cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

አግዛቸው ተፈራ

"አምላኬ ሆይ፥ በፊትህ የምንለምን ስለ ብዙ ምሕረትህ ነው እንጂ ስለ ጽድቃችን አይደለምና ጆሮህን አዘንብለህ ስማ፤ ዐይንህን ገልጠህ ጥፋታችን... ተመልከት።" (ዳን. 9፥18)

Більше
Рекламні дописи
986
Підписники
Немає даних24 години
-17 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

01:53
Відео недоступнеДивитись в Telegram
14.96 MB
11
01:52
Відео недоступнеДивитись в Telegram
14.96 MB
5
ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰዱና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ቃል ወይም ሐሳብ ተጨምሮባቸው ከነጭማሪው በየሰዉ አንደበትና በጽሑፎችም ጭምር የሚዘዋወሩ ጥቅሶች አሉ። ከእነዚህ መካከል አንዱ “እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፥ አንቀላፋም፤ ከጐኑም አንዲት ዐጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው።” (ዘፍ. 2፥21) በሚለው ጥቅስ ውስጥ፣ “ከጐኑም” የሚለው “ከግራ ጐኑ” ተብሎ ነው በብዙዎች የሚነገረው፣ ምናልባትም የሚጻፈው። ልክ እንደዚሁ፣ ከጌታ ኢየሱስ ጋራ በቀኙና በግራው ስለ ተሰቀሉት ወንበዶችም፥ ሎቱ ስብሐት (ክብር ምስጋና ለርሱ ይኹንና) ጌታችንን “… አንተስ ክርስቶስ አይደለህምን? ራስህንም እኛንም አድን ብሎ” የሰደበው በግራው የተሰቀለው ነው። በመልካም ቃል ተናግሮ በመጨረሻ፣ “ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትኽ በመጣኽ ጊዜ ዐስበኝ” ያለው ደግሞ በቀኙ የተሰቀለው ነው እየተባለ ነው የሚጠቀሰው፤ የሚጻፈው። መጽሐፍ ቅዱስ ግን፥ ተሳዳቢውን ወንበዴ፣ “ከተሰቀሉት ከክፉ አድራጊዎቹም አንዱ” ብሎ ሲገልጸው፣ ተሳዳቢውን የገሠጸውንና ጌታን ዐስበኝ ያለውን ደግሞ፣ “ኹለተኛው” ብሎ ነው የጠቀሰው (ሉቃ. 23፥39፡40)፣ እንጂ ተሳዳቢውን በግራው የተሰቀለ፣ ርሱን የገሠጸውን ደግሞ በቀኝ የተሰቀለ በማለት አልገለጸውም። ይህን ስለ ወንበዶቹ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚለው በማለፍ የሚነገረው ቃል፣ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ርእስ ኾኖ ገብቶ ማየት ያጠያይቃል። በ፳፻፲፬ (2014 ዓ.ም.) በታተመው የግእዙ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 23 ከቍጥር 39 እስከ 43 የተሰጠው ርእስ “ዘከመ አምነ ፈያታዊ ዘየማን” (በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ እንዳመነ) የሚል ነው። በክፍሉ (በንባቡ ውስጥ) ግን ካልኡ (ኹለተኛው) ተብሎ እንጂ “በቀኝ የተሰቀለው” ተብሎ አልተገለጸም። የ፳፻ (የ2000 ዓ.ም.) ዕትም የዐማርኛው ሰማንያ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ እንኳ “ስለ ኹለቱ ወንበዴዎች” ነው የሚለው። አንድምታ ወንጌሉ ደግሞ ከቍጥር 33-43 ላለው ክፍል የሰጠው ርእስ፣ “በእንተ ተሰቅሎተ ኢየሱስ” (ስለ ኢየሱስ መሰቀል) የሚል ነው። ያመነው ወንበዴ በቀኝ የተሰቀለው ይኹን በግራ ባልተገለጸበት ኹኔታ፥ ታዲያ ግእዙ ከየት አምጥቶ ነው “ዘከመ አምነ ፈያታዊ ዘየማን” ያለው? በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚጨመረውን የሰው ሐሳብ ማረም ሲገባ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ያላለውን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መጨመር ተገቢ ነውን? - በርእስ ደረጃም ቢኾን። ለግእዙ መጽሐፍ ቅዱስ “ዘከመ አምነ ፈያታዊ ዘየማን” የሚል ርእስ የተሰጠው፣ በኢኦተቤ ሥርዐተ ቅዳሴ ውስጥና በሌሎችም፣ “በመንግሥትኽ በመጣኽ ጊዜ ዐስበኝ” ያለው በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ነው ስለሚል፣ ከዚያ ጋራ ለማስማማት ይኾናል። ነገር ግን ሥርዐተ ቅዳሴው ከመጽሐፍ ቅዱሱ ጋራ መስማማት አለበት እንጂ፣ መጽሐፍ ቅዱሱ ለሥርዐተ ቅዳሴው (በርእስ ደረጃም ቢኾን) መገዛት የለበትም።
Показати все...
