uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

Відкрити в Telegram

👉plexiglass 👉engraving 👉orginal cosmotics 👉 natural face products like Kesil 👉Gift packages 📞0942410512 metis_bag 🏠🏠 Megenagna 3M Mall 1st floor

Показати більше
1 883
Підписники
-124 гОдини
-87 днів
-2030 днів
Архів дописів
የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ የንግድ ተግባሩን ባስተጓጎሉ 25 ሺህ 68 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በሰጡት መግለጫ
የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ የንግድ ተግባሩን ባስተጓጎሉ 25 ሺህ 68 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በሰጡት መግለጫ በንግድ ተቋማቱ ላይ ከማስጠንቀቂያ እስከማሸግ የደረሰ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል። በዚህም 13 ሺህ 350 ተቋማት ሲታሸጉ 404 የንግድ ተቋማት ደግሞ ፈቃዳቸው መታገዱን ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈም 890 የንግድ ፈቃድ መሰረዙን እና ለ10 ሺህዎቹ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱንም አስታውቀዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም 420 ግለሰቦች ታስረዋልም ነው ያሉት ሚኒስትሩ። ሚኒስትሩ በመግለጫቸው የምርት አቅርቦትን ለማሻሻል እና ምርትን በሀገር ውስጥ ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል። @AddissZemen @AddissZemen

#በሀገራችን ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 21 ደረሰ... በትላንትናው ዕለት ብቻ 5 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን 4 ከአዲስ አበባና 1 ከድሬዳዋ ከበሽታው ማገገም መቻላቸውን የጤና ሚኒስትር
#በሀገራችን ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 21 ደረሰ... በትላንትናው ዕለት ብቻ 5 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን 4 ከአዲስ አበባና 1 ከድሬዳዋ ከበሽታው ማገገም መቻላቸውን የጤና ሚኒስትር አስታውቋል ። በዚህን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 21 መድረሱ ተነግሯል። @AddissZemen @AddissZemen

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ... በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ... በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 1073 የላብራቶ
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ... በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ... በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 1073 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት (2) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 116 ደርሷል። የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦ ታማሚ 1 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የመኖሪያ ቦታው በአፋል ክልል ገዋኔ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው። ታማሚ 2 - የ54 ዓመት አሜሪካዊ (በትውልድ ኢትዮጵያዊ) ከአሜሪካ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ። @AddissZemen @AddissZemen

በድሬዳዋ በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው በለይቶ ማቆያ ያሉ ዜጎች ከህብረተሰቡ ጋር እየተቀላቀሉ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ። ከጅቡቲ ድሬዳዋ መጥተው ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ የተደረጉ ሰዎች ከህብረተሰቡ ጋር እየተቀላቀሉ መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም የተናገሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት በቅርቡ ከጅቡቲ ወደ ድሬዳዋ መጥተው ለ14 ቀናት በሃይስኩል ለይቶ ማቆያ ውስጭጥ ናቸው። ይሁንና እነዚህ ተጠርጣሪዎች ምግብ ለመመገብና አንዳንድ ቁሳቁሶችን ለመግዛት ከለይቶ ማቆያ እየወጡ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ተመልሰው እየገቡ መሆኑ ስጋት ፈጥሮብናል ብለዋል፡፡ በተለይም በማቆያነት እያገለገለ የሚገኘው ትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢው የተጠናከረ ባለመሆኑ ሰዎች በቀላሉ ወጥተው መግባት እንዲችሉ አድርጓቸዋል ብለዋል። ይህ ደግሞ ከስደት ተመላሾች ለይቆ ማቆያ እንዲገቡ መደረጉን ትርጉም አልባ ያደርገዋል ሲሉ ነዋሪዎቹ ሃሳባቸውን አካፍለውናል፡፡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በአስተዳድሩ የጸጥታ ዘርፍ በኩል ተመላሾቹ ከጊቢ እንዳይወጡና ከህብረተሰቡ ጋርም ንክኪ እንዳይኖራቸው እየተደረገ ነው ብለውናል፡፡ ሆኖም ችግሩ በትክክል ስለመኖሩ ጥቆማውን ወስደን ማጣራት እናደርጋለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በጅቡቲ በርካታ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተከትሎ አሁን ስጋቱ በምስራቁ የሃገራችን ክፍል ላይ ሆኗል፡፡ ድሬዳዋ ከተማ እና አፋር ክልል ከጅቡቲ ጋር የሚዋሰኑና ቅርብ እንደመሆናቸው በቀላል የትራንስፖርት አገልግሎት የሁለቱ ሃገራት ዜጎች የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ነው፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብም ማህበራዊ መስተጋብራቸው ጥብቅ መሆኑ ትልቅ ስጋትን ፈጥሯል። በአካባቢው ምን የተለዬ ጥንቃቄ እየተደረገ ነው ስንል በሃገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ-19 ቅድመ ዝግጅትና ምላሽ ምክትል ዋና አስተባባሪ አቶ ዘውዱ አሰፋን ጠይቀናቸዋል፡፡ በአዲስ አበባና ሁሉም ክልሎች የሚደረገውን አይነት ጥንቃቄ እየተደረገ መሆኑንና፤ይህም በክልል ጤና ቢሮዎች የሚመራ መሆኑን ነግረውናል፡፡ የመግቢያ በሮች ላይም ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎች እንዳሉና ተገቢውን ክትትል እያደረጉ መሆኑን አቶ ዘውዱ ነግረውናል፡፡ Via Ethio Fm @AddissZemen @AddissZemen

