cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ህልውናው ናፈቀኝ!!!

ይህ ቻናል ባሉበት ቦታ ሆነው በ Amharic & Oromic Language ከእግዚአብሔር ጋር ያሎትን ግንኙነት እንዲጠነክር ይረዳዎታል፡፡ ከምናቀርባቸው መርሐ-ግብሮች መካከል፡ 👉 አዳዲስ እና የድሮ መዝሙሮች 👉 የተለያየ ይዘት ያላቸው ጽሁፎች 👉 ጥቅሶች 👉 የህይወት ምስክርነቶች 👉 ጥያቄና መልሶች 👉 ሌሎችም ብዙ ዝግጅቶችም አሉን:: አላማችን የፅዮን መንገደኞችን ለጉዞአቸው ማዘጋጀት ነው።

Більше
Рекламні дописи
262
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
-130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ዘለቄታ የሌለው ነገር ዘላቂ የሆነ ነገር አይሰጠንም፣ የሆነ ቦታ ላይ ያልቃል - ልክ እንደ እጃችን ስልክ ባትሪ። ዘላለማዊን ነገር ጊዚያዊ ከሆነ ነገር አንሸምትም፡፡ ዘላለማዊ ነገር ዘላለማዊ ማንነትን ይጠይቃል። ኤሳው በበላው የምስር ወጥ ውስጥ፣ አካን ሰርቆ በደበቃቸው ብርና ወርቅ ውስጥ ይሁዳም ጌታውን ሽጦ ባገኛት ሰላሳ ብር ውስጥ ዘላለማዊነት የለም:: ዘላለማዊነት ክርስቶስ ጋር አለ: ለዚህም እርሱ ብሉኝ ጠጡኝ አለ ከእርሱ በልተን ጠጥተን ዘላለማዊነትን እናገኝ ዘንድ:: Do not expect permanent thing from impermanent things. @Thegracee @Thegracee
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Показати все...
ሰው እንዴት እንደሚያስብና ለሐሳቡ ደግሞ ምን አይነት አመክንዮአዊ መነሻ እንዳለው ማወቅ በጣም ደስ ይለኛል፡ በተለይ መጽሐፍ ሳነብ ጸሐፊው መጽሐፉን ለመውለድ ያበቃውን የታመቀ መረዳት ሳገኘው ደስታዬ የላቀ ነው፡ ከተለያዩ ወገኖችም ጋር በሚኖረኝ ውይይት የሐሳባቸውን “ሀሁ” መረዳትና ለዛ የሚያቀርቡትን መደገፊያ ነጥቦች መስማትም መረዳትም ከሚሰጠኝ ደስታ ሌላ ብዙ እማርበታለሁ: በተለይ ከታች ምስሉ ላይ ያለውን መጽሐፍ የጻፉትን አይነት አዋቂና የልባቸውን ምንም ሳይቀባቡ በፍጹም ቅንነትና ግልጽነት የሚናገሩ ሰዎችን መስማትም ሆነ አንኳር ሐሣባቸውን ማግኘት ወደር የለውም። እኚህ Brian Mclaren የሚባሉ ሰው (ከታች ምስሉ ላይ ያለውን መጽሐፍ ያበረከቱልን ) ብዙ መጽሐፍት ከትበውልናል፡ እድሉን አግኝቼ የታችኛውን ጨምሮ አራት መጽሐፎቻቸውን አንብቤያለሁ፡ ከእነዛም መካከል ይሄኛው በጣም ጫን ያለውና ብዙዎቻችን ልናስብባቸው የሚገቡንን ርዕሰ ጉዳዮች ያነገበ መስሎ ስለታየኝ ላካፍላችሁ ወደድሁ። ከርዕሱ ጀምሮ ጠጠር ያለ ነው፡ “Do I Stay Christian?” ምን አይነት በውስጣቸው የሚፋተግ ሐሳብ እንዳለባቸው መገመት አይከብድም፡ እሳቸው ሆነው በዛ ላይ ደግሞ የበሉትንና የጠጡትን የማይደብቁ አሜሪካዊ ሆነው እንጂ እኛ ብንሆን እንኳን እንዲህ አይነት ሐሳብ ላይ ለመጻፍ አይደለም ሐሳቡን የሚያነሳብንን ሰው ራሱ ልክ ሰይጣን በአካል የተገለጠ ይመስል ተስፈንጥረነው