8👍 2
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አንዳንዱ የክርስትና መልክ የተሰጠው በዓል፥ ከዚያ በፊት በአምልኮተ ጣዖት ውስጥ የነበረውን የበዓል ቀን እንዲተካ የተደረገ መኾኑ ይታወቃል። ልደታ ለማርያም ተብሎ የተሰየመው ግንቦት ፩ ቀንም፥ ቀደም ሲል ቦረንትቻ ተብሎ የሚከበረውን ባህላዊ እምነት ለመተካት የገባ ሳይኾን አይቀርም የሚል ትልቅ ግምት አለ። ደስታ ተክለ ወልድ “አምልኮ ባዕድን ለማጥፋት ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የእመቤታችንን ልደት ግንቦት ፩ ቀን አደረገው” ሲሉ ጽፈዋል። የማርያም ልደት መስከረም 10 ነው የሚሉ መኖራቸውን የሚጠቅሰው የተኣምረ ማርያም መቅድም ደግሞ፥ “እኛ ግን በተረዳ ነገር አባቶቻችን ሊቃውንት እንዳስተማሩን ልደቷን ግንቦት ባንድ ቀን ነው እንላለን” ይላል። ቀኑ ላይ ልዩነት የተፈጠረው ምናልባት ቦረንትቻን ለማስቀረት ወይም ለመተካት በሚል የተኣምረ ማርያም መቅድም ግንቦት ፩ ቀን ላይ ስለ ሠራው ይኾናል። “ቦረንትቻ በግንቦት ወር መባቻ ዠምሮ የሚደረግ የቦረን አምልኮ፤ አምልኮውም በበረት በግ ማረድ፤ ጌሾ ያልገባበት ጕሽ መጠጣት፤ በያይነቱ ቈሎ መብላት፤ ከሥጋው ብልት ኹሉ ቀንጥቦ ፈርስና ርሚጦ (በረመጥ ተጠብሶ የበሰለ የውሻ መኖ) ጨምሮ በበረቱ ፉካ ማኖር ነው።” የማርያም ልደት በሕዝቡ ዘንድ የሚከበረውም፥ በተለይ በገጠር አካባቢ ዛፍ ሥር ተሰባስቦ ንፍሮ በመቀቀል፥ ቂጣ በመጋገር፥ ከብት ዐርዶ ደም በማፍሰስ፥ ከተዘጋጀው ንፍሮና ቂጣ በመበተን ወዘተ. ነው። ይህም መመሳሰል በሕዝቡ ዘንድ በልደታና በቦረንትቻ አከባበር መካከል መወራረስ መኖሩን ያሳያል። መመሳሰሉም የመጣው አንዱ ሌላውን ለመተካት የተደረገው ጥረት ሳይሳካ በመቅረቱና ልደታ ቦረንትቻን ከመተካቱ ይልቅ ቦረንትቻ በልደታ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በማሳደሩ ምክንያት ነው ማለት ይቻላል። ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ እንደ ጻፉትም፥ የቦረንትቻ አምልኮ ክርስቲያን በኾኑም ባልኾኑም ኦሮሞዎች፣ እንዲሁም በዐማሮችና በሌሎችም ኢትዮጵያውያን በግንቦት ወር የቅድስት ማርያም ልደት (ልደታ) ተብሎ በሚታመንበት ዕለት ይከበራል። ይህን በዓል ለማክበር ሰዎች ‘አድባር’ በሚሉት እንደ ቅዱስ በሚታሰብ ዛፍ ሥር ይሰበሰቡና ምግብ (ንፍሮ) ይቀቅላሉ፤ የያዙትን ስጦታም ከቅድስት ማርያም ጋር ለሚያምታቱት ለቦረንትቻው ይሰጣሉ። ፕሮፌሰሩ በቦረንትቻና በማርያም የልደት ቀን መካከል መምታታት መፈጠሩን ይንገሩን እንጂ፥ በክርስትናው አካኼድ ቦረንትቻን ለማስቀረትና በማርያም ልደት ለመተካት የተደረገ ጥረት መኾኑን ማስተባበል አይቻልም። እንዲህም ጥረት ተደርጎ ቦረንትቻን ማስቀረት ሳይቻል፥ የማርያም ልደት በቦረንትቻው መንገድ መከበር መቀጠሉ አስገራሚ ነው። እንዲህ ሲባል ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ በይፋ የማርያምን ልደት እንጂ ቦረንትቻን እንደማታከብር፥ ይልቁንም እንደምትቃወመው መግለጥ ይገባል። የማርያም ልደት በራሱ መልኩን የቀየረ ሌላው ቦረንትቻ መኾኑ ግን አልቀረም። የጌታ እናት ቅድስት ማርያም የተወለደችበት ቀን በግእዙ “ልደታ” ተብሎ በተኣምረ ማርያም ታውጆ እንዲከበር መደረጉን ከላይ ተመልክተናል። ግንቦት ፩ ልደታ ተብሎ ሲሰየም፥ ቀስ በቀስ ቀኑ ግዘፍ ነሥቶና ማንነትን ተጐናጽፎ፥ ጾታም ተሰጥቶት በሴቴ አንቀጽ መጠራት ከጀመረ ዘመናት ተቈጥረዋል። ምናልባት ለአንዳንዶች ልደታ የማርያም ተለዋጭ ስም ወይም ማርያምን የመሰለች ሌላ ቅድስት እንስት እየመሰለች ነው። ይኹን እንጂ የልደቷን ቀን አንቺ ብሎ መጥራት ሲጀመር፥ ማንን ነው እንዲህ የምንለው? የልደቷን ቀን ሰው አስመስለን በሴት አንቀጽ አንቺ ብለን የጠራነውስ ለምንድነው? ብሎ የሚጠይቅ ግን የለም። “ልደታ ለማርያም” ማለት “የማርያም ልደት” ማለት ነው እንጂ፥ “ልደታ” የምትባል ሌላ አካል የሚፈጥር ሐረጋዊ ቃል አልነበረም፤ በጊዜ ኺደት ግን ፈጠረ። ይኹንና በዚህ ቀን እየኾነ ያለው ምንድን ነው? የማርያምን ልደት በማክበር ስም የተያዘውስ ምንድን ነው? ኹነቱን በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ስንፈትሽ አምልኮ ባዕድን መፈጸም ኾኖ ይገኛል። በዚህ ቀን በተለይ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ በየመንደሩ የሚከበረው ዘመናዊ መልክ የተላበሰ አምልኮ ባዕድ ነው። ሰዉ በየሰፈሩ ተሰባስቦ ዕርድ በማረድ፣ ስለት በመሳል (ልደታ/ልደትዬ በቀጣዩ ዓመት እንዲህና እንዲያ ካደረገችልኝ ይህንና ያን አደርጋለኹ በማለት)፣ በመብል፣ በመጠጥና በጭፈራ መንገድ እየተከበረ ነው ያለው። ይህም ቤተ ክርስቲያን የማትቈጣጠረውና ከርሷ ዕውቅና ውጪ የሚፈጸም በመኾኑ፥ የማርያም ልደት እየተከበረ ነው በሚል ሽፋን እየተካኼደ ያለው አምልኮ ባዕድ ከመባል ውጪ ሌላ ስም ሊሰጠው የሚችል አይመስልም። በውጪ በሚካኼደውና ከቦረንትቻ ጋር ተወራራሽ በኾነው የአከባበር ገጽታ ላይ ትኵረት ተደረገ እንጂ፥ የማርያም ልደት በቤተ ክርስቲያን ሲከበርም በማርያም ስም አምልኮት አይፈጸምም ማለት አይደለም። የዕለቱ የማሕሌት ቀለም (ድርሰት)፥ ቅዳሴና ስብከቱ ኹሉ ማርያምን ማእከል ያደረገ፥ ለርሷ ውዳሴና ምስጋና የሚቀርብበት ነው። ይህን አምልኮት የሚቀበለው ደግሞ ከዚህ ኹሉ ትዕይንት በስተጀርባ የሚሠራው ያው ጠላት ሰይጣን ነው። ስለዚህ አንሳት! በማርያም ልደት ስም ከሚፈጸም አምልኮ ባዕድም ራሳችንን እንጠብቅ። ጠላት ዲያብሎስ ሰዎችን ከሚያስትባቸው መንገዶች አንዱ የማያምኑትን ሐሳብ ማሳወር ነው። ሐሳቡ የታወረበት ሰው በጨለማ የሚኼድ ስለ ኾነ ምንም አይታየውምና ይህ እንዴት ኾነ? ለምን ኾነ? ወዘተ. ብሎ አይጠይቅም። የእግዚአብሔር ቃል እንደሚመሰክርልን ግን፦ መቼም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ፤ ነገር ግን በሰማይ ኾነ በምድርም ኾነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ፥ ለእኛስ ነገር ኹሉ ከርሱ የኾነ፥ እኛም ለርሱ የኾንን አንድ አምላክ አብ አለን። ነገር ኹሉም በርሱ በኩል የኾነ፥ እኛም በርሱ በኩል የኾንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን (1ቆሮ. 8፥5-6)። እንደዚሁም፥ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የኾነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በኾነው በርሱ አለን፤ ርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችኹን ጠብቁ (1ዮሐ. 5፥20-21)። (ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እና አባ እስጢፋኖስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 198-200)
Показати все...
14👍 11
"መጽሐፍ እንደሚል፦ ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል፦ በሦስተኛው ቀን ተነሣ" (1ቆሮ. 15፥3:4)
Показати все...
10
01:47
Відео недоступнеДивитись в Telegram
10.68 MB
7
ሆሳዕና ይፈጸም ዘንድ ትንቢቱ፣ የዋሁ ኢየሱስ ትሑቱ፣ በውርንጫዪቱ ተቀምጦ፣ በምስጋና በክብር አጊጦ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ፣ ምድር ተጨንቃ ተጠብባ፣ ዘመረች፤ እንዲህ እያለች፦ ሆሳዕና በአርያም፣ ለሚመጣው፣ በእግዚአብሔር ስም፣ ቡሩክ አምላክ ዘለዓለም። ሕዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ፣ ለምስጋና ተከማችቶ፣ ከኢየሱስ ጋራ ተጕዞ ልብሱን አንጥፎ ጐዝጕዞ፣ ዘንባባውን በእጁ ይዞ፤ ከሕፃናቱ አንደበት፣ ከሚጠቡት ልጆች አፍ፣ የምስጋና ጅረት ሲፈስስ፣ የውዳሴ ጐርፍ ሲጐርፍ፣ የተገባው፣ ኢየሱስ፣ ርሱ ብቻ፣ ሲወደስ፤ ስለ ተከተለው ዓለሙ፣ አለቆች አጕረመረሙ። ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና፣ ይገባዋልና ምስጋና፤ መኳንንት በሩን ክፈቱ፤ ለክብር ንጉሥ ለትሑቱ። ይብቃ ከእንግዲህ ተውኔቱ፣ መጋረጃ መዝጋት መክፈቱ፤ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ፣ ተንከራትቶ ማንከራተቱ፤ ወደ ኢየሱስ ካላደረሰን፣ ምሳሌ መመሰል ከንቱ። ይልቅ ይከፈት የልባችን በር፣ የሱስ ክርስቶስ ገብቶ እንዲኖር፤ ቀድመው የገቡት ከልባችን፣ ስላልሞቱልን፣ ስላልዋጁን ስፍራ ይልቀቁ፤ ለዋጀን ጌታ፤ በክቡር ደሙ፣ በነፍስ ስጦታ። የማይዳበል፣ ከፍጡር ጋራ፤ የታጨንለት አንድ ሙሽራ፣ ስፍራውን ሲያገኝ በልባችን፣ ሆሳዕና በአርያም እንላለን።
Показати все...
13👍 1
01:30
Відео недоступнеДивитись в Telegram
4.89 MB
2
02:03
Відео недоступнеДивитись в Telegram
46.14 MB
2
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.