cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Kedir🥁Al Hadra Official👏👏👏

🥁 ከድር አብደላ(አል-ሀድራ)🥁 ነኝ ይህ የኔ ኦፊሺያል ቻናል ነው በዚህ ቻናል የኔን ስራዋችና የሸሆቻችን መንዙማዎች ቂሳዎች ዲናዊ ደርሶችን የወደድኩአቸዉን ያመንኩባቸውን ያስደስታቹሀል ያልኮቸውን ጉዳዮች የማጋራቹ ይሆናል ሰብስክራይብ በማረግ አብራቹኝ ስላላቹ ከልብ አመሰግናለው

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
231
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

#Challenge_accepted እንሆ ሰአቱ ደረሰ 1:10 የታላቹ ወዳጆቻችን ውድ የመንዙማ አክባሪያንና ወዳጆች! የአል ቡርዳ ጀመዐን እንደሚወዱ አንጠራጠርም! ታድያ ይህን አንጋፋ ጀመዓ የሚያበረታቱበትን ቀላል መንገድ እንጠቁምዎ? ይከተሉን: — በቀጣዩ እለት ማለትም ረቡዕ (እሮብ) ከምሽቱ 1:00 ሰአት ጀምሮ እርሰዎ በሚጠቀሙባቸው face book, telegram, Instagram የመሰሉ ማህበራዊ ድህረ ገፆች ላይ ይህን የአል ቡርዳ ጀመዐ ልዩ የአልበም ምርቃት ፕሮግራም ካስተዋወቁና ይህን ፅሁፍ ለ 10 ወዳጆችዎ ካስተላለፉ እርሰዎ በርግጥም የ አል ቡርዳ ጀመዐ ወዳጅና በአቅምዎም ጀመዐውን የደገፉ ይሆናል! ለሚያደርጉት ድጋፍ ከወዲሁ እናመሰግናለን!
Показати все...
#የረጀብ_ስጦታ በ ካሊድ ማዲሑ ረሱል ♥ T #ከወርቃማ_የጉራጌ_ሙስሊም_ታሪኮች_ማህደር #ክፍል 1 👉 #ሰይድ_ኢብራሂም የአብሬት አወል ሸይኽ #የቁባ_አባ ( #ሰይድ_ባኡ_ሳኒ ) አባት ሲሆኑ የሙጥጥየ ጎይታ ኩየ የመጀመሪያ ወንድ ልጅ ነበሩ ፣ ከእስልምና በፊት #ወጃተ ተብለው ይጠሩ ነበር :: #በቦዥ ( መብረቅ ) አምልኮ #የጎይታ_ኩየ ስነ ስርአት የጎይታ ኩየ የመጀመርያ ወንድ ልጅ ቀጣዩ #ጎይታ_ኩየ ሆኖ ይሾማል ፣ ጎይታ ኩየ ብሎ ማለት #የ7ቤት_ጉራጌ በአጠቃላይ ማለት ይቻላል ያምንበት የነበረ የቦዠ አምልኮ ዋና ተጠሪ ሲሆኑ ከንጉስም በላይ የተከበሩ የሚፈሩ 7ቤት ጉራጌ ሁሉ የሚገብርላቸው መሪዎች ነበሩ ፣ በዚህ መሰርት ሰይድ ኢብራሂም ( ወጃተ ) የሚቀጥለው ጎይታ ኩየ መሆን ነበረባቸው ፣ ይሁንና እሳቸው ገና ከሶብይነት ጀምሮ አሏህ በቀልባቸው ኑረል ኢማን አኑሮላቸው ነበር #የኑፐአር ባእል እና ሌሎችም #የቦዥ ( መብረቅ ) ሀይማኖታዊ እርድ በተደረገ ወቅት ሁሉ የእናታቸውን ጡት አይጠቡም ነበር ፣ በሁዋላም ከአባታቸው ሀብት አልፈልግም