uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

Відкрити в Telegram

👉plexiglass 👉engraving 👉orginal cosmotics 👉 natural face products like Kesil 👉Gift packages 📞0942410512 metis_bag 🏠🏠 Megenagna 3M Mall 1st floor

Показати більше
1 892
Підписники
-124 гОдини
-37 днів
-2330 днів
Архів дописів
የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርት በሚጀምሩበት ሁኔታ ላይ የሚመክር የውይይት መድረክ በሀዋሳ ተጀምሯል። በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ዛሬ በሀዋሳ በተጀመረው የውይይት መድረክ
የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርት በሚጀምሩበት ሁኔታ ላይ የሚመክር የውይይት መድረክ በሀዋሳ ተጀምሯል። በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ዛሬ በሀዋሳ በተጀመረው የውይይት መድረክ ላይ ሚኒስትሮችና የሁሉም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ተገኝተዋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በወቅቱ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲዎች ኮሮናን በመካላከል ትምህርት ለማስጀመር ለሚያደርጉት ጥረት አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል። ለሶስት ቀናት በሚቆየው መድረክ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተዋቀረው ኮሚቴ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመገኘት ያደረገውን ግምገማ ሪፓርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል። በዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የቅበላ ጊዜ ከመቼ እንደሚጀመር ይፋ እንደሚደረግም ከመርሀ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

📚 ወቅታዊ የትምህርት መረጃዎችን እና የየክላሱ ትምህርቶች በቪዲዮ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ https://t.me/joinchat/AAAAAET1-uSCn0qvNQRdAg

የአፍና አፍንጫ መሸፈና ጭንብል ያልደረሳቸው ትምህርት ቤቶች ጥቅምት 9 ትምህርት እንዳይጀምሩ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ። ------------------------------------------ የትምህርት ሚኒስቴር በአዳማ ኢንደስትሪ ፓርክ ያስመረተውን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ተረከቧል። የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ተረክበው ለየክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና ተወካዮች አስረክበዋል። በወረዳና ከዚያ በታች ያሉ ትምህርት ቤቶች ጥቅምት 9 ትምህርት እንዲጀምሩ ይደረጋል ያሉት ሚኒስትሩ በቦታዎች ርቀትና በተለያዩ ምክንያቶች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያልደረሳቸው ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዳይጀምሩ አሳስበዋል። ሌሎች ዝግጅቶች እንደተጠበቁ ሆነው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እንደደረሳቸው ግን ትምህርት መጀመር ይችላሉ ብለዋል። እስከ ጥቅምት 30 ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ትምህርት ለማስጀመር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከተቀመጡት መስፈርቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የማስክ አቅርቦት ስራ በሁሉም ትምህርት ቤቶች እየተከናወነ ነው። በሃዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ የተመረተውም ወደየ ትምህርት ቤቶች የማድረስ ስራ እየተሰራ ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የኢንደስትሪ ፓርክ ኃላፊዎችን ጨምሮ በዚህ ስራ ለተሳተፉት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

📚 ወቅታዊ የትምህርት መረጃዎችን እና የየክላሱ ትምህርቶች በቪዲዮ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ https://t.me/joinchat/AAAAAET1-uSCn0qvNQRdAg

የትምህርት ሂደቱን በፈረቃ ለማስቀጠል የተያዘው እቅድ እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ የሚወሰን መሆኑን ትምህር ሚኒስቴር አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል በሀገር አቀፍ ደረጃ በርካታ ዝግጅቶች መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡በዚህም ተማሪዎችን አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲማሩ ለማድረግ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን መገንባት እና የመማር ማስተማር ሂደቱን እስከ ሶስት ፈረቃ ማድረግ ዋነኞቹ ናቸው ብለዋል፡፡ የመምህር እጥረትን ለመቅረፍም ከዚህ በፊት የማስተማር ልምድ ያላቸው እና አዲስ ተመራቂ ተማሪዎች ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ መቅረቡንም አንስተዋል።ጥሪ የተደረገላቸው መምህራንም በበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚሳተፉ እንጂ ቅጥር የሚፈፅሙ አለመሆናቸውንም ነው ያነሱት፡፡በበጎ ፍቃዱ አገልግሎቱ የሚሳተፉ የአፕላይድ ሳይንስ ተመራቂዎችም አጭር የማስተማር ክህሎት ስልጠና ወስደው አገልግሎቱን የሚሰጡ ይሆናልም ነው ያሉት።እነዚህ ተመራቂዎች በመምህርነት ስራ የመቀጠል ፍላጎት ካላቸው በቀጣይ ቅጥር በሚካሄድበት ጊዜ ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ጠቁመዋል፡፡ መደበኛ አስተማሪዎች ከዚህ ቀደም ከሚያስተምሩት ክፍለ ጊዜ በተጨማሪ አምስት ክፍለ ጊዜ በበጎ ፈቃድ እንዲያስተምሩ የሚደረግ መሆኑን አውስተዋል፡፡ለዚህም መምህራን ለወራት ተቋርጦ የቆየውን የመማር ማስተማር ሂደት በማስቀጠል ሀገራዊ ሃላፊነታቸው እንደሚወጡ እምነታቸው መሆኑን ነው የገለጹት፡፡የመማሪያ ክፍል እጥረትን ለማስወገድ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ጣቢያዎችን፣ የቀበሌ ፅህፈት ቤቶችን እና የሃይማኖት ተቋማት አገልግሎሎት እንዲሰጡ ይደረጋል ብለዋል፡፡የመማር ማስተማር ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ እንዲቀጥል ወላጆችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

