችን ያልተለመደው SSDrive ከHDDrive የተሻለ የፍጥነት
አቅም እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና
መገልበጥ (copy)ያስችለናል፡፡
6 .የምስል ጥራት፡ የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል
እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት
ያለው ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080
የተሻለ ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡Full HD 1080P በመባልም
ይታወቃል፡፡
7 .የባትሪ ቆይታ፡ አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት
የላፕቶፕ አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም
የሚቆዩ ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡
8 . ብራንድ፡ የተላያዩ የላፕቶፕ ብራንዶጭ ባሉበት ገቢያ
የተኛውን መግዛት እንዳለብን አስቀድመን ማወቅ አለብን።
⚜ @ ysakelectronics@
⚜ @ @ysakelectronics®
⚜ @ @ysakelectronics®
➖➖➖❇️ @ysakelectronics❇️➖ ➖➖
❇️ ብዙ ሰዎች የማያዉቋቸው የGSM ሞባይል ሚስጥራዊ ኮዶች!
1. ስልክዎ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት አልዋለም እንዲልላቹ ከፈለጋቹ! ወደ *21*900# ይደውሉ ወይም 1 ዲጂት በመቀነስ ወደ ራስዎ ስልክ ማድረግ! ለምሳሌ ስልክ ቁጥርዎ 0910****** ከሆነ ወደ *21*0910******# ይደውሉ ለማጥፋት ሲፈልጉ #21# ብለው ይደውሉ! ከላይ የተገለጸው በ900 ቦታ የፈለጉት ሌላ ትክክለኛ የስልክ ቁጥር ያልሆነም ማድረግ ይችላሉ!
➜ሁሉም ጥሪዎችና መልእክች ወደ ሌላ ቁጥር ዳይቨርት ለማድረግ ሲልጉ
*21*0144******# በ0144****** ቦታ የፈለጉትን የሞባይል ወይም መደበኛ
ስልክ ቁጥር ያስገቡ ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፈለጉ #21# ብለው ይደውሉ ማለትም ስልክዎ ዳይቨርት ከተደረገ #21# ሲደውሉ ወደ ኖርማል ይመለሳል ዳይቨርቱ ይጠፋል *#21#
ከሆነ ስልኩ ዳይቨርት ተደርገዋል ወይስ አልተደረገም የሚል መረጃ ይሰጠናል
2. ስልክዎ ቢዚ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *67*የፈለጉትቁጥር# ብለው
ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #67# ይደውሉ
3. ስልክዎ ካልተነሳ ብቻ ዳይቨርት ለማደረግ *61*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #61# ይደውሉ
4. ስልክዎ ከኔትዎርክ ዉጪ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *62*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ለማጥፋት ሲፈልጉ #62# ብለው ይደውሉ!
5. ኮል ወይቲንግ አክቲቭ ለማደረግ ሲፈልጉ *43# ብለው ይደውሉ! ኮል ወይቲንግ ለማጥፋት ሲፈልጉ #43# ብለው ይደውሉ! ኮልወይቲንግ አክቲቬት መደረጉ ወይም አለመደረጉ ለማወቅ *#43# መደወል
