uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ

MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ

Відкрити в Telegram

ይህ የMS League (የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ) ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ሌሎች የማህበራዊ ድህረ ገፆቻችንን ይወዳጁ YouTube https://youtube.com/@muslim_studentsleague?si=vRpAxHG7xgXIusXh Facebook https://www.facebook.com/emsleague Instagram https://www.instagram.com/msleague23

Показати більше
8 304
Підписники
+424 години
+117 днів
+9430 днів
Архів дописів
ከተዘነጉ ሱናዎች «أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ يَتَنَفَّسُ فِي الإِنَاءِ ثَلاثًا» (رواه مسلم) «ነቢዩ (ﷺ)
ከተዘነጉ ሱናዎች «أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ يَتَنَفَّسُ فِي الإِنَاءِ ثَلاثًا» (رواه مسلم) «ነቢዩ (ﷺ) በመጠጫ ዕቃ ውስጥ (ውሃ ሲጠጡ) ሶስት እስትንፋስ ይተነፍሱ ነበር።» (ሙስሊም) በዕለት ተዕለት ውሏችን በሚያጋጥሙን ጫናዎች  ውስጥ ሆነን ጥማችንን ለመቁረጥ ስንጣደፍ ውሃን ሳናስብበት በአንድ ትንፋሽ ልንጠጣ እንችላለን። በተለይ በሰሞኑ ሀሩር ። ይሁን እንጂ የነቢያችን (ﷺ) ሱና ውሃን ሶስት ጊዜ በማቆራረጥ፣ ተቀምጦ እና ከእያንዳንዱ መጎንጨት በኋላም ዕቃውን ከአፍ በማራቅ በእርጋታ መጠጣትን ያስተምረናል። ይህንን ቀላል ተግባር  በመተግበራችን አካላዊ ጤንነታችንን ከመጠበቅና ጥማታችንን በደንብ ከማስታገሱ ባሻገር፣ በየዕለቱ በምናደርጋቸው ትናንሽ እንቅስቃሴዎች ጭምር የነቢያችንን (ﷺ) ፈለግ በመከተል ሱናቸውን ህያው ከማድረግ ባሻገር ምንዳ እንድናገኝ የሚረዳን ሰዓት የማይወስድ ቀለል ያለ ስራ ነው።

ምዝገባ ተጠናቋል! ቦታ፡ አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ (Addis cinema complex) ቀን፡ ጥቅምት 22
ምዝገባ ተጠናቋል! ቦታ፡ አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ (Addis cinema complex) ቀን፡ ጥቅምት 22

ለአላህ ዲን ፣ ለ ታላቅ ዓላማ ለመቆም አልፎም በአርአያነት እና በተምሳሌትነት ለመወሳት ዕድሜ ፈጽሞ መሰናክል እንደማይሆን የጀግናችን የሕይወት ገጾች ድንቅ ማሳያ ናቸው ። ረሱል (ﷺ) አቡ በክር እ
ለአላህ ዲን ፣ ለ ታላቅ ዓላማ ለመቆም አልፎም በአርአያነት እና በተምሳሌትነት ለመወሳት ዕድሜ ፈጽሞ መሰናክል እንደማይሆን የጀግናችን የሕይወት ገጾች ድንቅ ማሳያ ናቸው ። ረሱል (ﷺ) አቡ በክር እና ዑመርን (ረ.ዐ) ጨምሮ ታላላቅ ሶሃቦችን ያቀፈው ሰራዊት ላይ የ18 ዓመቱን ወጣት ኡሳማ ቢን ዘይድን የጦር አዛዥ አድርገው ሹመውታል። የአላህ መልእክተኛ የልብ ወዳጅ ተብሎ የሚጠራው ይህ ወጣትም የሮምን ኃያል ሰራዊት ለመጋፈጥ ጦሩን በብቃት መርቷል።በዕድሜው ትንሽ ቢሆንም በነብዩ (ﷺ) እምነት ተጥሎበት ታላላቅ ጀግኖች በተሰለፉበት ሠራዊት ላይ አዛዥ ሆኖ መሾሙ፣ ወጣቶች በአላህ መንገድ ላይ ትልቅ ኃላፊነት ወስደው ለኡማው ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ ለዘንጊ አስታዋሽ ነው።

