cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ዝማሬ ዳዊት ወ ማኅሌተ ያሬድ

#በዚህቻናል ጥያቄና መልስ ውድድር ይካሄዳል:የተለያዩ ወቅቱን የጠበቁ ዝማሬዎች: ወረብ ትምህርት መጽሐፍት እንዲሁም ስነጽሁፍ ይቀርቡበታል። 👉ለአስተያየት ለመስጠት👇👇👇 💬 @Orthodoxmezmur21Bot 👉ቻናሉን👇 📢https://t.me/joinchat/VzqXlYDjagdf7Yly ግሩፑን👇👇 👪 @Orthodoxs_question

Більше
Рекламні дописи
4 783
Підписники
-324 години
-227 днів
-7130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።               ታላቅ የንግስ ጉዞ ወደ: ሰውሯ ጽላት የምገኝበት ደብረ መጥማቅ #ፃድቃኔ ማርያም ገዳም ዋጋ 700        ቅዳሜ እና እሁድ ዘብር ቅ/ገብርኤል ኩክየለሽ ማርያም ፃድቃነ ማርያም ሰሚነሽ ኪዳነምህረት 📞0973171717 📞0923552424 📞0954939595
Показати все...
👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
👍 1
​​👉 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ ⚡⚡⚡ሰኞ⚡⚡⚡ 👉ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ ⚡⚡⚡ማክሰኞ⚡⚡⚡ 👉ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 ⚡⚡⚡ረቡዕ⚡⚡⚡ 👉አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ ⚡⚡⚡ሐሙስ⚡⚡⚡ 👉አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ ⚡⚡⚡ዓርብ⚡⚡⚡ 👉ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ ⚡⚡⚡ቅዳሜ⚡⚡⚡ 👉ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ ⚡⚡⚡እሁድ⚡⚡⚡ 👉ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ #ሼር 💚 @mahibertsadikan💚 💛 @mahibertsadikan💛 ❤️ @mahibertsadikan
Показати все...

👍 7
✝️ትንሣኤከ ለእለ አመነ✝️ ትንሳኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ከፈኑ ዲቤነ /2/        የትንሳኤው በጎል የሰው ልጆች ሂወት ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስቷል በእውነት በዝግ መቃብር ውስጥ ተነሳ ሳይከፍተው አዳምንም ከሞት ከሲኦል አወጣው በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/     አዝ===== የሲኦል መውጊያዋ ፍላፅው ተነስቷል የኛ መድኃኔዓለም ሞትን ድል አድርጓል የእዳ ደብዳቤ በሲኦል ያለውን ደምስሶት ተነሳ አውጥቶ ነብሳቱን በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/     አዝ===== ማርያም መቅደላዊት የጠራሽ በስምሽ በዓይንሽ ያየሽውን ሐዋርያት ይስሙሽ መላዕክቱም አሉ ተነስቷል ተነስቷል የነገራችሁን እዩ ተፈፅሟል በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/     አዝ===== የሞት ሐይሉ ታየ ሲዋረድ በጌታ በድንግል ማርያም ልጅ በፍጥረት አሌንታ እናቱ እናቴ እመቤቴ ወልዳው በትንሳኤው ደሞ ሰላሜን አገኘው በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/     አዝ===== ለትንሳኤው ልጆች ለምናምን ለኛ ብርሐንን ላከልን ላይጨልም ዳግመኛ እንዘምር ለክብሩ ከበሮ ይመታ ተነስቷል ኢየሱስ እንዳይቆም እልልታ በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/
በዘማሪ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @mahibertsadikan✥ ✥ @mahibertsadikan✥ ✥ @mahibertsadikan ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Показати все...