እንሸመጥጠዋለን። እኚህ ሰው “ክርስቲያን እንደሆንሁ እቆያለሁ?” በሚለው መጽሐፋቸው ውሥጥ ሦስት ዋና ሐሳቦች ላይ የሚያጠነጥኑ ሲሆን ለእያንዳንዳቸውም በርከት ያለ ንኡስ ርዕሶችን አካተውላቸዋል። ለዚህ የመፅሐፋቸው ርዕስ አድርገው ላነሱት “Do I Stay Christian?” ለሚለው ጥያቄ አስቀድመው የሰጡት መልስ NO የሚል ነው፡ ይሄ በአጽኖት “ፈጽሞ!” ብለው ለመለሱት መልስ ከሚያቀርቧቸው ምክንያቶች መካከል የሚከተሉት አራቱ ይገኙባቸዋል፦ 1. Because Christianity Has Been Vicious to Its Mother (Anti-Semitism) 2. Because of Christianity’s Real Master (Money) 3. Because Christianity is Stuck (Toxic Theology) 4. Because of Christianity’s Great Wall of Bias (Constricted Intellectualism) በሁለተኛ ደረጃ የሠጡት ምላሽ ደግሞ YES የሚል ሲሆን ከሚያቀርቧቸውም ምክንያቶች መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፤ 1. Because Where Else Would I Go? 2. Because I am Human 3 Because Christianity is Changing (for the Worse and for the Better) 4. To Free God በሦስተኛ ደረጃ የሚሰጡት የመፍትሄ ሐሳብ ሲሆን ርዕሱም HOW? የሚል ነው: የሚከተሉትንም ነጥቦች አካቷል፤ 1. Start with the Heart 2. Re-Consecrate Everything 3. Renounce and Announce 4. Stay Loyal to Reality 5. Stay Human እጅግ የሚገርምና ብዙ የምንማርበት መጽሐፍ ስለሆነ እንድታነቡት እጋብዛችኋለሁ። YES ብለው የመለሱትን መልስ ለማጠናከር ካቀረቧቸው ነጥቦች መካከል To Free God የሚለው ዕጅግ በጣም ልቤን የነካው ነው፡ ምክንያቱም የፈታንን እግዚአብሔርን በኃይማኖትና በሰው ስርአት እኛ ደግሞ እንዳሰርነው ምንም ጥርጥር የለኝም፡ ስለዚህም ብዙ ክርስቲያን እንደሆንሁ እንድቀር የሚያደርጉኝ ምክንያቶች ቢኖሩኝም ለእኔም እንደእኚህ ሰው To Free God የሚለው አንደኛው ነው። አላዛርን “ፍቱትና ይሂድ” ያለውን ጌታ እኛ ደግሞ በአጓጉል ሃይማኖታዊ ውቅርና ከእኛ ሌላ አዋቂና ፀዳቂ የለም፣ እንዲሁም እኛ የምንለው ብቻ ነው ዳኛም አቃቤ ህጉም በሚል የጠበበና አሰልቺ ትብታብ አስረነዋል፡፡ Whatever it takes me I, Yilkal Daniel, live to “free God” from any kind of man-made container and religious garments. በብዙ ነገር እንደ ኩሬ ውሃ ታቁረን የቀረነው ምናልባት ብትንትን አድርገው ለሚሞግቱን እንደዚህ አይነት ላሉ መፅሐፍት ቦታ ስለሌለን ይሆን? እንደኛ የፈታውን "እረኛ" ያሰረ "መንጋ" ይኖር ይሆን? @Thegracee @Thegracee
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Показати все...
