cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

🎞📺🎥• የኔ ህይወት •♫•♬•

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
408
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Repost from N/a
አሉ ደሞ ስግጥናን እንደ አራዳነት ተቀብለው ስለ ሴት አለባበስ የሚያወሩ እንትና እንዲ ለበሰች እንትና እርቃኗን ምናምን ወንድሜ ለመሆኑ ስለ ሀመር ታውቃለህ እነሱን ብታይ ምን ልትል ነው ......... Bro ለምን እንደ ሄዋን እርቃኗን አትሄድም ከፈለገች ካስደሰታት እሷን ካልደበራት ኑሮህን ኑር አይምሮህን ብትከፍተው እኮ ከዚህ በላይ ብዙ የሚያሳስብህ ነገሮች አሉ አንተ ግን ደፍነኸዋል ያልበላህን አትከክ 🙌🏿❗️ @Yenu_yene_bicha
Показати все...
ክብርሽን እያሰብሽ..! ፨፨፨፨////////፨፨፨፨ መጪ ሁሉ አላፊ ነውና "ምን ሊያደርገን ነው" የተባሉ ብዙ አስከፊ ጊዜያት አልፈዋል፤ ቸርነት ተደርጎልን ክፋቱን ተሻግረናል፤ መከራውን ተወጥተናል። ብዙ የደስታ፣ የሃሴት፣ የማግኘት ጊዜያትም አልፈዋል። በልጅነት አዕምሮ፣ በወጣትነት እሳቤ የሚያረጅ የለም። እድሜን ተከትሎ የሚመጣ እውቀትና ማስተዋል አለ። የዛሬ ልጅነትሽ፣ የዛሬ ወጣትነትሽ ምንም እንኳን መማሪያሽ ቢሆን እያወቁ ተሳስቶ ለመማር መሞከር ግን ትልቅ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀርም። የዛሬ ተግባርሽ ነገም ይከተልሻል፤ የቀረበሽ ሁሉ ታሪክነቱን ለመቀበል ቢሞክር እንኳን ላንቺ ግን በእውቀት አስበሽ ያደረግሽው ነውና በእራስሽ ማዘንሽ አይቀርም። ነገር ግን ይህም ድርጊትሽ ያልፍና ወይም ያኮራሻል ወይም ያሳፍርሻል። አዎ! ጀግኒት..! ዛሬ የተዝናኑብሽ ነገ ይፈርዱብሻል፤ ዛሬ ያሞገሱሽ ነገ ይዘልፉሻል፤ ዛሬ ያበረታቱሽ ነገ ይሳለቁብሻል፤ ያዝኑብሻል። እራስሽን ለማንም ግልፅ ማድረግሽ፣ ገሃድ ማውጣትሽ ችግሮችሽን አይቀርፍም፤ ብዙ ሃሳብ መቀበል ከጭንቀት አያወጣሽም። ተግባርሽ ማንነትሽን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ቦሃላ የፈለግሽን ነገር እስከፈለግሽው ልታወሪ፣ ልታስተባብይ፣ ምክንያት ልትደረድሪ ትችያለሽ ካደረግሽው ነገር፣ ከፈፀምሽው ተግበር፣ ሆነሽ ከታየሽው ነገር በላይ ግን በፍፁም ተቀባይነት ሊያገኝ አይችልም። አዎ! ክብርሽን እያሰብሽ፣ ሴትነትሽን ጠብቂ። አብዝተሽ ለድርጊቶችሽ ተጠንቀቂ፤ የማያልፍ ጊዜ የለም። የዛሬ መጥፎ ድርጊትሽ የሚያሳቅቅሽ፣ ሰው ፊት ለመቆም የሚሸማቅቅሽ ጊዜ ይመጣል። ትማሪያለሽ፣ ታድጊያለሽ፣ ትለወጪያለሽ "እንዴት እንደዚ አደርጋለሁ? ምን ሆኜ ነው?" የምትይበት ጊዜ ይመጣል። ደግሞ ሩቅ አይደለም በቅርብ ይከሰታል። ምን ስላደረግሽ ይመስልሻል ብዙ ተመልካች ያገኘሽው? በብዙዎች ድጋፍ የተቸረሽ? ብዙዎች የሚወዱሽ? ትልቅ ታሪክ ስለሰራሽ? ሃገርን ስላስጠራሽ? ቤተሰብሽን ስላኮራሽ? በፍፁም አይደለም። ዋናው ምክንያት ትኩረትሽ አንቺ ሳትሆኙ ተመልካቾችሽ ስለሆኑ ነው። እያንዳንዱ ተግባርሽ ስህተትና እንደማይጠቅምሽ ብታውቂም ጭብጨባውና ጩሀቱ ግን ትክክል እንደሆነ እንድታስቢ ያደርግሻል። የስራሽ ትክክለኛነት ማረጋገጫ ውጫዊው ጭብጨባ ሳይሆን የውስጥ ሰላም፣ የውስጥ እርካታ ነው። ተደነኩኝ፣ ተወደድኩኝ፣ ተሞገስኩኝ ብለሽ የሰውነትሽን ገደብ፣ የማንነትሽን ልኬት አትለፊ። ትልቁን የሴትነት ክብር አለሽና ክብርሽን በስስት ጠብቂው፤ አስቢው። አዎ! ጀግናዬ..! እልፍ አዕላፍ ተከታይ፣ ቁጥር አልባ ተመልካችና አድናቂ ቢኖርህ ስራህ ልክ የሚሆነው ለገዛ ህሊናህ ነው። ነገ የኋሊት ስትመለከት የምትቆጭበት ስፍራ አትገኝ፤ የሚያሳፍርህን ስራ አትስራ፤ ልብህ እያወቀው ለማስመሰል አትሳሳት፤ በማይሆን ተግባር እውቅናን አታግኝ። ማምሻም እድሜ ነውና በቻልከው መጠን ነገህን እያሰብክ ዛሬህን በሚያስደስትህና መልካም በሆነ ተግባር ላይ አሳልፍ።
Показати все...
