cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ተዋህዶ መሸሸጊያዬ ኦርቶዶክስ መጠለያዬ

ተዋሕዶ መሸሸጊያዬ ኦርቶዶክስ መጠለያዬ ሰላምሽ ከፍ ይበልልኝ እናቴ ሁሌም ኑሪልኝ🙏 ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች 🙌 Join us 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ➫ @yaminadabseregela channel ➬ @dengelmariyam group ➺ @yaminadabseregela_bot for comment ➥ t.me/yaminadabseregela

Більше
Рекламні дописи
780
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-1430 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

🔆🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🔆            አዲስዓመት      መልካምአዲስዓመት   መልካም        አዲስዓመት መልካም           አዲስዓመት መልካም             አዲስዓመት መልካም             አዲስዓመት                         አዲስዓመት                        አዲስዓመት                      አዲስዓመት                    አዲስዓመት                  አዲስዓመት             አዲስዓመት         አዲስዓመት       አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመት                አዲስዓመት አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት              አዲስዓመት         መልካምአዲስዓመት መልካምአዲስዓመትአዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት     መልካምአዲስዓመትስዓመት           መልካምአዲስዓመት                  አዲስዓመት                   ዓመት             አዲስዓመት መልካምአዲስዓመት             አዲስዓመት             አዲስዓመት             አዲስዓመት             አዲስዓመት             አዲስዓመት             አዲስዓመት             አዲስዓመት             አዲስዓመት             አዲስዓመት             አዲስዓመት             አዲስዓመት አዲስዓመትመልካምአዲስዓመት አዲስዓመትመልካምአዲስዓመት አዲስዓመትመልካምአዲስዓመት              አዲስዓመት         መልካምአዲስዓመት መልካምአዲስዓመትአዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት አዲስዓመትመልካምአዓመት መልካምአዲስዓመትአዲትዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት አዲስዓመት              አዲስዓመት መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት     መልካምአዲስዓመትስዓመት           መልካምአዲስዓመት                  አዲስዓመት                                                             🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆 🔆🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🔆 🔆🌼🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🌼🔆 🔆🌼🔸🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🔸🌼🔆 🔆🌼🔸🌻🌻 መልካም 🌻🌻️🔸🌼🔆 🔆🌼🔸🌻🌻  አዲስ    🌻🌻🔸🌼🔆 🔆🌼🔸🌻🌻  ዓመት    🌻🌻️🔸🌼🔆 🔆🌼🔸🌻️🌹⁣🌾🌻💐🌹🌻🔸🌼🔆 🔆🌼🔸🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊🔸🌼🔆 🔆🌼🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🌼🔆 🔆🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🔆
Показати все...
#የብፁዓን_አባቶች_የአዲስ_ዓመት_መልዕክት የጥፋት መሳሪያችሁንም አስቀምጣችሁ ወደ ሰላም ማድ ቀርባችሁ በወንድማማችነት መንፈስ ችግራችሁን በክብ ጠረጴዛ በውይይት በመፍታት የሀገሪቱንና የሕዝቡን አንድነት እንድታስቀጥሉ ሁሉን በሚያይ እግዚአብሔር ስም እንማጸናችኋለን፡፡" (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ) "ትናንት የነበረው ችግር እንዳይደገም ሁሉም በየአለበት ለአብሮነትና ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ችግሮቻችንን ሁሉ በመደማመጥና በመግባባት በመፍታት ለሀገራዊ አንድነት ትኩረት መስጠት አለብን" (ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ሊቀ ጳጳስ) "ዘመኑን መልካም የምናደርገው በዘመኑ መካከል ራሳችንን ለበጎ ነገር ዝግጁ ስናደርግ እና ከኃጢአት  ተመልሰን አዲስ ለመሆን ዝግጁ ስንሆን ነው" (ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ) "ባለፈው ዘመን ተለያይተን እርስ በእርስ የተጋጨንባቸውና ያለያዩንን ጉዳዮች በአዲሱ ዘመን በእርቅና በአንድነት ካልተካናቸው አዲስ ዘመን ብለን ማክበራችን ትርጉም አይኖረውም" (ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ሊቀ ጳጳስ) "ይህን ክፉ ዘመን በሚገባ አውቀንና ተረድተን ከክፉው ዘመን ጋር ተጠቅልለን ሳንጠፋ ዛሬን ለንስሐ ፤ ነገን ለአዲስ ሕይወት እንድንዘጋጅ ጥላቻውን በፍቅር ለውጠን ይህን አዲስ ዘመን ተቀብለን ልናከብረውም ልንከብርበትም ይገባል" (ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሊቀ ጳጳስ)
Показати все...
ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመት ሲመጣ መደሰት፣ ብዙ መብልና መጠጥ ማዘጋጀት፣ አዲስ ልብስም መልበስ ጥቅም የለውም፡፡ ነፍሳችን በኀጢአት እየተጨነቀች፣ ነፍሳችን ተርባና ተጠምታ ሳለ፣ የተዳደፈ የኀጢአት ልብስም ተጆቡና ሳለ አዲስ ዓመት ማክበር ለእኛ ምን ጥቅም ይሰጠናል? እንዲህ ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመትን ማክበር ማለት ለእኔ እንደ ልጆች የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ነው፡፡ ክርስቶስ ከዚሁ ሥራ አውጥቶናል፡፡ ከሕፃንነት አዕምሮ ወደ ማወቅ አሸጋግሮናል፡፡ ከምድራውያን ለይቶ ከሰማያውያን ጋር ደባልቆናል፡፡ ስለዚህ “መልካሙን ሥራችሁን ዐይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ” እንደ ተባለ አፍአዊ ሳይኾን መንፈሳዊውን ብርሃን ልናበራ ይገባናል (ማቴ.5፡16)፤ በአዲሱ ዓመት፡፡ ይህም ብርሃን ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን የሚያስገኝ ነው፡፡ ወዳጄ ሆይ! ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛ ቆሮ.10፡31)፤ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ይኼ ነውና፡፡ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ (ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ - #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ)
Показати все...
"የእግዚአብሔር የጥበብ ርቀት ምን ይረቅ ምን ይጠልቅ፡፡ ለዚህ አንክሮ ይገባል፡፡ ደግነቱንና ይቅርታውንስ ማን ይናገራል፡፡ በኃጢአት ቁስለኞች ፊት መድኃኒት አዘጋጀ፡፡ ተቀብተው በርሱ እንዲድኑ ነው፡፡ በኃጢአት በቆሰሉት ፊት የሕይወት የመድኃኒት ሽቱ አዘጋጀ፡፡ በእርሱ ተሻተው ከመከርፋት እንዲድኑ ነው፡፡ የሕይወትም ወሀ አዘቅትን አመለከተ ወደርሷ ሂደው በርሷም የመነጨው የንጽሕና ውሀ ተረጭተው ታጽበውም እንዲድኑ፡፡ የምድር ኃጥኣን ሁላችሁ ወደ ቅድስት ድንግል ኑ፡፡ በርሷ ስጦታ ጻድቃን ትሆኑ ዘንድ ልብሳችሁ ያደፈ ሁላቸሁ ወደዚች ቅድስት ምንጭ ኑ፡፡ የይቅርታ ውሀ ወደምትፈስ ልብሳችሁንም በልጅዋ ደም እጠቡ፡፡ ለሰማያዊ ሙሽርነት ዝግጁ ትሆኑ ዘንድ፡፡ ድውያነ ሥጋ ሁላችሁ ወደ ድንግል ኑ በጸሎቷ ኃይል እንድትፈወሱ የዕውቀት ድሆች ሁላችሁ ኑ፡፡ የዕውቀት ምንጭን ከሷ ትቀዱ ዘንድ፡፡ ያማረ የተወደደውን የጥበብ ምክር ታገኙ ዘንድ፡፡" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (አርጋኖን ዘአርብ)
Показати все...