photo content

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የሰባት ወጣቶች ህይወት አለፈ! አዳማ፤ ሚያዝያ 11/2012 (ኢዜአ)- በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ዲቢቢሳ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በዮሃንስ ቤተክርስቲያን ለጊዜው በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት ሰባት ወጣቶች ሞተው መገኘታቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ ። የመምሪያው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው አለሙ ለኢዜአ እንደገለጹት በአንድ አነስተኛ ክፍል ውስጥ ሞተው ከተገኙት ሁሉም እድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች ሲሆኑ ከሟቾቹ መካከል አንዷ ሴት ናት። ትላንት ከሎሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ሟቾቹ በተገኙበት ወቅት የመብራት አገልግሎት የተቋረጠ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ጀነሬተር እንደተለኮሰ ገልጸው አደጋው ከጄኔሬተሩ ጭስ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ እየተጣራ እንደሚገኝ አስረድተዋል። ከአደጋው ጋር በተያያዘ በአካባቢው 11 ግለሰቦች ተጠርጥረው መያዛቸውንና የማጣራት ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሟቾቹ አስከሬን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል መላኩን የገለጹት ኃላፊው በአሁኑ ወቅት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ሁሉም ቤተ ዕምነቶች ዝግ መሆናቸውንና አማኞችም በቤታቸው አምልኮ ማድረግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል። ክስተቱ እንዴት እንደተፈጠረና ወጣቶቹ እንዴት ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ሊገቡ እንደቻሉ እያጣራን ነው ያሉት ኮማንደሩ ጉዳዩን የሚያጣራ ግብረሃይል ተቋቁሞ የማጣራት ስራ መጀመሩን ተናግረዋል። ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ ሁሉም ሰው ርቀቱን ጠብቆ በዓሉን ማክበር አንደሚገባው ያስታወቁት ኮማንደር አስቻለው በቤተክርስቲያኑ የታየው ነገር አስደንጋጭና ትምህርት ሊወሰድበት አንደሚገባም አሳስበዋል። https://t.me/joinchat/AAAAAEz8VPFU1ccn8FacSw

ጊዜያቹን እቤት እያሳለፋቹ ላላቹ ምርጥ ምርጥ የፊልም ጥቆማዎች የሚያደርስ ቻናል ተከፍቷል አሁኑኑ JOIN በማለት የፍላጎታችሁን ፊልም ምረጡ👇
ጊዜያቹን እቤት እያሳለፋቹ ላላቹ ምርጥ ምርጥ የፊልም ጥቆማዎች የሚያደርስ ቻናል ተከፍቷል አሁኑኑ JOIN በማለት የፍላጎታችሁን ፊልም ምረጡ👇