6. ሲደውሉ ስልክ ቁጥርዎ እንዳይታይ ወይም በሌላ ቁጥር ተክተው ለመደወል
ሲፈልጉ #31#የሚደውሉት ቁጥር ከዛ መደወል
☞አንዳንድ ስልኮች #31# ከተደወለ በኀላ የምንደውለውን ቁጥር እናስገባለን በእኛ አገር ኔትዎርክ ላይሰራ ይችላል።
➖➖➖❇️ @ysakelectronics❇️➖ ➖➖
👋❤️ሰላም ሰላም ዉድ ቤተሰቦቼ❤️👋
ዛሬ ደሞ በብዙ amdroid ስልኮች ላይ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥም ችግርን 90% የሚፈታ መፍትሄ ይዤላችሁ መጥቻለሁ።
ሰልኮ app install ስታደርጉ
"App not installed"
ሲላችሁ ይቺን step ተጠቀሙባት።
Step 1: 'apk editor' የሚባል apk. ያዉርዱ (አፑን ከታች post አረገዋለዉ)
Step 2: አፑን install ካደረጋችሁ ብሇላ
Select APK from APP-->common edit
Step 4: install location የሚለዉን default አድርጉት።
Step 5: እና ዋነኛው "version code " የሚለዉን ቁጥር መቀየር ነዉ።
ኮዱን ስትቀይሩ ከ ስልካችሁ ጋር የሚሄድ መሆን አለበት(ሌላ install ከሆነ app ላይ አይታችሁ ኮዱን መቀየር ትችላላችሁ)።
Step 6: save አድርጎ install ማድረግ ነዉ።
እንዲ ለፍቼ ለማቀርብላችሁ መረጃ like(👍👍) ለማረግ ትሰስታላችሁ😢😢
Share እና like አርጉታ
👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAFEzzpz4Tn1x8Ns3ZA
ታዋቂው የሳይበር ደህንነት ኩባንያ አቫስት # avast ' የመረጃ ጥቃት አስተናግዷል
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የመረጃ በርባሪዎች ታዋቂውን የሳይበር ደህንነት ኩባንያ የአቫስት 'Avast' ኔትዎርክ ጥሰው መግባታቸውን መረጃ መበርበራቸው ተነግሯል፡፡
የተሰነዘረው ጥቃት በኩባንያው የግብይት ሰንሰለት ለመቆጣጠር በማሰብ ሲክሊነር #CCleaner ላይ ተነጣትሮ የተፈጸመ እንደነበር ተነግሯል፡፡
በፈረንጆቹ መስከረም 25/2019 የመረጃ ጥቃቱ የታወቀ ሲሆን የመረጃ በርባሪዎች ጥቃታቸውን በግንቦት 14 እንደጀመሩም ተገልጿል፡፡
ስለተፈጸመው የመረጃ ጥቃት ምርመራ እያደረገ መሆኑን አቫስት የገለጸ ሲሆን ደህንነቱ ባልተጠበቀ ስፍራ የነበሩ ማስረጃዎችን "የቨርቿል ፕራይቬት ኔትዎርክን" VPN"'ን አስታከው ጥቃቱን መፈጸማቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
ወንጀለኞቹ የሳይበር ጥቃቱን ለማድረስ እጅግ የዘመነ ቴክኖሎጂ መጠቀማቸውን የኩባንያው ከፍተኛ ኢንፎርሜሽን ደህንነት መኮንን የሆኑት ጃያ ባሉ ገልጸዋል፡ት
ሲክሊነር በጥቃቱ ኢላማ የሆነ የተቋሙ ምርት መሆኑን ተከትሎ "አቫስት" ችግሩን በመለየት የሲክሊነርን መደበኛ ማዘመኛ (update) መስከረም 25 አቋርጦ ነበር፡፡
ኩባንያው ሲክሊነር 5.62 እትም /version/ በተጠቃሚዎች ላይ ጉዳት አለማድረሱን ካረጋገጠ በኋላ ይፋዊ የሆነ መልኩ በፈረንጆቹ ጥቅምት 15 መልቀቁን ገልጿል፡፡
አቫስት ያቀረበው የተሻሻለው እትም 'version' ከ5.57 ወደ እትም 5.62 የተለወጠ ሲሆን ደንበኞች አዲሱን እትም በማውረድ እና በማዘመን ሊደርስባቸው የሚችለውን የመረጃ ጥቃት ሊከላከሉ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል፡፡