ብለው ምንም አይነት ንብረት ከቤተሰባቸው አልወሰዱም:: 👉 #ንቅየ_ጎይታ ኩየ የሙጥጥየ ጎይታ ኩየ አባት የሰይድ ኢብራሂም ደግሞ አያት ማለት ነው ከልጆቼ ውስጥ አንድ የኛን ሀይማኖት የሚክድ ልጅ ይመጣል ብለው ተናግረው ነበር ፣ ሰይድ ኢብራሂም እርድ በተደረገ ወቅት የእናታቸውን ጡት በተደጋጋሚ አልጠባም ማለታቸውን አባታቸው ሲያዩ " አባቴ ሀይማኖታችንን የሚክድ ልጅ ይመጣል ብሎ ያሉት ይህ ልጅ ሳይሆን አይቀርም " ይሉ ነበር ፣ የሰይድ ኢብራሂም እናት ደግሞ " አይ ከአንቱ ዘር እንኳን እንዲ አይነት ልጅ አይወለድም አይዟቹ " እያሉ ያረጏጏቸው ነበር :: 👉 ትንሽ ከፍ ብለው ነብሳቸውን እንዳወቁም ማንም ዳእዋ ሳያደርግላቸው ወደ #ቆነት_ሸይኽ (ኢማም አረብ) ሄደው #እስልምናን ተቀበሉ ፣ የቆነት ሸይኽ (ኢማም አረብ) በደምብ የሚታወቁ ትልቅ ሸይኽ እና አህለል በይት ነበሩ ፣ የቆነት ሸህ ለሰይድ ኢብራሂም ( ወጃተ ) እስልምናን እንዴት ተቀበላቹ ቤታቹ ውስጥ ምንም አላጣቹሁም ቅቤው ማሩ ስጋው ሁሉ ነገር ሙሉ ነው ብለው ሲጠይቋቸው እሳቸውም መልሰው ለቆነት ሸይህ እርሶስ እንዴት ሰለሙ? በማለት አሏህ ለፈለገው በፈለገው መልኩ ሂዳያ እንደሚሰጥ አመላከቱ ፣ ያኔ የቆነት ሸይኽ እንዲህ አሏቸው " ነብዩሏህ ኢብራሂም አልይሂ ሰላት ወሰላም ከጣኦት አምላኪ ቤተሰብ ነበር የወጡት ፣ አንተም ከቦዥ አምላኪ ቤተሰብ ወጥተህ እስልምናን ስለተቀበልክ ኢብራሂም ብለንሀል " ብለው ስማቸውን ኢብራሂም አሏቸው :: 👉በዛን ወቅት ቸሀ ላይ የነበሩ ኢማም ጁሀር የሚባሉ በጣም ታላቅ ሰው ነበሩ ፣ የጎይታኩየ ልጅ ሰለመ ሚባል ነገር ሲሰሙ እራሴ ጎይታ ኩየን ለምን አልጠይቃቸውም ብለው ተነስተው ጎይታኩየ ጋ ሄዱ ፣ ጎይታ ኩየ ለኢማም ጁሀር አንተማ ከድተሀን የለምም ወይ ብለው አሏቸው ፣ እሳቸውም እኔ ሰው ከድቼ አላውቅም ብለው ይሏቸዋል ፣ ዛሬ እንዴት መጣህ ? ብለው ጎይታ ኩየ ጠየቋቸው ፣ የርስዎ ልጅ ሰለመ የሚባል ነገር ሰምቼ እሱን ልጠይቆት ነው የመጣሁት ብለው ይሏቸዋል ፣ እዛው እንዳሉም ሰይድ ኢብራሂምን ከርሶ ጋር ቆይታ አለኝ ብለው ይሏቸውና እንዴት ይህንን ሁሉ ምቾት ሀብት ትታቹ እንዴት ሰለማቹ ? ብለው የቆነት ሸይኽ እንዴት እንደሰለሙ እንደ ጠየቋቸው ሁሉ ኢማም ጁሀርም ጠየቋቸው ፣ ሰይድ ኢብራሂምም ልክ ለቆነት ሸይኽ እንደመለሱላቸው ለኢማም ጁሀርም እርሶስ እንዴት ሰለሙ? ድሀ ብቻ የሚሰልም ቢሆን ኖሮ በእርሶ ስር ያሉ ድሀዎች ይሰልሙ ነበር ብለው መለሱላቸው ያኔ ኢማም ጁሀር አሁን የጀመርከውን ቁርአን