﴿ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اجْتَنِبُوا كَثِيرًا مِّنَ الظَّنِّ إِنَّ بَعْضَ الظَّنِّ إِثْمٌ ۖ وَلَا تَجَسَّسُوا وَلَا ي
﴿ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اجْتَنِبُوا كَثِيرًا مِّنَ الظَّنِّ إِنَّ بَعْضَ الظَّنِّ إِثْمٌ ۖ وَلَا تَجَسَّسُوا وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ﴾ «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከብዙ ጥርጣሬዎች ተቆጠቡ፤ አንዳንድ ጥርጣሬዎች ኃጢአት ናቸውና። እርስ በርሳችሁም አትሰልሉ፤ አንዳችሁም ሌላውን አታሙ። ከእናንተ አንዱ የሞተውን ወንድሙን ሥጋ መብላትን ይወዳልን? በእርግጥ ትጠሉታላችሁ። አላህንም ፍሩ፤ አላህ ንስሐን በጣም ተቀባይ፣ እጅግ አዛኝ ነውና።» (📖 ሱረቱል ሑጁራት፣12) ሰዎችን ከመፍረዳችን በፊት ራሳችንን እንመርምር። የሌሎችን ጉድለት ከመፈለጋችን በፊት የራሳችንን ስህተት እናስተካክል። የሌሎችን ክብር እንጠብቅ፤ አንድ ቃል ልብን ሊሰብር እንደሚችል አንርሳ። አንደበታችንን ከሐሜት፣ ልባችንን ከጥላቻ፣ ሐሳባችንንም ከመጥፎ ጥርጣሬ እንጠብቅ። ሰዎች የማያዩትን ሁሉ አላህ ያያል። ሰዎች የማያውቁትን ሁሉ አላህ ያውቃል። ስለዚህ ልባችንን በንጽሕና፣ አንደበታችንን በዚክር፣ ሕይወታችንንም በመልካም ሥራ እናሳምር። اللهم صل وسلم وبارك على محمد ቀልባችን ከመጥፎ ጥርጣሬ የምትፀዳበት ሀገራችን ሰላም የምትሆንበት፣በሩቋ ሀገር ያሉትም ያሉበትን ጭንቅ የሚረሱበት ከአላህ የሆነ እርዳታ እና ድል የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣ ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት፣ በሰለዋት፣ በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ የተዋበ... መልካም ጁምዐ✨

2 ቀን ብቻ ቀርቷል! 🚨 ምዝገባ ሊጠናቀቅ 2 ቀን ብቻ ቀርቷል! የኮሌጅ ተማሪዎች፣ ይህን ዕድል እንዳያመልጣችሁ! 👇 አሁኑኑ ተመዝገቡ! 🔗 https://ms-league.github.io/msl-ev
2 ቀን ብቻ ቀርቷል! 🚨 ምዝገባ ሊጠናቀቅ 2 ቀን ብቻ ቀርቷል! የኮሌጅ ተማሪዎች፣ ይህን ዕድል እንዳያመልጣችሁ! 👇 አሁኑኑ ተመዝገቡ! 🔗 https://ms-league.github.io/msl-event/ #MSL #MuslimStudentsLeague #RegistrationDeadline

ከተዘነጉ ሱናዎች «لاَ تُصَلِّ إِلاَّ إِلَى سُتْرَةٍ ، وَلاَ تَدَعْ أَحَدًا يَمُرُّ بَيْنَ يَدَيْكَ» «ወደ ሱትራ (ጋሻ) እንጂ ሶላት አትስገድ፤ ማንም ሰው ከፊትህ እንዲያልፍ አትተው።» (አቡ ዳዉድ) ሁለተኛው የእስልምና እርከን የሆነው ሰላት የአላህን( ﷻ) ትዕዛዝ በመፈፀም ከእርሱ ጋር የምናደርገው ወቅታዊ የልብ ወይይት እንደመሆኑ መጠን ትኩረታችን እንዳይሰረቅ  ከፊት ለፊታችን የሚያልፉ ነገሮችን መከላከል የሰላታችንን ጥራት ይጨምርልናል። በግቢ (Campus) አከባቢ፣ በዶርም ወይም በመስጂድ ብቻችንን በምንሰግድበት ጊዜ ከፊታችን ቦርሳችንን ወይም ወንበርን እንደ ሱትራ አድርገን ማስቀመጥ የነቢያችን (ﷺ)  ሱና ነው። ይህን ማድረግ ከሰዎች ማቋረጥ መጠበቅ ብቻ ሳይሆን፣ ልባችን በሰላቱ ላይ ብቻ እንዲያረፍ እና የሰላታችንን ደረጃ ከፍ እንድናደርግ የሚረዳን ቀላል መንገድ በመሆኑ ሁላችንም በዕለት ተዕለት ህይወታችን አስታውሰን ልናደርገው የሚገባ አስፈላጊ ተግባር ነው።

