cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

♈💔🍁 (hanun) ጣፍጭ ህመም

Join and share our channel አንተ ማለት ሀኑኔ ነህ ጣፍጭ ግን ህመም የበዛብህ ልክ ፅጌሬዳ ውብ ሆና እሾኾቿ እንደሚዋጉት 🍁 Cross @maranta67 join and share @yefkermenfese

Більше
Рекламні дописи
239
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

😔ማውራት እፈልጋለው😔 ከጀርባዬ ነበር አላየሁትም መልኩ ፣ ቁመቱ ፣ የፊቱ ገፅታ ፣ ምኑም ትዝ አይለኝም አላየሁትማ ድምፁን ግን ሰምቻለው የቀን ጎዶሎ ልቤን አድምቶብኝ የእንባዬን መጨረሻ አጥቼ ማቆሚያው ጠፍቶኝ ድምፄን አጥፍቼ በእንባዬ ውስጥ ሳለሁ ነበር "ማውራት ትፈልጊያለሽ" የሚል ድምፅ ከዃላዬ የሰማሁት በአካባቢው ሰው መኖሩን አላስተዋልኩም ነበር አንገቴን ከደፋሁበት ክንዴ ላይ ቀና አረኩት ለመዞር ግን አልፈለኩም.. ድሮም ነው እምባዬን ለሰው ማሳየት ይበልጥ ያመኛል ዝም ነበር ያልኩት በድጋሚ "ብታወሪው ይቀልሻል ልሰማሽ ዝግጁ ነኝ" አለኝ በሰአቱ ምቾት የነሳኝ የሱ ከጀርባዬ መቆም እንደሆነ አልገባውም በውስጤ ጮህኩበት ሂድ አልኩት ግን አሁንም ቆሟል ካንደበቴ ቃላትን አላወጣሁም ዝምታዬን ደገምኩለት ከቆይታ ቡሀላ ትከሻዬን የከበደኝ ነገር ቀለል ሲል ተሰማኝ በቀስታ ዞርኩኝ ከጀርባዬ ማንም የለም ውስጤ እርፍ አለ አልቆም ብሎ ሲያስጨንቀኝ የነበረው እንባዬም በሰበቡ ተረሳ ቆመልኝ በትንሹ ዳንኩኝ ማልቀሴን አቁሜ ወደቤቴ አቀናው ። ቀናቶች ተቆጠሩ.......... በሌላኛው ቀን.......... ልቤ እንደለመደው ተሸነቆረብኝ ጭረው አደሙኝ ከለመድኩት ቦታ ተገኝቼ ከእንባዬ ትግል ያዝኩኝ ለወትሮው ስቃይን ማዳኛዬ ሳይነኩት የሚፈስ እንባዬ ድርቅ አለብኝ ውስጤ ማልቀስን አልፈለገም አይኖቼ ምንም እንዳልተፈጠረ ነጭነታቸውን ይዘው ፀንተዋል "አልቅሺ እንጂ" አልኩኝ ለራሴ በሹክሹክታ (ምንም ላይቀየር) "አውሪው" የሚል ድምፅ ከልቤ በኩል ተሰማኝ ያለፈው ቀን ታወሰኝ ጆሮዬ ላይ ድምፁ በተደጋጋሚ አቃጨለብኝ "ማውራት ትፈልጊያለሽ" "ልሰማሽ ዝግጁ ነኝ" ወደጀርባዬ ዞርኩ ግን እሱ የለም ዛሬ *ማውራት እፈልጋለው* አልኩ ድምፄን ከፍ አድርጌ ግን ዛሬ ሊሰማኝ የሚፈልግ የለም ያለኝንም እንባዬን ሰርቆኝ ዝምታን ሰጥቶኝ ጠፋ...... ከእንባዬም ከንግግሬም ሳልሆን ውሎዬን ዘጋሁት ዝም እንዳልኩ ከአልጋዬ ከተምኩ...... እንቅልፌም አጋጣሚውን ያገኘ ይመስል ከኔ ሳይደርስ ንጋት ተበሰረ ለተዛባው አእምሮዬ ምሽት የተፈጠረው ለእንቅልፍ እንጂ ለማሰብ እንዳልሆነ እንዴት ብዬ ማሳመን እችላለው?? 🍂🍂🥀 @semhalyaa @yefkermenfese
Показати все...
