cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Cødé øf súççêss

#ጊዜ #ሚዛን ባክኖ እያባከነ ~ ዘመኑን በከንቱ ሲወለድ ቢሞትም ~ የኔ ቢጤ ገልቱ ህያው ስራ ሰርተው ~ ስም ተክለው ‘ሚሄዱ የቀብራቸው ቀን ነው ~ ጀግኖች ‘ሚወለዱ ===||=== @codeTse @bmilwww

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
208
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

⚡️Qwickbet is a new international sports betting company, giving new betting options to the Ethiopian market. 💵 The Qwickest way to win 💵 አሁኑኑ QwickBet ላይ በመመዝገብ የ10 ብር ቦነስ ያግኙ! ---------------------- CPA: 0.50 ETB | Type: Link ✅ Channel | ✅ Group | ✅ Chat. ----------------------
Показати все...
በእኛ የዳሰሳ ጥናት ለመሳተፍ ይህን ሊንክ ይከተሉ ፡፡ ለ 2ደቂቃ ጊዜዎን ስለሰጡን እናመሰግናለን ፡ https://telegram.me/maseroinsightbot?start=i613cb8062334f02caae9ed12
Показати все...
🌼 እንኳን አደረሳችሁ 🌼 እንኳን ለ አዲሱ አመት በ ሰላም አደረሳችሁ እያልን #ቲክቫህ_ስፖርት ከ አጋሩ #DSTV ጋር በ መተባበር በዓሉን ምክንያት አድርጎ ውድ ቤተሰቦቹን በ ስጦታ ሊጎበኝ ነው ። በ ቻናሉ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ቀድመው ትክክለኛ መልስ ለሚመልሱ ቤተሰቦቹ 5 የ #DSTV ዲኮደሮችን ከ ሜዳ ፖኬጅ ጋር አዲሱን ዓመት ተከትሎ ወደ የቤታቸው ይልካል ። በዚህ አናበቃም.....ከ ረጅም ጊዜ አጋሮቻችን በርከት ያሉ የ ካርድ ሽልማቶችንም ለእናንተ ውድ ቤተሰቦቻችን አዘጋጅተናል። በ አዲስ መንፈስ በ አዲስ ዓመት ስፖርታዊ መረጃዎቻችንን እየተከታተላችሁ ጥያቄዎችን በ መመለስ ከ ሽልማቱ እየተቋደሳችሁ ዓመቱን በ ደስታ ይጀምሩ ። ስለ ውድድሩ ከ ደቂቃዎች በኋላ በ @codeTse ላይ ይከታተሉ። 🌼 መልካም አዲስ አመት 🌼 @tikvahethmagazine @tikvahmagbot
Показати все...
ይህን መልዕክት ለሚወዱት ሰው ብቻ Share ያርጉ!  👉 ሌሎች የአዲስ አመት ምኞቶች @hararbeer👈 ---------------------- CPA: 0.40 Birr ✅ Channel | ✅ Group | ✅ Chat. ----------------------
Показати все...
ይህን መልዕክት ለሚወዱት ሰው ብቻ Share ያርጉ!  👉 ሌሎች የአዲስ አመት ምኞቶች @hararbeer👈
Показати все...
😂 771
❤️ 133
😡 23
ፍቀድ.... ፨፨፨፨፨፨////////፨፨፨፨፨፨ ሰላም ዋጋው ጥልቅ ነው፤ ችሮታው ረቂቅ ነው፣ መገኛውም በእራስ ነው። አንዳንዴ ከውጪው ሁካታ የውስጥ ግጭት፣ የውስጥ ሰላም እጦት ጥፋቱ ያይላል። በዚህ... ቅፅበታዊ ነገር ሁሉን መቀየር በሚችልበት ዓለም አየኖርን፣ ሰላምን ዘላቂና ቋሚ ማድረግ ትልቁ የህይወት ፈተና ነው። ከእራስ ጋር ሰላምን ማስፈን፣ እራስን ማዳመጥ፣ መረዳት፣ መታገስ ለእራስ የሚከፈል መሶዓትነት ነው። አዎ! ሰላምህን ስታጣ፣ እርጋታ ሲርቅህ፣ ስሜቶችህ ሲጋጩ፣ ለመወሰን ስትቸገር፣ የወሰንከውንም ባሰብከው ልክ ሳታደርገው ስትቀር፣ ካለፋ ታሪኮችህ ጋር ስትፋለም፣ ባልተጨበጠ ነገር ከልክ በላይ ስትባክን፣ በበደሉህ ላይ ስታቂም፣ በደልን በበደል ለመሻር ስትተራመስ ፣ በሌሉህ ነገሮች ስትብሰለሰል ብቻ እጅግ በበዙ የሰላምህ ጠላቶች ስትወጠር የሰላምህ ጠዓም እንኳ ይጠፋብሃል። በምትኩም ቁጭት፣ ንዴት፣ ጭንቀት፣ ብሶት ይዛመዱሃል። ነገር ግን የዝምድናቸውን እድሜ ማሳጠሩ አንተ ለሰላምህ ያለህን ዋጋ ያሳያል። አዎ! ጀግናዬ... ሰላምህ ምንያህል ያስፈልግሃል? ምንያህል ያሳስብሃል? ሰላምህን ለማግኘት እስከምን ትጓዛለህ፣ ምንስ ትከፍላለህ? አዎ! በሰላሙ የሚደራደር አለመኖሩ ቀንጣት ጥርጥር የለውም፤ እርሱን ለማግኘት የሚደረገው ትግል ግን ማጠያየቁ አይቀሬ ነው። ጀግናዬ..! ሰላምህን ትፈልጋለሃ! ይቅር በል፣ ይቅርታን ጠይቅ፣ መተወን ልመድ፣ ቂመን ተው፣ በልክህ ኑር፣ በእራስህ ግዛት ንገስ፣ በሚያኮራህ ቦታ ተገኝ፣ ክብርህ ከምንም በላይ ይግባህ፣ ለውጥህ ይለውጥህ፣ ይታይ፣ እርጋታህ ይመስክር። አዎ! ግዴለህም ፍቀድ፤ እድሜህ ይቀጥል ዘንድ ፍቀድ፣ ልብህ ያርፍ ዘንድ ፍቀድ መንፈስህ ይታደስ ዘንድ ፍቀድ፣ ጭንቀትህ ይፈወስ ዘንድ ፍቀድ፣ በስተመጨረሻም ያለምከው፣ ያሻሀው ሰላምህ ይሰጥህ፣ ይቸርህ ዘንድ ፍቀድ። ሰላሙን ያገኘ እራሱን አገኝ እራሱን ያገኘ ህይወቱን አገኝ እራስን ከማግኘትና ህይወትን ከማግኘት በላይ ምን ግብ አለ? ምንስ ስኬት አለ? ሰናይ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ join us 👇 @codeTse @codeTse @Tsegsh336
Показати все...
የአጋጣሚ ትንሽ የለውም፤ ፨፨፨፨፨፨//////////፨፨፨፨፨፨ የአጋጣሚ ትንሽ የለውም፤ ህይወት በክስተቶች የተሞላች ነች። የክስተቱ ባለቤት ማንም ይሁን ማንም፣ የክስተቱ ተቀባይ ግን አንተ ልትሆን ትችላለህ። አንድ ነገር ሲመጣብህና ሲመጣልህ አንድ አይነት ምላሽ አትሰጥም። አዎ! ጀግናዬ...! የመጣብህን እንዳመጣጡ ትመልሳለህ፣ የመጣለህን ግን በአግባቡ ትቀበለዋለህ፣ ትጠቀመዋለህ። ለዚህም የዘወትር ዝግጁነትህ ወሳኝ ነው። በህይወትህ የሚመጡልህ መልካም አጋጣሚዎች ህይወትህን እስከ ወዲያኛው የመቀየር ሃይል አላቸው። መቼም እስከ ዛሬ ስንት አጋጣሚዎችን እንዳሳለፍክ፣ እንዳባከንክ አንተ ታውቃለህ፤ ለሚቀጥሉት ድንቅ አጋጣሚዎች ግን በፍፁም ሳይጠቅሙህ እንዲያልፋ መፍቀድ የለብህም። አዎ! እራስህን በብዙ ማዘጋጀት ይኖርብሃል። ጊዜና አጋጣሚ አንድ ናቸው አብረው ይመጣሉ፤ አብረውም ላይመለሱ ይሔዳሉ። አዎ! አንዳች ነገር እንዳታመልጥህ ዘወትር ተዘጋጅተህ ጠብቅ። ከተጠቀምክበት ዓለም መጥፎና ከባድ ገፅ ብቻ ሳይሆን ቀላል ብልሃትህንና ዝግጁነትህን ብቻ የሚሹ ብዙ የህይወት በረከቶችምና ብዙ አጋጣሚዎችም አሏት፤ ዋናው ያንተ በተገቢው ሰዓት፣ በትክክለኛው ቦታ፣ በተገቢው አኳሃን የተገኘውን አድል፣ አጋጣሚ ሳያመነቱ ተጠቅሞ መገኘት ነው። ሰናይ ምሽት ይሁንልን!! 🌘🌒💫✨ join us 👇 @codeTse @codeTse @Tsegsh336
Показати все...