+++ "ስንሞት ያመናል እንዴ?" +++ ሕፃናት መጠየቅ ይወዳሉ። አንዴ መጠየቅ ከጀመሩ በኋላ ደግሞ ከእነርሱ የሚወጣው "ለምን ሆነ?" የሚለው የጥያቄ ዝናብ እንዲህ በቀላሉ ቶሎ የሚያባራ አይደለም። እኛም በእነዚህ ጥያቄዎቻቸው ቶሎ ተሰላችተን ወይም ተበሳጭተን ይሆናል። ይሁን እንጂ ጉዳዩ ግን የሕፃናቱ አዲስ አእምሮ ራሱን የሚያሳድግበትና የነገ ማንነታቸውን የሚቀርጽበት ወሳኝ ሂደት ነው። የነገ ወጣቶችን ማንነት የሚቀርጹት ዛሬ "ለምን?" እያሉ ለሚጠይቁ ሕፃናት የምንመልሳቸው መልሶች ናቸው። ስለዚህ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል። በጠና የታመመ ሕፃን ልጅ ያላት አንዲት እናት ነበረች። ይህች እናት በምትችለው ሁሉ ልጇን አሳክማና ተንከባክባ ለማዳን ብትጥርም፣ ይህ ልፋቷ ግን ሊሳካላት አልቻለም። ልጇን የያዘው በሽታ መድኃኒት ስላልነበረው ወደ ሞት አፋፍ አቅርቦታል። ታዲያ አንድ ቀን ሕፃኑ ልጅ እናቱን እንዲህ ሲል ጠየቃት :- "እናቴ፣ መሞት ምን ይመስላል? ስንሞት ያመናል እንዴ?" በእናትየው ዓይኖች እንባዎች ሞሉ። ፊቷም በኃዘን ደፈረሰ። የረሳችው ነገር ያለ ይመስል "ቆይ መጣኹ" ብላ ሮጣ ከክፍሉ ወጣች። ብቻዋን ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ልጇ የጠየቃትን ጥያቄ መመለስ እንዳለባት ብታውቅም ለዚህ ለጋ አእምሮ እንዴት አድርጋ መልስ እንደምትሰጥ ግራ ገብቷታል። እንደ ምንም ራሷን አረጋግታና ጥበቡን እንዲሰጣት ወደ ፈጣሪዋ ተማጽና ተመልሳ ወደ ልጇ ክፍል ገባች። ሕፃኑ መልሱን በጉጉት ይጠብቃል። እናትየውም የውስጧን ኃዘን ለመሰወር ለይምሰል ፈገግ ብላ እንዲህ አለችው "ልጄ፣ ታስታውሳለህ አንድ ጊዜ ጎረቤት ያለ ጓደኛህ ቤት ሄደህ ስትጫወት አምሽተህ ስለደከመህ በዚያው እንቅልፍ ወስዶህ ነበር። ከዚያም በማግስቱ ግን ስትነቃ ራስህ ያገኘኸው በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ ስለሆነ 'እንዴት እዚህ መጣኹ?' እያልክ ስትጠይቀኝ ነበር። እኔም አባት ወደዚያ መጥቶ በጥንካራ ክንዶቹ ተሸክሞህ የአንተ ወደ ሆነው ቤትህ እንዳመጣህ ነግሬሃለኹ። አስታወስክ?" ልጅየው :- "አዎን እናቴ" እናትየው ቀጠለች :- "የኔ ልጅ፣ ሞትም እንደዚሁ ነው። እኛ መኖሪያችን ባልሆነች በዚህ ዓለም ሆነን እናንቀላፋለን። የሰማይ አባታችን እግዚአብሔር ደግሞ ብርቱ በሆኑ እጆቹ አቅፎ ወደ ሰማይ ይወስደናል። ከዚያም ነግቶ እንደ ገና ስንነቃ ራሳችንን በገዛ አባታችን ቤት ውስጥ እናገኘዋለን" አለችው። እውነት ነው! ሞት ለክርስቲያኖች ሁሉ የሚኖረው ትርጉም ይህ ነው። ከእግዚአብሔር ተልከን ወደዚህ ዓለም እንደ መጣን ወደ እርሱ መመለሳችን ደግሞ የማይቀር ነው። ሞት ማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ድንኳን" ብሎ ከገለጸው ከጊዜያዊው መቆያችን ወደ እውነተኛው መኖሪያ አገራችን መሸጋገር ነው። በ2ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ግሪካዊው ፈላስፋ አርስጣደስ በጊዜው አዲስ ሃይማኖት