ትንሳኤከ ለእለ አመነ.mp312.25 MB
👍 4
ትንሳኤከ ለእለ አመነ.mp312.25 MB
#ሚስጥረ_እለተ_አርብ ( ስቅለት ) እለተ አርብ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የሚታሰብበት ቀን ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ ያያቸው ስቃይና መከራ ለዓይን የሚዘግንኑ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ከባድ ቀንን ለእኔና ለእናንተ ፍቅር ሲል አሳልፏል፡፡ " ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። " [ኢሳ. 53 : 7] 13ቱ ህማማተ መስቀል እራሱን በዘንግ ተመታ ፦ ተፉበትም መቃውንም ይዘው እራሱን መቱት ።[ማቴ 27÷30] ➋ በጥፊ ተመታ ፦ በጥፊም ይመቱት ነበር።[ዮሀ 19÷4] ➌ ምራቅ ተፉበት ፦ ተፉበትም መቃውንም ይዘው እራሱን መቱት። [ማቴ 27÷30] ➍ የሾክ አክሊል ጎንጉነው በእራሱላይ አቀዳጁት [ማቴ.27፥29 ] ➎ መራራ ሀሞት አጠጡት ፦ በሀሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም ።[ማቴ 27÷34] ➏ ጀርባውን መገረፉ ፦ በዚያን ጊዜም ጲላጦስ እየሱስን ይዞ ገረፈው ። [ዮሀ 19÷1] ➐ ጎኑን በጦር መውጋት፦ ነገር ግን ከጭፈራዎቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው ወድያውም ደምና ውሃ ወጣ።[ዮሀ 19÷34] ➑ ወደ ኃላ መታሰሩ ፦ የሾለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም ሌሎችም እየሱስን ይዘው አሰሩት። [ዮሀ.18÷12] ➒ ሳዶር ➓ አላዶር ➊➊ ዳናት ➊➋ አዴራ ➊➌ ሮዳስ 5ቱ ቅንዋተ መስቀል ችንክሮች :- ሳዶር ፣ አላዶር ፣ ዳናት ፣ አዴራ እና ሮዳስ ይባላሉ። ➊ #ሳዶር ፦ ማለት ቀኝ እጁ የተቸነከረበት ➋ #አላዶር፦ ማለት ግራ እጁ የተቸነከረበት ➌ #ዳናት ፦ ማለት እግሮቹ የተቸነከረበት ➍ #አዴራ ፦ ማለት ደረቱን የተቸነከረበት ➎ #ሮዳስ ፦ ማለት ከወገቡ (እብርቱ) አጣብቆ እንዲይዝ የተቸነከረበት መከራን ታገሰ:: በህይዋንና በሙታን ላይ የሚፈርድ እርሱን እንደበደለኛ ተፈረደበት አለምን ሁሉ በቅፅበት የፈጠረ እርሱ በስጋው ሞተ በመለኮት ህያው ሆነ:: 📖 ጌታችን_መድኃኒታችን_እየሱስ_ክርስቶስ ከ6-9 ስአት በመስቀል ላይ ሳለ የተናገራቸው 7ቱ የፍቅር ቃላት ❤ ኤሉሄ ኤሉሄ ለማስበቅታኒ (አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ ) ማቴ 27÷46 ❤ እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ። ሉቃ.23÷43 ❤ አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ። (ሉቃ 23÷43) ❤ አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው። (ሉቃ.23÷34) ❤ እናትህ እንኃት እንሆ ልጅሽ:: (ዮሀ 19÷26-27) ❤ ተጠማሁ። (ዮሀ 19÷28) ❤ ተፈፀመ። (ዮሀ 19÷30) # ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ የተፈፀሙ 7ቱ ታአምራት 1⃣ ፅሀይ ጨለመች 2⃣ ጨረቃ ደም ለበሰች 3⃣ ከዋከብት ብርሃናቸውን ነሱ 4⃣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከሁለት ተከፈለ 5⃣ አለቶች ተሰነጣጠቁ 6⃣ መቃብራን ተከፈቱ 7⃣ የሞቱት ተነሱ ክብርና ምስጋና አምልኮት ውዳሴ ስግደት ዝማሪ ይድረሰ ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ 🌿❤️ አቤቱ አምላካችን ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበን አሜን (፫) !!!
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ታላቅ የበረከት ጉዞ ሆሳዕናን በሆሳዕና እንዲሁም ዳግማዊ ጎለጎታ ና ደብረ ሊባኖስ ገዳም ጉዞ በልዩ ሁነታ እናዘጋጃለን እሁድ እና ቅዳሜ ዘብር ቅ/ገብርኤል ኩክየለሽ ማርያም ፃድቃነ ማርያም ሰሚነሽ ኪዳነምህረት 0973171717
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ታላቅ የበረከት ጉዞ ሆሳዕናን በሆሳዕና እንዲሁም ዳግማዊ ጎለጎታ ና ደብረ ሊባኖስ ገዳም ጉዞ በልዩ ሁነታ እናዘጋጃለን እሁድ እና ቅዳሜ ዘብር ቅ/ገብርኤል ኩክየለሽ ማርያም ፃድቃነ ማርያም ሰሚነሽ ኪዳነምህረት 0973171717
Показати все...
Показати все...