መፍትሔው የችግሩ እውቀት ነው! ፨፨፨፨፨፨፨//////////////፨፨፨፨፨፨ በቅድሚያ ችግሩን አሳደህ አግኘው፣ እወቀው፤ በመቀጠል መፍትሔውን ፈልግ። አስር አይነት መፍትሔ አንድን ያልታወቀ ችግር አይፈታውም። ችግርህን ሳታውቅ ብዙ አማራጭ መፍትሔዎችን ብትፈልግ በፍፁም ልትቀርፈው አትችልም። ያለበትን ችግር ምንንነት ያወቀ አንድ ሰው ከመፍትሔው ለመድረስ ከግማሽ መንገድ በላይ እንደተጓዘ ይቆጠራል። ስለታመምክ የምትወስደው መድሃኒት ሁሉ አያድንህም፤ ለመዳን የህመምህ አይነት መታወቅ ይኖርበታል። ብዙ ስለደከምክ ሃሳብህን አታሳካም፤ የሃሳብህን ምንንነት ማወቅ፣ መረዳት ግድ ይልሃል። አዎ! መዳረሻ የሌለው ሰው በፈለገው መንገድ መጓዝ ይችላል ምክንያቱም ማረፊያውንና የሚያስኬደውን መንገድ አያውቅምና። እንዲሁ ችግሩን ያላወቀ ሰው ምንም እንኳን ብዙ አማራጭ መፍትሔዎችን ቢሞክርም ትክክለኛውን መፍትሄ ሊያገኝ አይችልም። ከየትኛውም መፍትሔ በፊት የቸግሩ ምንጭ፣ የችግሩ ምንነት መታወቅ አለበት። ሃገራዊ ችግር ይሁን፣ ግላዊ ችግር ምንም የተፈለገው መፍትሔ ቢሞከር መሰረቱ እስካልታወቀ ከድካም ውጪ ትርፍ አልባ ነው። አዎ! ለመታረቅ የፀቡ መንስዔ መታወቅ አለበት፣ ለመስማማት ልዩነት ፈጣሪ ሃሳቦች ግልፅ ሊሆኑ ይገባል፤ ወደፊት ለመራመድ የጋራ መግባቢያ ሃሳቦች ይፋ መውጣት አለባቸው። እያንዳንዱ ከባድ ጉዳይ በጥቃቅን ሃሳቦች የተዋቀረ ነው። የመፍትሔ ሰው ነው የሚባል ሰው መፍትሔ በመዘርዘር የሚታወቅ ሰው አይደለም። በምትኩ ችግሮችን በመፈልፈል፣ መንስዔያቸውን በመለየት የሚታወቅ ነው። አዎ! ጀግናዬ..! መፍትሔው የችግሩ እውቀት ነው። ችግርህን ካላወክ መፍትሔውን እንዳታስበው፤ ችግሩን ከተረዳህ ግን በእርግጥም መፍትሔው በእጅህ ነው። የፍቅር ህይወትህ ዋናው ችግር ምንድነው? መንሰኤውስ? የቤተሰብህ ትልቁ ችግር ምንድነው? መነሻውስ? የእራስህ ችግር ምንድነው? ምክንያቱስ? እነዚህን ጥያቄዎች ከመለስክ መፍትሔው ሊጠፋብህ አይችልም። ችግርህን ለመቅረፍ ችግርህን እወቅ፤ ወደፊት ለመጓዝ መሰናክሎችህን አስቀር፤ ህልምህን ለማሳካት ሰበበኛ ሃሳቦችህን ተሻገር። ውብ ምሽት ይሁንልን! @felasefa
Показати все...
🌿መኖርን ለምን መረጥክ ? የሰው ልጅ የመሞቱን ያህል መኖሩን አይፈራውም። እውነት ሳስበው ያስገርመኛል። መንግስተ ሰማይ እንደሚገቡ እርግጠኛ እንደሆኑ የሚሰማቸው ሰዎች እንኩዋን ሞትን አብዝተው ይፈሩታል። መኖር እኮ እንደውም ያስፈራል። ምክንያቱም መሞታችን አንዴ እኛነታችን የሚቋረጥበት ሲሆን መኖራችን ግን ሁሌም በኛነት ጥያቄ ውስጥ ተይዘን የምንባዝንበት ነው። ትልቁ ጥያቄ ታድያ ይሄ ነው፦ ከመሞት ይልቅ መኖርህን ለምን መረጥከው? ጠዋት ከእንቅልፍክ ስትነሳ ምንድነው ያስነሳህ? ምንድነው እንድትኖር ያደረገህ ?ለምንስ መኖርክ ይሄን ያህል ዋጋ ተሰጠው? አየህ ይሄንን ነው መመለስ ያለብህ። ለምን ? ስለዚህ መኖርን መርጠህ እየኖርክ እስካለህ ድረስ የተሻለውን ምርጡን እና ትልቁን ህይወት ኑር። አለበለዚያ ግን መኖርህም መሞትህም ዋጋ የለውም። የምትኖረው ኖረህ ለማለፍ ነው ወይስ ሌሎችን ለማኗኗር ነው? አብዛኛው ሰው ኗሪ ሳይሆን አኗኗሪ ነው። የህዝብ ቁጥርን ሚጨምር ብቻ አለ። ስለዚህ ስትኖር ለምን? እድሜ ሲጨመርልህ ለምን ? አለዚያ ብዙ አበርክተው መሞት ሚፈልጉ አሉ ለነሱ ቦታ መልቀቅም ፅድቅ ነው። ስለዚህ የዘመንህ ጥያቄ ይሁን። ለምን እኖራለው ? ምን ልሰራ ? ምን ላበረክት? ምን ልሰጥ ነው የምኖረው ? ብለህ እራስህን ጠይቅ። አለበለዚያ ግን ህይወት ላንተ ትርጉም የላትም ስለዚህ ሞትን አትፍራው። ምክንያቱም ለመኖር ሚያጓጓ ነገር የለህም። 💫 https://t.me/felasefa 💫
Показати все...