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤትሰቦች፣ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ! በአሉን ስታከብሩ የኮቪድ-19ን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ባለመዘንጋት ይሁ
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤትሰቦች፣ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ! በአሉን ስታከብሩ የኮቪድ-19ን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ባለመዘንጋት ይሁን! መልካም በዓል!!!!! https://t.me/joinchat/AAAAAEz8VPFU1ccn8FacSw

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የኮሮና ቫይረስ ህክምና ማገገሚያ ሊሆን ነው፡፡ Via:- ELU https://t.me/joinchat/AAAAAEz8VPFU1ccn
የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የኮሮና ቫይረስ ህክምና ማገገሚያ ሊሆን ነው፡፡ Via:- ELU https://t.me/joinchat/AAAAAEz8VPFU1ccn8FacSw

የኃይል መቋረጥ ችግር፤ 905 አማሮናል! ●በበዓል መብራት ጠፍቶብን ውለናል አሁንም እንደጠፋ ነው የሚሉ መልዕክቶች ከአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም ከአሰላ ከተማ መልዕክቶች መጥተዋ
የኃይል መቋረጥ ችግር፤ 905 አማሮናል! ●በበዓል መብራት ጠፍቶብን ውለናል አሁንም እንደጠፋ ነው የሚሉ መልዕክቶች ከአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም ከአሰላ ከተማ መልዕክቶች መጥተዋል። ●ትናንት ለሊት በአዲስ አበባ ጀሞ አካባቢ በጋራ መኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች በትረንስፎርመር ለይ ኮንታትክት ተፈጥሮ በ905 ላይ ጥቆማ ለመስጠት ረጅም ሰዓት ስልክ ቢሞክሩም እንዳልተሳካና ችግሩ ከነጋ በኃላ እንደተፈታ ገልፀዋል። https://t.me/joinchat/AAAAAEz8VPFU1ccn8FacSw

●አንድ ተጨማሪ ሰው አገግሟል እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ ●ዛሬ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች :- 9 ●በአሁኑ ጊዜ በለይቶ ማቆያ ህክምና ያሉ ታማሚዎች :- 85 ●ፅኑ ህሙማን :- 1 ●ከበሽታው ያገገሙ :- 16 ●በሽታው ህይወታቸውን ያለፈ ድምር :- 3 @AddissZemen @AddissZemen

🐂በስጋ ቤቶች (ሉካንዳዎች) የሚተገበሩ ግዴታዎች ❗️ 1🐂ማንኛውም ስጋ ቤት ስጋ አስገብቶ ከመሸጡ በፊት ሙሉ ለሙሉ ስጋ ቤቱን እና መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን በውሃ ሳሙናና በረኪና በመጠቀም ማጽዳት አለበት፣ 2🐂ማንኛውም ስጋ ቤት የሚያስገባው ስጋ ህጋዊ እና ከታወቀ ቄራ ታርዶ የቀረበ መሆን አለበት፣ 3🐂ማንኛውም በስጋ ቤት የሚሰራ ሰራተኛ የስጋ ሽያጭ በሚያከናውንበት ጊዜ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ)፣ ቆብ እና ጋዎን መጠቀም አለበት፣ 4🐂በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ገንዘብ የሚቀበልና ስጋ የሚቆርጥ ሰራተኛ መለየት አለበት፣ 5🐂በማንኛውም ሉካንዳ ቤት ውስጥ ለሰራተኞች የእጅ ሳሙናና ውሃ ተዘጋጅቶ ደጋግመው እጃቸውን በመታጠብ አገልግሎት መስጠት አለባቸው፣ 6🐂በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ሽያጭ በሚከናወንበት ወቅት ተገልጋዮች ከመሸጫ መስኮቱ አንድ (1) ሜትር ርቀው እንዲቆሙና እንዲገለገሉ መደረግ አለበት፣ 7🐂በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ድርጅት ውስጥ የተገልጋይ ቁጥር ከሁለት በላይ በሚሆንበት ወቅት ድርጅቱ ተገልጋዮችን እያንዳንዳቸው ርቀታቸውን በየሁለት እርምጃ ጠብቀው እንዲቆሙና እንዲያገለግሉ ማድረግ አለበት፣ 8🐂ከምግብ ቤቶች ጋር የተያያዙ ሉካንዳ ቤቶች ውስጥ ያልበሰለ ስጋ (ቁርጥ/ጥሬ ስጋ፣ ያልበሰለ ክትፎ) ለምግብነት ማቅረብ ለበሽታው ስለሚያጋልጥ የተከለከለ ነው፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት! @AddissZemen @AddissZemen