​​​​​ "ሴትን አላምንም" ክፍል 5 Semhal🍂 ረጋ ካለው ሰላምታችን በኋላ…  የት/ቤቱን ግርግር አልፈን እንውጣ አልኳት። ምላሿን ሳላገኝ ከፊቷ ተቀድሜ የተማሪዎቹን ትርምስ አልፌ ውጪ ጠበቅኳት ትንሽ ቆይታ እሷም ግርግሩን አልፋ መጣች "የበራልኝን ብርሃን ዛሬ ማጨለም አልፈለኩም" ሳሪስ ከሆነች ሳሪስ ፣ ቦሌ ከሆነች ቦሌ ፣ ካዛንቺስ ከሆነች ካዛንቺስ ብቻ አብርያት መሄዴ የማይቀር ነው ዛሬ እሷ የምትሄድበት ነው መኖርያዬ። "ወዴት ነሽ"? አልኳት……ወደ "ኮልፌ ነኝ" ብቻሽን ነው የምትሄጂው? የማያቋርጠው የእኔ ጥያቄ "ዛሬ አዎ" ሌላ ጊዜ ግን ወንድሜ ነበር  ሚወሰድኝ አርብ ቀን ስራ ይበዛበታል ስለዚህ ያመሻል አለችኝ…  ልሸኝሽ ልበላት እንዴ?🤔 እኔና አንተ ልንጣጣም ማንችል ነን ብትለኝስ? ከአንተ ጋ በእግር ከመሄድ ወንድሜን ጠብቄ በሚደላ መኪና ሙዚቃ እያዳመጥኩኝ መሄድ ይሻለኛል ብትለኝስ? ከአንተ ጋ ስሄድ ፀሀይ ያጠቁረኛል ፣ ዝናብ ያበሰብሰኛል ብላ ያልጠበቅኩትን መልስ ብትመልስልኝስ? …… ከሃሳቤ ባንኜ ስምሽን ማን ልበል አልኳት እሷም  "አህላም" እባላለው አለችኝ ይህን ስም ወይም የዚህን ስም የቃል ትርጓሜ በደንብ አውቀዋለው አዎ አስታወስኩኝ አንድ የታሪክ መፅሀፍ ላይ። አህላም ማለት "ምኞቴ" ማለት ነው አዋቂ መስሎ ለመታየት ይሁን ትርጉሙ ስለገባኝ oh በጣም አሪፍ ስም ነው አልኳት። የማን ምኞት ነሽ ምን አልባት ቤተሰቦችሽ ከመጀመሪያውም ቆንጆና የታላቅ ስብእና ባለቤት እንደምትሆኚ ታይቷቸው ይሆን ይሄን ስም ያወጡልሽ? …… ስላት ፈገግ አለች ስትስቅ ጉንጮቿ ወደ ውስጥ ይገባል ፈገግታዋ ንፁህ ነው ሸፍጥ ተንኮል ፣ የሌለበት…  ከልብ የመነጨ ፈገግታ ነው። ፍቃደኛ ከሆንሽ ልሸኝሽ ለውለታሽ ቢያንስ "ሻይ ልጋብዝሽ"  ብዬ ፍቃዷን ጠየቅኩኝ ። ፍቃደኝነቷን አንገቷን በመነቅነቅ አሳየችኝ ልቤ በሀሴት ተሞላ ጉዞዋችንን   ቀጠልን እንዳይመሽ በልቤ ፈጣሪዬን እየተማፀንኩኝ መንገድ ጀመረን።  " ጉድጓድ ሚል ድምፅ "  ከሗላችን ተሰማ ግን መዳን አልቻልንም አህላምዬ ለመንገድ መስርያ ተብሎ በተቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ወደቀች። " ልቤ ከዳኝ ፣ እጄ ተንቀጠቀጠ ፣ እሷን ከውስጥ ለማውጣት አቅም አነሰኝ ፣ ዐይኖቼ በአንዴ ደም መሰሉ ሰማይ ምድሩ ጨለመብኝ።  ቢሆንም  አህላምዬ ተርፋለች ፣ ከጉድ ሰውሮኛል ፣ ጉድጓዱ ጥልቀት የለውም ቀኝ እግሯ ተንሸራቶ ስለገባ ድንጋይ መቷታል። …  ትንሻፌን ሰብስቤ ደገፍ አድርግያት መንገዱ ጫፍ ላይ አስቀምጭያት ውሃ ላመጣ ሄድኩኝ። ትንሽ ስለደማባት"ደሟን በሶፍት ጠራርጌ" ትንሽ አረፍ እንበል ብዬ ተደላድላ እንድትቀመጥ አመቻቸሁላት ስትወድቅ ያዩ አላፊ አግዳሚዎች  ብዙ ተጐዳች?  