cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Mind programming

Business and personal development opportunity 👇👇👇👇 @Gech1921 t.me/purposoflife

Більше
Рекламні дописи
222
Підписники
Немає даних24 години
+27 днів
+730 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

እንደ ህጻናት ካልሆናችሁ (By Master Minder Solomon W/Gebriel) መጽሐፍ ላይ “ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።” ይላል። ይሄ ነገር እውነት ለመንግስተ ሰማያት ብቻ ነው? ወይስ በዚህ አለምም ስኬታማ ለመሆን? ብዬ አሰብኩ። የመጣልኝ መልስ በዚህም የሚል ነው። ጥቂት ነጥቦች 1. አጥብቆ መፈለግ። ህጻን ልጅ የሆነ ነገር ሲፈልግ አጥብቆ ይፈልጋል። ለህጻን ልጅ መፈለግ ወይም አለመፈለግ የሚባል ነገር የለም።በቃ ህጻን ልጅ የሚፈልገው ነገርን ካላገኘ መፋታት የሚባል ነገር የለም።  ብዙ አዋቂ ሰው ግን ይፈልጋልም አይፈልግምም። ቀዝቃዛ ነው። ቢሆንለት ደስ ይለዋል። ባይሆንም እንደህጻን አያደርገውም። አዋቂ ነዋ! ሰው ምን ይለዋል! ህጻን ግን ይሉኝታ አያውቅም። ይፈልጋል ይፈልጋል። እና አንተ የምትፈልገው ነገር ለአንተም ለሰውም የሚጠቅም ከሆነ አጥብቀህ ፈልገው። ካስፈልገም አልቅስ። ምክንያቱም ጥልቅ ፍላጎት አለህና። 2. የሚፈልጉትን በግልጽ ማወቅ። ህጻን የሆነ ነገር ሲፈልግ በተመሳሳዩ አይሸወድም። የሚፈልገውን በግልጽ ያውቃል። ከእሱ ውጪ አማራጮችን አይቀበልም። ብዙ ትልቅ ሰው የሚፈልገውን በግልጽ አያውቅም። የሚመኘውም ጥሩ ኑሮ!  የተሻለ ኑሮ የሚባል ነገር ነው። ለመሆኑ የተሻለ ኑሮ፣ ጥሩ ኑሮ የሚባል ኑሮ ነገር አለ? የለም። እንደዛ ካልን ሁሉም ሰው የተሻለ ኑሮ ላይ ነው። ምክንያቱም በአንጻራዊነት ከእሱ ያነሰ  ኑሮ ውስጥ ያለ ሰው ስላለ የእሱ ኑሮ የተሻለ ነው።  ምን አይነት ኑሮ ነው ምትፈልገው? ሲባል እንዲህ ልሆን እፈልጋለሁ፣ እንዲህ ማድረግ እፈልጋለሁ እንዲህ እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ ማለት አለብን። ይሄ ለስኬት ትልቅ ቁልፍ ነው። ህጻናት የሚፈልጉትን በግልጽ ያውቃሉ። 3. ህጻን በእምነት ይጠብቃል። ብዙ ሰው አምኖ ለሚፈልገው ነገር መስራት ይቸግረዋል። ህጻናት አንዴ እሺ ከተባሉ በኋላ አምነው ለጥ ነው የሚሉት። ይሆናል ወይ ይሳካል ወይ ብለው ምናምን ሲባዝኑ አያድሩም። እስቲ መኪናዬ ይገዛልኝ ይሆን ወይ ብሎ እጁን አገጩ ላይ አስደግፎ በጭንቀት እህህ እያለ የሚያሰላስል ህጻን ልጅ ፎቶ አሳየኝ። የለም። በቃ ያምናል። ስለዚህ የምትፈልገውን በግልጽ ካወቅክ፣ አጥብቀህ ከፈልግከው። በእምነት የገባህን ስራ። ያመንከው ይመጣል። 4. ህጻናት አስቀድመው ይደሰታሉ፣ ያመሰግናሉ! ይስቃሉ። ብዙ አዋቂ ሰው የሚፈልገውን ነገር በጉንጩ ይዞ፣ በእጁም ሌላ አዘጋጅቶ፣ በአይኖቹም ወረፋ ይዞ፤ በእጁ እና በአፉ ያለውን ነገር ማጣጣም ስለማይችል እየበላ ይርበዋል። ይዞ አይደሰትም። ለምስጋናም ይዘገያል። ህጻን ግን እንኳን የሚፈልገው ቃል ተገብቶለት ያለምክንያት ይደሰታል፣ በትንሹ ያመሰግናል። ህጻን እስኪያድግ ድረስ ደስታ ቋሚ ማንነቱ ነው። መደሰት፣ ማመስገን ተፈጥሯዊ ዝንባሌያችን ነው። የምንፈልገው ነገር ላይ አተኩረን በምስጋና እና በደስታ ውስጥ ስንሆን የኤሌክሮ ማግኔቲክ ፊርማችንን እናስተካከላለን በእዛም ከምንፈልገው ነገር ጋር እንገጣጠማለን። ባለንም በቀብድም እናመስግን እንደሰት! 