🎞📺🎥• የኔ ህይወት •♫•♬•

ፍቅረኛዬን አንድ ጥያቄ ጠየቅኳት፡፡ እኔ ፡ ይህንን የርቀት ግንኙነታችንን ምን ብናደርገዉ 1:00 ●━━━━━━─────── 2:00 ⇆ㅤㅤ ㅤ ◁ㅤㅤ❚❚ㅤㅤ ▷ㅤ↻🎸🎵🎶? እሷ፡ እኔንጃ! እስኪ አንተ ንገረኝ? እኔ፡ እኔንጃ! አንቺ ንገሪኝ እንጂ? እሷ፡ በቃ ተወዉ! እኔ፡ አንቺ ራስሽ ተይዉ! እሷ፡ እንደዚህ ተራርቀን እንኳን መጨቃጨቅ

መላውን ዓለም ከመጨበጥ ይልቅ ራስን መጨበጥ የተሻለ ነው ምንጭ ፦ ህያውነት ፫ (ኦሾ) ተርጓሚ ፦ ሀብታሙ ተስፋዬ ተስፋሁን ምትኩ ሰው ሲወለድ እንደ ዘር ሆኖ ነው - እንደ አንድ እምቅ አቅም፡፡ ሲወለድ ልከኛ ሆኖ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ልዩ ነው - ምክንያቱም በመላው ህልውና ውስጥ ሰው ብቻ ነው አንድ አቅም ሆኖ የሚወለደው፤ ሌሎች እንስሳት ልከኛ ሆነው ነው የሚወለዱት፡፡ አንድ ውሻ ሲወለድ ውሻ ሆኖ ነውና መላ ህይወቱንም እንዲያ ሆኖ ይኖራል። አንድ አንበሳ ሲወለድ አንበሳ ሆኖ ነው፡፡ ሰው ሲወለድ ግን ሰው ሆኖ አይደለም፡፡ ሰው ሲወለድ እንደ ዘር ሆኖ ነው። ሰው ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። ሰው የወደፊት ተስፋ አለው! ሌሎች እንስሳት ግን ተስፋ የላቸውም፡፡ ሁሉም እንስሳት ሲወለዱ በደመነፍስ ፍፁም ሆነው ነው፡፡ ሰው ብቸኛው ፍፁም ያልሆነ እንስሳ ነው። ስለዚህም በሰው ላይ እድገት፣ ዝግመተ - ለውጥ ይቻላል። ትምህርት በእቅምና በልከኝነት መካከል ያለ ድልድይ ነው። ትምህርት በዘር መልክ ራሳችሁን እንድትሆኑ ያግዛችኋል፡፡ በተራ ትምህርት ቤቶች፣ በኮሌጆችና በዩኒቨርስቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው ትምህርት አይደለም። በእነዚህ ተቋማት የምታገኙት ትምህርት ጥሩ ስራ፣ ጥሩ ገንዘብ እንድታገኙ የሚያደርጋችሁ ብቻ ነው:: እውነተኛ ትምህርት አይደለም፤ ህይወትን አይሰጣችሁም። በቃ የኑሮዋችሁን ደረጃ ከፍ ቢያደርገው ነው፤ ነገር ግን የተሻለ ኑሮ የተሻለ ህይወት አይደለም፤ ሁለቱ አንድ አይደሉም። በዓለም የሚሰጠው ትምህርት ተብዬ ነገር ዳቦ እንድታገኙ ብቻ የሚያዘጋጃችሁ ነው። ኢየሱስ እንዳለው «ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም::>> ዩኒቨርሲቲዎቻችሁ ደግሞ ይህን ነው እያደረጉ ያሉት - በተሻለ፣ በቀለለ፣ በተመቸ፣ ጥረት፣ ድካም በሌለበት መንገድ ዳቦ እንድታገኙ ያግዛችኋል። ስራቸው በሙሉ እናንተን ዳቦና ቅቤ እንድታገኙ ማዘጋጀት ነው፡፡ ይህ አይነቱ ትምህርት በጣም፣ በጣም ኋላቀር ነው:: ለህይወት አያዘጋጃችሁም፡፡ ስለዚህም ብዙ ሮቦቶች ሲረማመዱ ታያላችሁ:: እንደ ተላላኪዎች፣ የጣቢያ ተቆጣጣሪዎች፣ ዋና ሰብሳቢዎች ብቃት አላቸው:: ፍፁማን ናቸው፣ ጥበበኞች ናቸው:: በጥልቀት ብትመለከቷቸው ግን ለማኞች እንጂ ሌላ ምንም እንዳልሆኑ ትረዳላችሁ፡፡ የህይወትን እንዲት ቅንጣት እንኳን አልቀመሱም፡፡ ህይወት ምን እንደሆነ፣ ፍቅር ምን እንደሆነ፣ ብርሃን ምን እንደሆነ አያውቁም፡፡ ስለ እግዚአብሄር ምንም አያውቁም፣ ህልውናን አልቀመሱም፣ እንዴት መዝፈን፣ መደነስ፣ መደሰት እንዳለባቸው አያውቁም:: የህይወትን ሰዋሰው የማያውቁ መሀይማን ናቸው። አዎ፣ ከሌሎች የበለጠ ያገኛሉ፤ ከሌሎች የበለጠ ብልጣ ብልጦች ናቸው፤ በስኬት መሰላል ከፍ ብለው ይወጣሉ - በውስጣቸው ግን ባዶ፣ ምስኪኖች ናቸው፡፡ ትምህርት ውስጣዊ ብልፅግናን ያጐናፅፋል፡፡ የበለጠ መረዳ መስጠት በጣም ኋላቀር የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ነው። ኋላ ቀር ነው ያልኩት በፍርሃት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው፤ ካልተማርኩ በህይወት መቆየት አልችልም፣ በሚለው አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው። ሗላቀር ነው ያልኩት በውስጡ ነውጥን ስላዘለ ነው፤ ውድድርን ያስተምራችሗል፣ ምኞታም ያደርጋችኋል። ሌላ ምንም ሳይሆን ሰዎች እርስ በርስ የሚጠላሉበት የውድድር ዓለም ለመፍጠር የሚደረግ ዝግጅት