አላህ ያሽርሽ ፣ ማሪያም አወጣችሽ? "መንገዱን ቆፋፍረውት እኮ ሰው ማለቁ ነው" ይላል አንድ አንድ የመንገዱ መበላሸት ብሶት ያማረረው ግለሰብ።  አጠገቧ ተቀምጬ ላየኝ ትውውቃችን የአንድ ቀን ሳይሆን የዘመናት  ይመስል ነበር አህላምዬ? አልኳት ደንግጬ ስለ ነበር ማቆላመጤን ረስቼዋለው…… ሰው ታሞም ያምርበታል ? ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ውብ መስላ ታየችኝ ፊቷ በህመም ይሁን በድንጋጤ ፍም መሰሎ ደሟ ሲዘዋወር ይታያል ህመም እና ድንጋጤ በተሞላበት ድምፇ "ወዬ" ብላ አንገቷን ትካሻዬ ላይ ጣል አድረገችው። …… የማረገው ጠፋኝ ታላቅ የኒሻን ሽልማት ትከሻዬ ላይ ያረፈ መሰለኝ  እንኳንም ወደቀች ባትወደቅ መቼ ትከሻዬ ላይ አንገቷን ትጥል ነበር? ጠረኗ እንዴት ከደም ስሬ ቅርብ ሆኖ ያውደኝ ነበር? ፍቅር ጨካኝ አደረገኝ በሷ መውደቅ ውስጥ ደስታዬን ያገኝሁኝ መሰለኝ ? ምን አለ " ትንፋሽ ቢያጥራት   " ከኔ ውጪ ማን ትንፋሽ ይሰጣት ነበር። ወይዬ ብላኝ ከሃሳቤ ክምር ከማፅናኛዬ ቃል ውስጥ ያለውን ሁሉ  ናደችብኝ።  ወድጄሻለው ልበላት? በእጅጉ እንደምወዳት ልገልፅላት ፈልጌ ነበር ግን ቋንቋ አልነበረኝም ፣  ለእሷ ያለኝን ፍቅር መግለጫ አልነበረኝም። በአንድ ቀን ግንኙነት እንዴት ወዶኛል ብላ ታስባላች ሴት እኮ ነች ሴት ልጅ ደሞ ብልህምም ብልጥም ነች ለማፍቀርም ለመውደድ ምክንያት ትፈልጋለች። እኔን ለመውደድ ምን ምክንያት አላት? ለረዥም ደቂቃ የፈሰሰው ደሜ ወይስ አሁን በእግሯ አስኳትኛት የመውደቋ ሰበብ መሆኔ? ብቻ ያንን የብዙዎች ምኞት የሆነውን አንገት ትከሻዬ ላይ ነው ያለው ግን ምን ያረጋል ብዙም መቆየት አልቻልንም። ዝናቡ ለመጣል ከሚነፍሰው ንፋስ ጋር ትግል ይዟል ፣ ቀና ብለን ስንመለከት የጨፈገገው ደመና ከበድ ብሏል በእሷ መውደቅ እና መታመመ ሀዘን ሰማይዋ ምታለቅስ መስላ ታየችኝ ። መንገደኛው  የያዘውን እቃ ለማስቀመጥ በጥድፍያ ላይ ይገኛል ሰው የዝናቡን ከባድነት  በመገመት ይሯሯጣል ይህ ሁሉ ትእይንት ደንታ ያልሰጠኝ እኔ ነበርኩኝ ጥላ ከለላዬን ትከሻዬ ላይ አርጌ ተቀመጭያለው። ዝናቡ ከመጣ ሊያበሰብሰን በመሆኑ ከፊታችን የቆመውን ላዳ አናግሬ መምጣት ሰለነበረብኝ አንገቷን ቀስ ብዬ ከትከሻዬ አንስቼ ላዳውን ላናግረው ሄድኩኝ ዓለሜን ከትከሻዬ ላይ በማውረዴ ቢከፋኝም በዋጋ ስለተስማማን አህላምዬን ቀስ አድርጌ  ወደ መኪናው ይዣት ገባሁኝ። አሁን ቀለል ያላት ትመስላለች ቁስሏም ማቃጠሉ በተወሰነ መልኩ በርዶላታል ሌላ ቦታዋ ስላልነተካ ደስ ብሎኛል መንገዳችን ጀመርን ከዚህ በሗላ አንገቷ ሌላ ትከሻ ላይ ማረፍ የለብትም ፣ የእግሯን ቁስል ሆነ ህመሟን ከኔ ውጪ ማንም እንዲያየው መፈቀድ የለብኝም።  ግን እንዴት?                  ክፍል ስድስት ይቀጥላል......