​🚨 REGISTRATION IS OFFICIALLY CLOSED! 🚨 ​Registration for the Everyday AI & Workflow Automation Masterclass has officially ended as of 1:00 PM (7:00 LT). ​🙏 Thank You! A huge thank you to everyone who registered and showed such incredible interest! We are thrilled to have you on board and can’t wait to dive into practical AI workflows and automation with you. ​📌 Next Steps for Registered Participants: If you have already registered but haven't joined our dedicated Telegram group yet, please join right now! All Zoom links, session updates, and your bonus AI Prompt Library & Cheat Sheet will be shared exclusively in the group. ​👉 Registered participants, join the group here: https://t.me/+UIDVGy4wU9NkNzZk ​See you in the session! 🚀

Reminder: Registration for Everyday AI & Workflow Automation Masterclass ends at 1:00 PM (7 LT). If you have already registered, make sure to join our dedicated Telegram group right now to get the Zoom links, session updates, and your bonus AI prompt library & cheat sheet. ​👉 Registered participants, join the group here:https://t.me/+UIDVGy4wU9NkNzZk If you haven't registered yet, please register here https://forms.gle/2BixSkSC6XbsTTsz7 and join the group.

​🚨 Registered for the 4-Day Everyday AI & Workflow Automation Masterclass? ​We kick off tomorrow! If you have already regist
+1
​🚨 Registered for the 4-Day Everyday AI & Workflow Automation Masterclass? ​We kick off tomorrow! If you have already registered, make sure to join our dedicated Telegram group right now to get the Zoom links, session updates, and your bonus AI prompt library & cheat sheet. ​👉 Registered participants, join the group here:https://t.me/+UIDVGy4wU9NkNzZk ​Event Quick Reminder: 🗓 Starts: Saturday, Oct 17 (4 Days) ⏱ Time: 9:00 PM (3:00 LT) 📍 Platform: Online (Zoom) 🎙 Led by: Arefat Muhammed Organized by MS-League ​(Haven't registered yet? Claim one of the last spots here: https://forms.gle/2BixSkSC6XbsTTsz7) ​#AI #PromptEngineering #WorkflowAutomation #Productivity #MSLeague

﴿إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ﴾ سورة الأحقاف: ١٣
﴿إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ﴾ سورة الأحقاف: ١٣ «ጌታችን አላህ ነው ያሉት፣ ከዚያም በእምነታቸው ላይ የጸኑት፣ በእነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም።» (ሱረቱል አሕቃፍ 13) 🤍 قال رسول الله ﷺ: «قُلْ آمَنْتُ بِاللَّهِ، ثُمَّ اسْتَقِمْ» 📚 رواه مسلم (٣٨) «በአላህ አምኛለሁ በል፤ ከዚያም በእምነትህ ላይ ጽና።» እውነተኛ የኢማን ውበት በቃላችን ብቻ አይደለም፤ በሥራችን፣ በትዕግሥታችን፣ በአምልኮአችንና በአላህ ላይ ባለን ጽናት ይገለጣል። ሰዎች ቢለወጡ፣ ሁኔታዎች ቢቀየሩ፣ መንገዱም ቢከብድ፤ ከአላህ ጋር ያለን ግንኙነት እንዳይዳከም እንጠብቅ። በመልካም ሥራ እንጽና፣ ከሐራም ነገረ እንራቅ፣ ምሕረቱንም በተስፋ እንጠብቅ። اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين በኢማናችን ላይ የምንፀናበት፣ሀገራችን ሰላም የሚሆንበት፣በሩቋ ሀገር ያሉትም ያሉበትን ጭንቅ የሚረሱበት ከአላህ የሆነ እርዳታ እና ድል የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣ ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት፣ በሰለዋት፣ በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የተዋበ... መልካም ጁምዐ✨