18 April 2024

👍 3
በዚህ ምንባብ ላይ እንደተገለጸው እግዚአብሔር አምላክ ለሁላችንም እርሱን የምናገለግልበትንና ለእርሱ በመታመን ዘለዓለማዊ ክብርን የምናገኝበትን ዕውቀትን፣ ማስተዋልን፣ እምነትን፣ ተስፋን፣ የሥነ ምግባር ሀብትን፣ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን እንጠቀምባቸው ዘንድ ለእኛ ለሰው ልጆች እንደየዓቅማችን መጠን ሰጥቶናል፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች የሥጋችንን ምኞት ለማስፈጸም የተሰጡ ሳይሆኑ ነፍሳችን የምትከብርበትን መልካም ሥራን የምንሠራባቸው መሣሪያዎቻችን ናቸው። በመሆኑም እርሱ በሰጠን የአገልግሎት በር ጸጋ በታማኝነት በማገልገል በሕይወት ዘመናችን ሁሉ መንፈሳዊውን ሀብት የምናተርፍ እንሆን ዘንድ የተላለፈልን አምላካዊ ምክር ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የተጠራነው ፍሬ ልናፈራና ሌላውንም ልናተርፍ መልካም ሥራን ልንሠራ እንጂ የሥጋችንን ፈቃድ በመከተል የኃጢአት ባሮች ልንሆን አይደለም፡፡ መጽሐፍ እንዲህ አለ “ወኲሉ ዘከመ ተጸውአ ከማሁ ለየሀሉ፤ ሁሉ እንደተጠራ እንዲሁ ይኑር” /፩ኛ ቆሮ. ፯፥፳/ ከላይ እንደተመለከትነው በልዑል አምላክ በእግዚአብሔር አንደበት አንተ በጎ ታማኝ አገልጋይ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ መባልን የመሰለ አስደሳችና አስደናቂ ነገር የለም፡፡ ይህ ደግሞ የሚገኘው ሃይማኖትን በሥራ በመግለጥ እንጂ ሃይማኖትን በልቡና በመያዝ ብቻ /ሙያ በልብ ነው/ በማለት ብቻ የሚገኝ አይደለም፡፡ ከእነዚህ እንደ አቅማቸው መጠን መክሊት ተሰጥቷቸው በትጋታቸውና በቅንነታቸው ሌላ መክሊት ካተረፉት በጎና ታማኝ አገልጋዮች የምንማረው እውነታም ይህ ነው፡፡ በብዙ ለመሾም ለማደግ ለመጽደቅ በጥቂቱ መታመን መፈተን መጋደል ግድ ነው፡፡ አንድ መክሊት የተሰጠውን ሰው ስንመለከተው ጌታውን ጨካኝና ፈራጅ አድርጎ ከመቁጠር ውጪ በተሰጠው መክሊት ወጥቶ ወርዶ ሊያተርፍ አልወደደም፡፡ መክሊቱንም ባስረከበ ጊዜ በጌታው ላይ የተናገራቸው ቃላት የእርሱን አለመታዘዝና አመጸኝነት ይገልጡ ነበር፡፡ በመሆኑም ይህ ሰው በጥቂቱ መታመን ያቃተውና በአስተሳሰቡ ደካማነት እጅግ የተጎሳቆለ ሰው ነው፡፡ በዚህ ምሳሌ መሠረት ይህ ባለ አንድ መክሊት የተባለው ሰው ዓላውያን ነገሥታት እሳት ስለት አሳይተው ቢያስክዱኝ መናፍቃን ተከራክረው መልስ ቢያሳጡኝ በማለት ሃይማኖቱን በልቡ ሸሽጎና ቀብሮ በተቀደሰ ተግባር ሳይገልጠው ከመያዙ ባሻገር በጌታ ፊት በድፍረት ቆሞ አንተ ሕግ ሳትሠራ በአእምሮ ጠባይዕ አውቃችሁ፤ መምህራንንም ሳትመድብ በሥነ ፍጥረት ተመራምራችሁ በሠራችሁ ብለህ የምትፈርድ ጽኑ ጨካኝ መሆንክን አውቃለሁና ፈርቼ ሃይማኖቴን በልቡናዬ ይዠዋለው በአዕምሮዬ ጠብቄዋለሁ የሚል ሃይማኖቱን ግን በሥራ የማይገልጥ ሰነፍ ሰውን ያመለክታል፡፡ ለዚህ ዓይነት ሰው የጌታ መልስ ደግሞ በምሳሌው መሠረት የሚከተለው ነው። እኔ ሕግ ሳልሠራ በአእምሮ ጠባይዕ አውቃችሁ ፤ መምህር ሳልሰጥ በሥነ ፍጥረት ተመራምራችሁ አውቃችሁ በሠራችሁት ብዬ የምፈርድ ጽኑ ጨካኝ መሆኔን ታውቃለህን? እንዲህስ ካወቅህ ሹመትክን ልትመልስልኝ ይገባኝ ነበር፡፡ ወጥቶ ወርዶ ለሚያስተምር በሰጠሁት ነበር፡፡ አሁንም የእርሱን መምህርነት ሹመት ነሥታችሁ (ወስዳችሁ) ለዚያ ለባለ ዐራቱና ለባለ ዐሥሩ ደርቡለት! እርሱን ግን አውጡት የሚል ነው። ምክንያቱም ከበጎ ምግባር የተለየች እምነት የሞተች እንደሆነ ተጽፏልና። ዛሬም እያንዳንዳችን በዓቅማችን መጠን መክሊት ተሰጥቶናል፡፡ ነገር ግን መክሊቱን እንደቀበረው እንደዚያ ሰው የተሰጠንን ቀብረን ለወቀሳና ለፍርድ እንዳንሰጥ በአገልግሎታችን ልንተጋ ይገባናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህንኑ ሲገልጥ “ወዘሂ ይትለአክ በመልእክቱ፤ ወዘሂ ይሜህር በትምህርቱ. . .፤ አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ የሚያስተምርም በማስተማሩ ይትጋ የሚሰጥም በልግሥና ይስጥ›› (ሮሜ. ፲፪፥፯) በማለት ተናግሯል፡፡ ለመሆኑ አሁን ባለንበት የስግብግብነት ወቅት ዛሬ ‹‹አንተ በጎ ታማኝ አገልጋይ…›› ተብሎ በእግዚአብሔር ሊመሰገን የሚችል ሰው ማን ይሆን? በእውነት እንዲህ ተብሎ የሚመሰገን በጎና ታማኝ ካህን በጎና ታማኝ መምህር በጎና ታማኝ ምእመን ታማኝ ሰባኪና ታማኝ ዘማሪ ማግኘት ይቻል ይሆንን? ነገር ግን መቼም አምላካችን ቸር ነውና በየዘመናቱ አንዳንድ ታማኝ አባቶችን እንደማያሳጣን ተስፋ አለን። ምክንያቱም ዛሬም ቢሆን እንደአባቶቻችን እንደቅዱሳን ሐዋርያት በእምነት፣ በትዕግሥት በፍቅር በተጋድሎ በየውሐት በትሕርምት በጸሊዓ ንዋይ በትሕትናና በትጋት በማገልገል የተሰጣቸውን መክሊት የሚያበዙ አገልጋዮች አሉ፡፡ የእነዚህ ክብራቸው በምድርም በሰማይም እጅግ የበዛና ራሳቸውን አስመስለው በትምህርት የወለዷቸው ልጆቻቸውም ለቤተ ክርስቲያን የተወደዱ የተከበሩ ልጆች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ነቢየ እግዚአብሔር ሙሴ ነቢየ እግዚአብሔር ኢያሱን ፤ ቅዱስ ጴጥሮስ ቀሌምንጦስን፣ ቅዱስ ጳውሎስም ቅዱስ ጢሞቴዎስን ለቤተ ክርስቲያን አበርክተዋል፡፡ ሌሎችም አበው ቅዱሳን በወንጌል ቃል መንፈሳውያንና ትጉሃን የሆኑ ምእመናንን በሚገባ አፍርተዋል፡፡ ያላመኑትንም አሳምነው ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመመለስ ለዘለዓለማዊ ክብር የበቁ እንዲሆኑ አስችለዋቸዋል። በተሰጣቸው ጸጋም አትርፈው አትረፍርፈው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሀብተ መንፈስ ቅዱስ እንድትጎበኝ አድርገዋል፡፡ የእነርሱም በረከታቸው ረድኤታቸው ቃል ኪዳናቸው ለሌሎች እንዲተርፍ ሆኖላቸዋል፡፡ በመሆኑም ክርስቶስ በደሙ የከፈለውን ወደር የሌለውን ዋጋ ዓለም አምኖና ተቀብሎ በክርስትና ሃይማኖት እንዲድንበትና እንዲጠቀምበት በማድረግ እንዲሁም በታማኝነትና በበጎነት አገልግሎታቸው ጥንትም ዛሬም ላለችዋና ወደፊትም ለምትኖረዋ ቅድስት ቤተክርስቲያን ድምቀትም ውበትም የሆኑት ቅዱሳን አበው ሊገኙ የቻሉት ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን ደስ ለማሰኘት በመድከማቸው ሳይሆን የተጠሩበትን ዓላማና የጠራቸውን እርሱን በሚገባ አውቀውና ከልብ ተረድተው ለዘለዓለማዊ ሕይወት ተግተው በመሥራታቸው ነው። ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚 @mahibertsadikan💚 💛 @mahibertsadikan💛 ❤️ @mahibertsadikan❤️
Показати все...
👍 1
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.