●ሚሊኒዬም አዳራሽ ለኮሮና ቫይረስ ህክምና ስፍራ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ።የማዘጋጀቱ ስራ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እየተከናወነ ሲሆን፣ 1000 አልጋዎችን እንዲይዝ ተደርጎ እየተዘጋጀ
●ሚሊኒዬም አዳራሽ ለኮሮና ቫይረስ ህክምና ስፍራ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ።የማዘጋጀቱ ስራ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እየተከናወነ ሲሆን፣ 1000 አልጋዎችን እንዲይዝ ተደርጎ እየተዘጋጀ ይገኛል፣ ስራው በያዝነው የፈረኝጆች ወር መጨረሻ ተጠናቆ አገልግሎት ይጀምራል። @AddissZemen @AddissZemen

#DrLiaTadesse በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 105 ደርሰዋል! በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 659 የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠኝ (9) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠ
#DrLiaTadesse በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 105 ደርሰዋል! በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 659 የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠኝ (9) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 105 ደርሷል። የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦ ታማሚ 1 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊት የጅማ ከተማ ነዋሪ ፤ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ በፊት ከሊባኖስ የመጣች። ታማሚ 2 - የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት። ታማሚ 3 - የ40 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት። ታማሚ 4 - የ13 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው። ታማሚ 5 - የ73 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ ከአሜሪካ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ። ታማሚ 6 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ነዋሪ፤ ከጅቡቲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ። ታማሚ 7 - የ20 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ነዋሪ፤ ከጅቡቲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ። ታማሚ 8 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የድሬዳዋ ነዋሪ፤ ከጅቡቲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ። ታማሚ 9 - የ38 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከእንግሊዝ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ። @AddissZemen @AddissZemen

“ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች በ14 እጥፍ ለኮሮናቫይረስ ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው” ●ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ጋር ሲነፃፀሩ ለኮሮናቫይረስ በ14 እጥፍ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን አዲስ ጥናት አመልክቷል
“ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች በ14 እጥፍ ለኮሮናቫይረስ ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው” ●ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ጋር ሲነፃፀሩ ለኮሮናቫይረስ በ14 እጥፍ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን አዲስ ጥናት አመልክቷል፡፡ ●በቱርክ የፀረ-ሱሰኝነት ቡድን አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ሙካሂት ኦዝቱርክ አንደገለፁት ትምባሆና የትምባሆ ውጤቶችን መጠቀም በኮሮናቫይረስ የመያዝ እድልን ያሰፋል፡፡ ●እንደጥናቱ ከሆነ አጫሾች በእድሜ ከገፉ ሰዎች ይልቅ በኮቪድ-19 የመሞት እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ●በመሆኑም ሰዎች ትምባሆን ጨምሮ ሌሎች ሱስ አስያዥ ንጥረ ነገሮችን ከመጠቀም መታቀብና ጤናቸውን መጠበቅ አለባቸው ነው ያሉት፡፡ ●ሲጋራ ማጨስ የሰዎችን ተፈጥሯዊ የበሽታ መከላከል አቅምን ያዳክማል፤ በቫይረሱ ለተያዙ ሰዎች የሚሰጠው ሕክምናም ውጤታማ እንዳይሆን ያደርጋል ብለዋል ፕሮፌሰሩ፡፡ ●የዓለም የጤና ድርጅት ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች በእጅ ጣቶቻቸው ከንፈሮቻቸውን በተደጋጋሚ ስለሚነኩ ለኮሮናቫይረስ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ይናገራል፡፡ ●ማጨስ ሳንባን ጨምሮ የተለያዩ የአካል ክፍሎችን ይጎዳል፤ ለኮቪድ-19 ተጋላጭነትን ይጨምራል፤ ጤናን ከወረርሽኙ ለመጠበቅ ማጨስን ማቆም አስፈላጊ መሆኑን ድርጅቱ ያሳስባል፡፡ ምጭ፡- አልጀዚራ via EBC @AddissZemen @AddissZemen