5. ህጻን አይደክመውም። አንዳንዴ 11 ሰአት ወይም 12 ሰአት ወደቤት ለምንድነው የምሄደው ብዬ ሳስብ ደክሞኛል ብዬ ለእራሴ ስለነገርኩት ወይም ሌላ ሰው ወደቤቱ ስለገባ ነው ብዬ አስባለሁ። ህጻናትን ካስተዋላችሁ አለመድከማቸው አይናችንን ያደክመናል እንጂ ብዙም አይደክሙም። በቃ ምናልባት ጥቂት ቢያርፉ እንጂ እንደኛ ደከመኝ ምናምን አያውቁም። Real hustler ናቸው። አዋቂዎች እኛ ካልሰሰትነው በቀር ልክ እንደህጻን የማያልቅ እንደወንዝ የሚፈስ ሃይል እና ጉልበት አለን።  ደከመኝ በሂደት የተማርነው ነገር እንጂ እኛ አዋቂ ሰዎች ልክ እንደህጻን ብርቱዎች ነን። በቀጣይነት የምንተጋ እንሁን! መልካም የህጻንነት ሳምንት
Показати все...
18:37
Відео недоступнеДивитись в Telegram
WOW.. የአመቱ ምርጥ ቴስቲሞኒ 👏👏👏👏
Показати все...
381.59 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የአልፋ ጥቅል ስልጠና       📍በጅማ ከተማ የኃያል ሂደት ስልጠና በአማርኛ የሚሰጥበት ቦታ፦   - ርብቃ ሆቴል ሐምሌ 05, 06,07/2016 ዓ.ም 📍The Alpha Package Training in Amharic language will be held at Rebika Hotel in Jimma on July 12, 13 and 14, 2024. ✨ባለራዕይ፣ ቅን፣ ጤናማ እና ባለፀጋ ትውልድን መፍጠር!✨ 📍አዲስ አበባ፣ ቦሌ  ክፍለ-ከተማ፣ ወረዳ 3 ሽልም ህንፃ 4ተኛ ፎቅ                                                             ✨Creating Visionary,Genuine,Healthy and Wealthy Generation!✨ 📍Addis Ababa ,Bole Sub -City ,Woreda 3 , Shilem Building, 4th floor 🌐 www.alphagenuine.com ☎️ +251930020395 Bole Branch +251903441155 Adama Branch +251954872508 or +251942137733 Mekelle Branch
Показати все...
00:13
Відео недоступнеДивитись в Telegram
3.94 MB
ወሬ...😏 ችግር የሚቀረፈው በስራ ነው! በወሬ የሚቀረፍ ችግር የለም። ችግራችሁን እየዞራችሁ ለሰው ማውራቱ ጥቅም የለውም ሁሉም ሰው ችግር አለው በህይወቱ ፈተና የሌለበት ችግር ያላጋጠመው ሰው በዚህ ምድር የለም። ማውራታችሁን ትታችሁ Action❗️ ድርጊት ውሰዱ። ስለ ችግራችሁ ከምትወዱስ ሰው ጋር በየቀኑ እየተገናኛችሁ 1 ወር ብታወሩ በ30ኛው ቀን ምን እንደሚፈጠር ታውቃላችሁ? ምንም!🤷 ድርጊት ለመውሰድ የሚፈራና ቆራጥ ያልሆነ ሰው ችግሩን ከመቅረፍ ይልቅ ችግሩን ለሁሉም በማውራት ለትንሽ ጊዜ ቀለል እንዲለው ይመኛል። Stop! እስካሁን ያወራችሁት ይበቃል ከዚህ በኋላ ስለችግራችሁ ለሰው አታውሩ። አሁን ጀምራችሁ መፍትሄው ላይ አተኩሩ ድርጊት ውሰዱ! ቻይኖች ምን ይላሉ..
