cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ዮሐንስ ጌታቸው

ርቱዕ ሐልዮ ጥያቄና አስተያየት ካልዎት ይስጡ! @tmhrte_tsdk_bot

Більше
Рекламні дописи
1 924
Підписники
Немає даних24 години
+167 днів
+3630 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ወደ ልቡናችን እንመለስ፡ እውነተኛውን መንገድ ብቸኛ ምርጫችን እናድርግ። በእርግጥ አኹን ላይ ማኅበራዊ ሕይወታችንም ልክ እንደ ቅይጥ ጋብቻው፡ ተመሰቃቅሏል። ክፋትን ከመልካምነት ቀይጠን የተምታታ አስተሳሰብን ገንዘብ አድርገናል። ኹሉንም ነገር "ዘና ፈካ" እንበል በሚል ወጥመድ ጠምደን በጽኑ ታመናል። እውነተኛውን ጸጸት ከልቡናችን አስወጥተን ድፍረትን ተክለናል። እግዚአብሔርን መስማት አቁመን ጊዜያዊ ስሜታችንን ሰምተናል። በዚህም መሠረታዊ ምክንያት ሕይወታችን ውጯ እንጂ ውስጧ በእጅጉ መርሯል። ጥፍጥናዋ ጠፍቶ ምረቷ ጨምሯል። ሩቅ የነበረችውን ሲኦል ጎትተን አምጥተን እውስጣችን ተክለናል። ስለዚህም በእሳትነቷ በእኛ ውስጥ ያለችው ሲኦል እኛኑ አቃጥላ መከራ አጽንታብናለች። በጣም የሚያስገርመው ተንቃሳቃሽ ሲኦል እስክንኾን ድረስ ተጎድተን ሳለ ጉዳታችንን መለየት አለመቻላችን ነው! ምረረ ሲኦል ይሏል ከየልቡናችን የሚመነጨው የኃጢአት ሐሳብ ነው! ልቡናችን በምታመነጨው የኃጢአት መርዝ ትሏ የማያንቀላፋ ኾኗል። እንግዲህ ቅይጥ ጋብቻን ያመጣነው በኃጢአት እዚህ ደረጃ ደርሰን መኾኑ ነው። በአንዴ ሲኦልንም ገነትንም ሽተን ኹለቱን ለመቀየጥ በመጣራችን ነዋ🤔 በእውነቱ ይህ የሕይወት ፍልስፍና ያስገርማል! እግዚአብሔር ከቅይጥነት ሕይወት በቸርነቱ ይታደገን፥ አሜን። https://t.me/phronema
Показати все...
ዮሐንስ ጌታቸው

ርቱዕ ሐልዮ ጥያቄና አስተያየት ካልዎት ይስጡ! @tmhrte_tsdk_bot

++#ቅይጥ_ሰርግ_ወይም_ጋብቻ#+++++ ሰርግ በጋብቻ ምክንያት የሚፈጸመውን ድግስ የሚመለከት ሲኾን ጋብቻ ደግሞ የባል እና ሚስትን በቅዱስ ምሥጢር አንድ መኾንን የሚያመለክት ቅዱስ ምሥጢር ነው። ኦርቶዶክሳዊው ጋብቻ ራሱን የቻለ ሥርዓት አለው። የሚፈጸመውም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት እንጂ በእኛ ስሜት መሠረት አይደለም። ምሥጢረ ተክሊል ተብሎ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ የኾነውም በኦርቶዶክሳዊው ሥርዓት አማካኝነት ነው። እንግዲህ ይህን መንገድ አፍርሶ ቅይጥና አጓጉል የኾነውን ነገር ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመክተት መጣር በእጅጉ ያሳዝናል። ክርስትናን ወደ ራስ ስሜት ልክ መጎተት ማለት ይኸው ነው። በቬሎ የሚደረገውን ዓለማዊ ሰርግ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሚፈጸመው ተክሊል ወይም የቍርባን ጋብቻ ጋር መቀየጥ ማለት፡ ኹለቱን መንገዶች መቀየጥ እንደ ማለት ነው። አንድ እምነትን፣ አንድ ልቡናን፣ አንድ ሰማያዊ ጸጋን መግፋት እንደ ማለት ነው። ጋብቻ አንድ ነው፥ ኹለት ሊኾን አይችልም። የተቀየጠ ወይም የተጫረ አስተሳሰብን ለትውልድ ማውረስ አደጋው ብዙ ነው። ከተክሊል በኋላ በቬሎ መሞሸር መራራ ነው። ምሬቱ የሚበቅለው ዋናውን ምሥጢር ትቶ ገላባ (የቬሎን ልብስ፣ ሊፕ ስቲክና ሌሎች ፊትን የሚለዋውጡ ቀለሞችን) መውደድ ላይ የሚመሠረት ነውና። Life ነው፥ በሕይወቴ አንዴ ነው እኮ አትበሉ! ይሄ ከቆሸሸ አእምሮ የሚበቅል ቆሻሻ ሐሳብ ነውና። የጋብቻ ቀን ምንም እንኳን የተለየ እና የከበረ ቀን መኾኑ ቢታወቅም፣ ያልተገባ ነገር ካደረግንበት ግን የተለየ መኾኑ ይቀራል። ክፉ ድርጊታችን ጋብቻውን ልዩ የሚያደርገውን እግዚአብሔርንና የእርሱ የኾኑትን ሊያስወጣ ይችላልና። እግዚአብሔርና ቅዱሳኑ የሚገኙት ነፍሳችን በፍቅርና በእውነተኛ ተአዛዚነት ስትተሳሰር ነውና። ይህን ልብ ማለት ይገባል። ኃጢአት የኾነን ነገር በከበረ ዕለት ስንፈጽመውና በሌላ ጊዜ ስንፈጽመው እኩል አይደለም። ለምሳሌ በበዐላት ዕለት የሚሰክር ሰው ከበዐላት ዕለት ውጭ ከሚሰክረው የበለጠ ይቀጣል። ምክንያቱም ኃጢአቱ እጥፍ ድርብ ይኾናልና። አንደኛው ስካር ኹለተኛው በዓልን መሻር ነውና። በተቀደሰ የጋብቻ ዕለትም ያልተገባ ነገር ማድረግ ስለ ጋብቻው ክብርና ስለ ድርጊቱ ኃጢአትነት ድርብ ቅጣት ያመጣል። በርግጥ የምሰክረው ለበዓል ብቻ ነው፣ የምጨፍረው በሰርግ ጊዜ ብቻ ነው፣ ዘፈን አልወድም የምወደው የቴዲ አፍሮን ብቻ ነው ... የመሳሰሉትን እያሉ ራስን አጽዳቂ መኾን ጥሩ አይደለም። እግዚአብሔር አይዘበትበትምና! ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የሠራችው በዋናው ሥርዓት በርነት ወደ ቬሎው ፍትወት እንድንገባ አይደለም። የጋብቻ ዋና ዓላማው ጽድቅ ነው። ጽድቅ ደግሞ የተቀያየጠ አይደለም። በጋብቻ ውስጥ ያለው አንድነት በእግዚአብሔር የሚኾን እንጂ በተጋቢዎቹ ፍላጎት ብቻ ላይ የተመሠረተ አይደለም። ጋብቻ ቅዱስ ነው፤ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የሚፈጸም ምሥጢርም ነው። ይህን የከበረ የሕይወት መንገድ እግዚአብሔርን ቅር በሚያሰኝ ነገር አንፈጽመው። የቤተ ክርስቲያን ዓላማዋ እኛን ወደ እግዚአብሔር መውሰድ እንጂ በዚህ ዓለም ኃላፊ ጣዕም ላይ መትከል አይደለም። ከተክሊል በኋላ በቬሎ መሞሸርን መውደድ ማለት የራስን ሕሊና ክስ ለማምለጥ የሚደረግ ትግል ነው፤ አንድም ተለዋዋጭ ጠባይ ያለው መኾን ነው። በሌላ በኩል የተክሊልን ክብር ማቅለል ነው። አንድም ተክሊል በቂ አይደለም ለማሰኘት የመጣ ጠማማ ሐሳብም ነው። አንድም ግብዝ መኾንን መግለጽ ነው! ማስመሰል የግብዞች መገለጫ ነውና። እንግዲያውስ ቤተ ክርስቲያን በሰርግ ጊዜ የምታለብሰን ልብሰ ተክሊል ትርጒም የለውምን? ለመኾኑ በቤተ ክርስቲያን የሚፈጸምልን ድንቅ ምሥጢር በምድራዊ ነገር መሸፈን ወይም በተራ ጌጻጌጽ መቀየጥ አለበት ማለት እንዴት አግባብ ይኾናል? እግዚአብሔር ትዳራችሁን እንዲባርክላችሁ በጸሎትና በምስጋና ብትጠይቁ አይሻልምን? በቅዱስ ቍርባን የተፈጸመ ጋብቻ ላይ ቬሎ መጨመር ሕሊና ያለውን ሰው እንዴት እሺ ይለዋል? ብዙ ፍሬ ሊገኝበት የሚችለውን ጋብቻ እባካችሁ አትቀይጡ! ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያንም ይሄን ክፉ ልማድ አታምጡ! በጋብቻችሁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መልክ አሳዩ። ጋብቻ ተራ ሴርሞኒይ አይደለም፤ ጋብቻ ለታይታ ሀብትን፣ ክብርን፣ ዝናን ለማሳየት የሚደረግ ሥርዓትም አይደለም። እነዚህ ነገሮችም ተጋብዎችን አያኖሯቸውም። ይልቅስ ጋብቻን የሚጸና ባርኮ የሰጠን እግዚአብሔር ነውና ቀድሰን ልንጠብቀው ይገባል። ተወዳጆች ሆይ! ስሜታችን ሲገዛን ይህንም ድርጊታችንን በጥቅስ ልናስደግፍ እንዳዳ ይኾናል። ያው እኛ እኮ ለዘፈንም፣ ለስካርም፣ ለጭፈራም ጥቅስ መጥቀስና መከራከር ጀምረን አይደል! ክርስትናን ከሕይወታችን ገፍተነውስ አይደል! በእኛ ሰውነት ውስጥ በሬ ከአህያ ጋር ተጠምዶ ሊታረስ አይገባውም። በኦሪት "በሬው ከአህያ ጋር ጠምደህ አትረስ" የሚል ንባብ አለ። ይህ ማለት ጽድቅን ከሐሰት ጋር ወይም ብርሃንን ከጨለማ ጋር ወይም ጻድቃንን ከኃጥአን ጋር አንድ አድርገህ አትቍጠር ማለት ነው። ተክሊል ቅዱስ ነው፤ በቬሎ የሚፈጸመው ግን ብዙ ሥርዓት አልበኝነት አለበት። ምስጋና እየቀረበ እንዴት እንዲህ ይተቻል አትበሉ! ምስጋናው ተቀባይነትን የሚያገኘው እንደ አቤል ኾኖ ሲቀርብ እንጂ እንደ ቃየል ከኾነ እግዚአብሔር አይቀበለውም፤ ወደ አቅራቢውም አይመለከትም። ስለዚህ ምክንያቶችን እናቍምና ወደ ሥርዓቱ እንመለስ። አገልጋዮችም ነገሩን ከማለዛዘብ ይልቅ ተገቢውንና ጠቃሚውን ምክር ልትሰጡ ይገባል። በተለይ የንስሓ አባቶች ይህን ነገር ማስቆም አለባችሁ። የኾነው ኾኖ መርሳት የሌለብን ነገር ቢኖር ሁሉም ነገር ዝብርቅርቅ ያለብን ውስጣችን የኃጢአትን ጣዕም እያጣጣመ በመኾኑ ነው። በኃጢአት ጣዕም ውስጥ እስካለን ድረስ የጽድቅ ጣዕም አይገባንም። እንዲያውም እውነቱን ራሱ ስሕተት ብቻ አድርገን ልናይ እንችላለን። እውነቱ ግልጽ ኾኖ እንዳይታየን ዐይነ ልቡናችን ጨልሟልና እንዴት ይኾናል!! ምን ችግር አለው ልብሱን ብቻ ለፎቶ ፈልገን እኮ ነው፥ ለአንድ ቀን ብቻ እኮ ነው፥ ባይካበድ ጥሩ ነው፣ አታጨናንቁን፣ ምናምን አይባልም። "ምን ችግር አለው?" እንደማለት ያለ ምንም ችግር የለም። እንዲያ እያላችሁ አትታለሉ፥ ፈጣሪን እንጂ ራሳችሁን ብቻ ለማስደሰት አትሩጡ። በርግጥ ንጹሕ ልብ የሌለው ሰው የደስታን ጣዕምም አያውቅም። ደስታ በንጹሕ ልቡና ኾነው የሚያጣጥሟት ነገር ናትና። ወዳጄ ሆይ ቬሎ ኦርቶዶክሳዊ አለባበስ ነው ብለህ ካመንህ ተሳስተሃል። ቬሎ ደግሞ አብሮት ብዙ ነገሮች ያሉት መኾኑንም ትረሳለህ! ሊፕ ስቲክም ላንተ ልክ ነው፣ ቀለማ ቀለሞችም ኾኑ ሰውን ወደ ዝሙት የሚወስዱ አለባበሶች ላንተ ችግር የለውም፥ ምክንያቱም ሁሉም ነገር እንዲመቻመችልህ ትፈልጋለህና ነዋ! ደግሞ እኮ ቬሎ ተከልክሏል የሚል የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የለም ትላለህ። ዘመን የሚያመጣው ኹሉ ቃል በቃል በፍትሐ ነገሥት እንዲኖር ትሻለህ😭 በርግጥ ቢኖር የምትቀበል ኾነህ ሳይኾን ፥ ቢኖር ኖሮ እቀበል ነበር ብለህ ልታስመስል ነው እንጂ!! እንግዲህ ከዚህ በላይ እውነተኛ አስመሳይ (Actual Actors) (አማናውያን ተዋንያን) መኾን ወዴት አለ?
Показати все...
ዮሐንስ ጌታቸው

ርቱዕ ሐልዮ ጥያቄና አስተያየት ካልዎት ይስጡ! @tmhrte_tsdk_bot

Показати все...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሃይማኖት፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 442)። ይህ እንግዲህ ከኬልቄዶናውያን የመከፋፈል አስተምህሮ ለመጠበቅ የተደረገ ጥንቃቄ ነው። አባ ቤተ ማርያምና ሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቍባ ጊዮርጊስም "ፈረንጅ ንስጥሮሳውያን መለካውያን ኹለት አካል ኹለት ባሕርይ ይላሉ የጸጋ ልጆችም እነዚህን ይመስላሉ። ከተዋሕዶ በኋላ በአምላክነቱ እንደ መንፈስ ቅዱስ ያውቃል በሰውነቱ አያውቅም፤ በአምላክነቱ በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ ይቀመጣል በሰውነቱ ከእናቱ ይኖራል ብለው ሥግው ቃልን ከኹለት ይከፍሉታልና" እንዲሉ። (አባ ቤተ ማርያም እና ሊቀ መዘምራን ዕቍባ ጊዮርጊስ፣ አምስቱ አዕማደ ምሥጢር ምስለ ሥነ ፍጥረት አንድምታ ትርጒም፣ 1991 ዓ.ም፣ ገጽ 56)። በዚህ አገላለጽ መሠረት ኬልቄዶናውያን "መለኮት ይገብር ግብረ መለኮት ወትስብእት ይገብር ግብረ ትስብእት፦ መለኮት የመለኮትን ሥራ ይሠራል፤ ሰውነትንም የሰውነትን ሥራ ይሠራል" ይላሉ። እነርሱ "በመለኮት" ሲሉ የመለኮትን የብቻ ሥራ ለመግለጽ ሲኾን፤ "በሥጋ" ሲሉ ሰውነት ብቻውን የሚሠራውን ለመግለጽ ነው። የሥግው ቃልን የአንድነት ሥራ ለኹለት ከፋፍለው በሥግው ቃል ኹለት ግብር አለ ይላሉ። እንግዲህ በዚህ አገላለጽም በግልጽ "በሰውነቱ" እና "በመለኮቱ" የሚለውን ኬልቄዶንያውያን የሚጠቀሙት ለያይተው ለኹለት ባሕርይ መኾኑን እናስተውላለን። አንባቢ ኹሉ ኬልቄዶናዊ ከኾነው አጠቃቀም ራሱን ሊጠብቅና አስቀድመን እንዳብራራነው ጽንዓ ተዋሕዶን በሚያስረዳ መንገድ በጥንቃቄ ሊጠቀም እንዲገባ ይገነዘቧል። ጥንቃቄ አድርገን መጠቀም እንዲገባ የ 'በ'ን ነገር መነሻ በማድረግ በአማን ነጸረ እንዲህ ይላል፦ በሙያ አሰጣጥ ከኾነ "በሥጋው" ሲል መለኮቱን፣ "በመንፈሱ" ሲል ሥጋውን ያሰማል ቢባል ቀና ይመስላል፤ ምክንያቱም "በሥጋው ሞተ" ሲባል ግሱ መለኮትን፣ "በመንፈስ ሕያው ነው" ሲል ግሱ ትስብእትን በባለቤትነት ያሰማል፤ በተዋሕዶ ሥጋ የመለኮትን፣ መለኮትም የሥጋን ሥራ መሥራቱን በአንክሮ ይነገራል። "ሞተ፡ ሐይወ" በማለት አንድን የዐረፍተ ነገር ባለቤት በማሰብ መነገሩ የኦርቶዶክሳውያን አበው የትኲረት ማዕከል ነው። ... በነገረ ተዋሕዶ ውስጥ የ "በ" ሚና ተዋሕዶን መናገር ነው። "በሥጋ" ሲባል "መለኮት ከሥጋ ተዋሕዶ/ በተዋሕዶ"፣ መለኮት የሥጋን ገንዘብ ገንዘቡ አድርጎ ተብሎ ይፈታል፣ "በመንፈስ/ በመለኮት" ሲባል "ሥጋ ከመለኮት ተዋሕዶ/ በተዋሕዶ"፣ ሥጋ የመለኮትን ገንዘብ ገንዘቡ አድርጎ ይባላል። ተዋሕዶን የምታመጣልን "በ" ናት። "እስመ ብሂለ 'በ' ይፌጽም ነገረ ተዋሕዶ" እንዲል መዝገበ ሃይማኖት። ይቺኑ "በ" ኬልቄዶናውያን ለምንታዌ ቍልፍ ቃል ሲያደርጓት እኛ ደግሞ ለተዋሕዶ መርኆ መክፈቻ አድርገናታል። አንዲት ፊደል የክርስትናውን ንፍቀ ክበብ የማስመር ሥልጣን አላት! ቃል አይናቅም! ፊደል ዋጋ አለው! ኬልቄዶናውያን "በሥጋ" ሲባል "መለኮት በሥጋ ኾኖ" ይላሉ፣ "በመንፈስ/ በመለኮት" ሲባል "ሥጋ በመለኮት ኾኖ" ይላሉ፤ የባሕርይ መጠፋፋትን ሲሸሹ ተዋሕዶን ዘንግተውታል።" ይላል። ( በአማን ነጸረ (ደብተራ)፣ ተኀሥሦ፣ የካቲት 2014 ዓ.ም፣ ገጽ 178 ግርጌ ማስታወሻ 239)። ይህ እንግዲህ ፊደላትን በጥንቃቄ መጠቀም ያለብን መኾኑን አመልካች ነው። ስለዚህ እኛ ኢየሱስ ክርስቶስ "በሥጋ ፍጡር" ይባላል ስንል ለጽንዓ ተዋሕዶ የምንል መኾኑን ጠንቅቅ! ኹለተኛው ሐሳብ "... በሥጋው ፍጡር ነው አይባልም። ፍጡር ሥጋንና ነፍስን ነሣ፥ ተዋሐደ እንላለን እንጂ ከተዋሕዶ በኋላ ፍጡር እንደ ኾነ የሚናገር ገጸ ንባብ የለም። ... በሥጋው ፍጡር ማለት ፍጹም ስሕተትና ታላቅ ክሕደት ነው፤ ፈጽሞ እንደዚህ አይባልም። ፍጡር ሥጋን ተዋሐደ የፈጣሪነትን ገንዘብ ሰጠው። ከላይ እንዳየነው "ኹሉ ከአባቴ ተሰጥቶኛል" ማለትም የራሱ አድርጎታል ማለት ነው።" እንዲል። (እንደ ላይኛው ገጽ 45-47)። ይህን ሐሳብ ያቀረበው ደግሞ መምህራችን ብርሃኑ አድማስ ነው። ይህን እኔ የተረዳኹት ከተዋሕዶ በኋላ ዕሩቀ መለኮት የኾነ ሥጋ የለም፤ ሥጋ የቃልን ገንዘብ የራሱ አድርጎ እንበለ ውላጤ አምላክ ኾኗልና ለማለት ነው። ስለዚህ "በሥጋው ፍጡር" አይባልም የተባለው ዕሩቅ ብእሲ የኾነ ሥጋ ከተዋሕዶ በኋላ የለም። ተዋሕዶ በተዓቅቦ እና በመገናዘብ ስለ ኾነ ዕሩቅ ሥጋ መለኮትን ተዋሕዶ ዕሩቅ ብእሲ መባል ቀርቶለታል ለማለት ነው። ምክንያቱም ከተዋሕዶ በኋላ ያለው ዕሩቅ ብእሲ ሳይኾን ሥግው ቃል ነውና። ተዋሕዶም ምንታዌን አጥፍታ አንድነትን አጽንታለችና። ከተዋሕዶ በኋላ ሥጋ ከመለኮት ተነጥሎ አይነገርለትም፤ ከተዋሕዶ በኋላ መለያየት ፈጽሞ የለምና። ስለዚህም ከዚህ አንጻር "በሥጋው ፍጡር" ወይም ዕሩቅ ብእሲ ማለት ፍጹም ስሕተትና ታላቅ ክሕደት ነው ለማለት የተገለጸ እንደ ኾነ ነው እኔ የተረዳኹት። ይህ እንግዲህ እኔ ሳነብ የተረዳውት ነው። ጠማማ ልቡና ያለው ሰው ይህን መጽሐፍ ባነበበ ጊዜ ግን መጽሐፉ ወደማይለው ለጥጦ ሌላ መልእክት ሊሰጠው እንደሚችል ይሰማኛል። እንዲያም እየተደረገ ነውና። ነገር ግን መጽሐፉ ሲዘጋጅ በአበው መጻሕፍት ውስጥ ያሉ ሐሳቦችን እንዴት መረዳት እንዳለብን በግርጌ ማስታወሻ ላይ አለማብራራቱቱ ትልቅ ድክመት ኾኖ አግኝቼዋለሁ። ድክመቱን ትልቅ የሚያደርገው ደግሞ ነገሩ ክርክር ላይ በኾነበት ጊዜ መጽሐፉ መውጣቱና ቃለ መጠይቁን ያቀረቡ መምህራንም የዛሬ አምስት ዓመት ያቀረቡት መኾኑ እየታወቀ አኹን ላይ እነርሱን ግልጽ እንዲያደርጉ ሳያስደርጉ አከራካሪ የኾነን ጉዳይ ማውጣቱ ነው። ይህ ትክክል እንዳልኾነ ይሰማኛል። በመጻሕፍት ላይ ያለውን ንባብ ማስወገድ አይቻልምና አረዳዱን ማስረዳት ሲገባ በደረቁ "በሥጋው ፍጡር" አይባልም ብሎ ብቻ መዝጋት ትክክል አይደለም። እንዳልኩት ጠማማ ልቡና ያለው ይህን አባባል ባገኘ ጊዜ "ፍጹም ስሕተት" የሚለውን ቃል ለቅዱሳን አበው መጻሕፍት የቀረበ ኹሉ አድርጎ ሊያስብ ይችላልና፤ በእርግጥ እንዲያ እንዲያስብም በር ሊከፍት የሚችል አጻጻፍ እንደ ኾነ ልብ ይሏል። መምህራኑ በሕይወት እያሉ በድጋሚ ተጠይቀው ግልጽ አድርገው ቢያቀርቡበት ኖሮ የበለጠ ጠንካራ የሚኾን ነበር። ያን አለማድረግ ብዙ ነገር አጉድሏል። ቢያንስ ክርክሩን ማባሱ በራሱ ትልቅ ችግር ነውና። ሌላው ቅብዓቶች "በሥጋው ፍጡር" የሚለውን በር አድርገው ከባድ ክሕደት ፈጽመዋልና የእኛ አገላለጽ ከእነርሱ ጋር ኅብረት የለውም። ጉዳዩን ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ እንዲህ ያስረዳሉ፦ "በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ ባዮች ባሳተሙት መጽሐፍ ላይ "... ይህ ፈጣሪነት ዐዋቂነት ግብሩ የኾነ ቃል ፍጡርነትን ተወካፊነትን ርስቱ ከኾነ ሥጋ ጋር ቢዋሐድ ፈጣሪነቱን ዕውቀቱን ሳይለቅ በሥጋ ርስት ፍጡር ደኃራዊ ተወካፊ ቢኾን ጊዜ ሳይሻ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ከአብ ቢወለድ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ ወሐቢ ዐዋቂ ሐዲስ አምላክ ኾነ" ይላሉ። (ወል.አብ. ገጽ 160)። ፈጣሪነቱን ዕውቀቱን ሳይለቅ በሥጋ ርስት በተዓቅቦ ፍጡር ደኃራዊ መባሉ እውነት፤ ነገር ግን ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ከአብ ቢወለድ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ሐዲስ አምላክ ኾነ መባሉ ኹለት ውሸቶችን ይዟል። አንደኛ ቅብዓ መንፈስ ቅዱስን ቢቀበል ከአብ ተወለደ መባሉ ነው። ይህን ለምን ውሸት እንላለን ቢሉ ጌታ ከእመቤታችን የነሣው ሥጋ የአብን አባትነት እና ልብነት የመንፈስ ቅዱስንም ሕይወትነት ያገኘው አካላዊ ቃል ከሥጋ ጋር በተዋሐደበት ቅጽበት ነው እንጂ ቅብዓት ቀድሞ ልጅነት ተከትሎ አይደለም። ኹለተኛው ስሕተት ሐዲስ አምላክ
Показати все...
