cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን መዝሙሮችን እንዲሁም ምክሮችን ያገኙበታል። ክርስቲያናዊ ሕይወትዎን ያዩበታል.......

Більше
Рекламні дописи
645
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
-730 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
🕊 [ † እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ መርቄሎስ እና ለነቢዩ ቅዱስ ዕዝራ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ] 🕊  †  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!  †  🕊 🕊  † ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ †  🕊 † ቅዱሱ በነገድ እሥራኤላዊ የሆነ የመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን ሰው ነው:: ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ሲያስተምር በምሥጢሩና በተአምራቱ ተማርኮ ተከትሎታል:: ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ይሆን ዘንድ አድሎታል:: ከጌታችን ሕማማትና ስቅለት በፊትም ድውያንን መፈወስና አጋንንትን ማስወጣት ከቻሉ አርድእትም አንዱ ነው:: ቅዱስ መርቄሎስ በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለወንጌል አገልግሎት ተሰማርቷል:: በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለሰላሳ አራት ዓመታት በማገልገሉ ሐዋርያት ስሙን "ጳውሎስ" ብለውታል:: ጳውሎስ ማለት ብርሃን ማለት ነውና:: ልክ ሳውል "ጳውሎስ" እንደተባለው ማለት ነው:: ስሙ የግብር [በሥራ የሚገኝ] ስም ነው:: በዚህም ምክንያት ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን የምትጠራው "ጳውሎስ የተባለው መርቄሎስ" እያለች ነው:: ቅዱስ መርቄሎስ በ፷ [60] ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በሮም ይሰብክ ነበር:: ኔሮን ቄሳር ሊቀ ሐዋርያትን ዘቅዝቆ ሲሰቅለው የተመለከተና ይህንኑ የጻፈ እርሱ ነበር:: ወታደሮቹ ቅዱስ ጴጥሮስን ገድለውት ሲሔዱ ቅዱስ መርቄሎስ እያነባ ቀርቦ: ችንካሮችንም ነቅሎ: ሊቀ ሐዋርያትን ከተሰቀለበት አወረደው:: በፍጥነት ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ አምጥቶ በቅዱስ ጴጥሮስ ሥጋ ላይ አፈሰሰና በፍቅርና በክብር ሊገንዘው ጀመረ:: በዚህ ጊዜ ሊቀ ሐዋርያት አይኑን ግልጥ አድርጎ መርቄሎስን ተመለከተውና አለው:- "ልጄ! ምነው ለእኔ ይህንን ያሕል ሽቱ አባከንክ?" አለውና ተምልሶ ዐረፈ:: ቅዱስ መርቄሎስም እግዚአብሔርን እያመሰገነ በንጹሕ በፍታ ገንዞ እርሱ በሚያውቀው ቦታ ሠወረው:: ሊቀ ሐዋርያትን በመገነዙ የክብር ክብር ተሰጥቶታል:: ቅዱሱ አሁንም ስብከተ ወንጌልን ቀጠለ:: ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን እርሱም ተይዞ በኔሮን ፊት ቀረበ:: ኔሮን ቄሳር ቅዱስ መርቄሎስን ጠየቀው:: "እንዴት ባለ አሟሟት ልግደልህ? እንደ መምህርሕ ጴጥሮስ ወይስ ሌላ የምትፈልገው ዓይነት አሟሟት አለህ?" ቅዱስ መርቄሎስ መለሰለት:- "የትኛውም ዓይነት ሞት እኔን አያስፈራኝም:: የምፈልገው ወደ ጌታዬ ቶሎ መሔድ ብቻ ነው::" አለው:: ንጉሡ ኔሮንም ዘቅዝቃችሁ ስቀሉት አላቸው:: ወታደሮቹም በዚህች ዕለት እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል:: 🕊  †   ቅዱስ ዕዝራ ነቢይ  †   🕊 ከክርስቶስ ልደት በፊት በ፭መቶ [500] ዓመት አካባቢ የነበረ ¤ እሥራኤል ከምርኮ ከተመለሱ በኋላ መጻሕፍት ተቃጥለው ጠፍተው ነበርና ስለ እነሱ አብዝቶ የለመነ ¤ ጥበብን ሽቷልና እግዚአብሔር ቅዱስ ዑራኤልን የላከለት ¤ በሊቀ መላእክት እጅም ጽዋዐ ልቡናን የጠጣ ¤ ብዙ ምሥጢራት የተገለጡለት ¤ ለአርባ ቀናት ምግብ ሳይበላ አገልጋዮቹ የጠፉ መጻሕፍትን እየነገራቸው የጻፉለት ¤ መጽሐፈ ዕዝራ የተሰኘ መጽሐፍን ያዘጋጀና ¤ በብሉይ ኪዳን ከነበሩ ዐበይት ነቢያተ ጽድቅ አንዱ የሆነ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ነው:: † ስለ ቅድስናውም ሞትን አልቀመሰም:: በዚህች ዕለት ቅዱሳን መላእክት ብሔረ ሕያዋን ውስጥ አስገብተውታል:: † እግዚአብሔር ከሐዋርያውና ከነቢዩ በረከትን አይንሳን:: [  † ሐምሌ ፮ [ 6 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ] ፩. ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ [ከሰባ ሁለቱ አርድእት] ፪. ቅዱስ ዕዝራ ነቢይ ፫. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ ፬. ቅድስት ቴዎዳስያ ሰማዕት ፭. ቅድስት ንስተሮኒን ዘኢየሩሳሌም [  †  ወርኀዊ በዓላት  ] ፩. ቅድስት ደብረ ቁስቋም ፪. አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን ፫. አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል ፬. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ ፭. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ፮. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ፯. ቅድስት ሰሎሜ ፰. አባ አርከ ሥሉስ ፱. አባ ጽጌ ድንግል ፲. ቅድስት አርሴማ ድንግል † " እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን: ሁለተኛም ነቢያትን: ሦስተኛም አስተማሪዎችን: ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን: ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ: እርዳታንም: አገዛዝንም: የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጓል:: ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸውን? . . . ነገር ግን የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ:: " † [፩ቆሮ. ፲፪፥፳፰] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Показати все...