📢 ምዝገባው ቀጥሏል! ቦታ ከመሙላቱ በፊት ከታች ባለው ሊንክ ተመዝገቡ! #MSL #CollegeStudents #SpecialEvent #AddisAbaba

የዓመቱ መጀመሪያ ላይ አብዛኞቻችን የትምህርት ውጤታችንን ለማሻሻል፣ ጤናችንን ለመጠበቅ፣ መጥፎ ልማዶችን ለመቀየር ወይም ጠቃሚ ልማዶችን ለመጨመር እቅድ እናወጣለን። ከጊዜ በኋላ ግን ስንፍና፣ ትኩረት ማጣትና መዘናጋት ካቀድነው ለመድረስ እንዲከብደን ያደርጋሉ። ስለዚህ ብዙ ጥናቶችና አነቃቂ መጻሕፍት ቢኖሩም፣ ነቢዩ ﷺ ራሳችንን ከስንፍና እንድንጠብቅ የተዉልንን ሱናዎች ማወቅና መተግበርን የሚደርስ የለም። ከስንፍና ራሳችንን ለመጠበቅ ዱዓ ማድረግ አንዱ መንገድ ነው። ነቢዩ ﷺ ከጭንቀት፣ ከሀዘን፣ ከአቅም ማነስ እና ከስንፍና አላህን ይማጸኑበት የነበረውን ዱዓ መጨመር እንዲሁም አካላዊ እንቅስቃሴን ማዘውተርም ይመከራል። ረሱላችን ሰ.ዐ.ወ በሕይወታቸው ንቁና ተንቀሳቃሽ ነበሩ፤ እኛም በየቀኑ ትንሽ እንቅስቃሴ በማድረግ ሰውነታችንን ከዝግመት መጠበቅና አእምሮአችንን ንቁ ማድረግ እንችላለን። በተጨማሪም ምግብንና እንቅልፍን በልኩ ማድረግ የሚበጅ ሲሆን  ቀጣይነት (consistency) የምንለው ጽንስ ሀሳብ ደግሞ ስንፍናን  ለማስወገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። ስለዚህ ትምህርት ላይ፣ ስራ ላይም ሆነ ሌሎች ኢባዳዎች ላይ አንዳች ስንፍና አልያም ከእቅዳችን እንደራቅን ሲሰማን ፣ ሁሉንም በአንድ ጊዜ ለመለወጥ ከመሞከር ይልቅ አንድ ሱና፣ አንድ ትንሽ ተግባር፣ አንድ እርምጃ በማለት እንጀምር።

«اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الهَمِّ وَالحَزَنِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ العَجْزِ وَالكَسَلِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ الجُبْن
«اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الهَمِّ وَالحَزَنِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ العَجْزِ وَالكَسَلِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ الجُبْنِ وَالبُخْلِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ غَلَبَةِ الدَّيْنِ وَقَهْرِ الرِّجَالِ» “አላህ ሆይ! ከጭንቀትና ከሀዘን፣ ከአቅም ማነስና ከስንፍና፣ ከፍርሃትና ከስስት፣ ከዕዳ መብዛትና ከሰዎች መጨቆን በአንተ እጠበቃለሁ።” ሰሒሕ አል-ቡኻሪ (6369)

Join the 4-Day Everyday AI & Workflow Automation Masterclass organized by MS-League Academic and Tech Empowerment Wing, led by Arefat Muhammed! Whether you are studying or working, discover how to turn tools like ChatGPT, Claude, and Gemini into your personal productivity engine. What you will master: 💡 High-impact Prompt Engineering & Ideation 📄 Synthesizing heavy documents & automated research 📅 Building realistic study & project roadmaps ✍️ Crafting polished reports, emails, and drafts in seconds 🎁 Bonus: Walk away with a personal AI prompt library & workflow cheat sheet! Details: 🗓 Start Date: Saturday, OCT 17 ⏱ Time: 9:00 PM (3:00 LT) 📍 Platform: Online (Zoom) ⏳ Duration: 4 Days ⚠️ Limited spots available! Slots are filling up fast, so make sure to claim yours before registration closes. 🔗 Register now: https://forms.gle/2BixSkSC6XbsTTsz7 #AI #PromptEngineering #WorkflowAutomation #Productivity #MSLeague