ጀርመን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠሯን ገለጸች.... የጀርመን ጤና ሚኒስትር የንስ ስፓን በአገራቸው በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ ማሳየቱን ተከትሎ አገራቸው ወረርሽኙን መቆጣጠሯን
ጀርመን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠሯን ገለጸች.... የጀርመን ጤና ሚኒስትር የንስ ስፓን በአገራቸው በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ ማሳየቱን ተከትሎ አገራቸው ወረርሽኙን መቆጣጠሯን ተናገሩ። ሚኒስትሩ እንዳሉት ከቅርብ ቀናት ወዲህ ከበሽታው የሚያገግሙት በበሽታው ከሚያዙት ሰዎች ቁጥር በቋሚነት እየጨመረ መሄዱ የእንቅስቃሴ ገደቡ ውጤታማ እንደሆነ ያሳያል ብለዋል። "ዛሬ ወረርሽኙ መቆጣጠር የሚቻል መሆኑን ተገንዝበናል" ሲሉ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት ሚኒስትሩ የአገራቸው የጤና እንክብካቤ ሥርዓት እስካሁን በወረርሽኙ ምክንያት ከአቅሙ በላይ የሆነ ችግር እንዳላጋጠመው ተናግረዋል። @AddissZemen @AddissZemen

አጫጭር መረጃዎች ~ በእየሩሳሌም አል አክሳ የሚገኘዉ መስጊድ በረመዳን ጾም ወቅት ዝግ እንደሚሆን ተነገረ፡፡ይህ ስፍራ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ሶስተኛዉ ቅዱስ ስፍራ በመባል ይታወቃል፡፡ለደህንነት ሲባል ምህመናን በቤታቸዉ ሀይማኖታዊ ስነስርዓትን እንዲከዉኑ ጥሪ ቀርቧል፡፡ ~ በግሪክ ለበዓል ዜጎች ወደ ቤተክርስቲያን እንዳያቀኑ ፖሊሶች መሰማራታቸዉ ተሰማ፡፡የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በሀገሪቱ በፍጥነት እየጨመረ የመጣ ሲሆን የ105 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ተደርጓል፡፡ ~ በእንግሊዝ 40‚000 የሚጠጉ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉ ሊያልፍ እንደሚችል ተጠቆመ፡፡እዉቁ የህብረተሰብ ጤና ፕሮፌሰር ኮስቴሎ የእንግሊዝ መንግስት ቫይረሱን ለመከላከል የዘገየ እርምጃ ወስዷል ሲሉ ተችተዋል፡፡ ~ በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት በኮሮና ቫይረስ የ585 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 19,315 መድረሱ ሪፖርት ተደርጓል፡፡በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 188,068 ደርሷል፡፡ ~ በሱዳን በኮሮና ቫይረስ ስጋት የጸሎት ስነስርዓት በቤተክርስቲያን እና መስጊድ ዉስጥ እንዳይካሄድ መከልከሉን ተከትሎ ይህንን የተቃወሙት የካርቱም ገዢ ከስልጣን ተነሱ፡፡የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር ሀምዶክ የካርቱም ገዢ ጀነራል ሀማድ መሃመድ ይህንን ዉሳኔ ለማስተግበር ፍቃደኛ አለመሆናቸዉን ተከትሎ ከስልጣናቸዉ እንዲነሱ አድርገዋል፡፡ ~ ከ50 ሺ በላይ የእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት ሰራተኞች የኮሮና ቫይርስ ምርመራ እንደተደረገላቸዉ የእንግሊዝ የጤና ዋና ጸሀፊ ማት ኩክ ተናገሩ፡፡ ~ የሳዑዲ አረቢያ ሙፍቲ ሼኪ አብዱላዚዝ አል ሴኪ የረመዳን እና የኢድ የጸሎት ስነ ስርዓት በመኖሪያ ቤት ዉስጥ ብቻ እንዲካሄድ መወሰኑን አሳወቁ፡፡ ~ ባለፉት 24 ሰዓት በጅቡቲ 1,056 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 141 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጣል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 732 ደርሷል። @AddissZemen @AddissZemen

