cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ልጅነት ይበልጣል

️ልጅነት ይበልጣል ወደ ገላትያ ሰዎች3:26   በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ #የእግዚአብሔር_ልጆች_ናችሁ. ልጅነት ከ አስትማሪነት ልጅነት ከ አገልጋይነት ልጅነት ከ ነብይነት ልጅነት ከ ሐዋርያነት ይበልጣል

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
174
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የጠራኝ እግዚአብሔር የታመነ ነው፡፡እርግጠኛ ነኝ አንተ ከእኔ ጋር ነህ!የባሪያህን ልመና ስለሰማህ በእኔ ዘንድ ምስጉን ነህ!አባት ሆይ ለቤተክርስቲያን ስላደረከው ቸርነት በብዙ እናመስግንሃለን! መዝሙር 126 ¹ እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስተኞች ሆንን። ² በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን፥ አንደበታችንም ሐሴትን ሞላ፤ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ፦ እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው ተባለ። ³ እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገልን፥ ደስም አለን። ⁴ አቤቱ፥ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ። ⁵ በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይለቅማሉ። ⁶ በሄዱ ጊዜ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፤ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ። ሃያላኖች በሃያልነት መንፈስ ከኢየሱስ ጋር ወደ ፊት!
Показати все...
*የምትታገሱት ጉዳይ ከሌላችሁ የምትነገሱበት ጉዳይ አይኖራችሁም፡፡ነገ የምትነግሱት ዛሬ በምትታገሱት ጉዳይ ነውና፡፡ *በትዕግስት የምታልፎቸው ቀናቶች ከሌሎአችሁ በክብር የሚቀበሉአችሁ ቀናቶች የሉአችሁም፡፡እስኪነጋ ታገስ እንጂ የሞተውን ጥለህ በህይወት ያለውን ትቀበላለህ፡፡ቀን እስኪመጣ ታገስ እንጂ የሃማህ ሰረገላ ላይ መቀመጥህ አይቀርም፡፡ ታግሶ ቀን ያልወጣለት የለም፡፡ታግሶ ያልነገሰና ያልከበረ የኪዳን ሰው የለም.....በትዕግስት ተጉዘህ መድረስ ያለብህ ከፍታ ላይ መድረስ ትችላለህ፡፡ "፤ እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። " (ወደ ዕብራውያን 12: 1-2) man of God kaleab Tadesse. @revelationtv @revelationtv @revelationtv
Показати все...
1ኛ ጢሞቴዎስ 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹¹ አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል። ¹² መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ። @CHILDRENSSOFGOD @CHILDRENSSOFGOD
Показати все...
ዘዳግም 33 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁸ ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ ቱሚምህና ኡሪምህ ለቅዱስህ ሰው ነው፥ በማሳህ ለፈተንኸው፥ በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፤ ⁹ ስለ አባቱና ስለ እናቱ፦ አላየሁም ላለ፥ ወንድሞቹንም ላላስተዋለ፥ ልጆቹንም ላላወቀ፤ ቃልህን አደረጉ፥ ቃል ኪዳንህንም ጠበቁ። ¹⁰ ፍርድህን ለያዕቆብ፥ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ፤ በፊትህ ዕጣንን፥ በመሠዊያህም የሚቃጠል መሥዋዕት ይሠዋሉ። ¹¹ አቤቱ፥ ሀብቱን ባርክ፥ የእጁንም ሥራ ተቀበል፤ የሚነሣበትን ወገብ ውጋው፥ የሚጠሉትም አይነሡ። @CHILDRENSSOFGOD @CHILDRENSSOFGOD
Показати все...
1ኛ ዮሐንስ 3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም። ² ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን። ☘ ️ልጅነት ይበልጣል ልጅነት ከ አስትማሪነት ልጅነት ከ አገልጋይነት ልጅነት ከ ነብይነት ልጅነት ከ ሐዋርያነት ይበልጣል @CHILDRENSSOFGOD @CHILDRENSSOFGOD
Показати все...
