cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Ethiopiawinnet CDCR( ኢትዮጵያዊነት) 🇪🇹

ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ድርጅት በሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ተመስርቶ ከመስከረም 05 ቀን 2013 ዓ.ም ጀመሮ በኢ.ፌ.ድ.ሪ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን በሰርተፍኬት ቁጥር 5099 የተመዘገበ ሃገር በቀል ድርጅት ነው። መልእክት / አሰተያየትዋን በ @ethiopiawinnet1 ወይም 09 65858580 ይላኩልን።

Більше
Рекламні дописи
423
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
+1630 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የድርጅታችን መስራችና በሰሜን አሜሪካ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር እርቁ ይመር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ይከታተሉ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=GH-AzIy--5s&t=1131s
Показати все...
ኢትዮጵያዊነት ለጊዜው በብሔረተኞች ቢፈተንም ዳግም ተጠናክሮ ያንሰራራል--የኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ዶ/ር እርቁ

የኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር እርቁ ይመር ኢትዮጵያዊነት ለጊዜው በብሄረተኞች ቢፈተንም ዳግም ተጠናክሮና ጎልብቶ መቀጠሉ አይቀሬ መሆኑን ያስረዳሉ #Ethiopia #Ethiopian #Amhara #Oromo #Tigray #Amharic #AmharicSongs #EVN

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ዌቢናሩን ለመታደም በቀጣዩ ሊንክ በመክፈት እንዲመዘገቡ በአክብሮት እንብዛለን ይመዝገቡ፡: https://us06web.zoom.us/webinar/register/WN_TXdo1-akSJmMRGUEFykW5g Share to Others
Показати все...
ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ የአማራን ሕዝብ እንደ ጨቋኝ ያስፈረጀው ትርክቶች ያስከተሉት ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበረሠባዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳቶች” በሚል ርዕስ ሁለተኛው የዌቢናር ጉባዔ ቅዳሜ ኦክቶበር 21, 2023 10:00 AM EST ጀምሮ ይከናወናል። ይህ ባለፈው ሳምንት በዌቢናር 1 ተደርጎ የነበረው "የፀረ አማራ ትርክቶች መንስኤዎች ምን ምን ናቸው? በሚል የተደረገው ታሪካዊ ውይይት ተከታይ ነው። በመጭው ሳምንት ኦክቶበር 28፣ 2023 ዓ/ም ደግሞ፣ ከዚህ ምን እንማራለን ፣ ምንስ ማድረግ አለብን? በሚል በመፍትሔ ላይ ያተኮረ ውይይት፣ በምሁራንና ታዳሚዎች ይደረጋል። ይህ ይህ የመጨረሻው ክፍል ይሆናል። እርስዎም የእነዚህ ዌቢናሮችታዳሚ እንዲሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን። ይመዝገቡ።
Показати все...
👍 1
ስለ ኢትዮጵያዊነት፣ ኢትዮጵያዊነት የዜጎች ምብት ማስከበሪያ ድርጅት (ኢትዮጵያዊነት) እ.ኤ.አ በ 2012 ዓ/ም የተቋቋመ፣ በውጭና በሀገር ቤት የሚንቀሳቀስ፣ ፆታ፣ብሔር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ወዘተ የማይለይ፣  የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ የማህበረሰብ (ሲቪክ) ድርጅት ነው።  ድርጅታችን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያየተደረጉትን ጥረቶች ፣ በከፊልም ቢሆን የሚገልፁ ፣ ሀገራዊ ይዘት ያሏቸውን ምስሎችና  ቪዲዮዎችን በ ዩትዩብ : Voice of Ethiopiawinnet ላይ ያገኛሉ። ዌብሳይት፡- https://www.ethiopiawin.net    ፌስ ቡክ: https://www.facebook.com/ETHIOPIAWINNET.AA ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopiawinnetaa ሊንክደን፡ https://www.linkedin.com/company/79367322/ ዩትዩብ : Voice of Ethiopiawinnet በቀጥታ ለማግኘት   [email protected]  / [email protected] ብለው ይፃፉልን።
Показати все...

