cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የግጥም ረመጥ✍️

የግጥም ረመጥ አንዴ join ካሉ ሱስ የሚያስይዙ ግጥሞች የሚያገኙበት ስለፍቅር ስለሀገር ስለቤተሰብ ስለሁሉም ጉዳዮች የተገጠሙ ግጥሞችን የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል ከግጥም ቻናሉ ያልተስሞሟት ነገር ካለ እንዲስተካከል አስተያየት ይስጡን እናስተካክላለን። ለአስተያየቶች @SUNMAN111 👈👈 ይህን ይጠቀሙ። @Abelaaaaam @Abelaaaaam @Abelaaaaam

Більше
Рекламні дописи
531
Підписники
-124 години
-47 днів
-1130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

በ 40 ዓመቷ በጨጓራ ካንሰር ከመሞቷ በፊት በዓለም ታዋቂዋ ዲዛነር እና ደራሲ " ክሪስዳ ሮድሪጌዝ " እንዲ ስትል ፅፋለች ። 1⃣ ጋራዥ ዉስጥ የአለማችን ዉድ መኪና ነበረኝ ፣ አሁን ግን በዊልቸር መቀሳቀስ አለብኝ ። 2⃣ ቤቴ ሁሉንም አይነት ብራንድ ያላቸዉ ልብሶች ፣ ጫማዎች እና ዉድ እቃዎች ይሸጣል ፣ አሁን ግን ሰዉነቴ በሆስፒታሉ በተዘጋጀ ትንሽ ጨርቅ ተጠቅልሏል ። 3⃣ በባንክ ዉስጥ ብዙ ገንዘብ አለኝ ። አሉን ግን ከዚህ መጠን ምንም አልጠቀመኝም ። 4⃣ ቤቴ እንደ ቤተ መንግስት ነበር አሁን ግን በሆስፒታል ዉስጥ በሁለት አልጋዎች ተኝቻለዉ ። 5⃣ ከባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል . አሁን ግን በሆስፒታል ዉስጥ ከአንድ ላብራቶሪ ወደ ሌላ በመቀስቀስ ጊዜዬን አሳልፋለዉ 6⃣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ፊርማ ሰጥቻለሁ ነገር ግን በዚህ ጊዜ የሕክምና መዝገቦች የእኔ ፊርማ ናቸዉ ። 7⃣ ፀጉሬን ለመስራት ሰባት ፀጉር አስተካካዮች ነበሩኝ ፣ አሁን ግን በራሴ ላይ አንድ ፀጉር የለኝም ። 8⃣ በግል ጄት ላይ ፣ የትኛዉም ቦታ መብረር እችላለሁ ፣ አሁን ግን ወደ ሆስፒታል በር ለመራመድ ሁለት እርዳታዋች ያስፈልጉኛል ። 9⃣ ምንም እንኳን ብዙ ምግቦች ቢኖሩም አሁን የእኔ አመጋገብ በቀን ሁለት ኪኒን እና ምሽት ላይ ጥቂት የጨዉ ዉሃ ጠብታዎች ናቸዉ ። 1⃣0⃣ ይህ ቤት ፣ ይህ መኪና ፣ ይህ አዉሮፕላን ፣ ይህ የቤት ዕቃ ፣ ይህ ባንክ ፣ ብዙ ዝናና ዝና ፣ አንዳቸዉም አይመጥኑኝም ነበር ። አሁን ግን ከእነዚህ ዉስጥ አንዳቸዉም ሊደርሱልኝ እና ሊጠቅሙኝ አልቻሉም ። " የሰዉ ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለም ና ተጠንቀቁ ÷ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ ..... ። " ሉቃስ 12 ÷ 15
Показати все...
3
ዉበት ማለት ዉጫዊ ቅርፅ ብቻ ሳይሆን ዉስጣዊ ንፁህ ልቦናም ጭምር ያካትታል !
Показати все...
2
ጓደኛ ማለት ዛሬም ሆነ ነገ የማይለወጥ የደስታም ሆነ የሐዘን ተካፋይ መሆን የሚችል ክፋት የማይፈፅም ለተንኮል የማይሰለፍ ችግር ሲያጋጥም የማይሸሽ እና አብሮ የሚጋፈጥ ማለት ነዉ ።
Показати все...
1