እኛን ያናገረን። ይህን የተረዳ መምህር ትውፊቱን መሠረት አድርጎ በጥንቃቄ ይገልጻል እንጂ ምእመናንን አያውክም። ኹሉም የየራሱን ችግር አስወግዶ ነገሮችን በጥንቃቄ ለማስረዳትም ለመረዳትም ከሞከረ ችግሩ ይቀረፋል። አረዳዳችንም ቅርጹን ጠብቆ አንዱን የአበውን አእምሮ ገንዘብ ያደረገ ይኾናል። ስለዚህ እንጠንቀቅ! እንግዲህ ይህን በጥንቃቄ ከማስተዋል ጋር፥ አንዱ እና ሌላው ወይም አሐዱ ወካልዑ (One and the Other) በሚል ኬልቄዶናዊ አገላለጽም አንዱን ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስን መግለጥ አይገባም። "ወደ ቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ተጠርቶ የገባው ሰውነቱ ነው፤ ውኃውን ወይን ያደረገው አምላክነቱ ነው፤ ምራቁን እንትፍ ያለው ሰውነቱ ነው፤ የእውሩን ዓይን ያበራው እንደ አምላክነቱ ነው፤ ተጠማኹ ብሎ ሳምራዊቷን ሴት ውኃ የለመናት እንደ ሰውነቱ ነው፤ የሕይወትን ውኃ እሰጥሻለሁ ያለው እንደ አምላክነቱ ነው" እያልን ከፋፍለን በፍጹም አንናገርም። ወይም አምላክነቱ ዐዋቂ ነው፤ ሰውነቱ አላዋቂ ነው፣ አምላክነቱ ፈጣሪ ነው፤ ሰውነቱ ፍጡር ነው፣ አምላክነቱ ፈራጅ ነው፤ ሰውነቱ ለማኝ ነው ... እያልንም ከተዋሕዶ በኋላ በኹለት ባሕርይ በኹለት ግብር ፈጽሞ አንናገርም። ሥግው ቃል አንድ ኢየሱስ ክርስቶስ እንላለን እንጂ። መጻሕፍት "የሕይወትን ራስ ገደላችሁት"፣ "ዐውቀውስ ቢኾን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት ነበር"፣ "አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁኝ"፣ "እኔና አብ አንድ ነን"፣ "እርሱም በሰማይ የሚኖር የሰው ልጅ ነው"፣ "የምወደው ልጄ እርሱ ነው፡ እርሱን ስሙት" ... እያሉ በአንድነት ሥግው ቃልን ባለቤት አደርገው እንደሚጠሩ እኛም እንዲሁ ሳንከፋፍል በአንድነቱ ተጠንቅቀን እንጠራዋለን። https://t.me/phronema
Показати все...
ዮሐንስ ጌታቸው

ርቱዕ ሐልዮ ጥያቄና አስተያየት ካልዎት ይስጡ! @tmhrte_tsdk_bot

የሚለው ነው፤ ሐዲስ ሰው እንጂ ሐዲስ አምላክ የሚል በመጻሕፍት አይገኝም፤ ቢኖርም እንኳን እግዚአብሔር ኹል ጊዜ ዘመናትን አስረጅቶ ይኖራል እንጂ ዘመናት የማያስረጁት በመኾኑ የተነገረ እንጂ ሰው በመኾኑ ምክንያት አዲስ አምላክ ሊባል አይችልም።" በማለት ዘርዘር አድርገው ያስረዳሉ። (ስምዓ ኮነ መልአክ (ሊቀ ሊቃውንት)፣ ቃለ ጽድቁ ለአብ፣ ኹለተኛ ዕትም የካቲት 2008 ዓ.ም፣ ገጽ 119-120)። "በሥጋው ፍጡር" የሚለውን ተጠቅመው ቅብዓቶች ከአብ መወለድንና ሐዲስ አምላክ መሰኘትን በቅብዓት አገኘ ብለው በተዋሕዶ የኾነውን ዘንግተው በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ራሱ ወልድ እንደገና የአብ ልጅነትና አምላክነት ያገኘ የሚያስመስል የክሕደት ቃል ይናገራሉ። ምንም ቃል ፍጡርነትን በተዋሕዶ ገንዘቡ ቢያደርግም የአብ ልጅነትንና አምላክነትን አልለቀቀምና ያን ሊሉ አይገባም። "ፈጣሪነቱን ዕውቀቱን ሳይለቅ" ካሉ በኋላ መልሰው ያን እንደለቀቀ የሚያስመስል "የአብ ልጅነትን፣ ሐዲስ አምላክነትን በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ አገኘ" በማለት እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሐሳብ ያቀርባሉ። ስለዚህ አበው ኢየሱስ ክርስቶስ "በሥጋው ፍጡር" ይባላል ሲሉ ከእንዲህ ዓይነቱ የቅባቶች ትምህርት ጋር ምንም ዓይነት ኅብረት የሌላቸው መኾኑን ልብ ይሏል። የአበው አገላለጽ ማዕከሉ ጽንዓ ተዋሕዶ ነውና። መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ "ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው" የሚለውን አገላለጽ ለሥግው ቃል ስንጠቀም በጥንቃቄና አንድነትን በሚገልጽ ኹኔታ አድርገን ልንጠቀም እንዲገባና ያስረዳሉ። ይኸውም፦ "ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሚለው አነጋገር ግን ጠማማ ልቡና ሲይዘው ፍጹም አምላክ ባለ ጊዜ ዕሩቅ አምላክ ማለትን፤ ፍጹም ሰው ባለ ጊዜ ዕሩቅ ብእሲ ማለትን አሰምቶ፤ ኹለት አካል ኹለት ባሕርይ ማለትን የሚያስከትል መስሎ ስለሚታይ ክርስቶስ ፍጹም ሰው የኾነ ፍጹም አምላክ ነው በማለት ንግግሩ እንዲሻሻል አሳስብዎታለሁ።" ይላሉ። (አድማሱ ጀንበሬ (መልአከ ብርሃን)፣ መድሎተ አሚን፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 229)። ሊቁ ይህን የሚሉት ከጥንቃቄ የተነሣና ምሥጢር እንዳይፋለስ፤ የሰዎችም ሕሊና ከፋፍሎ ወደ ማየት ወይም በምንታዌ ወደ መረዳት እንዳይንከባለል ለመጠበቅ ነው። የአበውን ጥንቃቄ የተረዳ ሰው ሃይማኖትን የሚያህል ትልቅ ነገር ቀለል አድርጎ በሰዎች ሕሊና ውስጥ ረብሽ ሊፈጥር የሚችል አገላለጽ አይጠቀምም። የሰማዕያንን ወይም የአንባቢያንን ሕሊናቸውን ወደ ቤተ ክርስቲያናዊ አረዳድ ሊወስድ በሚችል አገላለጽ ተጠንቅቆ በሚጠቀማቸው ቃላት ወይም ንግግሮች ይጠብቃል። ሊቁ አድማሱ ጀንበሬ በተጨማሪ "በመለኮቱ ፍጹም አምላክ ነው በሰውነቱ ፍጹም ሰው ነው" አንልም ይላሉ። ዝርዝሩን፦ "ኢትዮጵያውያን ስለ ክርስቶስ ሲናገሩ መለኮት በተዋሕዶ የሥጋን ርስት ገንዘብ አድርጎ ነድየ፣ ርህበ፣ ጸምዐ፣ ተፀነሰ። ደኸየ፣ ተራበ፣ ተጠማ፣ ተቸገረ እንደ ተባለ ትስብእትም በተዋሕዶ የቃልን ርስት ገንዘብ አድርጎ "ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር፤ አንተ ውእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር" ተባለ ብለው ይናገራሉ እንጂ፤ ከተዋሕዶ በኋላ አንድ ክርስቶስን ለያይተው በመለኮቱ ፍጹም አምላክ ነው፤ በሰውነቱ ፍጹም ሰው ነው አይሉም። እንዲህማ ከኾነ ከተዋሕዶ በኋላ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ማለት ወዴት ይገኛል?" ይላሉ። (አድማሱ ጀንበሬ (መልአከ ብርሃን)፣ መድሎተ አሚን፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 232)። እንግዲህ እንዲህ ዓይነት ጥልቅ የኾኑ የአበውን ጥንቃቄ ኹል ጊዜም ቢኾን በማሰብ በአበው ድርሳናት በተገኙ ደረቅ ምንባባት ላይ እንኳን መሠረተ ሐሳቡን ጠብቀን መናገር አለብን። ይህን የማናደርግ ከኾነ ባገኘነው ንባብ ኹሉ እነርሱ ማለት ያልፈለጉትን ማለት እንደ ፈለጉ አድርገን ከባድ ስሕተት ልንፈጽም እንችላለንና። ጉዳዩም የቃላት ጫወታ ሳይኾን መሠረታዊ ሐሳቡን የመጠበቅ ጉዳይ ነው። ሌላው የተዋሕዶን ነገር ስናስረዳ ጥንቃቄ ልናደርግበት የሚገባው "ፍጡር" የሚለው ቃል ከተዋሕዶ በኋላ ወገን በመለያየት "መለኮት ፈጣሪ፣ ሥጋ ፍጡር" እየተባለ አይነገርለትም። በሌላ አነጋገር "አምላክ እና ሰው" ተብሎ አይነገርም። የኹለትነትን ሐሳብ በሕሊና ላይ በሚያመጣ አገላለጽ ከተዋሕዶ በኋላ ፈጽሞ አይነገርም። "አምላክ እና ሰው፣ ፈጣሪ እና ፍጡር፣ ጌታ እና ባሪያ፣ ገዢና እና ተገዢ" እየተባለ "እና" በሚል ልዩነትን በሚያሳይ አጫፋሪ ተያይዞ የሥግው ቃል ነገር አይነገርም። ይህን ዓይነት አጠቃቀም የምናየው በኬልቄዶናውያን ዘንድ ነውና። አባ ሳሙኤል እንዲህ ይላሉ፦ "... እነርሱ ግን "አምላክ ወሰብእ" የሚለውን ንባብ ለኹለት ባሕርይ ምስክር አድርገው ወስደውታል፣ ትርጒሙን ከነምሥጢሩ ከነ ምስክሩ ለሚያውቁት ግን "አምላክ ወሰብእ" የሚለውን ንባብ ኹለት ባሕርይ የማለት ትርጒም በፍጹም አይነካካውም። "ወ" እዚህ ላይ አጫፋሪ አይደለም፤ "ሰማይ ወምድር፦ ሰማይና ምድር እንደሚለው "አምላክ ወሰብእ" የሚለውን ንባብ "አምላክ እና ሰው" ተብሎ በምሥጢረ ሥጋዌ አይፈታም፤ አይተረጎምም። "ወ" እዚህ ላይ "ዋዌ" ነው። "ድንግል ወእም" እንዳለው ፍቺው ትርጒሙ "እናትም ድንግልም" ማለት ነው፣ "እናትና ድንግል" ተብሎ አይፈታም፤ አይተረጎምም። "አምላክ ወሰብእ" ማለትም በምሥጢረ ሥጋዌ "አምላክም ሰውም" ተብሎ ይፈታል እንጂ።" ይላሉ። (አባ ሳሙኤል (ሊቀ ጳጳስ)፣ ፈለገ አሚን ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ 2004 ዓ.ም፣ ገጽ 91-92)። በዚህ መሠረት በምሥጢረ ሥጋዌ "አምላክ ወሰብእ፣ እግዚእ ወገብር፣ ፈጣሪ ወፍጡር" ሲባል "ወ" የሚፈታው "ም" በሚል ነው። ይኸውም፦ "አምላክም ሰውም፣ ጌታም አገልጋይም፣ ፈጣሪም ፍጡርም" ተብሎ ተዋሕዶን በሚያስረዳ መንገድ ይገለጻል። ምንም እንኳን "ፍጡር ወፈጣሪ" የሚለው ቃል ተዋሕዶን የሚያስረዳ ቢኾንም በአባቶቻችን የአገላለጽ ልማድ መሠረት "ፈጣሪ" የሚለውን አምላክ ብንል፣ "ፍጡር" የሚለውን "ሰው" ብንል የተሻለና ለአንባቢ የተረዳ ነው። መሠረታዊ ሐሳቡ ልዩነት ባይኖረውም አንባቢያን "ፍጡር" የሚለውን ቃል ሲሰሙ የሕሊና መከፈል ስለሚገጥማቸው የግድ በዚህ ብቻ መገለጽ አለበት ማለት ተገቢ አይደለም። በእርግጥ ፍጡር የሚለው ቃል በምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርት ሰውነትን የሚያመለክት መኾኑ እሙን ነው። ኾኖም ግን "ፍጡር" የሚለው ቃል ሰውነትን አመልካች መኾኑ የታወቀና የተረዳ ቢኾንም፣ "ፍጡር" የሚለውን "ሰው" በሚል ተክቶ "አምላክ ወሰብእ" ማለት ምሥጢሩ የበለጠ እንዲጠበቅ የሚያደርግ መኾኑን በንጹሕ ልቡና የሚያስብ ኹሉ የሚረዳው ነው። ይህን ጽሑፍ ስጽፍ አስቀድሜ "ቃላት ነገረ እግዚአብሔርን በምልአት መግለጽ የማይችሉ፣ ብዙ ጉድለቶችም ያለባቸው መኾኑን" ጠቆም ማድረጌ ለዚህ ነው። እኔ አንድን ጉዳይ በተገለጸበት መንገድ ተረዳው ማለት ሌላውም በዚያ መንገድ ይረዳዋል ማለት አይደለም። ሌሎች እንዳልተረዱ እስከ ገባን ድረስ በአቅማቸው ሊረዱ በሚችሉበት አገላለጽ መሠረተ ሐሳቡን ሳይስቱ እንዲረዱ ማድረግ ይጠበቅብናል እንጂ የበለጠ እንዲወዛገቡ ማድረግ ከጉዳት በቀር ጥቅም የለውም። ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው በተለያዩ ምሳሌዎች ሰማዕያኑ እንዲረዱት አድርጎ ያቀረበውም እርሱን አብነት እንድናደርግ እንጂ ለሰማዕያኑ ሳንጨነቅ በማይገባቸው ኹሉ እየተናገርን እንድንረብሻቸው አይደለም። ይህን ልብ ማለት እጅጉን ተገቢ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ እግዚአብሔር ዝቅ ብሎ በእኛ ቋንቋ እኛ እንዲገባን አድርጎ ራሱን የገለጠበት ቅዱስ መጽሐፍ ነው። ወላጆች ሕፃናት ልጆቻቸውን በሚያናግሩበት ቋንቋ ዓይነት ነው እግዚአብሔር
Показати все...