𝙀𝙂𝙊 𝙞𝙨 𝙟𝙪𝙨𝙩 𝙖 𝙨𝙢𝙖𝙡𝙡 𝙩𝙝𝙧𝙚𝙚 𝙡𝙚𝙩𝙩𝙚𝙧 𝙬𝙤𝙧𝙙, 𝙬𝙝𝙞𝙘𝙝 𝙘𝙖𝙣 𝙙𝙚𝙨𝙩𝙧𝙤𝙮 𝙖 𝙗𝙞𝙜 𝙩𝙬𝙚𝙡𝙫𝙚 𝙡𝙚𝙩𝙩𝙚𝙧 𝙬𝙤𝙧𝙙 𝙘𝙖𝙡𝙡𝙚𝙙 𝙍𝙀𝙇𝘼𝙏𝙄𝙊𝙉𝙎𝙃𝙄𝙋. @Thegracee ሸምጥጦ ወይም አፍጥጦ፣ ደፍጥጦ ወይም አናፍጦ በሁሉ ነገር ማሸነፍ እንጂ መሸነፍ የማይፈልግ ተሸክመነው የምንዞረው የቅርብ ወዳጅ መሳይ ጠላት፡ በሰይጣን ከተፈተነው በላይ በዚህ የቅርብ ጠላት መከራችንን ያልበላን የለንም፡ በሰይጣን ፖሰስድ አልሆንም ነገር ግን ኢጎን እስካፍንጫችን ጢም ብለን ተሞልተነዋል፡ እልፍ ጊዜ ቢገሰጽ “አልሸሹም ዞር አሉ” ነው ነገሩ፡ ትክክለኛው ቦታ መስቀሉ ብቻ ነው፡ ለዚህ ነው ጳውሎስ “ከክርስቶስ ጋር እንደተሰቀላችሁ አታውቁምን?” በማለት የሮሜን ሰዎች ሬቶሪካል ጥያቄ የሚጠይቃቸው። ቢያምም መስቀሉ ብቻ ነው ከዚህ ቢገስጹት ዞር ከማይል አቅፎን ከሚዞረን ጠላት የሚያድነን። ፍላጎቱ ሁሉ ኃይለኛ ጸላይ፣ ኃይለኛ አምላኪ፣ ኃይለኛ ዘማሪ፣ ኃይለኛ ሰባኪ፣ ኃይለኛ መጋቢ፣ ኃይለኛ ዐቃቢ፣ ኃይለኛ ተከራካሪ፣ ኃይለኛ ጸሃፊ፣ ኃይለኛ ተቺ፣ ኃይለኛ ምናምን መሆነ ነው፡፡ ይቅርታ ዓድርጉልኝን፣ ተሳስቼአለሁ ባይነት፣ አላውቀውም፣ የአንተ ሐሳብ ትክክል ነው ባይነትን ፈጽሞ አያውቃቸውም፡ ሳይተፉበት ይተፋል፣ ሳይሰድቡት ይሳደባል፣ ሳይመቱት ይማታል፡ “ምነው? ለምን?” ተብሎ ሲጠየቅ “ለእግዚአብሔር ቀንቼ ነው” ይላል፡ ለእግዚአብሔር ቀንቶ ሰውን እንዳልነበር ያደርጋል፡ ነገሩ ግን ለእግዚአብሔር ሳይሆን በውስጡ ላነገሰው የእኔነት “እግዚአብሔር” ነው። አንድ ሰው እንዳሉት Ego የሦስት ፊደላት አንድ ቃል ቢሆንም ከአስራ ሁለት ፊደላት የተዋቀረውን Relationship የሚለውን ቃል ይንደዋል። የበሰለ ብዙ ያነበበ ወይም ተከራክሮ ያሸነፈ ሳይሆን ኢጎውን ጸጥ ያሰኘ ነው። የእናቱን ጡት እንዳስጣሉት ሕጻን ኢጎአችንን ዝም እናሰኘው። ሞታችኋልና። @Thegracee @Thegracee
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ዘንድሮስ እንዳምናው ወደ ኋላ ለመሳብ እንፈቅዳለን? ያልተሳበ ሕይወት አይስፈነጠርም: አብዝቶ የተሳበ ደግሞ እሩቅ ይሄዳል: መሳብ ቢያምም ለበጎ ነው: ነገር ግን በእግዚአብሔር እጅ መሆኑን እርግጠኛ እንሁን: ዛሬም ፈጣሪ ወደ ኋላ እየሰበ ብቻ ነው ወደፊት የሚያስኬደን: በጣም የተሳበ ደግሞ በሄደው ርቀት ያስታውቃል:: ባላውን ምን ያህል እንደሚወጥረው የሚያውቀው ባላውን የያዘው ሰው