cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

አያሌው ቢታኔ በማናቸውም የፌዴራል እና የክልል ፍርድ ቤቶች ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ቢሮ

ይህ ገፅ ለማንኛውም ሰው ስለ ህግ እና ህግ ነክ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሚሰጥበት ፣ በተለያዩ ጊዜያት የወጡ አዋጆች ፣ደንቦች እና መመሪያዎች የሚጋሩበት ነው ለበለጠ መረጃ 0911911313 Telegram username:- @Justicehastobeserved

Більше
Рекламні дописи
859
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
+1230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣች ሶሊያና ዳንኤል የተባለችውን የሁለት ዓመት ሕፃን በመጥለፍ እና በከባድ ስርቆት ወንጀል የተከሰሰችው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣች፡፡ ሕፃን ሶሊያና ዳንኤል በቤት ሰራተኛቸው ተሰርቃ የተወሰደችው መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ሳሪስ አዲስ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ነበር፡፡ ቤዛዊት በቀለ በተባለችው የቤት ሰራተኛቸው ተሰርቃ የተወሰደችውን ሕፃን ለማግኘት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሐየራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት፣ ከአዲስ አበባ ውጪ ወደ ተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች እና አካባቢዎች በመሄድ ጭምር አስፈላጊ መረጃዎችን በማሰባሰብ ከፍተኛ ጥረትን የጠየቀ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ፖሊስ አስታውሷል፡፡ በተደረገው ክትትልም ቤዛዊት በቀለ መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም ሱሉልታ ከተማ "ኖኖ መና አቢቹ" ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ሕፃን ሶሊያና ዳንኤልን ሸሽጋ በተቀመጠችበት በቁጥጥር ስር መዋሏ ይታወሳል፡፡ እንደ አዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ፤ ግለሰቧ በቁጥጥር ስር መዋሏን ተከትሎ ፖሊስ ባከናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ ከዚህ ቀደም በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠረችባቸው 5 የተለያዩ ቤቶች ውስጥ ልዩ ልዩ ንብረቶችን መስረቋ መረጋገጡ ተገልጿል፡፡ ከሰረቀቻቸው ንብረቶች መካከልም 2 ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣ 1 ሞባይል ስልክ እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ፖሊስ ባደረገው ጥረት ከሸጠችበት በምሪት እንዲመለሱ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡ በግለሰቧ ላይ ምርመራ ተጣርቶ በከባድ ስርቆት እና ሕፃን ልጅ መጥለፍ በሚል ወንጀል በአቃቤ ሕግ ክስ ከተመሰረተ በኋላ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ቤዛዊት በቀለ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
Показати все...
👍 3 1
ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገልጋዮች በሙሉ ወደ ፍርድ ቤቱ  አቤቱታ፣ መልስ እና የመልስ መልስ በሰነድ ከሚቀርበው በተጨማሪ በሶፍት ኮፒ በሲዲ መቅረብ  እና ከመዝገቡ ጋር መያያዝ ያለበት መሆኑ ይታወቃል ሆኖም ፍርድ ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽ ለማድረግ ቀድሞ በሲዲ ብቻ ሲቀርብ ከነበረው በተጨማሪ ከቀን 18/10/2016 ዓ.ም ጀምሮ በፍላሽና በሌሎች በማንኛውም ሊገለበጡ በሚችሉ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች አማካኝነት ሬጅስትራር ጋር በመቅረብ የሶፍት ኮፒ ቅጅዎችን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Показати все...
ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነፃ ስለመሆን ከግብር ነፃ ከሆነው በስተቀር ቀጣሪው ለተቀጣሪው በሚከፍለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን ላይ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ይከፈልበታል፡፡ ከመቀጠር ከሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነጻ የሚሆኑባቸው ሁኔታዎች አሉ ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡- የሚከተሉት ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነፃ ይሆናሉ፡-¬ — ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፤ — በሥራ ውል መሠረት ለሠራተኛው የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፤ — በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈል አበል፤ — ሠራተኛው ከመደበኛ ሥራው ውጪ ሥራውን ለማከናወን ሲንቀሳቀስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ እና የውሎ አበል፤ — የመጓጓዣ ወጪው በቅጥር ውሉ መሠረት የተከፈለ ከሆነ ከሥራ ቦታው ውጪ ተመልምሎ ለተቀጠረ ሠራተኛ ወደ ሥራው ሲመጣ ወይም ሥራውን አጠናቆ ሲመለስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ፣ እንዲሁም የውጭ ሀገር ሠራተኞች ከሀገራቸው ሲመጡና ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የሚከፈል የመጓጓዣ ወጪ፤ — የማዕድን ማውጣት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርና የንግድ ሥራ የሚሠራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብና መጠጥ፤ — የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በውጭ አገር ለሚመድባቸው ሠራተኞች የሚከፈል አበል፤ — የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም የፌደራልና የክልል መንግሥታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፤ — ለሠራተኛው ጥቅም ተብሎ ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ 15 % (አሥራ አምስት በመቶ) ባልበለጠ መጠን በየወሩ በቀጣሪው የሚዋጣ የጡረታ መዋጮ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ፤ — በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እና በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ የጡረታ ገቢ፤ — የኢትዮጵያ የፌደራል፣ የክልል ወይም የአካባቢ መንግሥታት ወይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛ ሥራዎቻቸው ጋር በተያያዘ የሚያገኙት ገቢ፤ — በዓለም አቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፤
Показати все...
👍 3
ከአሜሪካ ውጪ በግሪን ካርድ በመኖር ወይም በመጓዝ ግሪን ካርዳችንን ልናጣ እንችላለን? በሙሉዓለም ጌታቸው 1) የአሜሪካ ከስተም እና ቦርደር ፕሮቴክሽን (CBP) በግሪን ካርድ ከአሜሪካ ወጥተን ስንመለስ፤ በብዙ ጥያቄዎች ይወጥሩናል። የዚህ ትልቁ ምክንያት እነዚህ ኦፊሰሮች የመኖሪያ ፍቃድ ያለው ግለሰብ በአሜሪካ የመኖር መብቱን ማጣቱን እና አለማጣቱን ለመወሰን ነው። የCBP ኦፊሰሮች ያን ውሳኔ ማስተላለፍ ሕጉ የሚፈቅድላቸው ሲሆን፤ በተጨማሪም USCIS Notice to Appear Before Court በመላክ በኢምግሬሽን ዳኛ በኩል ያን ውሳኔ ሊያስተላልፍ ይችላል። ግሪን ካርዳችንን ላለማጣት ምን እናድርግ? አሜሪካ ውስጥ በዘላቂነት ለመኖር ማሰባችንን ማሳየት ያስፈልጋል፤ አንድ ሰው ምን ያህል አጭር ጊዜ ከአሜሪካ ውጪ ቆየ አይደለም ዋነኛው የሕግ ጥያቄ፤ ነገር ግን አሜሪካ ውስጥ ተመልሶ የመኖር በማስረጃ የተደገፈ ፍላጎት አለው ነው። ለምሳሌ አንድ የፍርድ ቤት የሄደ ክስ ላይ ግለሰቡ በቃሉ አሜሪካ ውስጥ የመኖር ፍላጎቱን ቢገልጽም፣ ዋነኛው መኖሪያውን በሀገሩ ስላደረገ እና ከሁለት ዓመት በላይ በዛ በሀገሩ ስለኖረ የኢምግሬሽን ኤጀንሲውም ያን በማስረጃ ማሳየት ስለቻለ የመኖሪያ ፍቃዱን አጥቷል። ግሪንካርድን ላለማጣት ወደ አሜሪካ የመመለስ እና የመኖር ፍላጎታችሁን የሚያሳዩ ሰነዶችን መያዝ ያስፈልጋል። ለምሳሌ የሞርጌጅ ክፍያን፣ የቤት ባለቤትነት ሰነድ፣ የኢንሹራንስ እና የታክስ ዶክመንቶች፣ የመንጃ ፍቃድ እንደማስረጃ ሊያገለግሉ ይችላሉ። 2) ያለ Reentry Permit (ፍቃድ) ከአንድ ዓመት በላይ ከአሜሪካ ውጪ አለመኖር፤ ከአሜሪካ ስትወጡ በአንድ ዓመት ውስጥ ለመመለስ እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል። አለበለዚያ ግን በአሜሪካ ኤምባሲ ቀርባችሁ Returning Resident ቪዛ መጠየቅ እና ከአሜሪካ ውጪ የቆያች ሁበት ምክንያት ያልታሰበ ጉዳይ ገጥሟችሁ መሆኑን ማስረዳት (በማስረጃ) ይጠበቅባችዋል። በኤርፖርት ላይ የሚጠይቀን የቦርደር (CBP) ኦፊሰር ፥ ግሪን ካርዳንን እንደተውን (abandonment or relinquishment) እና ያን መብት ለመንፈግ የሚያያቸው ማስረጃዎች ምን ምን ምንድናቸው? 1) በአሜሪካ ውስጥ ታክስ እየከፈልን እንደሆነ፤ 2) ቤት ወይም አፓርትመንት እንዳለን ወይም የረጅም ጊዜ ሊዝ እንደገባን፤ 3) በውጭ ሀገር ተቀጥረን እንደሆነ፤ 4) ወደ ሌላ ሀገር ቤተሰባችንን አብረን የወሰድን እንደሆነ፤ 5) ወደ አሜሪካ የተመለሰነው በአንድ አቅጣጫ (one-way) የዓየር ቲኬት ወይም ወደ መጣንበት መመለሻ ትኬትም እንደቆረጥን፤ 6) ከአሜሪካ ጋር ጠንካራ የሆነ የሚያያይዘን ግንኙነት እንዳለ እና እንደሌለ፤ በማየት ውሳኔ ያስተላልፋል። ከአሜሪካ በግሪን ካርድ ለረዥም ጊዜ መውጣት ስናስብ እነዚህን ሰነዶች ይዘን ለመመለስ ማቀድ ይኖርብናል። ያለበለዚያ ግሪንካርዳችንን ልናጣ እንችላለን። እነዚህን ሰነዶች አሳይተን ብንገባ እንኳን የUSCIS መስሪያ ቤት ለዜግነት ስናመለክት የቆየንባቸውን ቀኖች እና መልሶቻችንን ድጋሚ በማየት እና በመመርመር ግሪንካርዳችንን ሊነጥቁን ይችላሉ። በዚህ ዙሪያ የሕግምክር የምትፈልጉ እና ልታናግሩን የምትወዱ ሰዎች በእነዚህ ቁጥሮች +1 (651)528-2677 ወይም +1 (612) 643-3449 ደውሉልን፤ በኢትዮጵያም ሆነ ከሌሎች ሀገራት በዋትስ አፕ ልትደውሉልን ትችላላችሁ።
Показати все...
👍 2
አዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ሞዴል ውል.pdf2.59 KB
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.