ጨርስ እድሜህ ለትዳር ሲደርስ ልጄን አሲያን ሰጥቼሀለው ና አባትህ ፊት ኒካ ልሰርልህ ብለው የዛኔውኑ የቁባ አባን እናትን እሜት አሲያን ኒካሀ አሰሩላቸው :: 👉 #ሰይዲ_ሰይድ_ኢብራሂም በዲናቸው በጣም ጠንካራ ነበሩ በቀን ዙህር ፣ አስር እና መግሪብ ከ ኢናንጋረ #ቆነት ለጀመኣ ይመላለሱ ነበር ፣ ከኢናንጋረ ቆነት ከ2 ሳኣት በላይ የሚያስኬድ አድካሚ መንገድ ነው ፣ አሏህ ብርታቱን እና የግዜ በረካውን ሰጥቷቸው እንጂ በሰውኛ የሚቻል አይደለም ፣ እሳቸው ለሰላት የተመላለሱበት መንገድ ከኢናንጋረ ቆነት ድረስ የእግር መንገድ ምልክት አውጥቶ እንደነበር በታሪክ አዋቂዎች ይነገራል :: 👉 እዛው ኢናንጋራ አንድ ሰው ዳእዋ አድርገው አሰልመው #ሰሏተል_ፈጅር እሱ ቤት ድረስ በመሄድ ለሰሏት ቀስቅሰውት እቤቱ ደጅ አፍ #ሰላተል_ጀመአ ሰግደው ወደ ቤታቸው ይመለሱ ነበር ፣
Показати все...
ነጃሺይ ነብዩ ﷺ ማንም እሱ ዘንድ አይበደልም ብለው የመሰከሩላቸው፣ የነብዩ ﷺ ሶሃቦችን ያስጠጉ፣ ሲሞቱም "ዛሬ ምርጥ የአሏህ ባሪያ ሞተ" ብለው ነብዩ ﷺ ያበሰሯቸው ታላቅ ሰዉ ነበሩ። ታዲያ ዛሬ ያ የተቀበሩበት ታሪካዊ ቦታ እና መስጂዱ ባልጠበቅነው መልኩ መመታቱ እና መጎዳቱ እጅግ በጣም ቀልባችንን የሰበረ ፣ ያሳዘነ እና ያስደነገጠ ክስተት ሁኗል። **** ኢንሻ አሏህ በቅርቡ ይህን የእስልምናና የሃገር አንድነት ምልክት እንዲሁም አርማ ከነበረበት በተሻለ መልኩ ተገንብቶ የምናየው ያድርገን ! አሚን ✦✦✦✦✦✦✦✦
Показати все...
ማሻ አሏህ ዛሬም አስደሳች ዜና አለን በብዙ ስራዎቻቸው የምናውቃቸው እና ለብዙ ማዲሆች አርአያ የሁኑት ሸይኽ ዓብዱል ወሀብ በአምባሳደር አዳራሽ ለሚደረገው ለጥር 02 መውሊድ እንደሚገኙ ዛሬ ለማዎቅ ችለናል :: ★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★ ትኬቶችን አሁንም ሳያልቁ በተቀመጡ ቁጥሮች ደውለው ይረከቡ :: ቤተል አካባቢ ያላችሁ ፡ +251929183037 ጦር ሐይሎች አካባቢ ያላችሁ ፡ +251923282856 ወይም ፡ +251945752264 ወይንም ፡ +251949887780 በነዚህ ቁጥሮች ድደዉላችሁ ትኬቶችን መረከብ ትችላላችሁ ፡፡ Al- Faruq TUBE አል- ፋሩቅ ቲዩብ
Показати все...
Watch "ማዲህ ዑመር የሚገርም ብቃት የሚያምር መንዙማ menzuma" on YouTube https://youtu.be/sFarOVGdoSw
Показати все...
ማዲህ ዑመር የሚገርም ብቃት የሚያምር መንዙማ menzuma

