cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

💛 የ መዝሙር ግጥሞች 💛

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇 👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት   👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት 💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ 📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako

Більше
Рекламні дописи
134 391Підписники
+16424 години
+3337 днів
+80530 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

💛 ሙሉ ለሆሳዕና እና ለህማማት የሚሆኑ ለስልኮ ፕሮፋይል ገራሚ ፎቶዎችን ለማግኘት  ይቀላቀሉ👇👇 JOIN 📍https://t.me/+mr8X2nJRHYY3Yjlk 📍
Показати все...
💯ለፕሮፋይል ፒክቸር💯
✝ ለህማማት ✝
💝አማርኛ ጥቅሶች💝
🤍JOIN🤍
ጌታ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ እየሩሳሌም ገባ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 እንኳን አደረሳችሁ! #ሆሳዕና https://t.me/joinchat/AAAAAFajLWdNNedg8xUN3Q 💛 @Ei_du 💛
Показати все...
34🙏 7👍 3
Samsung  Galaxy  note  3 አዲስ  አንደታሸገ  32  gb 3 gb ram ዋጋ 4000  ብር በማከፋፈያ ዋጋ Call me 👇👇👇👇 ☎️ 0909255008 ☎️ 0912739699 ተጨማሪ ስልኮችን  ለመመልከት አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ 👇 ቤተሰብ ይውኑ 👉https://t.me/used_phone_ethiopian
Показати все...
የሆሳዕና እና የትንሳኤ መዝሙር 👇👇 https://t.me/+FhXRM9Tp8f5jZTBk
Показати все...
የ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የመዝሙር ግጥሞች

ከ መዝሙር ግጥሞች ቻናል ያገኛችሁትን መዝሙር ለማጥና በጋራ ለመለማመድ  የተለማመዱትን  በ Voice አብሮ ለመዘመር  ማወቅ የምትፈልጉትን መዝሙር ለመጠየቅ ይህን group ይቀላቀሉ:: በዚ ግሩፕ ሁሉም አጥኚ አስጠኚም ነው.. owener @Miki_Mako