#ስለ_ነገረ_ክርስቶስ_መጽሐፍ_የተሰማኝ_ተያያዥ_ጥንቃቄ_የሚያስፈልጋቸው_ጉዳዮች! በእኔ መረዳት በማኅበረ ቅዱሳን አሳታሚነት የተዘጋጀው "ነገረ ክርስቶስ" የተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ የተገለጹት "በሥጋው ፍጡር" አይባልም የሚሉ ምንባባት "በሥጋው ፍጡር" ይባላል ብለው ምንጭ በሚገልጹ አካላትም ዘንድ ኾነ "በሥጋው ፍጡር" አይባልም በሚሉት አካላት ዐውዱን በአግባቡ ያለመረዳት ችግር ተገንዝቤያለሁ። በእኔ መረዳት ይህ የመነጨው ከችኩልነትና የእኔን ብቻ ስሙ ከሚል ግትርነት ከተሞላበት አረዳድ ይመስለኛል። የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐሳብ ምን እንደ ኾነ በዕርጋታ ከመመርመር ይልቅ የራስን መረዳት ፍጹም ትክክል አድርጎ በድርቅና መሞገት ለማንም ቢኾን አያዋጣም፤ አይጠቅምም። እንግዲህ ሰዎች የራሳቸውን ሐሳብ ለማጽደቅ ሲሉ ያልተባለውን እንደ ተባለ አድርገው ሊጓዙና በፍጥነት ወደ መከፋፈልና መጠላላት ሊጓዙ እንደሚችሉም ግምት ወስጃለሁ። ይህ እንዲሰማኝ እንዳደረጉኝም ስገልጽ በኀዘን ነው። እግዚአብሔር ንጹሕ ልቡናን ይሰጠን ዘንድ ከመለመን ጋር እባካችሁ ቀስ ብለን ጸሎት አድርገን አንዳችን የአንዳችንን ሐሳብ እንረዳ። በመጻሕፍት ያሉ ንባባትን ኹላችንም በምናነብበት ጊዜ አንድ ዓይነትና ትክክል የኾነ ትርጓሜና መረዳት ወደየ ሕሊናችን ይመጣል ብለንም በስሕተት መገመት የለብንም። ያ ቢኾን ትርጓሜ አበው ባላስፈለገ ነበር። የተለያየ አረዳድ የሚኖረን መኾኑ ከታመነ በአበው ሕሊና በኩል አንድ ዓይነት አረዳድ እንዲኖረን መትጋት ይገባናል እንጂ የሌሎችን ሐሳብ በማይሉት መንገድ መተቸት አይገባም። የነገረ ክርስቶስ መጽሐፍ ዋና ዓላማው የምእመናንን ሕሊና መጠበቅና መሠረታዊ ሐሳቡን እንዳይስቱ መጠንቀቅ እንደ ኾነ እኔ በግሌ ተረድቻለሁ። ርቱዕ ሕሊና ያለው ሰው አንድ ደራሲ የደረሰውን መጽሐፍ ሲያነብ ደራሲው ማለት የፈለገውን ሐሳብ ይፈልጋል እንጂ ደራሲው ሊለው ያልፈለገውን እንዳለው አድርጎ የእርሱን መረዳት ብቻ ባገኘው ንባብ ላይ ወሳኝ አድርጎ ሊያነብ አይገባውም። ይህማ ከኾነ ንባቡ የጸሐፊው ሲኾን መረዳቱ ግን የአንባቢው ኾኖ ሌላ መጽሐፍን ይሠራል። ቅዱስ ጳውሎስ "ሌላ ኢየሱስ፥ ሌላ መንፈስ፥ ሌላ ወንጌል" ያለው የተጻፈውን ንጹሕ ወንጌል ይዘው በግል ስሜታቸው ምክንያት ወንጌሉ የማይለውን መረዳት ያመጡ ስሑታንን ነው። መጽሐፍ ቅዱስን የማይቀበሉ ሰዎች "እግዚአብሔር ተጸጸተ" የሚለውን ንባብ ሲያገኙ በሕሊናቸው ውስጥ የሚመጣላቸውን የየግል ትርጓሜ እንዳለቀለት እውነት አድርገው አሳስተው መረዳታቸው አይቀሬ ነው። ስለዚህም እነዚህ ሰዎች በንባብ ላይ ብቻ ተመሥርተው እግዚአብሔር ያልኾነው እንደ ኾነ አድርገው አጥብቀው ሊከራከሩ ይችላሉ። እንዲህ ለማለት ነው ሲባል፥ አይ እኛ የምንፈልገው የምናስበውን መረዳት ብቻ እንድትነግሩን ነው ዓይነት ድርቅና ይደርቃሉ። ለዚህም ይመስለኛል የአንዱ እምነት አማኝ የሌላኛውን እምነት አማኝ ሐሳብ በወል እንኳን ሳይረዳ ችኩል ድምዳሜ ላይ በመድረስ መልስ በመስጠት የሚስተው። እንዲህ ዓይነት ስሕተት በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባለን አማኞች ዘንድ ሲኾን ደግሞ እጅጉን የሚያሳዝን ነው። በነገረ ክርስቶስ መጽሐፍ ውስጥ ያለውን ሐሳብም እኔ በግሌ የተረዳኹት በኹለት መንገድ ነው። አንደኛው ከምንታዌ ለመጠበቅ ሲባል "በሥጋው ፍጡር" የሚለውን ቃል መጠቀም እንደሌለብን የሚያስረዳ ነው። ለምሳሌ "... እነዚህ ሰው ስለ ኾነ እንዲህ ያደርጋል፤ አምላክ ስለ ኾነ እንዲህ ያደርጋል፤ የሚሉ ከፋፋዮች ናቸው። ይህን የሚሉት እነርሱ በኹለት ባሕርይ ለመክፈል እንዲመቻቸው ነው። ለምሳሌ ክርስቶስ አምላኬ ያለው በሥጋው ነው ስንል ሰው ጥንቃቄ አድርጎ እንዲረዳው ነው። ክርስቶስ በሥጋው አምላኬ አለ ማለት ለጥንተ ትስብእት፣ ከተዋሕዶ በፊት ላለ ትስብእት እንደ ኾነ ሰው ብጥር አድርጎ ሊረዳ ይገባል" ይላል። ምንም እንኳን በመጽሐፉ ላይ የተጻፈው ጽሑፍ አባ ገብረ ኪዳን ከተናገሩት ትንሽ ሸርተት ያለ ቢኾንም እኔ ግን ከቪዲዮው ላይ አቅንቼ ለመጻፍ ሞክሬያለሁ። እንግዲህ በዚህ ንባብ ውስጥ በአንድ በኲል ሰዎች "በሥጋው" የሚለውን ቃል ለምንታዌ እየተጠቀሙ የሚሳሳቱ መኾኑን ሲያስረዱ በሌላ በኩል ኢየሱስ ክርስቶስ አብን አምላኬ ማለቱ በሥጋው እንደ ኾነና ይህም ዕሩቀ መለኮት የኾነን ሥጋ ለማመልከት መኾኑን ያስረዳሉ። ክርስቶስ ገንዘቡ ያደረገው ሥጋ ቅድመ ተዋሕዶ ኖሮ ሳይኾን ዕሩቀ መለኮት የኾነ ሥጋ ኹሉ ፍጡር እና አምላክ ያለው መኾኑን ለማስረዳት ነው። ቀጥለው "በጣም በሚገርም ኹኔታ ዛሬም በዘመናችን ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ነው የሚሉ ሰዎች አሉ፤ በሥጋው ፍጡር ነው ማለት ግን ምን ማለት ነው? ምክንያቱም ሰዎች ሐሳባቸውን "እስመ ሰብእ ለእከዩ ሃይማኖተ ያለብሳ፤ ሰው ምን ጊዜም ክፋቱን ሃይማኖት ይቀባታል" እንዲሉ እንዲህ የሚሉት ምን ሊሉ ፈልገው ነው? ክርስቶስ ፍጡር ሥጋን ተዋሐደ አምላኬ አለ፤ ስለ ሥጋው፣ ስለ ትስብእቱ አምላኬ አለ ስንል ከተዋሕዶ በፊት ስላለ ከዚህ በኋላ ግን ይህ ራሱ አምላኬ ጌታ እግዚአብሔር መባልን ገንዘቡ አድርጓል ብሎ መረዳት ይገባል።" እንዲሉ። (ፈቃዱ ሣህሌ (መ/ር፣ አርታዒ)፣ ነገረ ክርስቶስ፣ 2016 ዓ.