cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

🔔አንቀጸ አድሕኖ 🔔

√በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221

Більше
Рекламні дописи
349
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Показати все...
ዱባና ጤፍ ተመዘኑ አሉ፦ ጤፍ በለጠ... እንዴት ቢባል? የተመዘኑት በእህል ሚዛን ነዋ!!😊 "ልክህን ልታውቅ ስትፈልግ ሚዛንህን⚖ መለየት አለበህ። ብዙ ሰው ነው በሚዛኑ ምክንያት የትም ወድቆ የቀረው፤ ብዙ ሰው ነው ውሃ ልክ በሌለው ሚዛን ተመዝኖ ጨለማ ቤት ወድቆ የቀረው።" ለዚህ ነው አዝማሪው ባንጃው... ዘመም ዘመም ወደ ግራ ዘመም፣ እውነትን እያዩ ጎብጦ ለመታመም። ያለው ልክህን ማወቅ አለብህ፤ ሚዛንህን⚖ መለየት አለብህ!! #ከፍራሽ_አዳሹ_አንደበት... √በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221
Показати все...
🔔አንቀጸ አድሕኖ 🔔

√በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221

Repost from In Africa Together
በእለተ ሐሙስ የሚነበብ የሚተረጎም የሚጸለይ የእመቤታችን ምስጋና ይህ ነው። YouTube chanal ✥bisrat negari tube ✥ ብስራት ነጋሪ https://youtu.be/_yaEBlM2jgE
Показати все...
በእለተ ሐሙስ የሚነበብ የሚተረጎም የሚጸለይ የእመቤታችን ምስጋና ይህ ነው። YouTube chanal ✥bisrat negari tube ✥ ብስራት ነጋሪ

“አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ” ሉቃ 1 ፡28 ጾመ ፍልሰታ በከበረች ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የምንኖር የእግዚአብሔር ልጆች በረከትን ከምንቀበልባቸው የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ሲሆን በየዓመቱ ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 16 ቀን በታላቅ መንፈሳዊ ፍቅር ከወትሮው በበለጠ ሁኔታ ለእግዚአብሔር በመገዛት በተሰበረ ልቦና እና በተሰበሰበ ህሊና ከጥሉላት መባልዕት (ለሰውነት ብርታት ከሚሰጡ የእንስሳት ተዋፅኦ እና ቅባትነት ካላቸው ምግቦች) እና ከክፉ ስራ ሁሉ ተለይተን በበረከት የምንትረፈረፍበት የጾም ወቅት ነው። ፍልሰታ የሚለው ቃል ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መዛወር፣ የነበሩበትን ስፍራ ለቆ ወደ ሌላ ስፍራ መወሰድ ወይም መፍለስ ማለት ነው። ጾም አምላካችን እግዚአብሔርን የምናስብበት፣ ነፍስና ሥጋችንንም የምናስገዛበት ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ነው። በጾም የተጠቀሙ ቅዱሳን አበው ጾም የጸሎት እናት፣ የእንባ ምንጭ፣ የነፍስንም ቁስል የምትፈውስ መድኃኒት መሆኗን አስተምረውናል። በመሆኑም በከበረ ጾም የለበሱት መንፈሳዊ ጸጋ ዛሬም ድረስ ስማቸው በሚጠራበት ክብራቸው በሚዘከርበት ቦታ ሁሉ አጋንንትን የሚቀጠቅጥ ኃይልና የትሩፋት ፍሬ ሆኖ ይገኛል። ጾመ ፍልሰታን በመጀመሪያ ጊዜ የጾሙ ቅዱሳን ሐዋርያት ናቸው። የጾሙበት ምክንያትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥር 21 ቀን ነፍስዋ ከሥጋዋ ተለይታ አርፋለች። ከጌታችን ዕርገት በኋላ በእርስዋ ሲጽናኑ የነበሩ ቅዱሳን ሐዋርያት በእመቤታችን እረፍት አዝነው፤ አልቅሰው የከበረ ሥጋዋን ተሸክመው በክብር ለማሳረፍ ወደ ጌቴሴማኒ ሲጓዙ አይሁድ በክፋት ተነሱባቸው። ቀድሞ ‘ልጅዋ ተነሳ ዐረገ’ እያሉ ያስቸገሩን አንሶ ደግሞ እርስዋንም ‘ተነሳች ዐረገች’ እንዳይሉን ሥጋዋን እናቃጥል ብለው በኃይል መጡባቸው። ከእነዚሁ አይሁድ መካከል ጉልበታም የነበረ ታውፋንያ የተባለ ሰው በጉልበቱ ታምኖ የእመቤታችንን የከበረ ሥጋዋን ጎትቼ እጥላለሁ ብሎ የአልጋውን ሸንኮር ቢይዝ የእግዚአብሔር መልአክ ሁለት እጁን ቀጥቶታል። ወዲያውም መላኩ የከበረች የድንግልን ሥጋ ከወንጌላዊው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በደመና አሳርጎታል። የቀሩት ቅዱሳን ሐዋርያት ስለ እመቤታችን ሲያዝኑ ሲተክዙ ቅዱስ ዮሐንስን አግኝተው የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ? ቢሉት በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አለች ብሎ አጽናንቷቸዋል። ከዚህ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት በመንፈሳዊ ፍቅር እና ቅናት ተነሣሥተው ለቅዱስ ዮሐንስ የተገለጠ ምስጢር ለእኛም ይገለጥልን ብለው ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ገቡ፤ በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ሰነበቱ። ሁለተኛውን ሱባኤም ሲጨርሱ በ14ኛው ቀን እግዚአብሔር ልመናቸውን ሰምቶ የከበረ መዓዛ ያለውን የእመቤታችንን ሥጋ በመላእክት እጅ አምጥቶ ሰጥቷቸዋል። ቅዱሳን ሐዋርያትም በፍጹም ምስጋናና በታላቅ ክብር እመቤታችንን በጌቴሰማኒ ቀብረዋታል። ይህ በሆነ በሦስተኛው ቀን ማኅደረ መለኮት ናትና መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳትል የልጇ ሥልጣን ፍጹም ኃይል ሆኗት በክብር ተነሥታለች። ትንሣኤዋን ‘ከመ ትንሣኤ ወልዳ’ ወይም ‘እንደ ልጇ ትንሣኤ’ ነው ያሰኘውም ይሄ ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሙታን ተነሥታ፣ በውዳሴ መላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ ከቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ አግኝቷታል። ሐዋርያው ቶማስም ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ከወንድሞቼ ተለይቼ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሣኤ ለማየት አልታደልኩም ብሎ በጣም አዘነ። እመቤታችንም ቶማስን ‘ከአንተ ቀድሞ ትንሣኤዬን ያየ የለም እንግዲህ ሄደህ ለወንድሞችህ ሐዋርያት ተነሣች ዐረገች ብለህ የምሥራች ንገራቸው፣ ምልክትም ይሆን ዘንድ እነሆ መግነዜን (ሰበኔን) ውሰድ ፣ አንተ ዕርገቴን እንዳየህ እነርሱም ይህን አይተው እንዲያምኑ’ ብላው ወደ ሰማይ ዐረገች። የሐዋርያው ቶማስ ሀዘንም ወደ ደስታ ተለወጠ። ይህ ሐዋርያ ኢየሩሳሌም ደርሶ ሌሎቹ ሐዋርያትን አገኛቸው ‘የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ?’ ብሎም ጠየቃቸው። እነርሱም እንደቀበሯት ነገሩት። ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ይህ እንዴት ይሆናል? አላቸው። እነርሱም መጠራጠር ልማድህ ነው እያሉ መቃብሯን ሊያሳዩ ወሰዱት። ሲደርሱም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙት ፣ እጅግም ደነገጡ። ቶማስም አትደንግጡ እመቤታችን ከሙታን ተነሥታ በውዳሴ መላእክት፣ በክብር ስታርግ አግኝቻታለሁ። እንዲያውም የተከፈነችበትን ሰበን ሰጥታኛለች ሲል ከእመቤታችን እጅ የተቀበለውን ሰበን አሳያቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም በሆነው ሁሉ ተደነቁ። በቶማስ እጅ ያለውንም የእመቤታችንን ሰበንዋን ለበረከት ተከፋፈሉት። በሰበኑም ሙት ያስነሱበት፣ ድውይ ይፈውሱበት፣ አጋንንትን ያርቁበት ነበር። ዛሬም ድረስ ያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ አርፎበት የነበረው መቃብር በምዕመናን ይጎበኛል። ቅዱሳን ሐዋርያት ሐዋርያው ቶማስ ያየውን የእመቤታችንን የትንሳኤዋንና እርገቷን ክብር ያዩ ዘንድ በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን ደግመው ሱባኤ ገቡ። በ16ኛው ቀን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከከበረች እናቱ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ተገለጠላቸው። እመቤታችንን መንበር፣ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ ቅዱስ እስጢፋኖስን ዋና ዲያቆን አድርጎ እርሱም ገባሬ ሰናይ ካህን ሆኖ ቀድሶ አቁርቧቸዋል። የቅዱሳን ሐዋርያቱም ሱባኤ ሰምሮላቸዋል። በዚሁ መሰረት የከበረች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ምዕመናን ቅዱሳን ሐዋርያቱን አብነት በማድረግ እነርሱ በዚህ ታላቅ ሱባኤ እመቤታችንን እንዳገኙ፣ የማያልቅ የእናትነት በረከቷን ለማግኘት፣ በተወደደ አማላጅነትዋም የልጇን ይቅርታና ምህረት ለማግኘት፣ በየዓመቱ ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን። ቅድስት ቤተክርስቲያን በቅዱሳን ሐዋርያት ተባርኮ በተሰጠን በዚህ ጾመ ፍልሰታ ሌሊቱን በሰዓታት፣ ነግሁን በኪዳን እና በመንፈስ ቅዱስ ከተሞሉት ቅዱሳን አባቶቻችን ከቅዱስ ኤፍሬምና ከአባ ሕርያቆስ በፈቃደ እግዚአብሔር የተገኙትን የእመቤታችንን ምስጋናዎች የውዳሴዋን እና የቅዳሴዋን ትርጓሜ በማሰማት ቅዱስ ወንጌሉ ተሰብኮ በከበረ ቅዳሴ የመድኃኔዓለምን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ታቀብላለች። ይህ ምስጢር የተረዳቸው በርካታ ምዕመናን ሱባኤውን በታላላቅ ገዳማት ተወስነው ሲያሳልፉ እጅግ ብዙዎች ደግሞ በያሉበት ደብር ሥርዓተ ቅዳሴውን እያስቀደሱና በጸሎት እየተማጸኑ ይጠቀሙበታል። እንግዲህ በያለንበት ቦታ በዚህ ሱባኤ በንስሐ በታጠበ ሕይወት በረከተ ቅድስት ድንግል ማርያምን ለማግኘት እንድንተጋ ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታሰማለች። የእግዚአብሔር አብ ጸጋ ፣የእግዚአብሔር ወልድ ቸርነት፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ከሁላችንም ጋር ይሁን አሜን።

Показати все...

በከንቱ እንዳንደክም መጾም እንደሚገባን እንጹም በመጾም እየደከምን ሳለ የጾም አክሊልን ካላገኘን፥ እንዴትና በምን ዓይነት አኳኋን ይህን ልንፈጽመው እንደሚገባው ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ ፈሪሳዊዉም ጾሞ ነበርና፤ ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤቱ የኼደው ባዶ እጁንና የጾሙን ፍሬ ሳያገኝ ነውና (ሉቃ.18፡12)፡፡ ቀራጩ ደግሞ በአንጻሩ አልጾመም ነበር፤ ነገር ግን ከጾመው ፈሪሳዊ ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘው እርሱ ነው፡፡ ይህም የኾነበት ምክንያት [ቀራጩ ባይጾምም ተጠቀመ፤ በመፃዒ ሕይወቱም ጾም አላሻውም ለማለት ሳይኾን ከተአምኖ ኃጣውእ ጋር] ሌሎች ግብራት ካልተከተሏት በቀር ጾም ረብ ጥቅም እንደሌላት [እና ትሕትና የጾም አጣማጅ መኾኑን/ የምትሠምረው ከትሕትና ጋር መኾኑን] እንድታውቅ ነው፡፡ የነነዌ ሰዎች ጾመዋል፤ የእግዚአብሔር ምሕረትንም አግኝተዋል (ዮና.3፡10)፡፡ እስራኤላውያንም ጾመው ነበር፤ ነገር ግን እያጉረመረሙ ተመለሱ እንጂ በመጾማቸው አንዳች ጠቀሜታን አላገኙም (ኢሳ.58፡3-7፣ 1ኛ ቆሮ.9፡26)፡፡ ስለዚህ እንዴት መጾም እንዳለባቸው ለማያውቁ ሰዎች የጾም ጉዳቱ ትልቅ ነውና በጥርጣሬ እንዳንኼድ፣ እንዲሁ አየርን እንዳንደልቅ፣ እንዲሁ ከጨለማ ጋር እንዳንጋደል፥ ይህን የምናከናውንባቸውን ሕጎች ልንማር ያስፈልገናል፡፡ ጾም መድኃኒት ናት፡፡ አወሳሰድዋን በትክክል ላላወቁ ግን ጥቅም የላትም፡፡ ይህችን መድኃኒት የሚወስድ ሰው በየስንት ሰዓቱና በምን ያህል መጠን እንደምትወሰድ፣ ለምን ዓይነት በሽታ እንደምትጠቅም፣ በየትኛው አከባቢና የአየር ኹናቴ እንደምትወሰድ፣ ከእርሷ ጋር የሚኼዱና የማይኼዱ ምግቦችን እንዲሁም ከእርሷ ጋር የማይስማሙ ሌሎች ነገሮችን ለይቶ ማወቅ አለበት፡፡ እነዚህን ግምት ውስጥ አስገብቶ የማይወስዳት ሰው ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ታመዝንበታለች፡፡ አንድ በሐኪም የታዘዘልንን የደዌ ዘሥጋ መድኃኒት እንዲያሽለን ስንፈልግ በጥንቃቄ ልንወስደው ያስፈልጋል፤ የነፍሳችንን ደዌና በአእምሮአችን ውስጥ ያሉ ቁስሎችን ለመፈወስ ብለን በምንወስደው መድኃኒት ደግሞ ከዚህ የበለጠ መጠንቀቅ ይገባናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #በእንተ_ሐውልታት_መጽሐፍ √በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221
Показати все...
🔔አንቀጸ አድሕኖ 🔔

√በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221

ዐቢይ ጾም ዐቢይ ለምን ተባለ ቢሉ ‹‹#ዐበየ›› ማለት ከፍ አለ ማለት ሲሆን ከዚህም ግስ አቢይ የሚለው ቅጽል ይገኛል፡፡ዐቢይ ማለት ከፍ ያለ ትልቅ ማለት ነው፡፡ ዐቢይ ጾም የተባለበት ምክንያት፡- ሀ. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም ስለሆነ ለ. በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት የሚበልጥ ስለሆነ ሐ. ሦስቱ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም ➛ ትዕቢት ➛ ስስት ➛ ፍቅረ ነዋይ ድል የተመቱበት ስለሆነ ነው በቤተክርስቲያን ስያሜ መሰረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፡- 1. ዘወረደ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው 2. ቅድስት ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ስለዚህም ዕለተ ሰንበት ቅድስት ተብላለች 3. ምኩራብ ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኩራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ይህች ዕለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ ገብቶ እንዳስተማረ የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ ምኩራብ ማለት የቤተ አይሁዳውያን የጸሎት ቤት ነው 4. መጻጉዕ ይህ የአራተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ እውራንን ማብራቱ ለምጻምን ማንጻቱ ሽባዎችን መተርተሩ የሚያነሳ መዝሙር የሚዘመርበት እንዲሁም እነዚህ ሁሉ ድንቅ ገቢራተ ታምራቶች የሚዘከሩበት ዕለት ነው 5. ደብረ ዘይት ይህ የአምስተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ነገረ ምጽአቱን እንዳስተማረ የሚወሳበት ሰንበት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ማለት ወይራ የበዛበት ተራራ ማለት ነው 6. ገብርኄር ይህ የስድስተኛው ሳምንት ሰንበት ስያሜ ሲሆን ይህም ዕለት ለጌታው ታማኝና በጎ የሆነው ባርያ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ተብሎ እንደተመሰገነ የሚነገርበት ዕለት ነው 7. ኒቆዲሞስ ይህ የሰባተኛው ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ይህም ዕለት ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ መምህር በሌሊት ወደ ጌታው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየመጣ ይማር እንደነበረ ይታሰብበታል በዚም ዕለት የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል 8. ሆሳዕና ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቷ እና በውርንጭላይቷ ላይ ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ተብ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚተሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን √በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221
Показати все...
🔔አንቀጸ አድሕኖ 🔔

√በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221

#አባ_ዮሐንስ_ሐጺር_ትምህርቶች የጠላቱን ከተማ ለመቆጣጠር የዘመተ ንጉሥ አስቀድሞ የውኃውን መንገድ ይዘጋል ፣ የእህሉንም መግቢያ ይይዛል። ያንጊዜ ጠላቶቹ ይራባሉ ይጠማሉ። በመጨረሻም እጃቸውን ይሰጣሉ። የነፍስን ፆር ለማሸነፍም በተመሳሳይ መንገድ መጠቀም ይገባል። አንድ ሰው በጾምና በረኃብ ከጸና የነፍሱ ጠላቶች ይዳከማሉ። ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ እኔ በትልቅ ዋርካ ሥር የተቀመጠንና አራዊት ሊጣሉት የመጣን ሰው እመስላለሁ። ሊቋቋማቸው እንደማይችል ከተረዳ ሸሽቶ ወደ ዛፉ በመውጣት ነፍሱን ያድናል። በእኔም የተፈጸመው ይኼው ነው። በበዓቴ ተቀምጬ ክፉ ሐሳቦች ሊቃወሙኝ ሲመጡ ፣ ልቋቋማቸው እንደማልችል ባወቅኹ ጊዜ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ሸሽቼ እመሸጋለሁ። በዚያም ከጠላቶቼ ፍላፃ እድናለሁ። ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ መለወጥ የምትፈልግ ነፍስ በተመለከተ አባ ዮሐንስ እንዲህ አለ፦ በአንዲት ከተማ ውስጥ ብዙ ወዳጆች የነበሯት አንዲት አመንዝራ ሴት ነበረች። ከገዥዎቹ አንዱ ቀረባትና "መልካም ሴት ለመሆን ቃል ግቢልኝና አገባሻለሁ" አላት። እርሷም ቃል ገባችለትና ተጋቡ። ወደ ቤቱም ወሰዳት። የቀድሞ አፍቃሪዎቿ ያቺን ሴት ፈለጓት። እርስ በእርሳቸውም "ያ ልዑል ወደ ቤቱ ወስዷታል ፤ ወደ ቤቱ ብንሄድ ይቀጣናል። ነገር ግን በጓሮ በኩል እንሂድ ፣ ለእርሷም እናፏጭላት፥ የፉጨቱን ድምጽ ስትሰማ ከድርሱ ወርዳ ወደኛ ትመጣለች፤ በዚህም ያለ ችግር እናገኛታለን" ተባባሉ። ወደ ቤቷም ጓሮ ተጉዘው ያፏጩ ጀመር። እርሷ ግን የፉጨቱን ድምጽ ስትሰማ ጆሮዎቿን ደፈነች። ወደ ውስጣዊው እልፍኝም ገባች። በሩንም ጥርቅም አድርጋ ዘጋች። ይህች ሴት የእኛ ነፍስ ምሳሌ ናት። ወዳጆቿ የተባሉም ፈተናዎቿ ናቸው፣ ገዥ የተባለውም ክርስቶስ ነው፣ እልፍኝ የተባለውም ዘለዓለማዊው ቤት ነው። እነዚህም የሚያፏጩት ክፉዎች አጋንንት ናቸው፣ ነገር ግን ነፍስ ሁልጊዜም በክርስቶስ አምባነት ትሸሸጋለች። ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ አባ ዮሐንስ ልቡናው ከእግዚአብሔር ጋር ስለነበረ ምድራዊ ነገሮችን ይዘነጋ ነበር። አንድ ቀን አንድ ወንድም ቅርጫት ሊወስድ ወደ አባ ዮሐንስ በአት መጣ። አባ ዮሐንስም ምን ፈልጎ እንደሆነ ጠየቀው። ያም ወንድም "ቅርጫት ፈልጌ ነው" አለው። አባ ዮሐንስ ወደ በኣቱ ተመለሰና ዘንግቶት ወደ ሽመና ሥራው አመራ። ጥቂት ቆይቶ ያ ወንድም አንኳኳ አባ ዮሐንስም