ኩባያው ሰርጎገቦች ለመያዝ እስካሁን የቪፒኤን ፐሮፋይሉን ንቁ በማድረግ እና የደራሽነቱን ሁኔታ (access) በመከታተል የጉዳት መቀነሻ እርምጀዎች እስኪኪጫኑ ድረስ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን አሳውቋል፡፡
ምንጭ፡- www.bleepingcom
© INSA
ሁለቱ ሕጎች
“የውሸተኛ ቅጣቱ በሰዎች ያለመታመን ብቻ አይደለም፣ ከዚያ የከፋው ቅጣቱ እርሱ ራሱ ማንንም ለማመን አለመቻሉ ነው” - George Bernard Shaw
አንዳንድ ሰዎች መልካምና ጨዋ የሚሆኑት ካላቸው ጨዋ ማንነት ወይም የመልካም ስነ-ምግባር ዲሲፕሊን ተነስተው ሳይሆን ቅጣት ስሚፈሩ ብቻ ነው፡፡ ይህ ጠባብ አመለካከት ወደተበላሸ ማንነት እንድንወርድ የሚዳርግ አመለካከት ነው፡፡ ከአንድ ትክክል ካልሆነ ነገር መቆጠብ የሚገባን ዋና ምክንያት፣ ነገሩ ትክክል ስላልሆነና ጎጂ ስለሆነ ሊሆን ሲገባው፣ ለጊዜው ከቅጣት ለማምለጥ ወይም ጊዜያዊ ጥቅምን ለማግኘት ከሆነ ሁኔታው የማንነትን ብልሹነት አመልካች ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ማንኛውም ክፉ ተግባራችን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከቅጣት አያመልጥም፡፡
በአለም ላይ ሁለት አይነት ሕጎች አንዳሉ በማሰብ መጀመር እችላለን፡፡ አንዱን ሕግ “የተፈጥሮ ሕግ” በማለት መሰየም ስንችል፣ ሁለተኛውን ሕግ ደግሞ “ሰው-ሰራሽ” ሕግ በማለት ልንሰይመው እንችላለን፡፡ ማንኛውም ተግባራችን ከእነዚህ ከሁለቱ ሕጎች በአንዱ ከመዳኘት በፍጹም አያመልጥም፡፡
“ሰው-ሰራሽ” ብለን የሰየምነው ሕግ አንድ የተከለከለ ነገር አድርገን ስንያዝ በተደነገገው ሰው-ሰራሽ ሕግ መሰረት ስንዳኝና ስንቀጣ ማለት ነው፡፡ “የተፈጥሮ ሕግ” ብለን የሰየምነው ደግሞ ምንም እንኳ ለጊዜው ከሰው-ሰራሽ ሕግ የምናመልጥበትን መንገድ ብናመቻች የሰራነው ስራ ቀስ በቀስ ዘሩ በቅሎ ሊቀጣን የመቻሉ ሁኔታ ነው፡፡
የምናደርጋቸውንም ሆነ ከማድረግ የምንገታባቸውን ነገሮች በሙሉ ከእነዚህ ሁለት ሕጎች አንጻር ብንመለከታቸው አመለካከታችንን የማስፋት ጠቀሜታ አለው፡፡
የምናደርጋቸውና ከማድረግ የምንገታቸው ክፉም ሆኑ ደግ ተግባሮቻችን የሚዳኙት በሁለት ሕጎች መሆኑን መገንዘብ የአመለካከት ዘይቤአችንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የመቀየር ጉልበት አለው፡፡ ዛሬ የማደርገውም ሆነ የምናገረው ጤና-ቢስ ነገር እጅ በእጅ ባይቀጣኝም ፈጠነም ዘገየም ፍሬው በቅሎ ጭማቂውን እንደምጎነጨው ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡
እያንዳንዱ ተግባሬ እንደዘር ስለሆነ ማለት ነው፡፡ ዛሬ አንድ መልካም ነገር ማድረግ እንደሚገባኝ እያወኩኝ ምንም እንኳን ማድረግ ባልፈልግና እጅ-በእጅ የሚከፈለኝ ዋጋ እንደሌለ ባስብም፣ በውስጤ ካለው መርህ የተነሳ በማድረጌ ምክንያት ነገ የሚበቅለውን ጣፋጭ ፍሬ መመገቤ አይቀርም፡፡ ይህ በፍጹም ሊሻር የማይችል ዘላቂ ሕግ ነው፡፡ ወይ እንተባበረዋለን፣ ወይም ደግሞ በተቃራኒው ሄደን የማንፈልገውን ውጤት ስንቀበል እንኖራለን፡፡ ምርጫው የእኛው ነው፡፡
ለህሊና እንኑር … ለሕዝብ እንኑር … ለመልካምነት እንኑር !
