cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ገነተ ጽጌ ስንክሳር

ይህ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ትምህርት ቤት የየዕለቱ ስንክሳር እና ግፃዌ ማንበቢያ ነው ። እንኳን በደህና መጡ

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
193
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

+ ከታቦር ተራራ አትቅር + የወንጌላውያን ትሕትና ይደንቃል ፣ ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ስለ ደብረ ታቦር ሲጽፉ ዮሐንስ አልጻፈም። ዮሐንስ ተመርጦ የተገኘበትን ታሪክ "ተመርጬ" ብሎ አልጻፈም። የቀሩት ወንጌላውያን ደግሞ "እኛ የሌለንበትን ነገር አንጽፍም" አላሉም። አንድ ወንጌል እየሰበኩ የሚፎካከሩ ፣ የአንድ ቤት ጣሪያ እየሠሩ ቆርቆሮ የሚሻሙ የእኛ ዘመን አገልጋዮች አልነበሩምና እነርሱ ያልተመረጡበትን ታሪክ ለመናገር ተሯሯጡ። እኛን የማያካትት ክብር ፣ እኛን የማይጨምር ድግስ ጉዳይ ሲነሣ ለማይጥመን ፣ እኛ የሌለንበትን ፎቶ እንኳን ለማየት የማንፈልግ ፣ በእኛ በኩል ያለፈን ነገር ብቻ የምናራግብ ፣ የሌለንበትን ነገር ጥሩም ቢሆን እንኳን ለምናጣጥል "በእኔ በቀር ባዮች" ትምህርቱ ድንቅ ነው። ሌላ ማሳያም አለ ማቴዎስ ወንጌላዊው ስለ ራሱ ታሪክ ሲጽፍ "ማቴዎስ የተባለ ቀራጭ በመቅረጫው ተቀምጦ" ብሎ በኃጢአት ከተዘፈቀበት ሥራ ላይ ወደ ክርስትና እንደተጠራ በግልጽ ሲጽፍ ሌሎቹ ወንጌላውያን ግን በሐዋርያት ዝርዝር ላይ ማቴዎስ ያሉትን ሰው ስለ ቀድሞ የቀራጭነት ሥራው ሲጽፉ ግን ሌዊ የሚል ተለዋጭ ስሙን ተጠቅመዋል። ትሑቱ ማቴዎስ ግን በሌሎች ወንጌላውያን የተሸሸገ የቀድሞ የኃጢአት አኗኗሩን ለእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ማሳያ እንዲሆን ስለፈለገ ጭራሽ በሐዋርያት የስም ዝርዝር ላይ "ቀራጩ ማቴዎስ" ብሎ ራሱን ጠርቷል። የሚገርመው ከቀራጭነት ከተጠራ በኋላ በቤቱ ታላቅ ድግስ ደግሶ ጌታችንን ከኃጢአተኞች ጓደኞቹ ጋር የተቀበለ መሆኑን በሌሎች ወንጌላውያን ሲጽፉ ማቴዎስ ግን ቀራጭነቱን አጉልቶ እንዳልጻፈ ሁሉ የግብዣው ነገር ደጋሹ እርሱ መሆኑን አድበስብሶ በመጻፍ አልፎታል። ★ ★ ★ ቅዱስ ጴጥሮስ "ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው" አለ። "ለእኛ" መልካም ነው የሚለው ቃል ድንቅ ነው። በእግዚአብሔር ቤት መኖራችን መልካምነቱና ጥቅሙ ለእኛ ነው እንጂ ለእግዚአብሔር አይደለም። የማንጠቅም ባሪያዎቹ ስሙን በአሕዛብ ዘንድ ከማሰደብ በቀር ለእርሱ ምን እንጠቅመዋለን። ለዚህም ነው ቅዱስ ባስልዮስ "ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም" ያለው። ስለዚህ ጴጥሮስ "ለእኛ መልካም ነው" አለ። "ብትወድስ ሦስት ዳስ እንሥራ" አለ ፣ ጌታ ካልወደደ እንኳን ሦስት አንድ ዳስ መሥራት አይቻልም ፣ እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ" ስለዚህ "ብትወድስ" አለ። የዋሁ ጴጥሮስ ለእኔ ልሥራ አላለም ፣ የሐዲስ ኪዳን ሐዋርያ ነኝ ብሎ የብሉይ ኪዳን ነቢያትን ከማክበር ወደ ኋላ አላለም። "አንተ ዓለት ነህ በዚህች ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራታለሁ" በተባለ ማግስት ለነቢያቱ ድንኳን ሊቀልስ የጠየቀ ከጴጥሮስ በቀር ማን አለ? ከእግዚአብሔር አብ ግን "አትሙት" እስከማለት ለደረሰው ለነጴጥሮስ ንግግር "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል ትእዛዝ መጣ። ሃሳቡ ድንቅ ቢሆንም ቃሉን ሳይሰሙ ዳስ መሥራት መጀመር አይቻልም። በዚያ ላይ ጌታ የመጣው በደብረ ታቦር ድንኳን አስጥሎ ሊኖር ሳይሆን በቀራንዮ በተሰቀለበት በመስቀሉ ካስማ በደሙ ድንኳን ተክሎ ሊያስጠልለን ነው። ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ "ጴጥሮስ ሆይ ለአንተ የፊቱን ብርሃን እያየህ በዚህ መኖር መልካም ነው ፣ እኛ ግን የምንድነው በተራራው ሲኖር ሳይሆን ወርዶ ፊቱን በጥፊ ሲመታ ነው" ብሎታል። ጴጥሮስ የዋሁ "በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ" ላለው ለክርስቶስ ድንኳን ሊቀልስ ጠየቀ። በሰማይ "በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ድንኳን" ላለችው ሊቀ ካህናት ድንኳን ሊሠራ ለመነ። እዚህ አለ ሲሉት እዚያ ለሚገኘው ፣ በመንፈስ እየተነጠቀ አድራሻውን ለመወሰን ያስቸግር ለነበረው ኤልያስ እንዲቀመጥ ተስፋ አድርጎ ድንኳን ልሥራ አለ። እጅግ የተዋበችና በወርቅ በሐር ያጌጠችን የኦሪት ድንኳን ለሠራው ሙሴ ዓሣ አጥማጁ ጴጥሮስ ድንኳን ልሥራለት አለ። ሐዋርያት ነቢያቱን ሊያስተናግዱ የለመኑባት ደብረ ታቦር ፣ ሐዋርያት ነቢያቱን ለጌታ ቀኝ አዝማች ግራዝማች አድርገው በድንኳን አስቀምጠው እነርሱ እንደ ሎሌ ከደጅ ሊኖሩ የጠየቁ እነ ጴጥሮስ እንደምን ይደንቃሉ? ጴጥሮስ ሆይ አሁን በሰማይ ድንኳኖች ውስጥ እያገለገልህ ይሆንን? ደብረ ታቦርን አይተህ በደስታ "እንኑር" ያልከው ጴጥሮስ ሆይ የገነት ደስታ ስታይ ምን ተሰምቶህ ይሆን? በእሳት ድንኳን ለመኖር ተስፋ የምናደርግ "በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል" የተባልን እኛስ ምንኛ የታደልን ነን? ★ ★ ★ በታቦር ተራራ ላይ የጌታችን ልብስ እንደ ፀሐይ አበራ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ከፀሐይም በላይ ነው ፣ ፀሐይ አይቶ የወደቀ የለም የጌታችንን ልብስ ሲያዩ ግን የወደቁት