ማዲህ ዑመር የሚገርም ብቃት የሚያምር መንዙማ እና አዳያመልታችሁ subscribe በማድረግ ተቀላቀሉን

በወንጀሏ መብዛት ምክንያት ወደ ዲን (ወደ አላህ) ለመመለስ ለከበዳት ነፍስ ሁሉ ከአሏህ የተሰጠን መልካም ተስፋ!!! ۞ قُلْ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ أَسْرَفُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا۟ مِن رَّحْمَةِ ٱللَّهِ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَغْفِرُ ٱلذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلْغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በሞላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡ አዝ-ዙመር፣53 @yemuhabawzulal
Показати все...
Watch "ከአዲሱ መንዙማ (clip) ተጋበዙልኝ።" on YouTube https://youtu.be/o8f9JqXXrW4
Показати все...
ከአዲሱ መንዙማ (clip) ተጋበዙልኝ።

👉Selehadin hussen official በቀላሉ የ ዩቲዩብ ፔጄን ለማግኘት 👇👇👇

https://www.youtube.com/channel/UCruhmbFsCVpuoRp2v9-nCxA

👇👇👇 ቻናሌን Like,share, subscribe...

አሰላሙ ዓለይኩም ወረሕመቱሏሒ ወበረከቱሁ #መውሊድ በአል ፋሩቅ ቲዩብ የተዘጋጀ በአይነቱ ልዩ የሆነ በርካታ ማዲሆች የሚገኙበትና ልዩ የኢስላማዊ ኪነ ጥበብ ውጤቶች የሚቀርቡበት ልዩ ፕሮግራም:: እሁድ ጥር 02/2013 ከጠዋቱ 2:00 ሰአት ጀምሮ በአምባሳደር ሲኒማ አዳራሽ :: እንዳያመልጥዎ በጣም ብዙ ሰርፕራይዞችን እና አዳዲስ ስራዎችን አዘጋጅተን እየጠበቅንዎት እንገኛለን !!! #አል_ፋሩቅ_ቲዩብ ******************** ትኬቱን በነዚህ ቁጥሮች ደዉላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ ቁጥር (1) +251923232856 ቁጥር (2) +251945752264 ቁጥር (3) +251949887780 ⚠️ ማሳሰብያ ትኬቱን እኛ ስልካቸውን ካስቀምጥነው ሰዎች ውጭ ማግኘት አትችሉም :: በየአካባቢው ያሉንን ትኬቶች የት እና እንዴት እንደምታገኙ እኛ የምናሳውቃችሁ ይሆናል ፡፡ ********* አስተያየትዎን በዚህ ሊንክ ያድርሱን 👇👇👇 ******** https://t.me/ALFARUQTUBE5 https://t.me/ALFARUQTUBE5 https://t.me/ALFARUQTUBE5 https://t.me/ALFARUQTUBE5 Like እና Share በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ የYoutube ቻናላችንን Subscribe በማድረግ በየጊዜው የሚለቀቁ Videoዎችን ይመልከቱ || https://www.youtube.com/c/ALFaruqTube የፌስቡክ ገፅ || https://www.facebook.com/FALfaruuq/ ቴሌግራም || https://t.me/alfaruqtub
Показати все...
AL- FARUQ TUBE

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.