Ready to stop wasting hours on repetitive tasks and make AI work for you? 🚀
+1
Ready to stop wasting hours on repetitive tasks and make AI work for you? 🚀

ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ (MSL) ከአዲስ አበባ ከሚገኙ ኮሌጆች ጋር በመተባበር ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅቶላችኋል! በፕሮግራሙ በመሳተፍ የሚከተሉትን ዕድሎች ያገኛሉ፦ ✅ የMSL አባል የመሆን ዕድል ✅ MS
ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ (MSL) ከአዲስ አበባ ከሚገኙ ኮሌጆች ጋር በመተባበር ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅቶላችኋል! በፕሮግራሙ በመሳተፍ የሚከተሉትን ዕድሎች ያገኛሉ፦ ✅ የMSL አባል የመሆን ዕድል ✅ MSL በሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞች ላይ የመሳተፍ ዕድል ✅ የሊደርሺፕና የግል እድገት ስልጠናዎች ✅ ሰርተፊኬት የሚሰጥባቸው ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ✅ አካዳሚክ ሜንቶርሺፕ 🎁 ልዩ ሰርፕራይዝም ይጠብቃችኋል! 📌 ዕድሉን እንዳያመልጣችሁ ከታች ባለው ሊንክ አሁኑኑ ተመዝገቡ፦ 🔗 [https://ms-league.github.io/msl-event/]

እኛም እንሮጣለን። ለውጤት፣ ለዲግሪ፣ ለሥራ፣ ለቤተሰብ፣ ለወደፊት። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ሩጫ ውስጥ፣ አንድ ጥያቄ በጸጥታ ይከተለናል፦ ወዴት እየሄድን ነው? ዓለምን ለማሸነፍ እየሮጥን ነው?ወይስ  አኼራችንን ? አላህ እንዲህ ይላል፦ وَٱبْتَغِ فِيمَآ ءَاتَىٰكَ ٱللَّهُ ٱلدَّارَ ٱلْـَٔاخِرَةَ ۖ وَلَا تَنسَ نَصِيبَكَ مِنَ ٱلدُّنْيَا ۖ وَأَحْسِن كَمَآ أَحْسَنَ ٱللَّهُ إِلَيْكَ ۖ وَلَا تَبْغِ ٱلْفَسَادَ فِى ٱلْأَرْضِ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلْمُفْسِدِينَ "አላህ የሰጠህን ነገር ተጠቅመህ የአኼራን ሕይወት ፈልግ፤ ነገር ግን ከዱንያም ያለህን ድርሻ አትርሳ። አላህ እንዳመለከተልህ አንተም መልካም አድርግ"። ቁርአን 28፥77 ይህ አያ ብዙ ነገር  የሚያስተምረን አንድ ትልቅ ሚዛን ነው።ዱንያን ትተን አኼራን ብቻ አንፈልግም፤ አኼራን ረስተን ዱንያንም አንከተልም።እውነት ነው መማር ፣መሥራት እና ሕልማችንን መከተል አለብን። ነገር ግን የሶላት ጊዜ ሲደርስ ፣ ተጣሪው  ሲጣራ፣የቁርአን ድምፅ ስንሰማ የፈተናውን ገጽ ለጥቂት ደቂቃዎች እንዝጋ፤ ብዕራችንን እናስቀምጥ፤የምድርን ጩኸት ዝም አስብለን ወደ ፈጣሪያችን እንጠጋ ፤ ከመጽሐፉ ተነስተን ወደ ሰገድንበት ምንጣፍ እንመለስ። ምክንያቱም የምንማርበትን አእምሮ ፣ የምንይዘውን ጊዜ እና የምትከተለውን ሕልም በልባችን ያስቀመጠውም እርሱ ነው። አንድ ቀን ይህ ክፍል ባዶ ይሆናል፤ የዛሬው ፈተና ይረሳል፤ የዛሬው ውጤት ቁጥር ብቻ ይሆናል፤ የዛሬው ዲግሪም ከእጃችን ይወጣል፤ ነገር ግን ከአላህ ጋር ያሳለፍነው ጊዜ፣ ያደረግነው መልካም ሥራ፣ ያለን ኢማን ለወዳኛው ቤታችን ይቀመጥልናል። መጽሐፋችንን አንክደን ቁርዓናችንም አቧራ አይልበስ። ዲግሪያችንም የዓለም መንገዳችንን ያሳምርልን።ኢማናችን ደግሞ የአኼራውንን መንገድ ያብራልን።ሁለቱንም እንያዝ፤ አንዱን ለሌላው ሳንሰዋ። በአንድ እጁ መጽሐፍ፣ በሌላ እጁ ደግሞ ሱጁድ ለማድረግ መሬቱን ይደገፍበታል። እንዲህ ነው የሙስሊም ተማሪ ጉዞ።