📚 ወቅታዊ የትምህርት መረጃዎችን እና የየክላሱ ትምህርቶች በቪዲዮ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ https://t.me/joinchat/AAAAAET1-uSCn0qvNQRdAg

🤑🤑101% ቤቲንግ ለተበላ በ ጥቂት ጊዜ ዉስጥ ትርፋማ የሚያደርገዉ ቻናል እንጠቁማቸዉ 💰✅✅ ❇️ በየቀኑ በምንሸጠዉ ትኬቶች በቀን 50 ODD+ በላይ የሚበላበት ብቸኛዉ የ ቤቲንግ ቻናል እነሆ
🤑🤑101% ቤቲንግ ለተበላ በ ጥቂት ጊዜ ዉስጥ ትርፋማ የሚያደርገዉ ቻናል እንጠቁማቸዉ 💰✅✅ ❇️ በየቀኑ በምንሸጠዉ ትኬቶች በቀን 50 ODD+ በላይ የሚበላበት ብቸኛዉ የ ቤቲንግ ቻናል እነሆ

ለሁሉም የዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ፣ ለምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ለተማሪ ህብረት ፕሬዝዳንቶች የቀረበ ጥሪ ፨ጉዳዩ፡ ኮሮናን እየተከላከሉ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትን መልሶ የመክፈትና ሰላማዊ አድር
ለሁሉም የዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ፣ ለምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ለተማሪ ህብረት ፕሬዝዳንቶች የቀረበ ጥሪ ፨ጉዳዩ፡ ኮሮናን እየተከላከሉ ትምህርትና ስልጠና ተቋማትን መልሶ የመክፈትና ሰላማዊ አድርጎ የማስቀጠል የዝግጅት ምዕራፍ ግምገማ ማጠቃለያ መድረክ ለጥቅምት 5/13 ሃዋሳ #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

📚 ወቅታዊ የትምህርት መረጃዎችን እና የየክላሱ ትምህርቶች በቪዲዮ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ https://t.me/joinchat/AAAAAET1-uSCn0qvNQRdAg

በአዲስ አበባ ከጥቅምት 16 ጀምሮ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ እና ቀሪ መደበኛ ተማሪዎች ደግሞ ከጥቅምት 30 ጀምሮ ወደ ትምህርት ገበታ እንደሚመለሱ የአዲስ አበባ ከ
በአዲስ አበባ ከጥቅምት 16 ጀምሮ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ እና ቀሪ መደበኛ ተማሪዎች ደግሞ ከጥቅምት 30 ጀምሮ ወደ ትምህርት ገበታ እንደሚመለሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛዉ ገብሩ አስረድተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ የትምህርት አመቱን የስርአተ ትምህርት ምጣኔና የክፍለ ጊዜ ድልድልን አስመልክቶ እንዳብራሩት በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በአዲስ አበባ ዘንድሮ መማር ማስተማሩ በሁለት ፈረቃ እንደሚሰጥ እና በዚህም ከጥቅምት 30 ቡኃላ ትምህርት የሚጀምሩ ተማሪዎች በሳምንት ሶስት ቀን 24 ክፍለ ጊዜ እንዲማሩ ፕሮግራም የተያዘላቸው ሲሆን የትምህርት አገልግሎቱም በሁለት ፈረቃ ማለትም ሰኞ ፤እሮብ ፤አርብ እንዲሁም ማክሰኞ ፤ሀሙስ እና ቅዳሜ እንዲሆን መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎቸ ደግሞ ከጥቅምት 16 ጀምሮ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በሳምንት ስድስት ቀን እንዲማሩ ፕሮግራም የተያዘላቸው መሆኑንና ትምህርቱን ሲያጠናቅቁም ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ 7ኛ ክፍል ሙሉ እና ከ8ኛ ክፍል የአንደኛ ሴሚስተርን ብቻ ያካተተ ፈተና እንደሚዘጋጅ እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎችም ደግሞ የ11ኛ ክፍል የሁለቱም ሴሚስተር እና 12ኛ ክፍል አንደኛ ሴሚስተር የተማሩትን ትምህርት ያካተተ ፈተና እንደሚፈተኑ ተገልጻል፡፡ ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