ነው። ስለዚህም ዓለም የእብዶች መኖሪያ ሆናለች። በዚህ ሁኔታ ፍቅር ሊወጣ አልቻለም። አንዱ የሌላኛውን ጉሮሮ በሚበጥስበት በዚህ ነውጠኛ፣ ምኞታም የውድድር ዓለም ውስጥ እንዴት ፍቅር ሊታይ ይችላል? ሗላ ቀር ነው ያልኩት «በደንብ ካልተማርኩ፣ በቂ ከለላ ካላገኘው፣ ደህና መረጃ ካልያዝኩ በህይወት ፈተና ውስጥ አሸናፊ አልሆን ይሆናል>> በሚል ፍራቻ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው። ህይወትን እንደ ትግል ብቻ ነው የሚመለከታት፡፡ እኔ ትምህርትን የማየው ህይወትን እንደ ትግል ሳይሆን እንደ ደስታ ሲቀርፅ ነው፡፡ ህይወት ውድድር ብቻ መሆን የለባትም፣ ደስታ ጭምር እንጂ፡፡ ትምህርት በዓለም ላይ ከሚገኙ ዘፈን፣ ዳንስ፣ ቅኔ፣ ሙዚቃ፣ ስዕል፤ ዛፎች፣ አዕዋፋት፣ ሰማይ፤ ፀሃይ፣ ጨረቃ እና ሌሎች ነገሮች በሙሉ ሊያዋህዳችሁ ይገባል፡፡ ትምህርት ራሳችሁን እንድትሆኑ ሊያዘጋጃችሁ ይገባል። አሁን ግን አስመሳዮች እንድትሆኑ እያዘጋጃችሁ ነው፤ ሌሎችን እንዴት መምሰል እንዳለባችሁ እያስተማራችሁ ነው፡፡ ይህ ትምህርት ማሳት ነው፡፡ ትክክለኛ ትምህርት ራሳችሁን በእውነተኛ መንገድ እንዴት እንደምትሆኑ ያስተምራችኋል። እናንተ የተለያችሁ ናችሁ። እናተን የሚመስል ማንም የለም ፡ ወደፊትም አይኖርም። ይህ እግዚአብሄር ያጐናፀፋችሁ ታላቅ በረከት ነው። ይህ የእናንተ ክብር ነው! ልዩ መሆን ነው፡፡ አስመሳይ አትሁኑ፤ የካርቦን ቅጂዎች አትሁኑ። እናንተ ትምህርት የምትሉት ነገር ግን ይህን እያደረገ ነው፡፡ የካርቦን ቅጂዎችን ይፈጥራል፤ እውነተኛ መልካችሁን ያጠፋል። <<ትምህርት>> የሚለው ቃል ሁለት ትርጉሞች አሉት፤ ሁለቱም ደግሞ ውብ ናቸው። አንደኛው ትርጉሙ ተግባር ላይ ባይውልም በደንብ ይታወቃል- አንድ ነገር ከውስጣችሁ ማውጣት። <<ትምህርት» ማለት በውስጥ ያለን ማውጣት፣ ውሀን ከጉድጓድ እንደ ማውጣት አቅምን በተግባር ማውጣት ነው። ይህ ግን አልተተገበረም፡፡ ከዚህ ይልቅ ነገሮች ወደ ውስጥ እንዲገቡ እንጂ እንዲወጡ አልተደረገም። ህብረተሰብ እና ታሪክ፣ ሳይንስ እና ሂሳብ ወደ ውስጣችሁ ያንቆረቁርላችኋል። እናም ፓሮቶች ትሆናላችሁ። ልክ እንደ ኮምፒዩተር ይጉሰጉሱባችኋል:: የእናንተ የትምህርት ተቋማት ነገሮች በጭንቅላቶቻችሁ ውስጥ የሚታጨቁባቸው ስፍራዎች ናቸው፡፡ እውነተኛ ትምህርት በውስጣችሁ የተደበቀውን (እግዚአብሔር በውስጣችሁ እንደ ሃብት ያስቀመጠውን) አውጥቶ፣ ገልጦ አንፀባራቂ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል፡፡ ትምህርት ሌላም ትርጉም አለው:: ትምህርት (Education) የሚለው ቃል የመጣው Educare ከሚለው ቃል ነው:: ትርጉሙም ከጨለማ ወደ ብርሃን ማምጣት እንደማለት ነው፡፡ ከጨለማ ወደ ብርሃን ማምጣት በጣም አስፈላጊ ትርጉም አለው፡፡ ዮፓኒሻዶች እንዲህ ይላሉ «ጌታችን ሆይ፣ ከሃሰት ወደ እውነት ምራን፡፡ ጌታችን ሆይ፣ ከሞት ወደ ህይወት ምራን፡፡ ጌታችን ሆይ ከጨለማ ወደ ብርሃን ምራን፡፡» ይህ ነው «የትምህርት» ትክክለኛ ትርጉም፡- ከጨለማ ወደ ብርሃን። ሰው ግን በጨለማ፣ ባለመንቃት ውስጥ እየኖረ ነው:: ሆኖም በብርሃን ምሉዕ መሆን ይቻላል፡፡ ነበልባሉ እዚያ አለ፡፡ ይሁንና መንበልበል፣ ወደ ውጭ መውጣት አለበት፡፡ ንቃት እዚያ አለ፤ ይሁን እንጂ መቀስቀስ አለበት:: ሁሉም ነገር ተሰጥቷችኋል! ስትወለዱ ይዛችሁት መጥታችኋል፡፡ ሰብአዊ አካል ስላለን ብቻ ሰው ነን ማለቱ ስህተት ነው፡፡ ለዘመናት ለብዙ መሳሳቶች መንስኤ የሆነው ይህ አስተሳሰብ ነው፡፡ ሰው ሲወለድ እንደ አንድ እድል፣ ሁኔታ ሆኖ ነው። ይህን የተጠቀሙበት ደግሞ እጅግ ጥቂቶች ብቻ ናቸው - ኢየሱስ፣ ቡድሀ፣ መሐመድ፣ ባሃውዲን። እውን ሰው የሆኑት እጅግ ጥቂቶች ናቸው- በብርሀን ሲመሉ የቀረ ጨለማ አይኖርም፣ በነፍስ ውስጥ የሚተርፍ አለመንቃት አይኖርም- ሁሉም ነገር ብርሃን ሲሆን፣ እናንተ ንቃትን ስትሆኑ... ንቃት፣ ንቃት ብቻ፣ ንፁህ ንቃት... ይህ ያለው ብቻ ምሉዕ ይሆናል። ይሄን ጊዜ ህይወት ቡራኬ ትሆናለች። ትምህርት ከጨለማ ወደ ብርሃን ይወስዳችኋል። @felasefa @felasefa
Показати все...