ያበራው ከዚያ በላይ ስለሆነ ነው" ይላል። ከጌታችን በዚያ ተራራ ከሙሴና ኤልያስ ጋር ነበረ። ሙሴ እንደምናውቀው ጽላቱን ተቀብሎ ሲወርድ ሕዝቡ "እባክህን ተሸፈንልን" ብለውት ፊቱን በመጎናጸፊያው ሸፍኖ ነበር። የሙሴ አምላክ ክርስቶስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ሲወድቁ አይቶ በልብሱ እንዳይሸፈን ያበራው ፊቱ ብቻ ሳይሆን ልብሱም ነበር። " አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ" ማር 9: 3 የሚለው ቃል ምንኛ የሚደንቅ ነው። በምድር ላይ ያለ አጣቢ ቢፈትግ ቢታገል የዚያን ያህል ሊያነጻው የማይችለው ነጭ እንዴት ያለ ነው? መቼም ሁላችን የምናውቀው ነጭ ነገር ሁሉ በምድር ላይ ባለ አጣቢ የታጠበ ስለሆነ እንዲህ ነው ማለት አንችልም። ብቻ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በምድር ያሉ አጣቢዎች ከሚያነጡት በላይ ልብስን ማንጣት ይችላል። ይህ ቃል በኃጢአት እድፍ ልብሳችን ላደፈ ሁሉ መጽናኛችን ነው። መቼም የምድር አጣቢዎች አቅማቸው ውስን ነው። ቆሽሸን ያዩን ሰዎች ብንታጠብም አያምኑንም ፣ ቢያጥቡልንም በኅሊናቸው የሚያስቀሩብን ቆሻሻ አለ። በሰው ዓይን አንዴ ቆሽሸህ አትገኝ እንጂ ከተገኘህ መቼም ነጭ አትሆንም። አንተ ግን የደብረ ታቦሩ ብርሃን መድኃኔ ዓለምን ብቻ "እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ" በለው "ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች። " ብሎ በገባው ቃል መሠረት ነጭ ያደርግሃል። እርሱ ወዳለባት የቅድስት ቤተክርስቲያን ተራራ በንስሓ ከደረስክና በታቦር ያበራውን ብርሃኑን ካበራልህ ነጭ ትሆናለህ። ከዚያ "አጣቢ የማያነጻውን ያህል ትነጻለህ" ከአብ የባሕርይ ልጅ ከብርሃኑ ፀዳል ስትቀርብ አንተም በጥምቀት ያገኘኸው የጸጋ ልጅነትህ ያንጸባርቃል። ነጭ በሆንህ ጊዜ የሚያዩህ ሁሉ "በበጉ ደም ልብስህ መታጠቡን"ና ነጭ መሆኑን አይተው ይደነግጣሉ ፣ ሊሰሙህ ያልወደዱ ሁሉ ለባሕርይ ልጁ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" ብሎ እንዳዘዘለት ለአንተም ጆሮ እንዲሠጡህ ያደርግልሃል። አንተ ብቻ ከደብረ ታቦር አትቅር ፣ ካልሞትህ እንደ ኤልያስ ፈጥነህ ና ፣ በበደል ከሞትክም እንደሙሴ ተነሥተህ ና። ብቻ ወደ ደብረ ታቦር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት ተስፋ አትቁረጥ ፣ እንደ ሙሴ ትሞታለህ እንጂ ምድረ ርስትን አታይም ብትባል ፣ እንደ ኤልያስ ትኖራለህ እንጂ ሞትን አታይም ብትባል ብቻ አንተ ከደብረ ታቦር አትቅር። ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ደብረ ታቦር 2010 ለንደን ፣ ብሪታንያ
Показати все...
👏 ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ ልጆች ሁሉ - - ሆ የኛማ ጌታ - - ሆ የዓለም ፈጣሪ - - ሆ የሰላም አምላክ - -ሆ ትሁት መሀሪ -ሆ በደብረ ታቦር - - ሆ የተገለጠው - ሆ ፊቱ እንደ ፀሐይ - ሆ በርቶ የታየው -ሆ ልብሱ እንደብርሃን -ሆ ያንፀባረቀው -ሆ ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(፪) የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(፪) ያዕቆብ ዮሐንስ-ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ-ሆ አምላክን አዩት - - ሆ ሙሴ ኤልያስ - ሆ አባቱም አለ - - ሆ ልጄን ስሙት - - ሆ ቃሌ ነውና - - ሆ የወለድኩት - - ሆ አዝ====== ታቦር አርሞንኤም-ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው- ሆ ሰላም ሰላም - - ሆ የታቦር ተራራ - - ሆ ብርሀነ መለኮት - ሆ ባንቺ ላይ አበራ -ሆ አዝ====== በተዋህዶ - - ሆ ወልድ የከበረው - ሆ የእግዚአብሔር አብ ልጅ - - ሆ ወልደማርያም ነው - -ሆ ቡሄ በሉ - - ሆ ቡሄ በሉ - - ሆ የአዳም ልጆች - - ሆ ብርሃንን - - ሆ ተቀበሉ - -ሆ አዝ====== አባቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ እናቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ ከአጎቴም ቤት - - - ሆ አለኝ ለከት - ሆ ተከምሯል - - ሆ እንደ ኩበት - - ሆ አዝ====== የዓመት ልምዳችን - - ሆ ከጥንት የመጣው - - ሆ ከተከመረው - ሆ ከመሶቡ ይውጣ - ሆ ከደብረ ታቦር - - ሆ ጌታ ሰለመጣ - ሆ የተጋገረው - ሆ ሙልሙሉ ይምጣ - ሆ አዝ====== ኢትዮጵያውያን - -ሆ ታሪክ ያላችሁ - ሆ ባህላችሁን - ሆ ያዙ አጥብቃችሁ - ሆ ችቦውን አብሩት -ሆ እንዳባቶቻችሁ -ሆ ምስጢር ስላለው -ሆ ደስ ይበላችሁ -ሆ አዝ====== አባቶቻችን - - ሆ ያወረሱን - - ሆ የቡሄን ትርጉም - - ሆ ያሳወቁን - - ሆ እንድንጠብቀው - ሆ ለእኛ የሰጡን - ሆ ይህን ነውና - - ሆ ያስረከቡን - - ሆ አዝ====== ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ ቅዱሳን ጻድቃን - - ሆ የሞሉብሽ - - ሆ በረከታቸው - - ሆ ያደረብሽ - - ሆ ሁሌም እንግዶች - ሆ የሚያርፉብሽ -ሆ ሀገረ እግዚአብሔር -ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ አዝ====== ለሐዋርያት - - ሆ የላከ መንፈስ - - ሆ ዛሬም ለኢትዮጵያ -ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ በበጎ ምግባር - ሆ እንድንታነጽ - - ሆ በቅን ልቦና - ሆ በጥሩ መንፈስ - - ሆ በረከተ ቡሄ - ሆ ለሁላችን፹ ይድረስ - ሆ ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና እንዲሁ እንዳላችሁ - -በፍቅር አይለያችሁ - - በፍቅር ላመቱ በሰላም - - በፍቅር ያድርሳችሁ - - በፍቅር ክርስቶስ በቀኙ - - በፍቅር ያቁማችሁ - - በፍቅር የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር ያድርጋችሁ - - በፍቅር እንዲሁ እንዳለን - - በፍቅር አይለየን - - በፍቅር ለዓመቱ በሰላም - - በፍቅር ያድርሰን - - በፍቅር አማኑኤል በቀኙ - - በፍቅር ያቁመን - - በፍቅር የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር ያድርገን - - በፍቅር የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት በሁሉም ቤት(፪) ይግባ በረከት(፪) እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት የአስራት አገር የአበው ቀደምት የቅዱሳን አባቶች ትውፊት ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት ባህላችንን የአባቶች ትውፊት (፫) https://t.me/stgeor https://t.me/stgeor https://t.me/stgeor
Показати все...

Показати все...
Показати все...
ጻድቅ ኢዮብ:- አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሁለት በዚህች ቀን ጻድቅ ኢዮብ አረፈ:: ስለ ቅዱሳን መጻፍ ለምን አስፈለገ የሚሉ የዘመኑ ስሁታን እናንተ ኦርቶዶክሳዊያን ይህን ስለ ቅዱሳን መጻፍ ለምን አትተውም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለምና ይሉናል:: አንዳንድ የኛም ምእመናኖች የመናፍቃን እንክርዳድ ያለባቸው በማወቅም ይሁን ባለማወቃቸው ቅዱሳን ሰማዕታት ይህ ሁሉ መከራ አምላካቸው ካለ እንዴት ይህ ሁሉ መከራ ይደርስባቸዋል ለሚሉ የዛሬው የኢዮብ ታሪክ መልስ ይሰጣል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከመጽሐፍ ቅዱስ አትወጣም ወጥታም አታውቅም:: በዛሬው ዕለት የምናስብው ጻድቅ ኢዮብም ሆነ ለሌች ቅዱሳን ዜና ሕይወት /ገድላት/ ለሚጻፉ መንገድ የከፈተና ማሳያ ነው:: እንግዲህ መጽሐፍ ቅዱስ በእንደንዚህ መልክ የቅዱሳንን ዜና ሕይወት ከጻፈ ዕለት ዕለት ብናስባቸውና ብንጽፍላቸው መሠረታችን መጽሐፍ ቅዱስ ነውና የአባቶቻችንን አምላክ እናመሰግናለን:: የዛሬው ታሪክ ይኸው፦ " ዖፅ በሚባል አገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበር:: ያም ሰው ፍጹምና ቅን እግዚአብሔርን የሚፈራ ከክፋትም የራቀ ነበር::" መጽ. ኢዮብ 1÷1:: ለዚህም ጻድቅ በዘመኑ እንደርሱ ያለ ዕውነተኛ ደግ ሰው እንዳልነበረ እግዚአብሔር መሰከረለት:: ሰይጣንም ቀንቶበት በገንዘቡና በልጆቹ ላይ ያሠለጥነው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ለመነ:: የጻድቅ ኢዮብን ትዕግሥት እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ሠይጣንን በኢዮብ ላይ አሠለጠነው:: ለመጪው ትውልድ አርአያና ምሳሌ እንዲሆን ፈቀደለት:: እዚህ ጋር አንባቢ ልብ ይሏል:: ሰይጣን የኢዮብን ሐብት÷ ንብረት÷ እግዚአብሔር ሊያስክደው ፈቃድ ሲጠይቅ እንመለከታለን:: ታዲያ በአንፃሩ ስንመለከት ቅዱሳን መላእክት ስለኛ በእግዚአብሔር ፊት ይማልዳሉ ምሕረትን ይጠይቃሉ ስንል መናፍቃን ለምን ይቃወማሉ ሰይጣን እኮ ለክፋት ፈቃድ ጠየቀ:: ስለ እርሱ ሐዋርያው ያዕቆብ በመልእክቱ እንሆ የጻድቅ ኢዮብን ትዕግሥቱን ሰምታችኋል አለ:: ከዚህ በኋላም በአንዲት ቀን የኢዮብ ገንዘብ ሁሉ ጠፋ፤ ሥጋው በደዌ ሥጋ ከራሱ ጠጉሩ እስከ እግሩ ጥፍሩ ድረስ ተመታ:: በዚህም በአስጨናቂ ደዌ ውስጥ ኖረ ደግሞ እግዚአብሔርን አመሰገነ:: አንዲት ቃልን እንኳ በፈጠረው እግዚአብሔር ላይ አላጕረመረመም፤ ነገር ግን "ረገማ ለዕለት ዘተወልደ ባቲ::" ……"የተወለደበትን ቀን ረገመ::" የነበሩት ከብቶቹ፣ ገንዘቡ፣ ሀብትና ንብረቱ ሁሉ በጠፋ ጊዜ:: እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔርም ነሣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን አለ:: የሰጠ ቢነሳ የለበት ወቀሳ አለ። ያ የከበረና የተመሰገነ ኢዮብ በዚህ መከራ በነበረበት ዘመናት በተራራ ላይ ተጥሎ ሳለ የወዳጆቹና የሚስቱ ዘለፋ በዝቶበት ነበር:: ሚስቱ አጋሩ ልታበረታው፣ ልትረዳው፣ ልታፅናናው ሲገባ ከወዳጆቹ ብሳ እንዲህ ብላ መከረችው:- "እስከ መቼ ድረስ በሞኝነት ትኖራለህ እንግዲህስ ስደበውና ሙት ዳግመኛ እግዚአብሔርን ደጅ እጠናዋለሁ መከራውንም እታገሣለሁ የቀድሞ ኑሮዬን ተስፋ አድርጋለሁ ትላለህ አለችው:: "ዳግመኛም አለችው:: እንዲህስ እንዳትል ከዚህ ዓለም እንሆ ስም አጠራርህ ጠፋ ሴቶች ልጆቼና ወንዶች ልጆቼ ሞቱ:: እኔም ዘጠኝ ወር ሳረግዝ ሳምጥ ስወልድ ላይረቡኝ ላይጠቅሙኝ በከንቱ ደከምኩ:: አንተም በመግል ተውጠህ በትል ተከበህ ትኖራለህ ሌሊቱን ሁሉ ስትዛብር ታድራለህ፤ እኔም እየዞርኩ እቀላውጣለሁ ካንዱ አገር ወዳንዱ አገር ካንዱ ቤት ወዳንዱ ቤት እሔዳለሁ:: ከድካሜ በእኔ ላይ ከመጣው ከችግሬም አርፍ ዘንድ ከጧት ጀምሮ ፀሐይ እስኪገባ ድረስ እጠብቃለሁ አሁን ግን እግዚአብሔርን የማይገባ ቃል ተናግረኽው ሙት አለችው:: ኢዮብም ሚስቱን እየተመለከተ በትዕግስት ሰማት:: እንዲህም አላት፦ ይህን ሁሉ እግዚአብሔር ለመልካም አደረገ ሥርዓት እንዳልተሠራባቸው አሕዛብ ሴቶች እንዳንዲቱ ተናገርሽ፤ ከዚህ ቀደሞ በጎውን ነገር ከእግዚአብሔር እጅ ተቀበልን ከዚህ በኋላ መከራውን አንታገሥም ዘንድ አላት:: ኢዮብ በዚህ ባገኘው መከራ ሀብቱ÷ ንብረቱ÷ ልጆቹ÷ መላ አካሉ በበሽታ ሲመታ ጤናው ሁሉ ሲታወክ አምላኩን አመሰገነ እንጂ አንድም የስንፍና ቃል በአምላኩ ላይ አልተናገረም:: ኢዮብም " ወተፈተነ ወተነጥፈ ከመ ወርቅ በእሳት::" ወርቅ በእሳት እንዲፈተን ፈጽሞ ተፈተነ:: ያለ መከራ ዋጋ ያለፈተና ፀጋ አይገኝምና እግዚአብሔርም በደመና ውስጥ ኢዮብን ተናገረው:: ከተናገረውም በኋላ ከደዌ ሁሉ ፈወሰው ሀብቱም ሁሉ ባርኮ ከቀድሞ እጥፍ አደረገለት የተባረኩ ልጆችም ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ሰጠው:: ኢዮብ ከደዌ ከተፈወሰ ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ የተባረከ ጤንነት የተሞላ መቶ ሰባ ዘመን ኖረ:: የኖረው ዘመን በጠቅላላ ሁለት መት አርባ ስምንት ዓመት ነው የኖረው:: እዮብም በበጎ ሽምግልና ኖሮ እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም አረፈ:: ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ሰው ጸሎት ይማረን የትዕግስቱንና የፅናቱን በረከትም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን:: @stgeor @stgeor @stgeor
Показати все...