በቅንነት ሼር ያድርጉ
https://t.me/joinchat/AAAAAFEzzpz4Tn1x8Ns3ZA
📷🌻🌻ብዙ ግዜ አዲሱ አመት ሲደርስ እቃ መግዛት የተለመደ ነው። በተለይ 🌻በመስከረም ወር🌻 አዳዲስ እቃዎች ስለሚገቡ ወይንም የተለያዩ ድርጅቶች ምርታቸውን የሚያስተዋውቅ ወቅት ነው። በዚህ ግዜ ደግሞ የሞባይል አና ካሜራ ምርቶች ይተዋወቃሉ። ይህን በማስመልከት እነዚህን እቃዎች ከመግዛት በፊት ይህን ማየት ያለብን ነጥቦች በዝርዝር ተሰናድቶል።📷📲🌸🌼
🎥አፔቸር(aperture)📹
በኦፕቲክስ አፔቸር (optics aperture)ማለት ብርሃን የሚጓዝበት ቀዳዳ ወይም ፎቶ ሌንስ ቀዳዳ ሲሆን ቀዳዳው በተለያየ መጠን ብርሃን ማስገባት የሚችል ብቃት አለው። የብርሃን ምጣኔው የሚቆጣጠረው አፈሙዝ ስፋት ሲኖረው ለፎቶ በሚመጥን የብርሃን ምጣኔ በመፍቀድ የፎቶውን የብርሃን ተጋላጭነት (exposure) ይቆጣጠራል። አፔቸር የሚለካው በኤፍስቶፕ(f/stops) ሲሆን ከ 1.4 እስክ 16 ድረስ ነው። ኤፍስቶፕ ባነሰ ቁጥር ፎቶው ድምቀት ይኖርዋል በተቃራኒው ቁጥሩ በጨመረ ግዜ የፎቶው ድምቀት ወይም ብርሃን መጠን ይቀንሳል።
🔦ISO📷
አፔቸር በካሜራችን ውሰጥ የሚገባውን የብርሃን መጠን መቆጣጠሪያ ሲሆን አይሶ ደግሞ የፎቶውን መጨለም እና መብራት ይቆጣጠራል። ይህ ማለት የካሜራው ሴንሰር ምንያህል ብርሀን ማስቀመጥ ይችላል ማለት ነው። የአይሶ ቁጥር በጨመረ ቁጥር የፎቶ ግራፉ ድምቀት እየጨመረ ይመጣል በተቃራኒው የአይሶ ቁጥር ሲያንስ ፎቶግራፉ የመጨለም ባህሪ ያሳያል። በዚህ ምክንያት አይሶ ለማታ ፎቶዎች ወይም በቂብርሃን በሌለበት ወቅት ጥሩ ፎቶግራፍ እድናነሳ ይረዳል። አሁን ያሉት ካሜራዎች ISO ሃይላቸው ከፍተኛ በመሆኑ የተነሳ በትንሽ ብርሀን ማለትም በትንሽ የሻማ ብርሀን ከፍተኛ የፎቶግራፍ ጥራት ማንሳት ተችሏል። ትንሽ ISO ማለት ሴንሰሩ ትንሽ ብርሀን የመያዝ አቅም አለው ማለት ሲሆን ትልቅ ISO ማለት ሴንሰሩ ትልቅ ብርሀን የመያዝ አቅም አለው ማለት ነው ። አሁን ያሉ ካሜራዎች ከ100 እስከ 3000 በላይ ISO መጠን አላቸው።
🚪📷ካሜራ ሸተር (Camera Shutter)🎥
በያንዳንዱ ካሜራዎች ውስጥ የተለያዩ ክፍሎች ሲኖር ከዛ ውስጥ አንዱ ሌንስ ይባላል። ሌንስ (መስታያት ካሜራ) ካሜራ ውስጥ ያለ አካል ሲሆን ብርሃንን በማተኮር ወይም የመበተን ስራን ይሰራል።ሸተር ካሜራ ውስጥ የሚገኘ ሲሆን በካሜራ ሴንሰሩ ፊትለፊት የሚገኝ መጋረጃ መሰል ነው። ይህ መጋረጃው ካሜራው ፎቶ ሲያነሳ ይከፈታል። ካሜራው ፎቶ በሚያነሳበት ግዜ ሸተሩ በደንብ በመከፈት የተቻለውን የብርሀን መጠን በማስገባት ካሜራ ሴንሰር በማሳረፍ ፎቶ ለመፍጠር በቂ ብርሃን ካገኘ በሁሃላ ሸተሩ ይዘጋል።ሸተር ስፖድ ማለት የካሜራው ሸተር የሚከፍት የግዜ ርዝመት ማለት ነው። ይህ ማለት የካሜራ ሴንሰሩ በምን ያህል ግዜ ውስጥ የካሜራ ሴንሰር ለብርሃን ይጋለጣል ማለት ነው። ወይም ካሜራው ፎቶ ለማንሳት የሚወስድበት ግዜ ማለት ነው።