<<ቅናት ከንጽጽራዊ ባህሪ የሚመነጭ ተረፈ ምርት ነው» ምንጭ ፦ ሁለንተና (ኦሾ) ትርጉም ፦ አባድር ቅናት የሚመነጨው ከንጽጽርና ከውድድር ነው፡፡ ከልጅነታችን ጀምሮ እያነጻጸርንና እየተነጻጸርን መኖር ለምደናል። ስንማረው ኖረናል፡፡ የሆነ ሰው የተሻለ ቤት አለው። ሌላው ውብ የሆነ ሰውነት ይኖረዋል። አንዳንዱ ከሌላው የበለጠ ገንዘብ አለው፡፡ ሌላኛው ደግሞ መስህብ ያለው ሰብእና ባለቤት ነው... እነዚህን ነገሮች እየተመለከትንና ከእነዚህ ሰዎች ጋር እራሳችንን እያነጻጸርን ነው የኖርነው፡፡ አሁንም ይህንን ተነጻጻሪነት እየገፋችሁበት እራሳችሁን በሌላው አካል መመዘኑን ከቀጠላችሁበት ውጤቱ ቅናት ይሆናል። ቅናት ከንጽጽራዊ ባህሪ የሚመነጭ ተረፈ ምርት ነው። እራሳችሁን ማነጻጸር ካቆማችሁ ግን የቅናት ስሜታችሁ ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል። እራሳችሁን እንጂ ሌላኛውን አካል እንዳልሆናችሁ ስትረዱ ንጽጽር የሚባለው ነገር ይቆማል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ተረፈ ምርቶችም ያበቃላቸዋል። እራሳችሁን ከዛፎች ጋር ማወዳደር የለባችሁም። ካወዳደራችሁ ግን እኔስ ለምን አረንጓዴ አልሆንኩም የሚል ከፍተኛ የቅናት ስሜት ይሰማችኋል። አምላክ ለዛፎቹ የቸራቸውን አበባ ስለምን ለእኔ ነፈገኝ የሚል አይነት ስሜት ያድርባችኋል። እራሳችሁን ከወፎች ከወንዞችና ከተራራዎች ጋር ካነጻጸራችሁ ደግሞ ቅናታችሁ ከሚፈጥርባችሁ የስቃይ ጭነት የተነሳ ከነአካቴው መኖር ይከብዳችኋል። እያንዳንዱ ሰው ልዩና ተነጻጻሪ ያልሆነ በመሆኑ ተነጻጻሪነት የማያስኬድ ባህሪ ነው። ሁሉም ሰው ልዩና የማይነጻጸር ነው። ማንም ሰው እራሱን እንጂ ሌላውን መሆን አይችልም፡፡ እራሱን በማያቋርጥ ሁኔታ ከሌላው ጋር የሚያነጻጽር ሰው ከራሱ በቀር ሁሉም ሰው ደስተኛ ይመስለዋል። በጎረቤቱ ግቢ ውስጥ ያለው ሳር እሱ ጋ ካለው በተሻለ እረንጓዴ እንደሆነ ያስባል፡፡ የጎረቤቱ ሚስት ውብ እንደሆነች በማሰብ እራሱን በቅናት ያንጨረጭራል። ጎረቤቱ ግን ይህን ጊዜ እንዴት ከሚስቱ ማምለጥ እንደሚችል እያሰበ ይሆናል። ሁሉም ሰው በሌላኛው ላይ ቀናተኛ ነው፡፡ በቅናት የተነሳ ይህንን የመሰለ ገሃነም መፍጠር ችለናል፡፡ አዛውንቱ ገበሬ ወንዙ ያስከተለውን ጉዳት ለስለስ ባለ ሁኔታ ሲቃኙ ቆዩና «ሂራም» ብለው ጎረቤታቸውን ጠሩት፡፡ ከጎረቤታቸው ያለው ገበሬ እንደደረሰም «ጅረቱ አሳማዎችህን ለቃቅሞ ወስዶዋቸዋል” አሉት፡፡ ጎረቤትየው የቶምሰንን አሳማዎችስ?›› ኣዛውንቱ ‹‹እነሱም በጅረቱ ተወስደዋል፡፡›› ጎረቤትየው «የላርሰንስ?›› አዛውንቱ ««እርሱም እንደዛው» ጎረቤትየው ««አፎይ» ሲል - በረዥሙ ተነፈሰና «እንግዲያውስ ያሰብኩትን ያህል መጥፎ አይደለማ፡፡» ሁሉም ሰው ችግር ውስጥ ከሆነ ጥሩ ስሜት ይፈጠራል። እያንዳንዱ ሰው ያለውን እያጣ ከሆነ ጥሩ ስሜት ይፈጠራል፡፡ ሁሉም ሰው ስኬታማና ደስተኛ ከሆነ ግን ጎምዛዛ የሆነ ስሜት ይፈጠራል። ለምንድን ነው ሌላኛውን የመመልከት ስሜት ውስጥ ሊሰርጽ የቻለው? ምክንያቱም የራሳችሁን ውስጣዊ ቡራኬ እንዲጎመራ አላደረጋችሁትም፡፡ ውስጠታዊው ህልውናችሁ እንዲያብብ አላደረጋችሁትም፡፡ ስለዚህ ውስጣችሁን ስትመለከቱት ባዶነት ይሰማችሁና የእያንዳንዱን ሰው ውጫዊ ገጽታ መመልከት ትጀምራላችሁ። የእራሱን ውስጣዊ ገጽታና የሌላውን ውጫዊ ገፅታ የሚመለከት ሰው ከፍተኛ ቅናት ይፈጠርበታል፡፡ ምክንያቱም የሁሉም ሰው ውጫዊ ገጽታ በፈገግታ የደመቀ ነው፡፡ ሁሉም ከውጭ የሚያሳየው ፈገግታ ከውስጡ የሚካሄደውን ነገር እንዳይታይ ይጋርድለታል፡፡ የሁሉም ሰው ውጫዊ ፈገግታ ውስጠቱ ባዶ እንደሆነ ለሚያስብ ሰው ስቃይን ይፈጥራል፡፡ አንድ በሱፊዎች ዘንድ የሚነገር ታሪክ አለ፡፡ አንድ በስቃይ የተሞላ ህይወትን የሚመራ ሰው ነበር:: ሰውዬው ወደ አምላኩ በሚጸልይበት ወቅት ሁሉ «ሁሉም ሰው ደስተኛ ሆኖ ለምን እኔ ብቻ እሰቃያለሁ? ለምን እኔ ብቻ?» ይል ነበር፡፡ አንድ ቀን ጥልቅ በሆነ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ለአምላኩ ጸለየ፡፡ ‹‹አምላኬ የማንኛውንም ሰው ስቃይ ብትስጠኝ ልቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡ እባክህ! እባክህ ጌታዬ የእኔን ግን ውሰድልኝ፡፡ ከዚህ በላይ ልሸከመው አልችልም›› ሲል ተማጸነ፡፡ ጸሎቱን ጨርሶ እንደተኛ ውብ የሆነ ህልም አየ። በህልሙ ውስጥ አምላክ ሰማይ ላይ ተከሰተና እንዲህ ሲል ተናገረ። ‹‹ስቃያችሁን ሁሉ ወደ ቤተ መቅደሱ አምጡ፡፡» እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ስቃይ የታከተው ስለነበር በተለያዩ ወቅቶች <<የማንኛውንም ሰው ስቃይ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡ የእኔን ግን ውሰድልኝ። ከዚህ በላይ መሸከም አልችልም›› ብሎ ይጸልይ ነበር። እንደተባለው ሁሉም ሰው ስቃዩን በቦርሳ አጭቆ ወደ ቤተ መቅደሱ አመራ፡፡ ባለታሪኩን ጨምሮ ሁሉም ሰው ጸሎቱ አምላኩ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘ በስፍራው ላይ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ነገሰ፡፡ ሁሉም ሰው ከቤተ መቅደሱ ሲደርስ አምላክ እንዲህ ሲል እወጀ፡፡ ‹‹ቦርሳችሁን ከግድግዳው ስር አስቀምጡት ሁሉም ሰው ቦርሳውን አስቀምጦ ከጨረሰ በኋላ አምላክ እንዲህ ሲል በድጋሚ አወጀ፡፡ «አሁን መምረጥ ትችላላችሁ። ማንኛውም ሰው የፈለገውን ቦርሳ መውሰድ ይችላል፡፡›› በጣም አስገራሚው ነገር ቀን ከሌት ሲጸልይ የነበረው ሰውዬ ሌላ ሰው ቦርሳውን እንዳያነሳበት እየተጣደፈ ወደ ቦርሳው ሮጠ። ሁሉም ሰው እንደ ሰውዬው የየራሱን ስቃይ ያጨቀበትን ቦርሳ ፍለጋ ተራወጠ፡፡ እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ስቃይ በድጋሚ ለመሸከም ዝግጁ ነበር፡፡ ምንድን ነበር የተከሰተው? በህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አንዳቸው የሌላቸውን ችግር ስቃይና መከራ ተመለከቱ፡፡ አንዳውም እራሳቸው ከያዙት ቦርሳዎች የሚበላልጡ የሌሎችን ሰዎች በስቃይ የታጨቁ ትልልቅ ቦርሳዎች እንዳሉ ተገነዘቡ፡፡ በተጨማሪ ሁሉም ሰው ከራሱ ስቃይና መከራ ጋር ተላምዷል። የራሱን ስቃይ ማባበልና መቻል ይችላል፡፡ የሌላውን ሰው የመከራ ቦርሳ ቢወስድ ግን ከቦርሳው ውስጥ ያለው አዲስ አይነት መከራ ምን አይነት እንደሆነ አያውቅም፡፡ ምናልባት የባሰም ሊሆን ይችላል፡፡ አላሚው ሰው ከእንቅልፉ ሲነቃ በድጋሚ ጸለየ፡፡ <<አምላኬ ስላሳየኸኝ ህልም አመሰግናለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነቱን ጥያቄ ደግሜ አልጠይቅህም፡፡ የሰጠኸኝን ነገር ሁሉ የሰጠኸኝ ለበጎ ነው። ለዛም ነው የሰጠኸኝ፡፡» የቅናት ስሜት ካለባችሁ በማያቋርጥ ስቃይ ውስጥ ትወድቃላችሁ። የምትቀኑ ከሆነ ሀሰተኛ ትሆናላችሁ፡፡ ማስመሰል ትጀምራላችሁ፡፡ ያልሆናችሁትን መስላችሁ ለመታየት ትሞክራላችሁ፡፡ የሆነ ሰው ጋር ኖሮ እናንተ ጋር የጎደለ ነገር ካለና ነገርዬውን ማግኘት የማትችሉ ከሆነ ከሰው ላለማነስ ብላችሁ የረከሱ ተተኪ ነገሮችን ማበጀት ትጀምራላችሁ። ለቀናተኛ ሰው ህይወት ሲኦል ትሆንበታለች። ስለዚህ ቀናተኛነታችሁ ይጠፋ ዘንድ እራሳችሁን ከሌላው ጋር ማነጻጸር አቁሙ። ይህን ስታደርጉ ያልሆናችሁትን መስላችሁ ለመታየት የምታደርጉትን ጥረትና ሌላውን ለማስመሰል የምታደርጉትን ሙከራ ታቆማላችሁ፡፡ ይኼ ሁሉ ሂደት የተሳመረ የሚሆነው ግን ውስጣዊውን ሀብታችሁን ማሳደግ ስትችሉ ነው። ለማደግ ጣሩ። ይበልጥ እውነተኛ ግለሰብ ለመሆን ሞክሩ። እራሳችሁን አፍቅሩ። ለእራሳችሁ ክብር ስጡ። ይህ ሲሆን የገነት በሮች ክፍት ይሆኑላችኋል። በእርግጥ ወደ በሮቹ ተመልክታችሁ ስለማታውቁ ነው እንጂ እስካሁንም በሮቹ ክፍት ነበሩ። @felasefa @felasefa
Показати все...