Talk 🗣️ doesn't cook Rice🍚
"ወሬ ሩዝ አያበስልም!" እንደማለት ነው። ማውራት አቁም! ማድረግ ጀምር! ............
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Jack Ma the richest man in China said, "If you put the Banana and Money infront of a monkey. The monkey will choose Banana because the monkey don't know that money can buy alot of Bananas." In fact, if you offer WORK and BUSINESS to people, they will choose to WORK because most people don't know that a BUSINESS can make more money than salary. One of the reason the poor are poor is because the poor are not trained to recognise the entrepreneurial opportunity. They spend alot of time in school and what they learn in school is work for a salary instead of working for themselves. Profit is better than wages because wages can support you, but profits can make Credit:- From social Media.
Показати все...
ዘመኑ መረጃ ሞልቶ የተትረፈረፈበት፤ ዕውቀት እንደጎርፍ የሚጎርፍበት ጊዜ ነው ብንል አልተሳሳትንም፡፡ ጊዜው ራሱ የእውቀት ዘመን (Knowledge Era) አይደለ የሚባለው፡፡ የሆነው ሆኖ መረጃው በየቦታው ቢንፎለፎልም፤ ዕውቀት በየጥጋጥጉ ቢበቅልም የሰው ልጅ የሚፈልገውን የእርካታና የሰላም፤ የደስታና የፍቅር ሕይወት መምራት አልቻለም፡፡ መንፈሳዊ እሴቶቻችን ማለትም የአዕምሮ ሰላም፣ የልብ ፍቅር፣ የነፍስ ደስታ፣ እውነተኛ እርካታ ቋሚ ያልሆኑት መሆን ስለማይችሉ ሳይሆን የዘመኑ ሰው ከቁሳቁስ መረጃውና ከዓለማዊው እውቀቱ ባሻገር ሰዋዊ የሆነውን መንፈሳዊውን ጥበብ መጨበጥ ስላልቻለ ነው፡፡ ብዙ ሰው በዘመን አመጣሹ መረጃ ተወስዷል፡፡ ጎርፉ ቀላል አይደለም፤ ብዙዎቻችን የመረጃው ጎርፍ፣ የዕውቀቱ ደራሽ አደጋ እንዳያስከትልና ጥቅም ላይ እንዲውል ቦይ ሰርቶ፣ መስኖ አበጅቶ ከመጠቀም ይልቅ ሁላችንንም ጠራርጎ እንዲወስደን ተመቻችተንለታል፡፡ ቦታ አልያዝንም፡፡ የመጣው ወጀብ እያስተናገደን ነው፡፡ መደገፊያም ሆነ ጎርፉን ማቆሚያ ታኮ ሃሳብ አላዘጋጀንም፡፡ ፍሬን መያዝ የለም፤ ነዳጅ መርገጥ ብቻ!! ረጋ ብሎ ማሰብ ጠፍቷል፡፡ ለምን፣ እንዴት ብሎ መጠየቅ አልተለመደም፡፡ ዞር ብሎ ማሰብ የፋራ ሆኗል፡፡ ከመገንዘብ ይልቅ ገንዘብን ማስቀደም ባህላችን አድርገነዋል፡፡ መረጃውን ዕውቀት የሚያደርግ፤ ዕውቀቱን ወደጥበብ የሚለውጥ ብልህ ትውልድ ተመናምኗል፡፡ በስሜት የሚነጉድ፣ በደመነፍስ የሚወነጨፍ፣ በስማ-በለው የሚነጉድ፣ በመንጋ የሚያስብ ትውልድ ቦታውን እየተረከበ ነው፡፡ ሰውን መከተል እንጂ እውነትን መከተል ኋላቀር እየሆነ ነው፡፡ ጓዶች ጉድ ሆነናል! መረጃ ስለአንድ ጉዳይ ወይም ስለሆነ ነገር ያለን ተያያዥና ትርጉም የሚሰጥ የጥሬ ሃቆች ስብስብ ነው፡፡ ዕውቀት ያንን መረጃ ለመጠቀም ወይም በተግባር ወደመሬት ለማውረድ የሚያስችል የአዕምሮ ብቃት ነው፡፡ ጥበብ ደግሞ ዕውቀቱን አስፍቶ ለአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጅ በሙሉ እንዲውል ለበጎ ነገር ብቻ የመጠቀም የቀናነት፣ የመልካምነትና የመንፈሳዊነት አቅም ነው፡፡ ጥበብ የሌለው ዕውቀት ዓለምን ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም፡፡ ዕውቀትን ሰዋዊ ስሜት እንዲሰጥ፣ ለብዙሃኑ መጥቀም እንዲችል የሚያደርገው ጥበብ ነው፡፡ እንግሊዛዊው ሙዚቀኛ ማይልስ ኪንግተን ስለእውቀትና ስለጥበብ ልዩነት ሲናገር፡- ‹‹ዕውቀት ማለት ቲማቲም ፍራፍሬ ስለመሆኑ ማወቅ ነው፡፡ ጥበብ ማለት ደግሞ ቲማቲሙን ከሰላጣ ጋር አብሮ አለማስቀመጥ ነው፡፡ (“Knowledge is knowing that a tomato is a fruit. Wisdom is not putting it in a fruit salad”)›› ይላል አዎ! ዕውቀትህን ምን ላይ እንደምታውለውና መቼ እንደምትተገብረው ካላወቅክ ጥበብ የለህም ማለት ነው፡፡ ዛሬ ብዙ ሰዎች እውቀት አላቸው፡፡ ነገር ግን ዕውቀታቸው ውስጥ ቀናነት የለም፡፡ የብዙዎቹ ዘመነኞች ዕውቀት ውስጡ ሌሎችን የሚጎዳ የስግብግብ ፖለቲካ መርዝ ሞልቶታል፡፡ ይሄ ዕውቀት ጥበብ ስለሌለው ዓላማው ክፋት ነው፡፡ ለሆዳቸው ያደሩ ከርሳም አዋቂዎች ለነሱ ጥቅም ብቻ የሚውል ግማሽ እውቀት ይሰራሉ፡፡ በክፋት ዕውቀት የተሞሉ ሊቅ ተብዬዎች ሳይንሱን ያሳንሱታል፡፡ ፍልስፍናውን ይልፈሰፈሱበታል፤ ህጉን ፍርደገምድል ያደርጉታል፡፡ ሃይማኖቱን ያምታቱበታል፡፡ እውነተኛ ጥበብ ከውጫዊው ሕይወት የበለጠ ውስጣዊውን ሕይወት ውብ ያደርጋል፡፡ ብዙዎቻችን ለውጫዊው ሕይወታችን ስለምንሮጥ ውስጣችንን ማስዋብ አልቻልንም፡፡ ሰው መንፈሱን ሳይገዛ ቁሳቁስ ሊገዛ የሚችል ገንዘብ ቢያከማች የዓይን አምሮቱን እንጂ ነፍሱን አያስደስትም፡፡ የዓይን አምሮት ውጫዊ ነው፤ የነፍስ አምሮት ግን ውስጣዊ ነው፡፡ በጥበብ እንድትበለፅግ፣ ሕይወትህ እንዲያምር፤ አዕምሮህ የሰላም ባለቤት እንዲሆን ለውስጣዊው ሐብትም ሩጥ! የእንጀራ ዕውቀት ብቻ የትም አያደርስህም!! ጥበበኛ መሆን ማለት መንፈሱን ያበረታ፣ ስሜቱን የገዛ፣ ደመነፍሱን የተቆጣጠረ ቀና አዋቂ ሰው መሆን ማለት ነውና! ወዳጄ ሆይ... ሩሚ ‹‹ትናንት ጎበዝ ስለነበርኩ ዓለምን ለመለወጥ እፈልግ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ብልህ ስለሆንኩ ራሴን እየለወጥኩ ነው፡፡›› የሚለው ወዶ አይምሰልህ፡፡ ሩሚ ይሄን ያለው ዓለምን ለመለወጥ ራስን መለወጥ ቀዳሚ ስራ መሆኑን ሲያሰምርበት ነው፡፡ ውስጣዊ ለውጥህ ውጫዊው ሕይወትህንም ይለውጣል እያለህ ነው፡፡ ለውጥህ ደግሞ ሊሳካ የሚችለው ባለህ ዕውቀት ሳይሆን በጥበብህ ነው፡፡ ዕውቀትህን በጥበብ ከያዝከው ከራስህ አልፈህ ዓለሙን ትለውጣለህ፡፡ ጥበብ በዕውቀት፣ በልምምድ፣ በማሰብ ሃይል እውን የሚሆን ስለሆነ በሰፊው መንፈሳዊ ጥበብ ለመስፋት ተጋደል እንጂ በዓለማዊው ዕውቀት ብቻ ጠብበህ በአጭር አትቅር! ብልጥ ሳይሆን ብልህ ሁን! አርባአራት ነጥብ! ቸር ጥበብ! ደግ ዕውቀት! ይህን ፅሁፍ አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ Share.. መልካም ቀን ይሁንላቹ
Показати все...
1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Dear Tsinukal Sintayehu, Congratulations on your promotion as National Team Builder (NTB). You really deserve it! BTSC hopes you will perform even better in the future. ✨Alpha our State for Significance! ✨ 📍Addis Ababa ,Bole Sub -City ,Woreda 3 , Shilem Building, 4th floor 🌐 www.alphagenuine.com ☎️ +251930020395 Bole Branch +251903441155 Adama Branch +251954872508 or +251942137733 Mekelle Branch
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ውድቀትን_የምታስተናግድበት_ዘዴ_ይኑርህ የሰር አሌክስ ፈርጉሰን የስኬት ቀመሮች እነዚህ ናቸው፦ 1- አደጋዎችን ለመጋፈጥ ተዘጋጅ 2- በቀላሉ መርካትን አስወግድ 3- ተለማመድ 4- መስዋትነቶችን ክፈል 5- ውድቀትን የምታስተናግድበት ዘዴ ይኑርህ 6- ጉልበትን አሳይ 7- በምሳሌ ምራ 8- ራስህን ሁን 9- አዎንታዊ አመለካከት ይኑርህ 10- ታላላቆችን አጥና የቱን ወደዳችሁት?  ሀሳብ አስተያየታችሁን ስጡን፤
Показати все...
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከመራራነት ውጣ! ሙሉ ሃላፊነትን ውሰድ:- “ስለ ህይወትህ በግልህ ሃላፊነትን መውሰድ አለብህ፡፡ በዙሪያህ የሚከናወነውን ነገር፣ የአየሩን ጸባይና ነፋሱን መቆጣጠርና መለወጥ አትችልም፣ ራስህን ግን መለወጥ ትችላለህ” – Jim Rohn ሰዎችን ይቅር በል:- “ደካማው ይቅር ሊል አይችልም፡፡ ይቅርታ ማድረግ የብርቱዎች ባህሪይ ነው” - Mahatma Gandhi ልምምዶችህን ለመልካም ለውጣቸው :- “ሌሎች ተራ ሕይወትን ይኑሩ፣ አንተ ግን አትኑር፡፡ ሌሎች ባልሆነ በሆነ ይጨቃጨቁ፣ አንተ ግን አታድርገው፡፡ ሌሎች በጥቃቅን ጉዳቶች ያልቅሱ፣ አንተ ግን አታልቅስ፡፡ ሌሎች የሕይወታቸውን ጉዳይ ለሰው አሳልፈው ይስጡ፣ አንተ ግን አትስጥ” – Jim Rohn
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.