ረዥም ሸተር ስፒድ በምንጠቀምበት ግዜ ሴንሰሩ ለከፍተኛ ብርሃን ይጋለጣል በዚህ ግዜ ፎቶው ደብዛዛ ይሆናል። ረዥም ሸተር ስፒድ ባለግዜ ተንቀሳቃሽ ነገሮች በፎቶ ላይ ደብዛዛ ይሆናሉ።ብዙ ግዜ በመኪና ማስታወቂያ ለይ የመኪናው ፍጥነት እዳለው ለማስመሰል እንጠቀማለን። አጭር ሸተር ስፒድ ተጠቀምን ማለት ደግሞ ሴንሰሩ ለተወሰነ ግዜ ብቻ ለብርሃን ተጋለጠ ማለት ሲሆን ይህ ማለት ቅዝፈታዊ ፎቶዎች ማንሳት ይቻላል። ሸተር ስፒድ ትንሽ ከሆነ የፎቶግራፍ የመደብዘዝ ሁኔታ ይቀንሳል። ለምሳሌ በፍጥነት የሚያለፍ እቃን በ1/30 ሰከንድ እና በ1/200 ሰከንድ ፎቶ ብናነሳ 1/30 ሰከንድ ፎቶግራፍ ደብዘዝ ያለ ሲሆን 1/200 ሰከንድ ደግሞ ቀጥያለ ወይም ያልደበዘዘ ፎቶ ይወጣወል።
💻📷ሜጋፒክስል🎥📹
ሜጋፒክስል ማለት የሚሊዮን ፒክስል ጥርቅም ነው። ፒክስል ደግሞ የዲጂታል ምስል የሚገኘ አካል ሲሆን የምስሉ አነስተኛ መለኪያ ነው። ፒክስልን እንደ ነጥም ማሰብ ይቻላል። ነጥብ ተሰብስበው መስመር እንደሚሰሩ ሁሉ ፒክስል ተሰባስቦ ደግሞ ምስል ይሰራሉ ግን እደ ነጥብ አይቆጠሩም ማለት አደለም። የሜጋፒክስሉ ቁጥር ብዛት የአንድ ምስል ልቀት(resolutions) ይወስናል እና ተጨማሪ ሜጋፒክስሎች ያለው ዲጂታል ምስል ተጨማሪ ልቀት አለው ማለት ነው።በዲጂታል ፎቶግራፍ ላይ ከፍተኛ ልቀት መኖሩ ጠቃሚ ነው። ይህም ካሜራ የበለጠ ምስሎችን ለመፍጠር ብዙ ፒክሴሎችን እንደሚጠቀም ይህም የበለጠ ትክክለኛ ምስል ለመፍጠር ይረዳል። የካሜራ ሴንሰሮች ፒክስል ተብለው የሚጠሩ ብርሃን ተቀባዮች በውስጡ ይዞል።እያንዳንዳቸው እነዚህ ተቀባይም የብርሃኑን በመለካት ይመዘግባሉ። አንድ ሴንሰር እነዚህን አይነት ተቀባዮች በሚሊየን አይነት ይኖሩታል። ስለዚህ ሚሊየን ተቀባዮች ሜጋ ፒክስል ተብለው ይጠራሉ።
ብዙ ፒክስል አለ ማለት የፎቶግራፍ ጥራት ይጨምረዋል ማለት ላይሆን ይችላል። ለምሳሌ ገበያ ላይ ያሉ ስልኮች እስከ 25 ሜጋፒክስል ድረስ ሲኖሩ የሳምሰንግ እና አይፎን ስልኮች ለምን ከ13 ሜጋፒክስል ሆነው እንዴት በጥራት ይበልጣሉ? ይህነን ለመመለስ ከላያ የተጻፉትን የካሜራ ባህራት ማየት ትሩ ነው። በነዚህ ስልኮች በላቀ መልኩ ይተገበራሉ በተጨማሪም የፎቶግራፍ ጥራቱ በሜጋፒክስሉ ብቻ ሳይሆን በሴንሰሩ የቁመት መጠን ይወሰናል። ለምሳሌ ካሜራው 30 ሜጋፒክስል ሆኖ ፒክስል ሴንሰሩ ትንሽ ከሆነ የ20 ሜጋፒክስሉ ትልቅ ሴንሰር ያለው የላቀ ጥራት አለው ማለት ነው። ስለዚህ ስልክ ወይም ካሜራ በምንገዛበት ግዜ ሜጋፒክስሉ ለይ ብቻ ትኩረት አለማረግ ተገቢ ነው።
#vpn ስንጠቀም ያለው ጥቅም እና ጉዳት ?
#ጥቅሙ
በአንድ ሀገር ኔትወርክ ላይ የታገደ(restrict)የተደረገን ድረገፅ (website) መጠቀም ያስቸለናል ማለትም ኢትዩጵያ ውስጥ ሁኖ እንዳይሰራ የተደረገን ድረገፅ vpn በመጠቀም መጠቀም እንድንችል ያስቸለናል::
#ጉዳቱ:-
ያለ vpn ኢንተርኔት ስንጠቀም በተጠቃሚው እና በኢንተርኔት አቅራቢው ብቻ ነው
vpn ስንጠቀም ግን ሶስተኛ ወገን ማለትም vpn በመሀል ይገባል ይህ ሆነ ማለት ደግሞ መረጃወቻችን በሶስተኛ ወገን ላይ ይገባል hack የመደረጋችን እድል ይሰፋል
.......join mychanal
https://t.me/joinchat/AAAAAFEzzpz4Tn1x8Ns3ZA
ከላይ በነገርኳችሁ መሰረት የSOFTWARU ስም ⚠️Odin⚠️ ይባላል።ይህ sw የሚጠቅመን ስልካችን ማንኛውም የsw ችግር ካለበት ይህንን ሶፍትዌር ተጠቅመን ማስተካከል እንችላለን ማለት ነው።📲📲📲
ፍላሽ ለማድረግ ይህንን 🥇Step ይከተሉ።
1⃣ ማድረግ ያለብን የስልካችንን ባትሪ አውጥተን 🔸ሞዴሉን🔸እና 🔶አንድሮይድ ቨርዥኑን🔶 እናያለን።
2⃣ የ❗️SAMSUNG OFFICIAL FIRMWARE WEBSITE ❗️ላይ እንሄድና የስልካችንን ሞዴል በመጠቀም ❗️Flash Filun❗️ዳውንሎድ እናደርገዋለን ።
3⃣ የስልካችንን 📱power button➕volum up button➕home button📲 ስንጫነው እራሱ ስልኩ ወደ ዳውንሎድ ሞድ ይገባል ።
4⃣ ከዛ ኬብል ተጠቅመን ስልካችንን ከኮምፒውተራችን ጋር እናገናኛለን ።
5⃣ odin ንን ከከፈትን ቡሓላ ዳውንሎድ ያደረግነውን ፍላሽ ፋይል 🔱 Browse 🔱 እናደርግለታለን ።
@ethioinfo®
6⃣ ከዛ 🔰 Start 🔰 እንለውና ከዛ ሁሉን ነገር ጨርሶ ❇️ Pass ❇️ እስኪለን እንጠብቃለን ። ከዛ ስልኩ በራሱ ሰአት restart ያደርግና ይከፍታል ማለት ነው ።
@ethioinfo ®
⚠️⚠️ማስጠንቀቂያ⚠️⚠️
1.ስልካችንን ፍላሽ ካስጀመርን ቡሓላ በፍጹም መንቀል የለብንም
2.ያወረድነው ፍላሽ ፍይል የራሱ የስልኩ ሞዴል መሆኑን ማረጋገጥ አለባችሁ።
ሰላም እንዴት ናችሁ የ🌟ethio info🌟 ቻናል ተከታታዮች ዛሬ የማወራቹ ስለ 1 ሶፍትዌር ነው።ይህ ሶፍትዌር የሚጠቅመን
ስልካችንን ፍላሽ ለማድረግ ነው ይሄ ደግሞ በትንሹ ከ#300 ብር በላይ ነው ሚያስከፍለን ።ስለዚህ ከዚህ ሁሉ ወጪ በነፃ ቻናላችንን
ተቀላቅለው ገንዘቦን እያተረፉ እውቀትን ይሸምቱ 👍👍👍https://t.me/joinchat/AAAAAFEzzpz4Tn1x8Ns3ZA
#100 ላይክ ግን ያስፈልገኛል አፍጥኑት
° ° ° ፍሬሽ_ወደ_ዩኒቨርስቲ_ሲገባ
የሚስተዋሉበት 12 ጉዶች። ° ° °
1°° ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደገቡ 3 ነገሮች ለማየት ይጓጓሉ፦ በግተራ፣ ካፌና ቤተ መፃህፍት
2°° ሸሚዝ በጨርቅ ሱሪ የለበሰና ቦርሳ የያዘ ሁሉ መምህር ይመስላቸዋል
3°° አስተማሪ ክፍል ሲገባ ከወንበር ይነሳሉ (በዛው አይቀጥሉበትም)
4°° ለሙድ፣ ለመመሳሰልና ለጥናት በሚል ጫት፣ ሲጋራና መጠጥ ይጀምራሉ
5°° ትላልቅ ሻንጣዎችንና በርካታ ይይዛሉ (ድጋሚ የሚመለሱ አይመስሉም)
6°° ለአንድ ሳምንት የዶርማቸው ፅዳት ቤተ መንግስት ያስንቃል፤ ከዛ በኃላ ግን ዶርሙ የቆሻሻ ቅርጫት ይመስላል
7°° በዶርም በጋራ መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን፦ መጥረጊያ፣ መወልወያ፣ ማጠቢያ አዋጥተው ይገዛሉ
8°° የአፋልጉኝ ማስታወቂያ (መታወቂያ፣ ሚል ካርድ፣ ዶክመንት) እና የዲፓርትመንት ቅያሪ በየቦታው ይለጥፋሉ
9°° ፈተና ወጥቷል ሲባሉ እየፈለጉ ያድራሉ
10°° ፍሬሽ ላለመባል ይጥራሉ (ሱሪ ዝቅ ያደርጋሉ፣ ይላከፋሉ..)
11°° የያዙትን ገንዘብ ቶሎ ይጨርሱና ለቤተሰብ ይደውላሉ ወይም ት\ቱን ትቼ እመለሳለሁ ይላሉ
12°° ኮርስ አውት ላይን ይቸክላሉ
° ° ° ° ° ° °
🔐 ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበ በ PATTERN ወይም Password የተዘጉ ስልኮች ካለ ምንም ኢንተርኔት እና ምንም መረጃ ሳናጠፋ እንዴት መመለስ እንደምንችል ከዚህ በፊት ሰፋ ባለ ፕሮግራም መልቀቃችን ይታወሳል ለማታቁት ዛሬም እናቀርባለን።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
✏️ ኣስፈላጊ ነገሮች:-🔍
1 aroma file manager በሌላ ስልክ ማውረድ ኣለብን
2 ሚሞሪ ካርድ(ያወረድነውን app
የምንናስቀምጥበት)
3 የተዘጋው ስልክ
~~~~~~~~~~~~~
Step1:- aroma file manager ካወረዳቹ ወደ ሚሞሪ ካርዱ ጫኑት እና ካርዱ ወደ ተዘጋው ስልክ ኣስገቡት
Step2:- ከዛ ስልኩ power off እናረገው እና የ recovery stock ወይም ስልካችን ካጠፋነው ቡሃላ የ power እና የ ድምፅ መጨመርያ ኣንድ ላይ ተጭነን እንቆያለን( እንደ የ ስልኩ ኣይነት ሊለያይ ይችላል)
Step3:- ወደ recovery mode ከገባን ቡኋላ የ ድምፅ መጫኞቹ ወደ ላይ እና ታች የ power መጫኛው ደሞ እንደ ok ሁነው ያገለግላሉ
Step4:- recovery mode ላይ install zip from sd card የሚለውን ላይ ok/power button እንጫን እና aroma file manager ያስቀመጥንበት folder ገብተን install እንለዋለን
Step5:- ከዛ aroma file manager ከከፈታቹ ቡኋላ ወደ nevigate የሚለውን ትወርዱ እና automount all devices on start የሚለውን ተጭናቹ ከዛ ዝጉት።
Step 6:- step4 ላይ እንዳደረጋችሁት step6 ላይም ድገሙት
Step7:- aroma file manager እንደገና ሲከፈት ወደ data folder ከዛ system folder ትገቡ አና 'gesture.key' or 'password.key' የሚል ታገኛላቹ
Step8:- ከዛ ያገኛችሁት gesture.key or password.key ኣጥፉት ከዛ ስልካቹ reboot ኣድርጉት
Step9:- ስልኩ ሲከፈት የማትረሱትን pattern ወይም password በማስገባት መክፈት ትችላላቹ።
በመጨረሻ ለጓደኛ ለዘመድሆ ሼር
አዳዲስ መረጃ 👆join my chanal