🌕 ስበት 🌕 አዲሱን የሳሚ ዳን ስበት አልበም ⬇️
Показати все...
▶️ ያድምጡ
የታሪክ ተራኪ ወይስ የታሪኩ ተተራኪ....? ፨፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨፨፨ እንዲነገርልህ የምትፈልገው ታሪክ አለህን? አንድ ታሪክ በጥሩም ይሁን በመጥፎ ሊነሳ የሚችለው አንድ የተለየ ነገር ስለተከናወነበት ነው። ተራ ነገር ሁሌም ተራ ነው። እንኳን ሊነገር ቀርቶ የሚያስታውሰውም አያገኝም። ቅሉ ግን ታሪክ ነጋሪ መሆን ሳይሆን ታሪክን ሰሪ መሆን ነው። አዎ! ጀግናዬ...! አንተስ በራስህ ህይወት ውስጥ ታሪክ እየሰራህ ነው ወይንስ ታሪክ እየተሰራብህ ነው? "ሜዳውም ይሀው ፈረሱም ይሀው" ነው ጉዳዩ። ታሪክ የምትሰራበት አውላላ ሜዳ አንተን መጠበቅ ከጀመር ውሎ አድሯል ይባሱንም ሰነባብቷል፣ እናስ ጀግናዬ አንተስ እስካሁን እርምጃህን አልጀመርክም፣ የታሪክህ ተካፋይ ለመሆን አልተዘጋጀህም፣ እንቅስቃሴህስ ወዴት ነው? አዎ! ንቃ..ንቃ አሁን ጊዜው የንቃት ነው፤ የታታሪነት ነው፣ ታሪክህ ባንተው እስክሪብቶ የሚከተብበት፣ በደማቅ ቀለም የሚቀለምበት፣ በልብህ አሻራ የሚሳልበት፣ ባንተ ብቻ የሚፃፍ የሚሰራ፣ ከዚህ በፊት ያልተሰራ፣ ካሁንም ቦሃል በማንም የማይሰራ አንተን ብቻ የሚጠብቅ ባንተ ብቻ የሚፃፍ ከአመት አመት ከትውልድ ትውልድ እየተነገረ የሚያልፍ አንፀባራቂ ታሪክ አለ። ያንተን.. የመሪ ተዋናዩን መምጣት በጉጉት የሚጠብቅ፣ አዎ! እርሱ ያምንሃል፣ እንደምትመጣለትም ያውቃል አንተስ ጀግናዬ ምን ያህል ታሪክህን ለመከተብ ዝግጁ ነህ? የታሪክ ተራኪ ሳይሆን የታሪኩ ተተራኪ ለመሆን ቆፍጠን በል። አዎ! ሁሌም በህይወትህ ላይ ታሪክ ለመስራት ተዘጋጅ! ሰናይ ምሽት ይሁንልን!! 🌘🌒💫✨ join us 👇 @codeTse @codeTse
Показати все...