✋ሰላም የትምህርት ሚኒስተር የቴሌግራም ላይብራሪ ተቀላቅለዋል? ካልተቀላቀሉ @MOE_Library በመጫን ይቀላቀሉ!! ሁሉም አይነት መፅሀፎች በሁሉም ቋንቋዎች ያገኙበታል። @MOE_Library @MOE_Library ለጓደኞቻቹ ሼር በማድረግ ውለታ ይዋሉላቸው!!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በሶስት ዙር ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ‼️ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ መከላከልን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ተማሪዎችን በሶስት ዙር ለመቀበል አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት በኮቪድ 19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊቀንስ ይችላል በሚል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ለመጀመር ከግንቦት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል:: ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በሁለት ዙር እንዲገቡ ለማድረግ ዕቅድ ይዞ ዝግጅት ቢያደርግም በኮቪድ 19 #የሚያዘው ሰው በከፍተኛ በመጨመሩ ተማሪዎችን በሶስት ዙር ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በአንድ ክፍል ከ25 በላይ ተማሪዎች እንደማይማሩና መምህሩ ደግሞ ከ35 ደቂቃ በላይ ማስተማር እንደሌለበት ተወስኗል ያሉት ፕሬዚዳንቱ ፤ በአሁኑ ጊዜ በኮቪድ 19 የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ ተማሪዎችን በሶስት ዙር ለመቀበል መወሰኑን ገልጸዋል፡፡እንደ ፕሮፌሰር ጣሰው ገለጻ፤ ተማሪዎች ፣የአፍ መሸፈኛ ጭንብል (ማክስ) አድርገው፤ መስኮቶች ተከፍተው እንዲማሩ ይደረጋል፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከጥቅምት 20 እስከ ጥቅምት 30 ተመራቂ ተማሪዎችን ለመቀበል እየተዘጋጀ ይገኛል ዙር አንድ ፦ • 2012 ተመራቂ የነበሩ 4,000 የሚሆኑ የቀን ተማሪዎች ይገባሉ ፤ በ45 ቀን ውስጥ ትምርታቸውን አጠናቀው እንዲመረቁ ይደረጋል። ዙር ሁለት ፦ • በ2ኛው ዙር 5 ሺህ የሚሆኑ 3ኛ እና 4ኛ ዓመት ተማሪዎች የሚቀበል ይሆናል። ዙር ሶስት ፦ • በ3ኛው ዙር ደግሞ 1ኛና 2ኛ ዓመት ተማሪዎች ይቀበላል። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

የወር አበባ በተመለከተ በሀኪሞች የተነገሩ የተሳሳቱ ነገሮች | የህመም ስሜት ማጥፊያ መንገዶች!! https://youtu.be/HnUMxO41lBQ ቪዲዮውን ለመመልከት ሊንኩን ወይም ምስሉን ይጫኑ!!

📚 ወቅታዊ የትምህርት መረጃዎችን እና የየክላሱ ትምህርቶች በቪዲዮ የሚያገኙበት ቻናል ይቀላቀሉ https://t.me/joinchat/AAAAAET1-uSCn0qvNQRdAg

ጎንደር፣ ዲላ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት መጀመር ይችላሉ ተባለ ጎንደር፣ ዲላ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማሩን ሂደት እንደገና ለማስቀጠል የሚያስችል አቋም ላይ እንደሚ
ጎንደር፣ ዲላ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት መጀመር ይችላሉ ተባለ ጎንደር፣ ዲላ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማሩን ሂደት እንደገና ለማስቀጠል የሚያስችል አቋም ላይ እንደሚገኙ ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተላከው የምርመራ ቡድን አረጋግጧል፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስን ግምት ውስጥ በማስገባት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት የሚጀምሩበትን ቁመና የሚገመግም ቡድን ወደየተቋማቱ መላኩ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረት ወደ ጎንደር፣ ዲላ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች የተላኩ የግምገማና ክትትል ቡድኖች ተቋማቱ በጤና ሚኒስቴር የወጣውን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች ተግባራዊ በማድረግ ትምህርት የማስጀመር አቋም ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲን ዝግጅት የገመገመው ቡድን መሪ አቶ ከበደ ግዛው እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ዝግጅት ለመገምገም የተላከው ቡድን መሪ አቶ ጌታቸው ተፈራ ዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎች በግቢዎቹ በሚኖራቸው ቆይታ አካላዊ ርቀታቸውን እና ንጽህናቸው ጠብቀው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚያስችል በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ የመመገቢያ ቤቶችን፣ ቤተ መጻሕፍት፣ ቤተ ሙከራዎችን እና ላውንጆችም የኮሮና ቫይረስ ኬሚካል ርጭት የተደረገባቸው መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡ በተጨማሪም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል አስተማማኝ የውሃ አቅርቦት እንዲሁም ማስክ እና ሳኒታይዘር መዘጋጀቱንም ተናግረዋል፡፡ #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE