uk
Feedback
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

Відкрити в Telegram

💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።

Показати більше
8 844
Підписники
+1724 години
+97 днів
+1130 днів
Архів дописів
🔖ተፍሲር ሱረቱል አል _ፋቲሐ ማብራሪያ       ~ 📍ክፍል አራት t.me/AbumuslimAlarsi/13095

✅ አላህ ለወፈቀው ነጋዴ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿التاجرُ الأمينُ الصَّدوقُ المسلمُ: مع [النَّبِيِّينَ، والصِّدِّيقينَ، و] الشُّهَداءِ يومَ القيامةِ﴾ ~“ታማኝና እውነተኛ ነጋዴ በእለተ ትንሳዔ ከነቢያት ከእውነተኞችና ከሰመአታት ጋር ነው የሚሆነው።” ✅📚 ሲልሲለቱ አሰሂሃ: 3453 t.me/https_Asselfya

~አንድ ሰው ከቁርአን ጋር ሳይተዋወቅ በፊት ያለው ህይወት እና ከቁርአን ከተዋወቀ ብኋላ የሚኖረው ህይወት ፍጹም የተለያየ ነው ከቁርአን ጋር ከተዋወቀ ብኋላ ባህሪው ፣ንግግሩ፣ አስተሳሰቡ፣ ፍላጎቱ፣ ህልሙ እና የልቡ ደስተኝነት እና ሰላም ማግኘት ፍጹም ከበፊቱ የተለየ ይሆናል ከአላህ ጋር ያለው ግንኙነት እራሱ ወደ ጠንካራነት እንደተቀየረ ይረዳል። منقول

ስለ ትናንቱ የኦንላይን ደዕዋ ~ በቅድሚያ አላህ ስላገራውም ስላደለንም አልሐምዱ ሊላህ። በመቀጠል ጊዜያቸውን ሰጥተው ውድ ምክሮችን ያካፈሉንን ሸይኽ ዐሊይ አራዚሒይን ከልብ እናመሰግናለን።  እንዲሁም ለሃሳቡ መነሻ የሆኑ ወንድሞችን ዐብዱልፈታሕ ሙሐመድዘይን (የመን በዒልም ፍለጋ ላይ ያለ ወንድማችን ነው)፣ አሕመድኑር ኸዲር ከወሎ ወረባቦ፣ ደዕዋውን በመተርጎም ላይ ያገዙ አቡል 0ባስ ናሲር፣ ዐብዱረዛቅ ባጂ፣ አቡ ሱፍያን እና የመን ከሸይኽ ዐሊይ ጋር ያለ ሌላ የሃገራችን ልጅ (ኻሊድ?) ሁላችሁንም ጀዛኩሙላሁ ኸይረን። ለታዳሚዎች ባጠቃላይ ለተፈጠረው የኔትዎርክ ችግር - ከኛ ቁጥጥር ውጭ ቢሆንም - ይቅርታ እየጠየቅን ፕሮግራሙን ስለታደማችሁ በጣም ደስ ብሎናል። አላህ በሰማችሁት የምትጠቀሙ ያድርጋችሁ። ለወደፊቱም በአላህ ፈቃድ ከሌሎች መሻይኾች ጋርም በመነጋገር ተመሳሳይ ፕሮግራም ለማዘጋጀት ሃሳቡ አለን። እንደዚሁም በሃገር ውስጥ መሻይኾች እና ኡስታዞችም ለማስተላለፍ የምናስብበት ይሆናል ኢንሻአላህ። = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

🔖ሳታገባ በመዘግይተህ መታገስህ መጥፎ ምርጫ ላይ ወድቀህ ከመታገሰህ በብዙ የተሻለና የቀለለ ነው! صبرك على تأخر الزواج أهون بكثير من صبرك على سوء الاختيار!

አገባሽ አይደል በቃ እንኳንም ሀላሉን አላህ ወፈቀሽ አልሀምዱ ሊላህ በይ  ሷሊህ የሆኑ ልጆችን እንዲወፍቅሽ ዱአ አድርጊ ።የባልሽን ሀቅ በአግባቡ ተወጪ አለቀ ! ሚድያ ላይ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለትን ምን አመጣው ። የእሱ ብቻ ፣የሱ ናፋቂ  ፣የሱ ምርኮኛ፣የሱ ብቸኛ፣የሱ ሱሰኛ፣የሱ ንግስት ምናምን ብሎ መለጠፋ ምን ጥቅም ይሰጣል? በቃ ይሄን ለሱ በይው ።አንዳንዷማ ጭራሽ ናፈቅከኝ ብላ ፕሮፋይል፣እስቶሪ ላይ ትለጥፋለች እህ! እና እኛ ምን እናድርግ? ለሱ በውስጥ ናፈቅከኝ ሀቢቢ በውይው.።ሚድያ ላይ ማውጣትሽ ለኛ መንገርሽ አይጠቅምሽም ። ለአይንም ጥሩ አይደለም። ፍቅር በሚስጥር ሲሆን ምንኛ ያምር?? ✍አቡ ሀፍሷ @AbuHafsuaImam

🔖ተፍሲር ሱረቱል አል _ፋቲሐ ማብራሪያ       ~ 📍ክፍል አራት t.me/AbumuslimAlarsi/13085

~ዋጋ ያላት ሴት ሁኚ !

ፎቶሽን ላኪልኝ! ~ በዚህ ዘመን የኸልዋ ቦታዎች አቤት መብዛታቸው፡፡ ፌስቡክ፣ ዋትሳፕ፣ ቲክቶኩ፣ ኢሞው፣ ቴሌግራሙ… እነኚህ ሁሉ ኸልዋዎቻችን ናቸው፡፡ ምን እንደምንሠራባቸው አላህ እና እኛ ብቻ የምናውቃቸው ቤቶች ናቸው፡፡ በነኚህ የቤት ግድግዳዎች ላይ በራሣችን እጅ የፃፍናቸው ስንት የኛ ጉዶች፣ ጉድፎች፣ ቆሻሾች፣ ነጃሳዎች አሉ መሰላችሁ።ተመልሰን ብናነነባቸው ከኛ መውጣታቸውን እንኳን የማናምናቸው ስንት አሳፋሪ ቃላቶች አሉብን!፡፡ ወላሂ እውቴን ነው!!፡፡ ስልካችሁ ይፈተሸ ቢባል ማን በልበ ሙሉነት ደፍሮ ያስፈትሻል!! ከፊሉ በፓስወርድ፣ ሌላው በፓተርን ከርችሞ ዘግቶታል፡፡እኛ ከሰው የደበቅናቸው አላህ ግን የሚያውቃቸው ስንት መንሸራተቶች አሉብን!! በርግጥ እነኚህን ቆሻሻ ወሬዎቻችንን በመጨረሻም ከስልካችን ልናፀዳ  እንችላለን፤ አላህ ዘንድ ግን ተፅፈው የሚቀመጡ እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡አላህ ሆይ ሲትራህን ከማለት ዉጭ ምን ማለት እንችላለን፡፡ ዛሬ በዉስጥ በኩል በጓዳ ሴትን ልጅ ያለ በቂ ምክኒያት ለማናገር «አሰላሙ ዐለይኩም» ማለት ብቻውን በቂ ነው፡፡ የጓዳ ሰላምታ አብዛኛው የጤና ሳይሆን የበሽታ ነው፡፡ ሰላምታው ካልተመለሰ ዉትወታው ይቀጥላል፡፡ ሰላምታ መመለስ እኮ ግዴታ ነው ይላል ስለ ግዴታነቱ የጨነቀው ይመስል፡፡ በሂደት የወሬው ሰንሰለት ይቀጣጠላል፡፡ አንድ ሁለት እየተባለ ይረዝማል፡፡ ሦስተኛው ወገን ሸይጧን ነውና ከወዲህና ከወዲያ ሆኖ ይገፋፋል፡፡ እሱ በዚህ ዓይነቱ ሥራ ተክኗል፤ ገበያው ነውና ይሯሯጣል፣ ጽሑፍን በምስልና በድምፅ አደራጅቶ ከነቅላፄው ያቀርባል፣ ቃላትን ከፈገግታና ከሁነት ጋር አዋህዶ ያሰርፃል፤ ልክ እንደሚተያዩ አድርጎ ፊት ለፊት አድርጎ ያቀርባል፡፡ ያኔ ታዲያ ለመውደቅ የግድ በአካል መገናኘት አያስፈልግም፡፡ የጓዳ ሰላምታ ጨዋ ሆኖ ይጀምራል፤ ሁነኛ ባለጉዳይ አስመስሎ ያስቀርባል፣ በሂደት ግን ስልክ ያለዋውጣል፣ ፎቶ ያላልካል፣ ኒቃብ ያስወልቃል፡፡    ከጀንጃኝም ከሸይጣን በላይ የተዋጣለት የሰው ሸይጧን አለ፡፡ አካበድሽው፣ ምን አስፈራሽ?  ምን ችግር አለው? በራስሽ አትተማመኚም እንዴ! ከኔና ካንች ዉጭ ይህን ነገር የሚውቅ አለ ወይ! …. ይላል አፈ ጮሌው ፣ ምላሰ ቅቤው … የሚፈልገውን እስኪያገኝ ድረስ ሆዴ ይላል ሆዱ ይዘርገፍና፣  ማሬ ይላል ኑሮው እሬት ይሁንበትና! ፍቅሬ ይላል ፍቅር ያሳጣውና! ዉዴ ይላል ከተራ ነገር አይውጣና ….   እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው መሰለሽ…ሁኔታው ካላማረሽ ፣የጓዳ ሰላምታ ይቅርብሽ፣ትርፍ ንግግር ራቂ፣ፎቶሽን አትላኪ፣ክብርሽን ጠብቂ፣ኒቃብሽን አታውልቂ! |•|t.me/Sle_qelbachn1

🔖ውዷ እህቴ ~ ~ ትዕግስትን (ሶብርን) ስንቅሽ! የአላህ ፍራቻ (ተቅዋ) ልብስሽ! የአላህን ቃል ቁርዓንን ጓደኛሽ! ተወኩልን ተስፋሽ አድርገሽ ይዘሽ! ዒልምን በመፈለግ ላይ ፅናት ይኑርሽ በአላህ
🔖ውዷ እህቴ ~ ~ ትዕግስትን (ሶብርን) ስንቅሽ! የአላህ ፍራቻ (ተቅዋ) ልብስሽ! የአላህን ቃል ቁርዓንን ጓደኛሽ! ተወኩልን ተስፋሽ አድርገሽ ይዘሽ! ዒልምን በመፈለግ ላይ ፅናት ይኑርሽ በአላህ ፍቃድ ለስኬት ትበቂያለሽ!!! ~ t.me/https_Asselfya

🔖ወሳኝ ምክር ለወላጆች ➖➖➖➖➖ 👉 ልጆቻችሁ መስጅድ አለማምዱ 👉 ለቀልድ ለጨዋታ ብቻ አትተዋቸው 👉አብረዋችሁ በጀመአ ይስገዱ 👉 መስጅድ የልጆች መድረሳ ነው 🎙صالح بن فوزان الفوزان حفظه الله

ሼይኽ ረቢዕ በሞት አፋፍ ላይ ወስያ ሲሉ በቁርአን አደራ እያሉ ነው !! ያረብ የቁርአንን ከፍታ ሚያውቁት ሰዎች ከፍታ ላይ ያሉ ኡለሞች ብቻ ናቸው! አናንተ እና እኔማ ... መች በወጉ ተረዳነው የቁርአንን ክብር እና ደረጃ ለዛምኮ ነው ይሄን ሁሉ አመት ኖርን ግን አሁንም ቁርአንን አስተካክለን መቅራት ና ተፍሲሩን መረዳት ያልቻልነው ያረብ እዝነትህን! ጌታየ ሆየ የቁርአን ሰዎች አድርገን... ቁርአንን በትክክል አንብበውት በትክክል ተረድተውት በትክክል ተግብረውት ከሚገናኙህ አድርገን ያረብ!!

መጥፎ ሴቶች .mp31.82 KB

የሰለፎች ኪታቦች ይዳኙን! ~ ሱብሓነላህ! ምንኛ ወኔ የሚቀሰቅስ ንግግር ነው! ጀግና ነበሩ ረቢዕ፣ የቃልም የተግባርም ሙጃሂድ። በሐቅ ላይ የወቃሽ ወቀሳ የማያስጨንቃቸው፣ የይሉኝታ ትብታብ፣ የመንጋ ግርግር የማያስደነግጣቸው። ይሄው ማንም ወደማያቀርበት ሃገር ሄደዋል። አላህ በፊርደውሱ ያሞናድላቸው! ስሙ አልፎ የናኘው - ከወዳጅ ከጠላት አባ ቅጣው ረቢዕ - የኢኽዋን መድሃኒት!! = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

📍ሀሰነል በስርይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ። የአንድ ዓሊም ሞት በእስልምና ውስጥ ቀንና ሌሊት ቢለያዩም በምንም ነገር ሊዘጋ የማይችል ቀዳዳ ነው። 📚[جامِع بيان العِلم وفضله -١\٥٩٥-] t.me/https_Asselfya

🔖ኢማም አዩብ አሰህትያንይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል። ከአህለሱና የሆነ የአንድ ሰው ሞት ስሰማ ልክ ከሰውነት አካሌ አንዱን እንዳጣሁ ያክል ይሰማኛል። 📚شرح أصول اعتقاد أهل السنة والجماعة t.me/https_Asselfya

الْأَرْضُ تَحْيَا إِذَا مَا عَاشَ عَالِمُهَا              مَتَى يَمُتْ عَالِمٌ مِنْهَا يَمُت طرَفُ كَالْأَرْضِ تَحْيَا إِذَا مَا الْغَيْثُ حَلَّ بِهَا               وَإِنْ أَبَى عَادَ فِي أَكْنَافِهَا التَّلَفُ https://t.me/DrRabeeM

وقال سفيان الثوري: "إذا ماتَ العالمُ، انثلمَ في الإسلامِ ثُلمةٌ لا يسدّها شيءٌ ما اختلف الليلُ والنهار" (سير أعلام النبلاء للذهبي 7/229)