Показати все...
የምትወዷቸውን ወጣት ገጣሚያን በመምረጥ የግጥም ስራቸውን እና ለ profile pic የሚሆኑ ፎቶዋቸውን ማግኘት ትችላላቹ👇👇
Показати все...
ኤልያስ ሽታሁን❤️😘
በላይ በቀለ ወያ❤🥰
አስታወሰኝ ረ/ሳ❤️❤️
የሌሎችንም🤗😘
ክፍል 5ዛሬ ምሽት ይጠብቁን 🌟🍂🙏🥀
Показати все...
Liyu new webetoa yewa ye fkr sew yemwedew negsta💜 Eyulg ergben le ene teftralech enew negn gojowa zora temetalce💙💙😍💜 @semhalyaa
Показати все...
5.11 KB
ለራሳችሁ ነፃነት አትስገዲ ፤ ነፃነታችሁም እንደ ቀንበር አትሸከሙት @yefkermenfese
Показати все...
........? #የዛሬው_ምክር_ላንቺ👸 ........ውበትሽን አይቶ የተመኘሽ እና ከውበትሽ ጀርባ ያለውን ማንነትሽን አውቆ ያፈቀረሽ ሰው የተለያዩ ናቸው። #ለምን_ነገርከኝ_እንዳትይ? እኛ ወንዶች የፈለግነውን እስክናገኝ ሴትን ንግስት ማድረግ እናውቅበታለን። ያፈቀረ ግን ተብታባ ነው፤ ውበትሽን ለመግለፅ እንኳን አንደበት የለውም፤ ነገር ግን በውስጣዊ ማንነትሽ እሱነቱን አጥቶ ሌት ተቀን አንቺን በምናቡ ሲያወጣና ሲያወርድ፣ የአንቺን ህይወት ለማድመቅ የራሱን ሲያፈዝ፣ ከሰው በላይ የነበረው መቀመቅ ሲወርድ ያኔ ላንቺ ያንስብሻል። ያኔ ላንቺ ተራ ሰው ይመስልሻል። እናም ፍቅርሽን ገላሽን ለተመኘው ትሰጪና ደግመሽ ብትፈጠሪ እንኳን የማታገኝውን ንፁህ አፍቃሪሽን ልብ አንኮታኩተሽ ትሰብሪዋለሽ። እሱም ለዘለዓም ልቡ ታሞበት እንደማቀቀ ፍቅሩን ተቀምቶ አዝኖ አፈር ይሆናል። አንቺ ሳታውቂ ራስሽን የሰጠሽው ግን አውቆ ይተውሻል። በቃላት ድርደራ በስጦታ ጋጋታ ንግስት ያስመሰለሽ ያሻውን ፈጽሞ ሲያበቃ ከጥፍሩ ቆሻሻ እንኳን አይቆጥርሽም። ለዚ ነው የተመኘሽ እና ያፈቀረሽ የተለያዩ ናቸው ያልኩሽ......! ❤️❤️❤❤️❤️😂❤️ @yefkermenfese
Показати все...
🥀°•You don't know what you did, did to me Your body like wait, speaks to me I don't know what you did, did to me Your body like wait, speaks to me ❤️🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂                    •🦋@semhalyaa
Показати все...
47a7f844-d6af-450d-992c-55c860b5a57b.mp32.99 MB
Atrakig bene mot💔💔 Yastarqen mewdede💔💔😔 @yefkermenfese ,መልካም አዳር 🌟
Показати все...
5_6066821981989241969.ogg10.19 KB
💜✨ጓደኝነት✨💜 🌹🌹"አንዳንድ ሰዎች ወደ ካህን ሲሄዱ፤ ሌሎች ደግሞ ወደ ጠቢባን ያመራሉ እኔ ግን ወደ ጓደኞቼ መሄድ እመርጣለሁ።☃⛄️ @yefkermenfese
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.