[ ስንክሳር ሐምሌ - ፮ - ] .mp32.66 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
💛 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊 ▷  " የጸጸትና ራስን የመመርመር ሕይወት ! " [    " ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ "    ] [                        🕊                        ] ----------------------------------------------- ❝ ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ ፥ በደሌንም አልሸፈንሁም ፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውህልኝ። .... አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነህ ፥ ከጣርም ትጠብቀኛለህ ፤ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ። ❞ [  መዝ . ፴፪ ፥ ፭  ] 🕊                        💖                     🕊                              👇
Показати все...
[ ራስን የመመርመር ሕይወት ] .mp36.50 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
                         †                           [      🕊  ፍኖተ ቅዱሳን   🕊      ] [ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  ተርእዮን [ መታየትን ] አለመውደድና ለታይታ ብሎ ምንም ነገር አለማድረግ !  ] 🕊 "  ከዚያ አታላይ ምን ትፈልጊያለሽ ? .... !  " ........ በጡቷ ካንሰር የነበረባት አንዲት ሴት ስለ አባ ሎንጊኖስ ሰማችና ልታገኘው ሄደች፡፡ የሚኖረው ከእስክንድርያ ወጣ ብሎ ነበርና ሴትዮዋ ስለ እርሱ እየጠየቀች ወደ እርሱ ስትሄድ በባሕሩ ዳርቻ እንጨት እየለቃቀመ አገኘችውና እርሱ መሆኑን ስላላወቀች ፦ "አባ፣ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሎንጊኖስ የሚኖረው የት ነው?" አለችው:: እርሱም ፦ "ከዚያ አታላይ ምን ትፈልጊያለሽ? ወደ እርሱ አትሂጂ ፣ እርሱ አታላይ ነውና። ግን ጉዳይሽ ምንድን ነው?" አላት፡፡ ሴትዮዋም ስለ ሕመሟ ነገረችው:: እርሱም በታመመው ሰውነቷ ላይ የመስቀል ምልክት አደረገና ፦ "ሂጂ፣ የሚፈውስሽ እግዚአብሔር ነው፣ ሎንጊኖስ ምንም የሚጠቅምሽ ነገር የለምና" አላት፡፡ እርሷም አምና ተመለሰች፣ በአንዴ ወዲያውኑ ከሕመሟ ተፈወሰች፡፡ ከዚያ በኋላ ይህን ነገር ለሰዎች አወራች፡፡ የሰውዬውን ሁኔታ ገለጸችላቸው፣ እነርሱም እርሱ ራሱ አባ ሎንጊኖስ እንደ ሆነ ነገሯት፡፡" የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡ †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
                        †                              †      🕊   እንኳን  አደረሰን    🕊    † በደመ ስምዖሙ ተማኅጸነ ፤ ለጴጥሮስ አቡነ ፥ ወጳውሊ ፍቁርነ ፤ ጸሎተነ አጽምዕ ፍጡነ ፤ እስመ ንጸንሐከ እምዘመን ዘመነ ! ቸሩ ሆይ ፥ ስለ ፈሰሰ ደማቸው ብለህ ከምድሩ መቅሠፍት፥ ከሰማዩ እሳት አድነን ! 🕊                        💖                       🕊
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
                         †                          [  የክብር ኮከብ ፤ የገዳም መብራት  ] 🕊 የማይሰለች ተጋዳይ ፤ የክብር ኮከብ ፤ የገዳም መብራት ስም አጠራሩ እርግናው የተመሰገነ ፤ ብፁዕ ቅዱስ ደግ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወርሐዊ በዓላቸው ነው። †     🕊   እንኳን  አደረሰን    🕊    † እግዚአብሔር አምላክ ስለ እውነተኛ ወዳጁ ስለ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ብሎ ይማረን፡፡ 🕊                        💖                       🕊
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.