#መናኸሪያዎች በተጓዦች ከመጨናነቅም በላይ አስፈላጊው ጥንቃቄ እየተደረገ አይደለም ሃገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎትን በሚሰጡ እና አዲስ አበባ በሚገኙ መናኸሪያዎች የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል
#መናኸሪያዎች በተጓዦች ከመጨናነቅም በላይ አስፈላጊው ጥንቃቄ እየተደረገ አይደለም ሃገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎትን በሚሰጡ እና አዲስ አበባ በሚገኙ መናኸሪያዎች የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል በሚል ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተጣጥሞ የወጣው መመሪያ በወጉ እየተገበረ እንዳይደለ አል ዐይን አማርኛ ከተለያዩ ምንጮች ያገኛቸው መረጃዎች አልክተዋል፡፡ የፋሲካ በዓልን ታሳቢ አድርገው ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመሄድ በመነኸሪያዎች የተሰባሰቡ ተጓዦችን የያዙ ምስሎችም በየማህበራዊ ሚዲያው ሲሽከረከሩ ውለዋል፡፡ ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ይግዛው ዳኘው መናኸሪያዎች የመጨናነቃቸውን እውነታነት አስረግጠውልናል፡፡ በየመነኸሪያውና በየተሽከርካሪው አስፈላጊ እና አስገዳኝ የተባሉ ጥንቃቄዎች በሚጠበቀው ልክ እየተተገበሩ እንዳልሆነም ዳይሬክተሩ አልሸሸጉም፡፡ ቀደም ባሉት ቀናት ተስተውለው የነበሩት የጥንቃቄ መንገዶቹን የመከተል ዓይነት አዝማሚያዎች አሁን ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ እየተተገበሩ እንዳይደለም ገልጸዋል፡፡ ©አል-ዐይን_አማርኛ @AddissZemen @AddissZemen

የስቅለት በአልና ግብይት ምን ይመስላል እስኪ መረጃ አድርሱን። @BISRATSPORT101BOT 👈 ነክታቹ START ካላቹ በኃላ ሀሳባቹን ግለፁልን።

"የግል ወይም የቤት ተሸከርካሪዎችን መጠቀም የሚቻለዉ የሠሌዳቸዉ የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ ወይም ዜሮ የሆኑት ዛሬ ሚያዚያ አርብ 09/08/12 ሲሆን በቀጣዩ ቀን የሠሌዳቸዉ የመጨረሻ ቁጥር ደግሞ ጎዶሎ የ
"የግል ወይም የቤት ተሸከርካሪዎችን መጠቀም የሚቻለዉ የሠሌዳቸዉ የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ ወይም ዜሮ የሆኑት ዛሬ ሚያዚያ አርብ 09/08/12 ሲሆን በቀጣዩ ቀን የሠሌዳቸዉ የመጨረሻ ቁጥር ደግሞ ጎዶሎ የሆኑት ነገ ቅዳሜ የሚንቀሳቀሱ ይሆናል"--- የፌደራል የትራንስፖርት ባለስልጣን ዛሬ ካወጣው መግለጫ የተወሰደ © eliyas meseret @AddissZemen @AddissZemen