ስለሆነበት ስለ ክርስትና እና ይህ የክርስትና እምነት በሞት ላይ ስላለው እሳቤ ለአንድ ወዳጁ በጻፈለት ደብዳቤ ላይ እንዲህ የሚል ንግግር አስፍሮ ነበር። "ከክርስቲያኖቹ ውስጥ አንድ ጻድቅ የሆነ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይ ምእመናኑ ደስ ይሰኛሉ። ለፈጣሪያቸውም ምስጋናን ያቀርባሉ። ያም ሰው ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ቅርብ ሥፍራ የተሸጋገረ ይመስል ሰውነቱን በመዝሙራትና በምስጋና አጅበው ይሸኙታል" ይላል። ክርስትና እንዲህ ነዋ! ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ክርስቲያኖች በሞት ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ እይታ ሲናገር "ከእኛ መካከል አንድ ሰው በሞተ ጊዜ፣ የማያምነው ሬሳ ሲያይ ክርስቲያኑ ግን ያንቀላፋ ሰውነት ይመለከታል። ያላመነው "የሞተው ሰው ሄደ" ይላል። በርግጥ በዚህ እኛም እንስማማለን። ነገር ግን ወደ የት እንደሚሄድም እናውቃለን። የሚሄደው ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ጴጥሮስ እንዲሁም ሌሎች የቅዱሳን ማኅበር ወደ አሉበት ነው። በኋላም ተስፋ መቁረጥ ባለበት እንባ ሳይሆን፣ በክብርና በማንጸባረቅ እንደሚነሣ እናስባለን!" +++ "ለባሪያዎችህ ሞት የለባቸውም ፍልሰት እንጂ" +++ የወንድማችንን የገብረ ኢየሱስን ነፍስ በዕረፍት ቦታ ያኑርልን! ዲያቆን አቤል ካሳሁን [email protected]
Показати все...
"እውነትና ፍቅር ሊለያዩ የማይችሉ ክንፎች ናቸው እውነት ያለ ፍቅር መብረር እንደማይችል ሁሉእንዲሁም ፍቅር ያለ እውነት ወደ ላይ ሊወነጨፍ አይችልም የስምምነት ቀንበራቸው አንድ ነው።" ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
Показати все...
"ነፍሴ ሆይ! የምትድኝበትን እኔ እነግርሻለሁ፥ ከዚህ ሁሉ ይልቅ ወደ ቅድስት ድንግል ጩኺ፣ እንዲህም በይ የብርሃን እናት ሆይ! በልጅሽ ፊት በደልሁ ኃጢአቴን አስተስርይልኝ፡፡" አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ
Показати все...
ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መውቀስ ትህትና አይደለምና ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው። (ቅዱስ ሰራፕዮን)
Показати все...
"ጌታ ሆይ ወርቅ ትሰጠኝ ዘንድ አልለምንህም ሀብት ንብረትም አልለምንህም እነርሱ ድኅነትን የሚያስገኙ አይደሉም። ይቅርታህን ማግኘት ግን ከወርቅ ይልቃል። የኃጢአት ሥርየትን ማግኘትም ከብር ይበልጣል።" (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)
Показати все...
"ቤተክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ የምታደርገን የልዑል እግዚአብሔር ደጅ ናት፡፡" መጽሐፈ ዲድስቅልያ
Показати все...