ም፣ ገጽ 237)። በዚህ አገላለጽ ውስጥ ደግሞ አባ ገብረ ኪዳን እያሉን ያሉት "በሥጋው ፍጡር" የሚለው ከተዋሕዶ በኋላ ክርስቶስን ለመከፋፈል የሚጠቀሙ ሰዎች አሉ። በዚያ መንገድ እኛ አንጠቀመውም ይልቅስ "በሥጋው ፍጡር" የሚለውን ሥጋው ፍጡር ነው ለማለት ተፈልጎ ከኾነ ከተዋሕዶ በፊት ላለ ዕሩቀ መለኮት ለኾነ ሰውነት የሚነገር ነው። የክርስቶስ ሰውነቱ ቅድመ ተዋሕዶ እኔ ባይ ኾኖ ነበረ እያሉን ሳይኾን በማንኛውም ዕሩቅ ብእሲ አንጻር እየነገሩን ነው። እንግዲህ የእርሳቸው ጥንቃቄ ከተዋሕዶ በኋላ ምንታዌን የሚጋብዝ አረዳድ እንዳንጠቀም ማስጠንቀቅ ነው። ከተዋሕዶ በኋላ የሥግው ቃል ባሕርይ፣ አካል፣ ፈቃድ፣ ግብር አንድ ኾኗልና መከፋፈልን ከሕሊናችሁ አስወግዱ ለማለት ነው። ስለዚህ "በሥጋ ሞተ" በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሠረት "በሥጋው ፍጡር" የሚለው በጥንቃቄ ለጽንዓ ተዋሕዶ አይገለጽም የሚል መልእክት አላገኘኹበትም። በእርግጥ "በሥጋው ፍጡር" የሚለውን ወደ ኹለት ባሕርይ በሚወስድ መንገድ እየተጠቀሙ ያሉ መኖራቸውን በሥጋው አብን ያመልከዋል ብለው በድፍረት ከተናገሩ ወንድሞች መረዳት እንችላለን። እንዲህ ዓይነት ልጆች "በሥጋው ፍጡር" የሚለውን ንባብ ስላገኙ ብቻ ሐሳቡን ሳይረዱ መጠቀማቸው ለስሕተት ዳርጓቸው ሳለ ይባላል እያሉ መድረቃቸው አሳዛኝ ነው። እነርሱ በሚሉት መንገድ ፈጽሞ አይባልምና። ኢየሱስ ክርስቶስ "በሥጋው ፍጡር" ነው ስንል ወደ ኹለትነት ከሚወስደው ከኬልቄዶናውያን አስተምህሮ ተጠብቀን ሊኾን ይገባል። በዚህ ረገድ ጥንቃቄ ማድረግ እንዲገባ ቀሲስ መዝገቡ ካሣ እንዲህ ይላሉ፦ " ክርስቶስ በመለኮቱ ከእግዚአብሔር ጋር በሰውነቱ ከሰው ጋር የተካከለ ነው አንልም። ምክንያቱም ይህ አገላለጽ በሰውነቱ ተርቧል በመለኮቱ ኅብስት አበርክቷል፤ በሰውነቱ ተሰቅሎ ሞቷል በመለኮቱ ከሞት ተነሥቷል የሚል ኹለት ባሕርይን የሚያመለክት አገላለጽ ነው። ክርስቶስ ማለት ሥጋን የተዋሐደ ቃል ማለት ነው። ቃል ሥጋ ከኾነ በኋላ በመለኮቱና በሰውነቱ እያልን የምንገልጸው መተካከልና ተግባር የለም። ሥግው ቃል ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም የተካከለ ነው፤ ሥግው ቃል ክርስቶስ ከሰው ጋር ፍጹም የተካከለ ነው ብለን እንናገራለን።" በማለት ያስረዳሉ። (መዝገቡ ካሣ (ቀሲስ ዶ/ር)፣ በትረ
Показати все...
ዮሐንስ ጌታቸው

ርቱዕ ሐልዮ ጥያቄና አስተያየት ካልዎት ይስጡ! @tmhrte_tsdk_bot

እንግዲህ "በሥጋው ፍጡር" ይባላል የሚለውን በአግባቡ ባለመረዳት ምክንያት በቅዱሳት መጻሕፍት ወዳልተጻፈ እምነትን ትቶ ሥነ አመክንዮን የነገረ ሃይማኖት ዕውቀት ምንጭና መጣኝ አድርጎ ብቻ በማሰብ በክፉ የድንቍርና ክሕደት ውስጥ እንዳንወድቅ ኹሌም ልንጠነቀቅ ይገባል። የምናነበውን ነገር በተመሐልሏዊ ሕይወት እንድንረዳ እግዚአብሔር መጠየቅና የራሳችንን ድክመት እየተረዳን አለማወቃችንንም ታሳቢ እያደረግን ልናነብ ይገባል እንጂ አእምሯችን መርምሮ ለመቀበል አልመች ያለውን ኹሉ ስሕተት አድርገን እያሰብን ከእምነት መንገድ አንውጣ። ዕውቀት በንባብ መገኘቱ እንደ ተጠበቀ ኾኖ የነገረ ሃይማኖት ርቱዕ መረዳት ግን ኹል ጊዜም ቢኾን አምነን ምሥጢራትን ስንሳተፍና በፍጹሕ ትሕትና ጾምና ጸሎት እንደ አጥንት የደረቀውን ነገረ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ለመንፈስ ቅዱስ ልናቀርብ ይገባል። መንፈስ ቅዱስም የልቡናችንን ዐይን ከፍቶ እንደ አጥንት የኾነውን አቅልጦ በመጠናችን በመንረዳው ልክ አድርጎ ያቀርብልናልና። አበውም በዚህ መንገድ ነው ሃይማኖትን ጠብቀው የሰጡን። እግዚአብሔር አምላካችን ሕሊናችንን ከረብሽ ይጠብቅልን። #ትምህርተ_ጽድቅን_ለነገረ_ክርስቶስ_ግንዛቤ_ያንብቡ! https://t.me/phronema
Показати все...
ዮሐንስ ጌታቸው

ርቱዕ ሐልዮ ጥያቄና አስተያየት ካልዎት ይስጡ! @tmhrte_tsdk_bot

ምክንያት ሥጋ ፍጡርነቱን ባለመልቀቁ ዕሩቀ መለኮት አድርገን እንዴት እናመልከዋለን እያልን አንታወክም። ይህን ምሥጢር ምሥጢር አድርጎ ሰጥቶን ዕፁብ ዕፁብ እያልን እንድናመልከው የወደደ እርሱ እግዚአብሔር ነውና። በሥነ አመክንዮ ብቻ እያሰብንም የእምነትን ኃይል ቀለል አድርገን በአመክንዮ ብቻ ካልተረዳው እያልን መጠናችንን አንዘነጋም። ስንኳንስ የእግዚአብሔር ነገር የእኛም ነገር እንኳን አንዳንዴ ከአመክንዮ በላይ ኾኖብን ረጋ ብለን ስናስብ እየተደነቅን የምንኖር መኾናችንን አንዘነጋም። ቅዱስ ቄርሎስ እንዲህ ይላል፦ "ሰው ስለ ኾነ ተፈጠረ፥ ሰው በመኾኑም ዓለምን ለማዳን ታመመ ቢባልም እርሱስ የአብ አንድ ልጁ ነው፤ ፍጡርም አይደለም። ዮሐ 1፥1-14።" ይላል። ሃይ ዘቄርሎስ ም 76 ክፍል 35 ቍ 2። ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ሥጋ በመዋሐዱ ምክንያት ፍጹም ሰውነትን ገንዘብ ማድረጉ ይነገራል እንጂ ፍጡር ነው አይባልም። ከላይ ቅዱስ ቄርሎስ አጽንዖት የሚሰጠን ከእንዲህ ዓይነት ረብሽ እንድንላቀቅና በጽኑ የእምነት መሠረት ላይ እንድንተከል ለማድረግ ነው። ሥጋ በተዋሕዶ የአምላክነትን ገንዘብ ገንዘቡ ስላደረገ የአምልኮ ስግደት ይሰገድለታል እንጂ፤ ፍጡርነትን ሳይለቅ ፈጣሪነትን ገንዘብ ስላደረገ በፍጡርነት ብቻ ጸንቶ እንዳለ ዕሩቅ ብእሲ ፍጡር ነው አይባልም። ከተዋሕዶ በኋላ ኹለትነት ስለሌለና ፈጣሪነትን ገንዘቡ ስላደረገ የአምልኮ ስግደት ይሰገድለታል። ቆዝሞስ "በመለኮት የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ፤ በሥጋ የአብርሃም ፣ የዳዊት ልጅ የኾነ አምላክ ነው፤ ለዚህ ለአንዱ ለወልድ አንዱ የሚሰገድለት፣ አንዱ (ሌላው) የማይሰገድለት ኹለት ባሕርያት አሉት የምንል አይደለም፤ ሰው የኾነ የእግዚአብሔር ቃል አንድ ባሕርይ እንጂ፤ ከሥጋውም ጋር አንድ ስግደት ይሰገድለታል።" እንዲል። ሃይ .