ቅዳሜ የተካሄደውን ዌቢናር መከተል ላልቻላችሁ በቀጣዩ ዩትዩብ ሊንክ መከታተል ትችላላችሁ https://youtu.be/ahCDr_7KSvU?si=M37tCpn_JPNnH8d-
Показати все...
ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ ትርክቶች መቸና እንዴት ተጀመሩ?

ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ ትርክቶች መቸና እንዴት ተጀመሩ? ይህ በውጭ ሃይሎች የተቀነቀነው የተሳሳተ ትርክት በሀገር በቀል ሃይሎች ተግባራዊ ሊሆን እንዴት ቻለ Contents -- TIMESTAMPS -- 00:00 Dr. Tessema Guebre X, Master of Ceremony 00:04:42 Dr. Erku Yimer, Opening Remarks 00:14:25 Professor Haile Larebo, በውጭ ሰዎችና ተቋማቾቻቸው ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ የሃሰት ትርክት አቀንቃኞች የተጫወቱት ሚና 00:49:11 Dr. Abeba Fekade, የሃገር-በቀል  ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ የሃሰት ትርክት አቀንቃኞች የተጫወቱት ሚና 01:23:50 Ato Geletaw Zeleke, ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ የሃሰት ትርክት በዛሬዋ ኢትዮጵያ እንዴትና ለምን ቀጣይነት አገኘ   01:49:40 Professor Minga Negash, Discussant 02:24:09 Question and Answer 04:08:17 Dr. Erku Yimer, Closing Remarks About Ethiopiawinnet: Ethiopiawinnet website:

https://ethiopiawin.net/

[email protected] Telegram:

https://t.me/ethiopiawinnetaa

Facebook :

https://www.facebook.com/ETHIOPIAWINNET.AA/

Twitter:

https://twitter.com/ethiopiawinnet

Support Ethiopiawinnet Bank account: Ethiopiawinnet CDCR Dashen Bank Account No. 0155219603011

የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በኢትዮጵያ [በትግራይ] ተሰማ...!! ባያድለን ነው እንጂ ይሄ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ሁሉ ኀዘን፤ የምድሪቱ ልቅሶ መሆን ነበረበት!! በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) "ኢትዮጵያ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚፈውስሽ ማን ነው. . . ?!"  እንደ መግቢያ፤ "የኢትዮጵያ ሀገሬ ታጠቂ በገመድ፤ የወንድ ልጅ እናት ታጠቂ በገመድ፤ ያም ልጅሽ ያም ልጅሽ፤ ያም ዘመድ ያም ዘመድ፤ ለማን ታድያለሽ ... ለማንስ ይፈረድ?! (የባህል ሙዚቃ ንግሥቷ ማሪቱ ለገሠ/እንደው ዘራፌዋ) የኢትዮጵያና የኢትዮጵያን የታሪክና የሥልጣኔ እምብርት፤ የክርስትና እና የኢስላም ሃይማኖቶች (የርዕሰ አድባራት አክሱም ጽዮን እና የአልነጃሺ) መሠረት/መነሻ ምድር ኢትዮጵያ/አክሱም/ትግራይ፤ ኢትዮጵያውያን ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ጫፍ ተጠራርተው ብሔርና ጎሳ፤ ሃይማኖትና ቋንቋ ሳይለያቸው በአጥንታቸው ብዕርነት በደማቸው ቀለምነት የነጻነትን ክቡር መንፈስ ከፍ ባደረጉበት፤ ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት ሰንደቅ በተውለበለበባት፤ የኢትዮጵያዊነት የቃልኪዳን ውሉ በተቋጠረባት በዐድዋ/በትግራይ ምድር፤ በወንድማማች ጦርነት በአንድ ጀምበር ለወሬ ነጋሪ አንዱ እንኳን ሳይተርፉላት አምስቱም ልጆቿ/ሁሉም ማለቃቸውን ሰምታ ራስዋን ስላጠፋች፤ ኀዘን አቅሏን ስላሳታት የትግራይ/የኢትዮጵያ ምስኪን እናት ምን ምላሽ፤ ምንስ የማጽናኛ ቃል አለን...?! በአማራ፣ በአፋር፣ በቤሻንጉል ጉሙዝ፣ በወለጋ... በሁሉም ኢትዮጵያ ምድር በጦርነት ነዲድ እየተለበለቡ በገፍና በግፍ ስላለቁትና እያለቁ ስላሉት የኢትዮጵያ ልጆች ምን እያልን፤ ምን እያሰብን ይሆን...?! በቤተ መቅደሱ ደጃፍ ስለታረዱት ካህናት፣ ደማቸውን ውሻ ስለላሰው፣ በድናቸውን ለአውሬና ለአሞራ ሲሳይ ስለዳረግናቸው ወገኖቻችን፤ ስለተደፈሩ መነኮሳት፤ የሴትነታቸው ክብር በአደባባይ ስለተዋረደባቸው፣ ስለተጎሳቆለባቸው ምስኪን እናቶቻችና እህቶቻችን ምን ቃል፤ ምንስ አንደበት ይኖረን ይሆን...?! የጦርነት ነጋሪት ስንጎስም፣ በወንድማማች ሕዝብ፤ በኢትዮጵያውያን መካከል የጥላቻን፤ የመለያየትን ዘር ስንዘራ የነበርን ነፍሰ-ገዳዮች/ቃኤላውያን ሆይ አሁን ገና የደም ግብራችን አልረካ ይሆን...?! የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በኢትዮጵያ [በትግራይ] ተሰማ...!! እነዚህ ኃይለ-ቃላት ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰዱ ጥቅሶች ሲሆኑ፤ በተለያዩ ጊዜያት የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ እስራኤል፣ ስለ ኢየሩሳሌም/ስለጽዮን ውርደት፣ መከራና ሰቆቃ የተናገሯቸው ናቸው። ጥቅሶቹ የእናት ምድራችንን የኢትዮጵያን ኀዘን፤ የኢትዮጵያውያን እናቶችን ሰቆቃ/ታላቅ ስብራት የሚገልጽ መስሎ ስለተሰማኝ ነው- ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በመተካት አካፍላችሁ ዘንድ የወደድኹት። "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ [በትግራይ] ተሰማ፤ ራሔል [ኢትዮጵያ] ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን ፈጽሞ እንቢ አለች።" (ትንቢተ ኤርምያስ ፴፩፤፲፭)። "ድምፅ በኢትዮጵያ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ የትግራይ እናት ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትንም አልወደደችም።" ኢትዮጵያ አለቀሰች፥ ደጆችዋም ባዶ ሆኑ በምድርም ላይ ጨለሙ፤ የእናቶች ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎአልና፤ የኢትዮጵያ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፤ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ፤ ደናግላን ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች [የአክሱም መንገዶች] አለቀሱ፤ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፤ ደናግሎችዋም ተጨነቁ፤ እርስዋም በታላቅ ምሬት ውስጥ አለች። በኢትዮጵያ ሴቶችን፥ በከተሞቿም ደናግልን አጐሰቈሉ፤ አለቆች በእጃቸው ተሰቀሉ፤ በመቅደሱ የካህናት፣ በአደባባይም የሽማግሌዎች ፊት አልታፈረም።  