ነው፡ እኛም የሕይወታችንን ባላ በያዘው በእግዚአብሔር እጅ ላይ እንዲሁ ነን፡ ምን ያህል ወደ ኋላ ስቦ እንደሚለቀን የሚያውቀው እሱ ብቻ ነው፡ ያለን ምርጫ አምኖ ራስን መስጠት ነው ምክንያቱም አንድ እውነት እናውቃለን እርሱ ከአቅማችን በላይ "አይስበንም":: "ጭቃው በሸክላ ሰሪ እጅ እንዳለ እንዲሁ እናንተም በእኔ እጅ ናችሁ" ይህንን በእግዚአብሔር እጅ የመሆን እውነት ማወቅና መረዳት ትልቅ ትርፍ ነው ምክንያቱም ከብዙ መወራጨት እናርፋለን:: @Thegracee @Thegracee
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Показати все...
@Thegracee @Thegracee አንዳንድ ጊዜ ነገ ለሚያልፈው ችግሬ ያገሩን ዛፍ ሁሉ እቆርጠዋለሁ፡ያገሩን በሬ ሁሉ አርደዋለሁ: ትንሽዬ ብታገስ እንደ እንፋሎት ለሚተነው ፈተናዬ የቀረውን እድሜዬን ሁሉ እንደነቀዝ የሚበላብኝን ውሳኔ እወስናለሁ: አንድ ቀን አላስተኛ ላለችኝ አይጥ ቤቴን አቃጥለዋለሁ፡ አንድ ቀን አፍንጫዬ ላይ ላረፈች ዝንብ ጠብ-መንጃ እመዛለሁ። ብዙዎቻችን የዚህ ዓይነት ዛሬን ብቻ እፎይ አስብሎን ነገር ግን እድሜ ልካችንን ቁና ቁና የሚያስተነፍሰንን ነገር እንፈፅማለን: ካለንበት የአንድ ቀን አጣብቂኝ ማድረግ የምንችለውን ነገር ሁሉ አድርገን ተስፈንጥረን "እንውጣ" እንጂ "ስንወጣ" ምን ውስጥ እንደምንገባ ሳናውቅ "ማርሽ እንቀይራለን" አንዳንድ መውጣቶች መግባት እንደሆኑ አናስተውልም፡ ከፍተን የወጣን ሲመስለን ለካ ከፍተን መግባታችን ነው። ምሳውን የራበውና ዛሬ አደን ያልቀናው ሰው ዛሬን ታግሶ ወይም ዛሬን በምናምን አድሮ ነገ ለአደን ይወጣል እንጂ እናትና አባቱ ሳይሆኑ ፈጣሪ ብቻ የሚለግሰውን ብኩርና መሸጥ የለበትም:: "ብኩርና" ፈጣሪ በቸርነቱ የሚሰጠውና የእድሜ ልክ ሲሆን ለአንድ ቀን እድሜ ብቻ ለሚያኖረን ምሥር ወጥ ( whatever that lentil stew is ) አሳልፎ መስጠት ሰጪውን መናቅ ብቻ ሳይሆን "የራስን እድል በራስ መወሰንም" ነው: ከዛም "ወዮ የብኩርና ያለ!!!" እያልን ብንጮህ ለጥፋታችን ምህረት ቢደረግልንም የብኩርና ትሩፋታችን ግን ተመልሶ አይመጣም - በዕንባ ተግቶ ቢፈልገውም አላገኘውም: አንዳንድ ነገሮች Once gone always gone ናቸው። ዛሬን ሰጥቶን ዘላለማችንን ከሚገነድስብን ውሳኔም ሆነ ድርጊት እግዚአብሔር ያድነን:: አንዳንዴ ካጋጠመን ነገር መገላገል መፈለጋችን፣ እንዲሁም