ዘቆዝሞስ ም 95 ቍ 11። ከተዋሕዶ በኋላ ሥጋን አምላክ ነው ብሎ የአምልኮ ስግደት የማይሰግድለት የተወገዘ መኾኑን አበው ተናግረዋል። ለምሳሌ ቅዱስ አትናቴዎስ "... መለኮት ያልተዋሐደው የዕሩቅ ብእሲ ሥጋ ነውና ጌታችን ለተዋሐደው ሥጋ አልሰግድለትም የሚለውን የጌታችን ሥጋ አምላክ ነውና እሰግድለታለሁ የማይለውን እንዲህ እንዲህ የሚሉትን የእግዚአብሔር ልጅ የሾመው ሐዋርያ እኛ ካስተማርናችሁ ሌላ ትምህርት የሚያስተምራችሁ ኹሉ የተወገዘ የተለየ ይኹን ያለውን ቃል ይዛ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታወግዛቸዋለች፥ ትለያቸዋለች። ገላ 1፥6-10።" እንዲል። ሃይ ዘአትናቴዎስ ም 23፡18። ሥጋ ከተዋሕዶ በኋላ ሰውነቱን ባይለቅም ፍጡር እየተባለ ግን አይጠራም። ምክንያቱም ዕሩቀ መለኮት የኾነ ሥጋ ከተዋሕዶ በኋላ የለምና። እንዳለም አድርጎ ማሰብ መነጣጠል ነውና። ይህም ደግሞ ከባድ ክሕደት ነውና። ይልቅስ ከተዋሕዶ በኋላ ቃልን የተዋሐደ ሥጋ ስለ ኾነ ያለው ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የባሕርይ አምላክ እየተባለ ይሰገድለታል። ቅዱስ አትናቴዎስ "መለኮት የተዋሐደው ያከበረው ሕያው አምላክ ያደረገው ሥጋ ለባሕርይ ኹለተኛ፤ ለአካል አራተኛ እንደ ኾነ በምን ነገር በምን ሥራ እናምናለን? ከቃል ጋር ፈጽሞ በመዋሐዱ ሥጋ አምላክነትን የማይመረመር ጌትነትን አገኘ እንጂ፤ የሚሞት ሲኾን የማይሞት ኾነ፤ ግዙፍ ሲኾን ረቂቅ ኾነ፤ ምድራዊ ሲኾን ከልዕልና በላይ ያለ ልዕልናን ገንዘብ አደረገ" እንዲል። ሃይ .ዘአትናቴዎስ ም 31 ቍ 18-19። እንግዲህ ከተዋሕዶ በኋላ ምንም እንኳን የሥጋ ፍጡርነት የጠፋ ባይኾንም ገንዘብ ባደረገው ፈጣሪነት ፈጣሪ እየተባለ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ይመለካል እንጂ ፍጡር ነው አይባልም። ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም "ክብር ተለይቶት የነበረ ሥጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው፤ የጸጋ ገዢነትን አጥቶ የነበረ ሥጋንም የባሕርይ ገዢ ሊያደርገው ወደደ፤" እንዲል። ሃይ ዘዮሐንስ አፈወርቅ ም 66 ክፍል 9 ቍ 18። ይህ የሊቁ ትምህርትም ግልጽ ትምህርት ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ሥጋ ያለመጠፋፋት የባሕርይ አምላክ መኾኑን የሚያስረዳ ነውና። በቃለ ግዘት ደግሞ ፦"ወደ ሰማይ ያሳረገው ሥጋ ከአምላክ ቃል ጋር ሊሰግዱለት አምላክ ሊሉት ሊያመሰግኑት የሚገባው መኾኑን ክዶ ደፍሮ አንዱ በአንዱ ያደረ የሚል፤ ከሥጋው ሳይለይ አንዲት ስግደትን የማይሰግዱለት ዐማኑኤልን የማያመሰግኑ፤ ቃል ሥጋ ኾነ ብለው የማያምኑ ሰዎች ቢኖሩ ውጉዛን ይኹኑ።" እንዲል። ሃይ. ቃለ ግዘት ም 121 ክፍል 8 ቍ 31። ከመዝገበ ሃይማኖትም የሥጋን አምላክነት በተመለከተ አባቶቻችን ያስቀመጡልንን እንይ፦ "ዳግመኛ በዮሐንስ ወንጌል አንተ ብቻህን አምላክ እንደ ኾንህ ያውቁ ዘንድ የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስንም አለ (ዮሐ 12፡3። ክርስቶስ "በሥጋው" አምላክ እንደ ኾነ ታወቀ። ዳግመኛም የሰማይና የምድር ሥልጣን ተሰጠኝ አለ (ማቴ 28፡18)። የሰማይና የምድር ሥልጣን ለመለኮት የአይደለ ለሥጋ እንደ ተሰጠ ታወቀ። መለኮትስ እሱ ሰጭ ነው እንጂ የሚሰጠው አይሻም። የሰማይና የምድር ሥልጣን ለሥጋ ከተሰጠው በእውነት አምላክ ነው፤ ከመለኮቱ ጋር ትክክል ነው። ... ሥጋ ከአብ ፈጽሞ ካነሰ፤ እንደ ምን በቀኙ ተቀመጠ? ሥጋስ ከአብ በእውነት የሚያንስ ቢኾን ገብርኤል በፊቱ እንደሚቆም በአብ ፊት በቆመ ነበር። ... በክብር ያረገው በአብ ቀኝ የተቀመጠው በእውነት ሥጋ ነው። መለኮትስ ምን ጊዜም ከዙፋኑ አልተራቆተም። ሥጋ በአብ ቀኝ መቀመጡ ከታወቀ እሱ ከመለኮት ጋር ትክክል ነው። ከፍጡራን በአብ ቀኝ የተቀመጠ ስለ ሌለ።" በማለት በአጽንዖት የሥጋን አምላክነት ያስረዳሉ። (መዝገበ ሃይማኖት ግእዝ አማርኛ፣ 2014 ዓ.ም፣ ገጽ 105-107)። ይህን የመሰሉ በርካታ ሌሎች የቅዱሳት መጻሕፍት ምንባባት አሉ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሥግው ቃል ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ምንታዌን ማሰብ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ መኾን ነው። በመኾኑም "በሥጋ ፍጡር" ይባላል ስላልን ቃል የተዋሐደውን ሥጋ አምላክ ነው ብለን አናምንም የምንል ከኾነ ቍጥራችን በተዘዋዋሪ መንገድ ከአርዮሳውያን ጋር ነው። ሥጋ በተዋሕዶ አምላክነትን ስላገኘ እናመልከዋልን፣ የአምልኮ ምስጋና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት እናቀርብለታለን። ቅዱስ አትናቴዎስ ወልድ ለአብ ይገዛል የሚሉትን እንዲህ በማለት ይገስጻቸዋል፦ "... ከሐድያን ጳውሎስ ሳምሳጢና መርቅልስ (መርቅያን) እንደተረጎሙላቸው መጠን ይልቁንም እርሱ እንደ ሰው ኹሉ ለሥላሴ ይሰግዳል፤ ያገለግላል፤ ይገዛላቸዋል ይላሉ እንጂ፡ ለርሱ አይሰግዱም፤ ሐዋርያት ያስተማሯቸው፡ አምላክ አዝዞ ያጻፋቸው መጻሕፍት ያልተናገሩትን የማይገባ ነገርንም ይናገራሉ አሉ። ከመምህራን ተለይተው በምክር አንድ ኾነው ሥጋን ሳይዋሐድ ሰው ከመኾን አስቀድሞ በጌትነት በምልአት የነበረ፤ ሰው በኾነ ጊዜም በጌትነት በምልአት ያለ፡ ሲኾን በኹሉ ለኹሉ ገዥ ይኾን ዘንድ ኹሉን ባስገዛለት ጊዜ ኹሉን እንዲገዛለት ላደረገ ለአብ ወልድም ይገዛል እያሉ እንደ ወደዱ ይተረጒሟቸዋል። 2ጴጥ 3፥16-18። ያደረበት ሰው ግን ከፍጡራን ኹሉ እንደ አንዱ ነው፤ ለእግዚአብሔር ይሰግዳል፡ ይገዛል አሉ፤ እንዲህ ባለ ድንቍርና እንደተያዙ ዕወቁ፤ ራሳቸው ዐዋቆች እንደ ኾኑ ያስባሉ፡ የወደቁበትን ይህን የአእምሮ ማጣትና የስንፍና ብዛትን እዩ፡ በመጻሕፍት የሌለውን ከመጻሕፍት የማይገኘውን ከልቡናቸው አንቅተው እስከመናገር ደርሰው። ኢሳ 5፥19-21፣ ዮሐ 8፥44-45።" ይላል። ( (ሃይማኖተ አበው፡ ዘአትናቴዎስ፡ ም 24፥2-4።)።
Показати все...