የዐቢይ ጾም ፰ኛ ሳምንት #ሆሳዕና በቅዳሴ ግዜ     #ምንባባት ሮሜ ም ፰፥፩-ፍጻ ፩ዮሐ ም ፩፥፲፫-፲፩ ግብ ሐዋ ም ፰፥፳፮-ፍጻ     #ምስባክ    መዝ ፹፥፫ ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ በእምርት እለት በዓልነ እስመ ሥርዓቱ ለዕሥራኤል ውእቱ       #ትርጉም በከፍተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዓቱ ይህ ነውና፥       #ወንጌል የዮሐንስ ወንጌል ም ፲፪፥፩-፲፪       #ቅዳሴ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮    @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Показати все...
👍 26 13🙏 4❤‍🔥 3🏆 2🤗 1
ሼር 💛
​​🌿በዓለ🌿 ሆሣዕና 🌿 ክፍል ሁለት ከላዕከ ወንጌል በእደ ማርያም ይትባረክ /ቀሲስ/ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የትምህርት ሥርጭት ኃላፊ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በአህያዋና በውርንጭላዋ ላይ በጥበብ በአንድ ጊዜ ተቀምጦባቸዋል ለእርሱ የሚሳነው ነገር የለምና፡፡ በአህያ የተቀመጠበት ምክንያት ደግሞ ቀድሞ ነቢያት ዘመነ ጸብዕ የሆነ እንደሆነ በፈረስ ተቀምጠው ይታያሉ፡፡ ዘመነ ሰላም የሆነ እንደሆነ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታያሉና ዘመነ ሰላም ደረሰ ሲል ትንቢቱን ባወቀ አናግሯል ምስጢሩም በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶም አይዝም እሱም ካልፈለጉኝ አልገኝም ከፈለጉኝ አልታጣም ሲል ነው፡፡ ሲሄዱም ሕዝቡ ልብሳቸውን በመንገድ አነጠፉ፡፡ እንኳንስ አንተ የተቀመጥክባት አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ነው፡፡ እንዲሁም ሕዝቡ፣ ሕፃናቱ ሳይቀሩ ዘንባባ ይዘው የሚቀድሙትም የሚከተሉትም "ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር"ለዳዊት ልጅ መድኃኒትን መባል ይገባዋል፤ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው/ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ያመሰግኑ ነበር፡፡ 🌿ሆሣዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነው፡፡ የዘንባባው ምስጢርም🌿፡- አብርሃም ይስሐቅን ይስሐቅ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ፤ እስራኤል ከግብፅ በወጡ ጊዜ ዮዲት ሆሎፎርኒስን በገደለች ጊዜ ዘንባባ ይዘው እግዚአብሔርን አመስግነዋልና በዚህ መሠረት ሕዝቡ፡- የሰላም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ላይ ተቀምጦ ሲሄድ ዘንባባ ይዘው አመስግነውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሲያመሰግኑ ከሕዝቡ መካከል ከፈሪሳውያን አንዳንዱ መምህር ሆይ፡- ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው አሉት፡፡ መልሶም እላችኋለሁ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ያመሰግናሉ አላቸው፤ ድንጋዮች ሳይቀሩ አመስግነውታል፡፡ ሉቃ ፲፱፥፵ በዚህ መሠረት ይህ በዓል የምስጋና በዓል ነው፡፡ እኛም ፈጣሪያችንን ሁልጊዜ ማመስገን አለብን የተፈጠርነውም ስሙን ለመቀደስ ክብሩን ለመውረስ ነው፡፡ ስሙን ለመቀደስ ማለት ስሙን ለማመስገን ማለት ነው፤ ክብሩን ለመውረስ ማለት ደግሞ መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ ማለት ነው፡፡ የተፈጠርነው ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ ስለሆነ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ማመስገን ይገባል፡፡ ምስጋናውም በፍጽም እምነት፣ በቅንነትና በንጹሕ ልብ መሆን አለበት፡፡ "እባርኮ ለእግዚአብሔር በኵሎ ጊዜ ወዘልፈ ስብሐቲሁ ውስተ አፉየ" /እግዚአብሔርን ሁልጊዜ አመሰግነዋለሁ ምስጋነውም ዘወትር በአፌ ነው/መዝ፴፫፥፩ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔርን ሁልጊዜ አመስግነን መንግሥቱን ለመውረስ እንድንችል የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም የቅዱሳን አማላጅነታቸው አይለየን፡፡ ለበዓለ ሆሣዕና ያደረሰን አምላክ ለብርሃነ ትንሣኤውም በሰላም ያድርሰን፡፡አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ቃለሕይወት ያሰማልን ~ተፈጸመ ~ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮ @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
Показати все...