የአንድ ወቶ አደር ሲቃ እናት ሀገር እናትዬ ፣ ላንቺ መድማት ፡ ላንቺ ብቆስል ይሁን ብዬ ፣ ካሳደገኝ ከእናቴ እቅፍ ፡ ከአባት ኩራት ተነጥዬ ፣ ከአያቶቼ የጀብድ ታሪክ ፡ ........ ከዚያች ሸጋ ፡ የአፍላ ፍቅሬን አንጠልጥዬ ፣ ወጣሁልሽ ፡ ስለ ሀገሬ አሜን ብዬ ................. ስለ እምዬ ። በዱር ባድር ፡ ከ እቶን ስር በበርሃ ፣ ድካም በዝቶ ስንገላታ ፡ እጎነጨዉ አጥቼ ዉሃ ። አፈር ምድሩን ፡ ባሩድ ሽታ እያወደ ፣ በዉሽንፍር በጥይቱ ፡ አካላቴ እየራደ ። ደግሞም ጥሎ ዶፍ መአቱ ፡ የበረዶዉ ቅዝቃዜ ፣ ከጭቃዉ ጋር ሲመሳሰል ፡ የልጅነት መልኬ ወዜ ፣ ተጫጭኖኝ ፡ ዐቢይ ድካም ወ ትካዜ ። ከምሽግ ስር እንደ ወደኩ ፡ ቢያልፉ ቀናት ፣ ሰላም ለኪ ብዬ ፡ አዛኝቱን ስማፀናት ፣ ልቤ ሲርድ ፡ ደም መርጨቱን እንዳቆመ እያስመሰለ ፣ ያ ጎልያድ ከበፊቴ ፡ እየፎከረ እየሸለለ ። ፍርሃት ወርሶኝ ፡ አካላቴ እያለቀ ፣ አዳኝ ጌታ እስኪ መስለኝ ፡ ከእኔ የራቀ ። አበቃለት ሞተ ዛሬ ፡ ሲሉኝ ንቀዉ ፣ እዉነቴን ነዉ ፡ ይህን ሁሉ ታግሻለዉ ፣ በምወደዉ ፡ በሰንደቅሽ እምላለዉ ። አምኖን ዛሬም ፡ ወንድምነቱን ዘንግቶ ፣ ክብርሽን ሊያጎድፍ ። ወስልቶ ፣ ድንግል አፈር መሬትሽን ፡ ቋምጦ ሽቶ ። ክፋት ወርሶት ፡ ጎኔን ሲወጋኝ ፣ ሳምነዉ ክዶ ፡ ቃየል ጨካኝ ሲሆንብኝ ። እስራትሽን ልፈታልሽ ፡ ያንን አዉሬ ስፋለመዉ ፣ ለካስ ያለዉ ጠላት ፡ ከጎኔ ነዉ ፣ በአላማ እንደ ወንድም ፡ እመኜዉ ፣ ሙሉ ልቤን ክፍት አድርጌ ፡ ባስጎበኘዉ ። ይሁዳ ነበር ፡ ባንዳነት ያለበት ፣ በደካማዉ ጎኔ ፡ ጥይት ሰደደበት ። ላንቺ መድማት ፡ ላንቺ ብቆስል ይሁን ብዬ ፣ እናት አለም ፡ እናት ሀገር ፡ እናትዬ ። ከአያቶቼ የጀብድ ታሪክ ፡ ..... ከዚያች ሸጋ ፡ የአፍላ ፍቅሬን ሳላጣጥም ፣ ..... ስለ ክብርሽ ፡ ትግል ስገጥም ። አለፍኩልሽ ፡ በእስትንፋሴ ፣ እስትንፋስሽን ፡ አስቀጥዬ ። Yibeltal Belay Zeleke
Показати все...
2
የቴዲ አፍሮ ወርቃማ አባባሎች ክፉን በመልካም ማሸነፍ ታላቅነት ነዉ ። በየትኛዉም ስፍራ ጥሩ ሆነህ ተገኝ ። ጥሩ ነገርንም አድርግ ። በህይወትህ የጎደለዉን እግዚአብሔር ይሞላልሃል ። እግዚአብሔር የምንፈራዉ በማዉራት ሳይሆን ከዉስጣችን ባለ ቅንነት እና የዋህነት ነዉ ። ብልህ ሰዉ ታናሹንም ያዳምጣል ።
Показати все...
2
ሁሌም ሰላም ደና ሁኑ በሁሉም ነገሮቻችዉ ላይ እግዚአብሔር ይርዳችዉ ሰላማችዉ ይብዛ እግዚአብሔር ይጠብቃችዉ
Показати все...
1
ደናዋሉ መልካም ቀን
Показати все...
1
እጅ እስካልሰጠህ ድረስ አልተሸነፍክም # የሰጠንን _ ብናዉቅ _ የጎደለን # የለም ። አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገዉ ። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም ። በደንብ ካስተዋልከዉ አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነዉ ። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸዉና ።
Показати все...
1
እናት ኮ አለም ናት ሁሉንም የቻለች ስንቱን ተሸክማ የምትኖር ሳትሰለች እናት ለምን ትሙት ትኑር ለዘላለም እርሷ የሌለችበት መራራ ናት አለም ስለያት ከጎኗ ካጠገቧ ስርቅ ሳቋ ብቻ ሳይሆን ቁጣዋ ' ሚናፍቅ ብበላ ብጠጣ አይደርስም ካንጀቴ ከጎኔ ከሌለች ገራገሯ እናቴ ፍቅሯ ወደር አልባ ቢነሳ ቢወደስ ፈገግተዋ ብቻ ከህመም የሚፈዉስ nahom
Показати все...
1
ደካማ መሆንን አትፍራ ጠንካራ በመሆንህ አትኩራ ማንም ምንም አለም ያሻዉን ይበል ዕራስህን ሁን መንገድህን ተከተል ዕድልህን ተጠቀምበት እንጂ አትልቀቀዉ ወደ ገርነት መመለስን አትተዉ
Показати все...
3