ጕልማሶች ወፍጮን ተሸከሙ፥ ልጆችም ከእንጨት በታች ተሰናከሉ። ሽማግሌዎች ከአደባባይ፥ ጕልማሶች ከበገናቸው ተሻሩ። አቤቱ፥ ተጨንቅናል፥ አንጀታችም ታውኮብናልና፤ ተመልከት፤ ልባችን በውስጣችን ተገላበጠብን፤ በሜዳ ሰይፍ ልጆቻችንን አጠፋ በቤታችንም ሞት አለ። ድንጋጤና ቍጣ፥ ጥፋትና ቅጥቃጤ ሆነብን። ስለ ወገናችን ሴት ልጆች ቅጥቃጤ ዓይናችን የውኃ ፈሳሽ አፈሰሰች። እግዚአብሔር ከሰማይ እስኪጐበኝና እስኪመለከት ድረስ ዓይናችን ሳያቋርጥ ዝም ሳይሉ እንባን ያፈሳሉ።  የልባችን ደስታ ቀርቶአል፤ ዘፈናችን ወደ ልቅሶ ተለውጦአል፤ ዓይናችን በእንባ ደከመች፥ አንጀታችንም ታወከ፤ ስለ ኢትዮጵያ ወገኖቼ ቅጥቃጤ ጉበታችን በምድር ላይ ተዘረገፈ።  ኢትዮጵያ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚፈውስሽ ማን ነው?  ነቢያቶችሽ ከንቱና ሐሰተኛ ራእይ አይተውልሻል፤ ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፤ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል። እንደ መውጫ፤ አንጋፋው ፖለቲከኛ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁሩ፣ አዛውንቱ ዶክተር ኃይሉ አርዓያ- በዛን ጊዜው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ/የአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበሩበት በ1950 ዎቹ ስለኢትዮጵያ የቋጠሩት ስንኝ ለአሁኗ ኢትዮጵያም የሚስማማት ይመስለኛል። እንሆ ከዶ/ር ኃይሉ አርዓያ እንጉርጉሮ/ስንኞች፤ "... ይኸው ትታያለች ለሕዝብ በይፋ፣ ጥቁር ተከናንባ ጥቁር ተጎናጽፋ፡፡ እኔስ መስሎኝ ነበር ዘመድ የሞተባት፣ የእናት ሞት የአባት ሞት፣ የልጅ ሞት ያጠቃት፣ ለካ እሷስ ኖራለች ዘመን የሞተባት...!! (ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕ. ፭) ---------- ፲፯፤ አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፤ ተመልከት ስድባችንንም እይ። ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ።  ፲፰፤ ድሀ አደጎችና አባት የሌለን ሆነናል፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆነዋል።  ፲፱፤ አቤቱ፥ አንተ ለዘላለም ትኖራለህ፤ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።  ፳፤ ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?  ፳፩፤ አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ።  ፳፪፤ ነገር ግን ፈጽመህ ጥለኸናል፤ እጅግ ተቈጥተኸናል። ሰላም ለኢትዮጵያ፤ ሰላም ለምድራችን🕊🕊
Показати все...
👍 1 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Happening Now: Attending consultation meeting on CSOs and Academia on promoting and consolidating HR and Democracy
Показати все...
ከላይ በመግቢያዬ እንደጠቀስኩት፤ መስቀል በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትልቅ ክብር፤ ልዩ ስፍራ አለው። ማንኛውም ሕንጻ ቤ/ክ ያለ ሞገሰ መስቀል አይሠራም። ስግደትና አስተብርኮም ይቀርብለታል። መስቀልን መሳለምና በመስቀል ማማትብ፤ መባረክም የቆየ የቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊ ሥርዓት ነው። መስቀልን በአንገት ማሰር፣ በግንባርና በክንድ ላይ መነቀስ፣ በአልባሳት፣ በአክሊል፣ በዘውድ፣ በገንዘብና በበትረ መንግሥት ላይ የሚደረገው የመስቀል ሃይማኖታዊ ምልክት እንጂ ጌጥ አይደለም። እንደ ቤተክርስቲያን ሥርዓት ለቅዱስ መስቀል አብያተ ክርስቲያናት ታንጸዋል። ከመስከረም ፲፭ እስከ ፳፭ ያለው ጊዜም ዘመነ-መስቀል ይባላል። በዚህ ወቅት ነገረ መስቀል ይነገራል፤ መዝሙረ መስቀል ይዘመራል። በአጠቃላይ መስቀል በኢትዮጵያ ቤ/ክ የጸሎት ጥንትና ተፍጻሜት ነው። በመጨረሻም፤ ንጉሠ ሣሕለሥላሴ ከ200 ዓመት በፊት በኢየሩሳሌም ስላለው የኢትዮጵያ ቤ/ክ ገዳም - ስለዴር ሱልጣን ጉዳይ ለእንግሊዛዊው ቆንሲል ሳሙኤል ጎባት የጻፉትን ደብዳቤ ስንመለከት የራስጌ ማሕተማቸው የመስቀል ምልክት እንደነበር ይታያል። ይህን ጥንታዊ ደብዳቤ ከዚህ ጽሑፍ ጋር አባሪ አድርጌያለሁ። ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ፤ "እግዚአብሔርም በእርሱ፥ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ጥልንም/ጥላቻንም በመስቀሉ ገድሎ፤ በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና፤" እንዲል የአባቶቻችን አምላክ በኢትዮጵያ ምድር ጥልና ጥላቻ/ጠላትነት ተወግዶ የሰላምን ዘመን ምናይበትን ጊዜ ያቅርብልን!! አሜን!! መልካም የመስቀል በዓል!!
Показати все...