የምንገላገልበት መንገዱ ልብን አነውላይነቱ ተደምሮ የምናጣውን ሁሉ ብናጣ ምንም እንደማይሰማን አድርጎ ይስልልናል: ያኔ መፍራት ነው! ምክንያቱም ለዛሬ ስንል የዘላለሙን ሁሉ ልንነግድበት እንችላለንና:: "በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ እነዚህን ድንጋዯች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ" የሚለው ፈተና ቀላል አይደለም - በተለይ በተለይ ደግሞ እንደራበን በታወቀበት ሰአት የሚቀርብ ከሆነ: ያለው ምርጫ ሁለት ነው፤ ወይ እንደ ዔሳው ምስር ወጥ በመብላት ርሃብን አስታግሶ ብኩርናን ግን እንዳትመለስ አድርጎ መሸኘት፣ ወይም እንደ ኢየሱስ የፈተናዬ ጊዜ ሳያልቅ ምንም አልቀምስም ከመስመሬም አልወጣም ብሎ የእግዚአብሔር ልጅነትን ለእግዚአብሔር በመገዛት መግለፅና mission accomplished ማለት ነው:: #ጳውሎስ ሊገለጥ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ስቃይ ምንም እንዳይደል አስባለሁ:: አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ነገሮች በማምለጥ ሣይሆን የምናመልጣቸው እዛው ሆነን ነገር ግን እንደ ጳውሎስ ነገን በማየት ነው፡ ማምለጥ ሁሉ ማምለጥ አይደለም። በውሳኔ ወድቅን በውሳኔ ብንነሳም ለአይጥ ግን ቤታችንን ከማቃጠል ያድነን። @Thegracee አዎ ብዙ ሰው ለአንድ አይጥ ብሎ ቤቱን አቃጥሏል፡ የሚጠበቅብን ቤታችንን ማቃጠል ሣይሆን ከአይጥ ጋር እንዴት መኖር እንዳለብን ማወቅ ነው፡፡ Not Situation but VALUE. @Thegracee @Thegracee
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ዛሬም ሲደርሱባችሁ እግዚአብሔር ይድረስላችሁና ደገፋ ይሁናችሁ:: የዳዊት "ፔንዱለም" ሕይወት: ሁለት የስሜት ፅንፎችን ያውቃቸዋል: #አንድ በመከራው ጊዜ ጠላቶቹ ሲደርሱበት የሚሰማው የነፍስ መውጣት ስሜት #ሁለት እግዚአብሔር ደርሶለት ደገፋ ሲሆነው የሚሰማው የነፍስ መመለስ ስሜት ሁለቱንም በሕይወታችን እናጣጥማቸዋለን: Confess ወይም Claim እያደረግን ሳይሆን አግዚአብሔር እየደረሰልን ነው የምናመልጠው:: ዛሬም ሲደርሱባችሁ እግዚአብሔር ይድረስላችሁና ደገፋ ይሁናችሁ:: @Thegracee @Thegracee
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.