እውነተኛ እርካታ ያለው ህይወት ምንጭ ፦ ውስጣዊን ማንነት ማወቅ( ክሪሽና ሙርቲ) ተርጓሚ ፦ ተስፋሁን ምትኩ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳታደርጉ በፀጥታ ተቀምጣችሁ ታውቃላችሁ? ሞክሩት ጀርባችሁን ቀጥ አድርጋችሁ ተቀመጡና አዕምሯችሁ ምን እንደሚሰራ አስተውሉ፡፡ ልትቆጣጠሩት አትሞክሩ፤ ከአንዱ ሃሳብ ወደሌላው፣ ከአንዱ ፍላጎት ወደሌላው መዝለል የለበትም አትበሉ፤ ዝም ብላችሁ ብቻ አዕምሯችሁ እንዴት እንደሚዘል አስተውሉ። ዝም ብላችሁ አስተውሉት፤ የወንዝ ዳርቻዎች በውስጣቸው የሚያልፈውን ውሀ ዝም ብለው እንደሚመለከቱት ተመልከቱት። በሚወርደው ወንዝ ውስጥ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ - ዓሶች፣ ቅጠሎች፤ የሞቱ እንስሳት - ወንዙ ግን ሁልጊዜ እንደተንቀሳቀሰ ነው:: አዕምሯችሁም ልክ እንደዛ ነው፡፡ ዘላለሙን ዕረፍት የለውም፤ እንደ ቢራቢሮ ከአንዱ ወደ አንዱ ይዘላል፡፡ አንድ ዘፈን ስታደምጡ እንዴት ነው የምታዳምጡት? የሚዘፍነውን ሰው ልትወዱት ትችላላችሁ፣ ፊቱ የሚያምር ይሆናል፤ የሚያወጣቸውን ቃላት ትርጓሜ ትከተሉ ይሆናል፤ ከዚህ ሁሉ ጀርባ ግን አንድ ዘፈን ስታደምጡ ምቶቹን በምቶቹ መካከል የሚገኙትን ፋታዎት ነው የምታዳምጡት፣ አይደለም እንዴ? በተመሳሳይ መልኩ ቁጭ በሉና የትኛውንም አካላችሁን ሳታንቀሳቅሱ አዕምሯችሁን አስተወሉት። እጅግ የሚያስደስት ነገር ነው፡፡ እንደ ጨዋታ፣ እንደ መደሰቻ ነገር ካያችሁት አዕምሯችሁ ምንም ጥረት ሳታደርጉበት ራሱ መረጋጋት ሲጀምር ታዩታላችሁ፡፡ ይሄን ጊዜ ፈራጅ ፣ መዛኝ፣ ፈታሽ አይኖርም፡፡ አዕምሮ በፍፁም ርጋታ ውስጥ ሲሆን ደስታ ምን እንደሆነ ትረዳላችሁ። ደስታ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ ወይ? ሳቅ ነው፤ በሆነ ወይም በምንም ነገር መደሰት ነው፤ የመኖርን አስደሳችነት ማወቅ ነው፤ ፈገግታ ነው፤ ሌላውን ያለ ፍርሃት ፊት ለፊት መመልከት ነው፡፡ የሰው ፊት በፅሞና አይታችሁ ታውቃላችሁ? የመምራችሁን፣ የወላጆቻችሁን፣ የአንድን ትልቅ ባለስልጣን፣ የአንድን ምስኪን ሰራተኛ ፊት አይታችሁ ታውቃላችሁ? አብዛኞቻችን የሌላን ሰዉ ፊት ፊት ለፊት ለማየት እንፈራለን፤ ሌሎችም በዚያ መልኩ እንድናያቸው አይፈልጉም- ምክንያቱም ይፈራሉ፡፡ ማንም ሰው ራሱን ማሳየት አይፈልግም። ሁላችንም ተከልለናል፤ በስቃይ፣ በመከራ፣በናፍቆት፣ በተስፋ መጋረጃዎች ተጋርደናል፡፡ ፊት ለፊት አይተዋችሁ ፈገግ የሚሉ ጥቂቶች ናቸው። ፈገግ ማለት፣ መደሰት በጣም አስፈላጊ ነው - ምክንያቱም በልቡ ዜማ የሌለ ህይወቱ ጨለማ ነው:: አንድ ሰው ከአንድ ቤተ መቅደስ ወደሌላው፣ ከአንዱ ባል ወይም ሚስት ወደሌላው፣ ከአንድ መምህር ወደሌላው መሄድ ይችላል፤ ነገር ግን ውስጣዊ ደስታ ከሌለው ህይወት እምብዛም ትርጉም አትሰጠውም፡፡ ይህን ውስጣዊ ደስታ ማግኘት ቀላል አይደለም- ምክንያቱም አብዛኞቻችን ደስታ የራቀን ከላይ ከላይ ብቻ ነው:: ደስታ ማጣት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? ደስታ ማጣትን መረዳት ከባድ ነው - ምክንያቱም አብዛኞቻችን በአንድ አቅጣጫ ወስነን ከልለነዋል። ብቸኛው ትኩረታችን እንዳንረበሽ በደንብ በተደራጁ ፍላጐቶችና ኩራቶች ራሳችንን በአስተማማኝ ሁኔታ ማደራጀት ነው። በመኖሪያ ቤቶችና በትምህርት ቤቶች ውስጥ ያለው ሁኔታም ተመሳሳይ ነው፡፡ መምህራኑ መረበሽ አይፈልጉም፤ ለዛም ነው አሮጌውን መንገድ የሚጠቀሙት - ምክንያቱም አንዱ እርካታ ባጣ ቅፅበትና መጠየቅ በጀመረ ጊዜ ረብሻ ይኖራል፡፡ ይሁን እንጂ መነሳሳት የሚመጣው እውነተኛ እርካታ በጠፋ ጊዜ ብቻ ነው። መነሳሳት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? አንድ ነገር ያለ ማንም ገፋፊነት ለማድረግ ስትነሱ ተነሳሳችሁ ይባላል፡፡ በኋላ የሚመጣው ነገር በጣም ትልቅ የሆነ ወይም የተለየ ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን አንድ ችግኝ ስትተክሉ፣ ቀና ሰዎች ስትሆኑ፣ ሸክሙ የከበደው ሰው ስታዩ ፈገግ ስትሉ፣ ከመንገድ ላይ ድንጋይ ስታነሱ ወይም በመንገድ ላይ የምታገኙትን እንስሳ ስትደባብስ ያን ጊዜ የመነሳሳት ፍንጣቂ ይታያል፡፡ ይህን ፈጠራ የሚሉትን ልዩ ነገር ማወቅ ካለባችሁ የግዙፉን መነሳሳት ጅማሮ ልታዩ የግድ ነው፡፡ ጥልቅ የሆነ አለመርካት ሲኖር ብቻ ዕውን በሚሆነው መነሳሳት ውስጥ ፈጠራ ስሮቹን ዘርግቶ ይኖራል፡፡ አለመርካትን አትፍሩት፤ ከዚሀ ይልቅ ፍሙ ነበልባል እስኪሆን ድረስ ተንከባከቡት፡፡ በሁሉም ነገር አትረኩም- በስራችሁ፣ በቤተሰባችሁ፣ በገንዘባችሁ፣ በስልጣናችሁ፣ በሀይላችሁ - ስለዚህም ለማሰብ፣ ለማወቅ፣ ተነሳስታችኋል። በእድሜ እየገፋችሁ ስትሄዱ ግን ይህን የመርካት መንፈስ መቋቋም ፈተና ይሆንባችሗል። ከእናንተ እርዳታ የሚጠብቁ ልጆች አሏችሁ፤ ከፍተኛ የስራ ውጥረት አለባችሁ፤ የጎረቤታችሁ፣ የማህበረሰቡ አስተሳሰብ እየዋጣችሁ ነው፤ እናም ይህ የአለመርካት ስሜት ነበልባል መውጣት ይጀምራል:: ደስታ ሲጠፋችሁ ሬድዮ ትከፍታላችሁ፤ ወደ መምህራችሁ ትሄዳላችሁ፤ ወደ አንድ ቡና ቤት ጎራ በማለት ትጠጣላችሁ፣ ሴቶችን ታሳድዳላችሁ - ያን ነበልባል ለማዳፈን። ነገር ግን ያለዚህ ያለመርካት ነበልባል የፈጠራ መነሻ የሆነው መነሳሳት አይኖራችሁም፡፡ እውነቱን ለማወቅ በተደራጀው ደንብ ላይ ማመፅ ይኖርባችኋል፤ ነገር ግን ወላጆቻችሁ ያላቸው ሃብት ብዙ ሲሆንና መምህራኖቻችሁ ይበልጥ በስራቸው ደስተኞች ሲሆኑ የእናንተን ተቃውሞ የመቀበላቸው ነገር ይቀንሳል፡፡ ፈጠራ ሲባል ዝም ብሎ ስዕል መሳል ወይም ግጥም መፃፍ አይደለም፤ ይህ በራሱ ጥሩ ቢሆንም በራሱ ትንሽ ነው:: አስፈላጊው ነገር ሙሉ በሙሉ እርካታ ማጣት ነው - ምክንያቱም ይህ አይነቱ ምሉዕ የእርካታ እጦት ነው ወደ መነሳሳት የሚወስደው:: መነሳሳት ሲበስል ደግሞ ፈጠራ ይሆናል፡፡ በዚህ መንገድ ብቻ እውነት፣ እግዚአብሔር ይገኛል። ስለዚህም ማንም ሰው ይህ ምሉዕ የእርካታ እጦት ያስፈልገዋል - ከደስታ ጋር፡፡ ገብቷችኋል? ማንም ሰው በደስታ፣ በሃሴት፣ በፍቅር ሙሉ በሙሉ አለመርካት አለበት፡፡ እርካታ ያጡ አብዛኞቹ ሰዎች በአስፈሪ ሁኔታ የተሰላቹ ናቸው ፤ ሁልጊዜ ይህ ትክክል ነው፣ ይህ ትክክል አይደለም ሲሉ ይነጫነጫሉ፤ ወይም በተሻለ ቦታ መገኘት ነበረብኝ ይላሉ፤ ወይም የአለመርካታቸው ሁኔታ ከላይ ከላይ ስለሆነ ብቻ ሁኔታዎች እንዲለወጡ ይፈልጋሉ፡፡ የእርካታ እጦት የሌለባቸው በሙሉ የሞቱ ናቸው፡ ልጆች ሳላችሁ ማመፅ ከቻላችሁ ስትጎለምሱ አለመርካታችሁን ከደስታና ከታላቅ ፍቅር ጋር ህያው አድርጋችሁ ታቆዩታላችሁ። እናም ያለመርካት ነበልባል እጅግ ልዩ ጠቀሜታ ይኖረዋል- ምክንያቱም አዳዲስ ነገሮችን ይገነባል፣ ይፈጥራል፤ ህያው ያደርጋል። ስለዚህም ትክከለኛ ትምህርት ያስፈልጋችኋል- አንድ ስራ እንድታገኙ፤ ወይም የስኬትን መሰላል እንድትወጡ የሚያዘጋጃችሁ ሳይሆን እንድታስቡ የሚያግዛችሁና ቦታ የሚሰጣችሁ- አንድ ትልቅ መኝታ ቤት የሚያክል ወይም ጣራው ከፍ ያለ ክፍል የሚመስል ቦታ ሳይሆን አዕምሯችሁ በማህረሰብ ወይ በማንኛውም አይነት ፍርሃትw ውሱን እንዳይሆን በደንብ የሚያንቀሳቅሰው ቦታ ያስፈልጋችዋል። @felasefa @felasefa
Показати все...
#ዞሬ_መጣሁ @felasefa
Показати все...
Repost from N/a
#ሰናዬ 😄ሮፍናን @zelalem_wedu
Показати все...