206
Підписники
Немає даних24 години
-27 днів
-530 днів
- Підписники
- Перегляди допису
- ER - коефіцієнт залучення
Триває завантаження даних...
Приріст підписників
Триває завантаження даних...
ልረሳሽ እየጣርኹ ነው።
(በዕውቄ)
በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲውለበለብ፥ ሰንደቅ ኾኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጽዋ
ውኃ ሲያቁር ከሕዋ
የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
መሬት ፍጥረትን ስትጸንስ
በዚህ ኹሉ ጸጋ መሓል፥ ያንቺን መሔድ ስተምነው
ኢምንት ነው ምንም ነው
ልረሳሽ እየጣርኹ ነው፤
መጣ መጣ መጣ፥ የዝናቡ ኮቴ አየለ
ክረምት የፍጥረት መሲሕ፥ በቀጠሮው ከተፍ’ አለ፤
ስሱ የጉም ዐይነ-ርግብ፥ ውብ ገጽታሽን ሸፋፈነው
የርጥብ አፈር ‘ርጥብ ሽታ፥ ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
ልረሳሽ እየጣርኹ ነው፤
የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
እንደብሥል ሾላ ፍሬ፥ አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
እንኳን የእግርሽ ኮቴ፥ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል፤
ልረሳሽ እየጣርኹ ነው ...