EB 4 CHRIST SOUND ART1 (all represent the 1☝️)
This one is for everyone who need rest from this miserable life and wish to come to living water Jesus Christ. This is art not rap This is Hope talk not false talk This is about Christ. Talk to us @EB4Christsounds_bot
Більше1 540
Підписники
Немає даних24 години
+47 днів
-1130 днів
- Підписники
- Перегляди допису
- ER - коефіцієнт залучення
Триває завантаження даних...
Приріст підписників
Триває завантаження даних...
👍 1
Hanna Tekle — Kahin
ካህን በገዛ ደምህ አዳንከኝ
ካህን በገዛ ቁስልህ አተረፍከኝ
ከፍለህ አቋደስከኝ ሕይወትህን
ቆርሰህ አካፈልክኝ ነፍስህን
ከዚህ የጨመረ ምን ፍቅር ይኖራል
ከዚህ ደርዝ ያለፈ ምን መውደድ ይገኛል
መስዋዕት ከመሆን ከመሞት የባሰ
ለነፍስ ነፍስ ከማጣት ከማለፍ ያለፈ
ብልህ የመውደድ ጥልቅ የመውደድ ዳርቻ
ሕይወቴ ተገኝቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
በክርስቶስ ብቻ
ሕይወቴ ተገኝቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
ጨለማዬ በርቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
ባንተ ፍቅር ብቻ
በቃል ብቻ ባንደበትህ መች ወደድከኝ
በግብር እንጂ በእውነት ትርጉም ያፈቀርከኝ
ፍቅርን አሳየኸኝ ራስህን ለቀህ
ሆነህ ከነፍስ ውጪ በፈቃድ ተገድለህ
ቅን ደጉ ታመምህ የዋህ ስቃይ ገባ
ፍቅር ተገደልህ ሕይወቴ እንዲገባ
ብልህ የመውደድ ጥግ የመውደድ ዳርቻ
ሕይወቴ ተገኝቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
በክርስቶስ ብቻ
ሕይወቴ ተርፎልኝ ባንተ ፍቅር ብቻ
ጨለማዬ በርቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
ብልህ የመውደድ ጥልቅ የመውደድ ዳርቻ
ሕይወቴ ተገኝቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
ባንተ ፍቅር ብቻ
ልታድነኝ ልታተርፈኝ ወደህ የሄድክበት
የሞት ነው ያልተገባህ በደም ያለፍክበት
ከሞትም የስቃይ በእንጨት ተንጠልጥለህ
ፃድቅ ያለኃጢአትህ ከአባይ መሃል ሆነህ
ቅን ደጉ ታመምህ የዋህ ስቃይ ገባ
ፍቅር ተገደልህ ሕይወቴ እንዲገባ
ብልህ የመውደድ ጥግ የመውደድ ዳርቻ
ሕይወቴ ተገኝቶ ባንተ ስቃይ ብቻ
በህማምህ ብቻ
ብልህ የመውደድ ጥልቅ የመውደድ ዳርቻ
ሕይወቴ ተገኝቶ ባንተ ፍቅር ብቻ
(የ)ምልህ አይገልጽህም ዘመኔም ያንስሃል
ለፈሰሰው ደምህ ምኔስ ይክስሃል
እንዲያው ዝም ብዬ ቤዛዬ እልሃለሁ
በቀረልኝ እድሜ ሳመልክህ እኖራለሁ
አዜምልሃለሁ
(ቤዛዬ እልሃለሁ)
(ብዙ ሕይወት)?? ባንተ አገኘሁ
(አዳኜ እልሃለሁ)
ድነት ባንተ አገኘሁ
@artforchrist116🎧
@artforchrist116🎺
@artforchrist116🥁
@artforchrist116🎹❤ 1