ወጥቶ "ምን ፈልገህ ነው?" አለው። "ቅርጫት ስጠኝ ብየህ ነበር" ሲል መለሰለት። ተመልሶ ወደ በኣቱ ሲገባ ልቡናው በሰማያዊ ነገር ስለተመሰጠ ዘንግቶት ወደ ሽመና ሥራው እንደገና ገባ። ለሦስተኛ ጊዜ ያ ወንድም ሲያንኳኳ አባ ዮሐንስ ተመልሶ መጣና "ምን ፈልገህ ነው?" አለው። "ቅርጫት ስጠኝ ብየህ ነበር" አለና መለሰለት። አባ ዮሐንስም እጁን ይዞ እየጎተተ ወደ በኣቱ አስገባውና "ቅርጫት ከፈለግህ ያዝና ሂድ፣ በእውነቱ እንዲህ ላሉት ነገሮች እኔ ጊዜ የለኝም" አለው። ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ አንድ ቀን አንድ ሰው ወደ አባ ዮሐንስ ሐጺር በኣት መጣና ሥራውን እያየ ያመሰግነው ጀመር። አባ ዮሐንስ ዝም አለውና ገመድ መሥራቱን ቀጠለ። እንግዳውም እንደገና ወሬውን ቀጠለ ፣ አባ ዮሐንስም ጸጥ አለው። ለሦስተኛ ጊዜ እንግዳው ወሬ ሲያበዛ "አንተ ወደ በኣቴ በመግባትህ እግዚአብሔር ወጥቶ ሄደ" ብሎ ተናገረው። ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ አባ ዮሐንስ እንዲህ አለ፦ "የብሕትውናን ኑሮ በከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነበረ። ያ ሰው በከተማው ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውና ባለዝናም ነበር። አንድ አረጋዊ አባት ከማረፉ በፊት ያንን ሰው ሊያየው እንደሚፈለግ ለዚያ ሰው ጥሪ ደረሰው። ያም ሰው በቀን ከተጓዝኩ ሰዎች ስለሚከተሉኝ ለኔ የተለየ ክብር ይሰጡኛል ብሎ አሰበ። ስለዚህም በሌሊት ሰው ሳያየው ለመጓዝ ወሰነ። በመሸ ጊዜም አሁን ማንም አያየኝም ብሎ ተነሣና ጉዞ ጀመረ። ነገር ግን ሁለት መላእክት ታዝዘው ፣ መብራት ይዘው መንገዱን ይመሩት ነበር። ይህንን የተመለከቱ የከተማው ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ ፣ መላ ከተማው ያንን የመላእክት ብርሃን እያየ ከኃላ ተከተለው። ከክብር በሸሸ ቁጥር የበለጠ ክብርን አገኘ። በዚህም "ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል ፤ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ከፍ ይላል።" የሚለው የወንጌል ቃል ተፈጸመ (ሉቃ. ፲፬፥፲፩)። ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ ነሐሴ 29 በዚችም ቀን የአባ ዮሐንስ ሐጺር ወደ አስቄጥስ ገዳም የሥጋው ፍልሰት ሆነ ። የአበው በረከት ይደርብን √በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221
Показати все...
🔔አንቀጸ አድሕኖ 🔔

√በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221

#ነሐሴ_29 #ቅዱስ_አባ_ዮሐንስ_ሐጺር ነሐሴ ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን የአባ ዮሐንስ ሐጺር ወደ አስቄጥስ ገዳም የሥጋው ፍልሰት ሆነ። ይህም የአባ እንጦንዮስ በሆነ በቊልዝም ገዳም ከአረፈ በኋላ ነው። ለእስክንድርያ አባ ዮሐንስ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ስምንተኛ የሆነ ነው። እርሱም ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ የከበሩ መነኰሳትም እንዲህ አሉት የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ሥጋ በዚህ በቤተ ክርስቲያኑ ቢሆን እኛም ሥጋው በአለበት ለፈጣሪያችን እግዚአብሔር እንሰግድ ዘንድ እንሻ ነበር። ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቸርነት አነሣሣችውና ስሙ ቆዝሞስ ለሚባል ለአንድ አበ ምኔት መልእክትን ጻፈ ከእርሱም ጋር የቊልዝም አገር የሆነ አረጋዊ አለ በደረሱም ጊዜ በዚያን ሰዓት ሥጋውን መውሰድ አልተቻላቸውም። የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ሥጋ የኬልቄዶንን ጉባኤ በተቀበሉ መለካውያን ዘንድ ይጠበቅ ስለነበረ ነገር ግን ቦታውን አወቁ ተረዱ ወደ ቦታቸውም ተመልሰው ሃይማኖታቸው የቀና ምእመናን ሰዎችን አገኙ እነርሱም በዚያች አገር የሚኖሩ ናቸው ስለርሱ የመጡበትን ነገሩአቸው። ከጥቂት ቀኖች በኋላም ከታላላቅ ዐረቦች ወገን ለቊልዝም አገር መኰንን ተሾመ እርሱም ለኤጲስቆጶስ አባ ሚካኤል ወዳጁ ነው ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስም ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ሥጋ ወደ ኤጲስቆጶሱ መልእክትን ጻፈ። በመልእክቱም የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ሥጋ ከከሐድያን መለካውያን እጅ እስከ አፈለሱት ድረስ መልእክተኞች አእሩግ መነኰሳትን ምክንያት ፈልጎ እንዲረዳቸው በማሳሰብ አዘዘው። ኤጲስቆጶሱም በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደስ አለው ሒዶም ወዳጁ ለሆነ ለመኰንኑ ጸሐፊ ነገረው። ጸሐፊውም ለመኰንኑ ነገረው። እነሆ መኰንኑም ከመነኰሳቱ ጋራ ሔደ ጸሐፊውም መነኰሳቱ ወደዚያ ቦታ እንዲገቡ ምክንያት እንዴት እናገኛለን አለ።መኰንኑም በልብሶቻቸው ላይ የዓረቦችን ልብሶች ያልብሱአቸውና ከእኔ ጋራ ወደዚያ ቦታ ይምጡ አለ እንዲሁም እንዳላቸው አደረጉ። ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሔደ ከእርሱም ጋራ ብዙ ፈረሰኞች ሰዎች ብዙ ሕዝብም የአስቄጥስ ገዳም የከበሩ አረጋውያን አሉ ወደቊልዝም ገዳምም ደረሱ። መኰንኑም በዚያ የሚኖራውን የመለካውያን ኤጲስቆጶስ እንዲህ ብሎ አዘዘው ያንተን ሰዎች ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ አስወጣቸው በዚች ሌሊት እኔ በውስጧ አድራለሁና ያ መለካዊም መኰንኑ እንዳዘዘው አደረገ። መነኰሳቱም እንስሶቻቸውን ከከተማ ውጭ አዘጋጅተው በሌሊት ወደዚያ ገብተው የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ሥጋ ይዘው ወደ ምስር ደረሱ ከዚያም ወደ አስቄጥስ ገዳም ደረሱ የአባ መቃርስ ገዳም መነኰሳትም መስቀሎችን፣ ወንጌሎችን፣ ማዕጠንቶችንና መብራቶችን በመያዝ እየዘመሩና እያመሰገኑ ተቀበሏቸው ወደ አባት መቃርስ ሥጋም አቀረቡትና ከእርሱ ተባረኩ በላዩም ብዙ ሽቱዎችን ነሰነሱ የቊርባን ቅዳሴንም ቀደሱ የከበረ ወንጌልም በሚነበብ ጊዜ ታላቅ ድንቅ ተአምር ተገለጠ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለመናዋ በሰማያዊ ብርሃን በራች። ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ በጎ መዓዛ ሸተተ ታላቅ ደስታም ሆነ በዚያም ቦታ ሰባት ቀን ኖረ። ከዚህም በኋላ ወደ ራሱ ቤተ ክርስቲያን ተሸክመው ወሰዱት ዕብራውያንም በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እያሉ መድኃኒታችንን እንደተቀበሉት ልጆቹ መነኰሳት ተቀበሉትና ወደ ቦታው አኖሩት ከእርሱም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስ በወጣ ጊዜ ወደ አባ ዮሐንስ ሐጺር ቤተ ክርስቲያን ገባ። ከእርሱም ጋር ብዙዎች ኤጲስቆጶሳትና የእስክንድርያ አገር ታላላቆች ከግብጽ አገር ሁሉ አሉ። የአባ ዮሐንስ ሐጺር ሥጋ የተጠቀለለበትን ሰሌን ገልጦ ከእርሱ ተባረከ መሪር ልቅሶንም አለቀሰ ያን ጊዜ ሥጋው ሲገለጥ መብረቅና ነጐድጓድ ሆነ።በቤተ ክርስቲያኑም ውስጥ ያሉት ሁሉም ደንግጠው ወደቁ ሊቀ ጳጳሳቱም ሰሌኑን መልሶ በፍጥነት ሥጋውን ጠቀለለ በሽብሸባ እየዘመሩና እያመሰገኑ እንደቀድሞው ሸፈነው። ከዚህም በኋላ ዳግመኛ እንዲህ እያሉ ሊያመሰግኑ ጀመሩ ፈጣን ደመና ሁነህ የመንፈስ ቅዱስን ዝናም የተሸከምክ ሠለስቱ ደቂቅ ወዳሉበት ወደ ባቢሎን የሔድክ በላይህ በአደረ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ እስከንድርያ አገር የተመለስክ ሁለተኛም ወደ ቊልዝም የሔድክ የጣዖታትን ቤቶች አፍርሰህ ሃይማኖትን የሰበክ በሽተኞችን የፈወስክ አጋንንትን ያስወጣህ ወደርስትህም የተመለስክ አንተ የበረከት ማደሪያ ነህና። የአባ ዮሐንስ ሐጺር የሥጋው ፍልሰት ከንጹሐን ሰማዕታት ዘመን በአምስት መቶ ሃያ ዓመት ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎት ይማረን √በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221
Показати все...
🔔አንቀጸ አድሕኖ 🔔

√በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221

"እኔ ከእርሱ [ከባልንጀራዬ] ጋር ምንም ግንኙነት የለኝምና የሚል ደካማ መልስም አትስጠኝ፡፡ ምንም ግንኙነት የሌለን ከዲያብሎስ ጋር ብቻ ነው፡፡ ከሰዎች ኹሉ ጋር ግን በጣም ብዙ የምንጋራቸው ነገሮች አሉ፡፡ ምክንያቱም አንድ ዓይነት ባሕርይ (ሰው መኾንን) አለን፤ እኛ በምንኖርባት ምድር ይኖራሉ፤ እኛ የምንበላውን ምግብ ይበላሉ፤ አንድ ጌታ አለን፤ እኛ የተቀበልነውን ሕግ ተቀብለዋል፤ እኛ ወደ ተጠራነው መንግሥትም ተጠርተዋል፡፡ ስለዚህ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ምንም የሚያገናኘን ነገር የለም አንበል፡፡ እንዲህ ብሎ መናገር ሰይጣናዊ ንግግር ነውና፡፡ ዲያብሎሳዊና ኢ-ሰብአዊነት ነውና፡፡ ስለዚህ ለወንድማችን ያለንን ጥንቃቄ እናሳይ እንጂ እንደዚህ ዓይነት ቃላትን አንናገር፡፡" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ √በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221
Показати все...
🔔አንቀጸ አድሕኖ 🔔

√በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221

#ዕርገተ_ማርያም - (#ነሐሴ_16) ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ። ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር ። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው ። ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ ። የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ሥር ተቀምጦ አየው ። የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው ። እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት ። ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ ። የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ ። ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፀዋት ሁሉም አዘነበሉ መላእክት የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት ። አባቷ ዳዊትም ንግሥት እመቤታችን ወርቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች እያለ በበገና አመሰገናት ። በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኋላ በልጁዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች ። ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው ። እርሱም እንደ አየ እንደ ሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንደ አሳረጓት ነገራቸው ። ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ ። ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና የፍቅር አንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ ። እነሆ እኔ እርሷን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል አላቸው ይህንንም ብሎ ከእርሳትው ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ ። ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ለሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሰየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በመጾም የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን ። በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ የነሐሴ ወር እንደ ዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው ። በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት። እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዒ ካህን ሆነ ። እስጢፋኖስም አዘጋጀ ዮሐንስም በመፍራት ቁሙ አለ ። ሁሉም ሐዋርያት በመሠዊያው ዙሪያ ቆሙ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ። ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው ። ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት። በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰብኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው ። መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ ። የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለችው ልጄ ሆይ እነሆ በዐይኖቻቸው አዩ በጆሮቻቸውም ሰሙ በእጆቻቸውም ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ደንቆች ሥራዎችን አዩ ። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ ። የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ ማትያስ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ) √በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221
Показати все...
🔔አንቀጸ አድሕኖ 🔔

√በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ስርዓትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶችን ያገኙበታል ። ፩ እምነት ፩ ዲት ጥምቀት ፩ ሃይማኖት (ኤ ፌ፬÷፭) ✥✥✥✥✥✥✥✥✥ t.me/AnkesteAdeheno1221