👍 16 14💯 1
ሼር ያድርጉ
✞ነገር ግን ያመንነው✞ ነገር ግን ያመንነው ያድነናል ብለው ጸንተው ተሰለፉ ለኃይማኖታቸው ሶስቱ ወጣቶችን ከእሳት ያወጣቸው ኃይማኖት ነው እኝጂ ሌላ ምን ሊሆን ነው ናቡከደነፆር በዱራ ሜዳ ላይ ጣዖቱን አቁሟል እንድንሰግድ እንድናይ        አዝ= = = = = እምቢልታ ሲነፋ መለከት ሲሰማ በአንድነት እንዲሰግድ ሰው ሁሉ ተስማማ ነገር ግን ትእዛዙን የማይቀበው ከሚነደው እሳት ይጨመራል ወዲያው        አዝ= = = = = ሰው ሁሉ ይንበርከክ ለወርቁ ለብሩ አምላክ ስለሆነ በአንድነት ያክብሩ ለግዙፉ ሐውልት ያልሰገደ ቢኖር ምህረት ሳያገኝ ወደ እሳት ይወርወር        አዝ= = = = = ሲድራቅ ሚሳቅ እና አብደናጎም ሆነው ሳይሰግዱ በድፍረት ቆመው አየናቸው ንጉሡ ቢቆጣም አልተደናገጡም አሉ እንጂ በድፍረት ለጣዖት አንሰግድም        አዝ= = = = = በዚህ አንመስልህም አስፈላጊ አይደለም አምላካችን አለ ከእቶን የሚያድነው ከእቶን ያድነናል ፍዱም እምነት አለን ባያድነን እንኳን የእሱ ፈቃድ ይሁን        አዝ= = = = = ናቡከደነፆር እጅግ ተናደደ እቶ        አዝ= = = = = በእሳት መካከል ሲመላለሱ አይቶ            መዝሙር          ይልማ ኃይሉ            ትንቢተ ዳንኤል ፫ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮  
Показати все...
👍 6 6👏 1
ሼር 💛
✞ኦርያ✞ ኦርያ የሚሏት ያቺ መልካም ደጅ ምህረት አሰጠችኝ ከነ ጴጥሮስ እጅ ጠዋት በሰው ሸክም ሄጄ እቀመጣለሁ ሳንቲም በመለመን ጊዜ አባክኛለሁ ያዘነው ሲሰጠኝ ሌላውም ሲያልፈኝ ከሰው በታች መሆን በጣም መረረኝ        አዝ= = = = = አጥንት የሌለው ነው የእኔ ሰውነት ድብልብል እያለ ጽናት ተስኖት ሲመሽ ሁል ጊዜ በጣም ይጨንቀኛል አድራሾቼ መጥተው የታል ብሩ ይሉኛል        አዝ= = = = = ወደ እኛ እኛ ሃይማኖት ግባ ሲለኝ ጴጥሮስ ልቤ ተማረከ አለብኝ ልፍስፍስ እጄን ቢጨብጠው ውስጤን ነዘረኝ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሳ አለኝ        አዝ= = = = = ውሃን ደም አርግቶ ነፍስን የሚዘራ እግር ሰጠኝና ቆምኩኝ ከሰው ጋራ ቤተመቅደስ ገብተው ምስጋና ሲያደርሱ መሃላቸው ቆሜ ዘመርኩ እንደ እነርሱ                          መልአከ ሰላም ቀሲስ            እንግዳወርቅ በቀለ "..ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።"                   ሐዋ፫፥፮ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮    @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Показати все...
5👍 4
ሼር 💛
✞ኒቆዲሞስ✞ ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ትሁቱ ተማሪ የኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅ መክበሩን በዳግመኛ ልደት ከውሃ ከመንፈስ እንዲገኝ ልጅነት የአይሁድ መምህር ከጌታ ሥር ሆኖ ጠይቆ ተረዳ ተቀበለው አምኖ        አዝ= = = = = የመከራው ጊዜ ዘመኑ ሲያበቃ የኦሪቱ መምህር የአይሁድ አለቃ ብሉዩን ከሓዲስ እያመሳጠረ ከጌታ እግር ሆኖ ቁጭ ብሎ ተማረ        አዝ= = = = = ሊቅ ሲሆን ተማሪ ሊሆን የተመኘ በጨለማ ሄዶ ብርሃኑን አገኘ ኒቆዲሞስ ትሁት ጽድቅን የተጠማ ምንጩን ተጎነጨ ወጣ ከጨለማ        አዝ= = = = = በአይሁድ ጭካኔ ብዙዎች ሲፈሩ የክፉ ቀን ወዳጅ ሆነ ለመምህሩ ጽድቅና መንግሥቱን እየመሰከረ በአዲስ መቃብር ሥጋውን አኖረ            መዝሙር         አቤል ተስፋዬ                  ዮሐንስ ፫ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮    @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Показати все...
👍 3 2
ሼር 💛
Показати все...
ሆሳዕና ] በብንያም ተስፋው የቀረበ

ውድ ኦርቶዶክሳውያን Subscribe Like share በማድረግ እንድታበረታቱን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን በሌላ ዝግጅት እስክንገናኝ መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ Telegram

https://t.me/Eyuram_tub

👍 3
🌴 ሆሳዕና በአርያም 🌴