ሻሎም የእግዚአብሔር ልጆች እውነተኛ መሪነት 👉 የ እውነተኛ መሪነት መነሻው ፍቅር ነው፡፡ መሪ ሰውን ከመውደድ ይጀምራል፡፡ 👉 በ እውነተኛ መሪ አይን ውስጥ ትንሽ፣የተጣለ፣የተተወ፣ የማይፈለግ የሚባል ሰው የለም፡፡ 👉 እውነተኛ መሪ እንደ እየሱስ ነው ፤ በሰው ዘንድ ትንሽ የሆኑትን ቦታ ያልተሰጣቸዉን አሳ አጥማጆች የጠራ፡፡ ✡ እውነተኛ መሪ ያሰበውን በፍቅር ለሠዎች ይገልጣል ከተቀበሉት ጋር ይቀጥላል ላልተቀበሉትም ሁሉ በፍቅር ይሰራል፡፡ 👉በእውነተኛ መሪነት ውስጥ የተደበቀ ወይም በመሪውና በተመሪዉ መካከል የተሰወረ ነገር የለም ምክንያቱም በመሪዉና በተመሪው መካከል በፍቅር የሆነ ወዳጅነት ስላለ ዩሐ 15፥15 👉 በፍቅር የሆነ መሪነት ሁለት ጊዜ ማሸነፍ ነው፡፡ አንድም የተመሪውን ልብ ሁለትም የጠላቱን ልብ፡፡ አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ እና የዛሬን ላብቃ ኔልሰን ማንዴላ ፕሬዝደንት ከሆኑ በኋላ አንድ እለት ከቅርብ ጠባቂዎቻቸው ጋር ለምን በእግራችን ወጣ ብለን አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው ወጡ። አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ ከፊት ለፊታቸው ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ ጋር ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ። ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ። እየተመገበ ሳለ እጁ ይንቀጠቀጣል ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ መሃል አንዱ "ማዴባ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነበርኮ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር" ይላቸዋል "አይደለም! ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር። ብዙ ግዜ ተደብድቤ ከቶርች ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው በምላሹ ይመጣና ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናል።አሁን የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት ፈርቶ ነው" ሀገር 'በመቻቻል እና #በፍቅር እንጂ በቂም በቀል አትገነባም። ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናትና- ሰላም ህልውናችን ነው ! 👉በዚህ ምሳሌ እንደምንረዳው ማንዴላ ሁለት ጊዜ አሸንፈዋል አንድም የወዳጆቻቸውን ሁለትም የጠላታቸውን ✡የእውነተኛ ይቅርታ ምንጭ እውነተኛ ፍቅር ነው ፍቅር የመሪነት ትልቁ ሀይልና መሰረት ነው፡፡ @CHILDRENSSOFGOD @CHILDRENSSOFGOD @CHILDRENSSOFGOD
Показати все...
መዝሙር 36 ⁸ ከቤትህ ጠል ይጠጣሉ፥ ከተድላም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ። ⁹ የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን። @GODSMESSENGER JOIN US @GODSMESSENGER
Показати все...
እግዚአብሔር ለሾማቸው አገልጋዮች መገዛት 👉 አንድ ሰው በቅድሚያ ራሱን ለሥልጣን ማስገዛት ሳይችል ( ሳያውቅ) የእግዚአብሔር አገልጋይ ለመሆን ብቁ አይደለም ፡፡ 👉 አንድ ሰው የራሱን የዐመፀኝነት ዝንባሌ ሳያስገዛ በሌሎች (በራሱ ትውልድ) ላይ የበላይ መሆንን ሊያውቅ አይችልም ፡፡ 👉 በእግዚአብሔር አይን አገልጋዮችን መቃወም እርሱን ከመቃወም ይቆጠራል፡፡ 💥 ለእግዚአብሔር ቀጥተኛ ሥልጣን ለመገዛት ትህትና አይጠይቅም ፤ ለአገልጋዮች ስልጣን መገዛት ግን ዝቅ ማለትና መሰበር ያስፈልጋል፡፡
Показати все...
👉አንድ ነገር የምንፈፅምበት ሁኔታ ከምንጀምርበት ሁኔታ የበለጠ ጠቃሚ ነው፡፡ 👉 በክርስትና ህይወት መሰረት እንደሚገባ መጨረስ ማለት ጌታ "አንተ ታማኝ አገልጋይ መልካም አደርገሃል" ሲለን መስማት ማለት ነው፡፡ ““ጌታውም፣ ‘ደግ አድርገሃል፤ አንተ መልካም ታማኝ አገልጋይ፤ በትንሽ ነገር ላይ ታማኝ ስለ ሆንህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።” — ማቴዎስ 25፥21 (አዲሱ መ.ት)
Показати все...
“እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።” — ዕብራውያን 12፥1-2
Показати все...