ጠዋት ነው። የዩኒቨርሲቲው ግቢ በተማሪዎች ድምፅ ተሞልቷል። አንዱ መጽሐፉን በእጁ ይዞ ወደ ክፍል ይሮጣል፤ ሌላው የፈተና ሰዐት ደርሶበት ይጣደፋል። ኮምፒውተሮች ተከፍተዋል፣ መጽሐፍት ተገልጠዋል፣ ሕ
ጠዋት ነው። የዩኒቨርሲቲው ግቢ በተማሪዎች ድምፅ ተሞልቷል። አንዱ መጽሐፉን በእጁ ይዞ ወደ ክፍል ይሮጣል፤ ሌላው የፈተና ሰዐት ደርሶበት ይጣደፋል። ኮምፒውተሮች ተከፍተዋል፣ መጽሐፍት ተገልጠዋል፣ ሕልሞችም በየልባችን ይሮጣሉ።

አዲስ አበባ ወስጥ ለምትገኙ ለኮሌጅ ተማሪዎች በሙሉ! ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ (MSL) ከአዲስ አበባ ከሚገኙ ኮሌጆች ጋር በመተባበር ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅቶላችኋል! በፕሮግራሙ በመሳተፍ የሚከተሉትን ዕድሎች ያገኛሉ፦ ✅ የMSL አባል የመሆን ዕድል ✅ MSL በሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞች ላይ የመሳተፍ ዕድል ✅ የሊደርሺፕና የግል እድገት ስልጠናዎች ✅ ሰርተፊኬት የሚሰጥባቸው ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ✅ አካዳሚክ ሜንቶርሺፕ 🎁 ልዩ ሰርፕራይዝም ይጠብቃችኋል! 📌 ዕድሉን እንዳያመልጣችሁ ከታች ባለው ሊንክ አሁኑኑ ተመዝገቡ፦ 🔗 [https://ms-league.github.io/msl-event/]

🎉 የምስራች ለኮሌጅ ተማሪዎች በሙሉ! ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ (MSL) ከአዲስ አበባ ከሚገኙ ኮሌጆች ጋር በመተባበር ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅቶላችኋል! በፕሮግራሙ በመሳተፍ የሚከተሉትን ዕድሎች ያገኛሉ፦
🎉 የምስራች ለኮሌጅ ተማሪዎች በሙሉ! ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ (MSL) ከአዲስ አበባ ከሚገኙ ኮሌጆች ጋር በመተባበር ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅቶላችኋል! በፕሮግራሙ በመሳተፍ የሚከተሉትን ዕድሎች ያገኛሉ፦ ✅ የMSL አባል የመሆን ዕድል ✅ MSL በሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞች ላይ የመሳተፍ ዕድል ✅ የሊደርሺፕና የግል እድገት ስልጠናዎች ✅ ሰርተፊኬት የሚሰጥባቸው ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ✅ አካዳሚክ ሜንቶርሺፕ 🎁 ይህ ብቻ አይደለም፤ ልዩ ሰርፕራይዝም ይጠብቃችኋል! 📌 ዕድሉን እንዳያመልጣችሁ ከታች ባለው ሊንክ አሁኑኑ ተመዝገቡ፦ 🔗 [https://ms-league.github.io/msl-event/]