cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙራትና አስተማሪ ጹሑፎች

ወደ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙራትና ምክሮች እንኳን በደህና መጡ ውድ የክርስቶስ ቤተሰቦች፣የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአሥራት የበረከት ልጆች እንዲሁም የጻድቃን የሠማዕታት ወዳጆች።🎖⛪️አስተያየት @Brooksep9

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
203
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን ! እንኳን ለመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት እና የመተሳሰብ ያድርግልን ዘንድ ከልብ እንመኛለን። በዓሉን ስናከብር በሀዘን ውስጥ ያሉ ፣ በችግር ላይ የወደቁ ዜጎቻችንን እያሰብን፣ ለሀገራችን እና ለሀገራችን ህዝብ ሁሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰጠን ፈጣሪን እየተማፀንን እንዲሆን አደራ እንላለን። መልካም በዓል🙏🙏🙏 https://t.me/Mezmurtewahido
Показати все...
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙራትና አስተማሪ ጹሑፎች

ወደ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙራትና ምክሮች እንኳን በደህና መጡ ውድ የክርስቶስ ቤተሰቦች፣የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአሥራት የበረከት ልጆች እንዲሁም የጻድቃን የሠማዕታት ወዳጆች።🎖⛪️አስተያየት @Brooksep9

የቤተ ልሄም ህፃን የግብፅ ስደተኛ የቆሮቶስ ባህታዊ የቀራንዮ በግ የትንሣኤ ብርሃን ለሠው ልጅ ሲል ሞተ እናም ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ መልካም በዓል ((((መልካም በዓል))) @Mezmurtewahido @Mezmurtewahido @Mezmurtewahido
Показати все...
‹ ምክረ አጋንንት › ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ዘላስታ ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል ፡፡ አንተም ትተወዋለህ ፡፡ ፡፡ ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል ፡፡አንተም ትተወዋለህ ፡፡ ፡፡ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል ፡፡ አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ ፡፡፡ ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል ፡፡ አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ ፡፡ ፡፡ ላስቀድስ ትላለህ ፤ ተው ትንሽ ተኛ ይልሃል ፡፡ አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ ፡፡ ፡፡ ጸበል ልግባ ትላለህ ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል ፡፡ አንተም አጋንንቱ እየተደራረበብህ ትኖራለህ ፡፡ ፡፡ ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ ፤ ተው ስራን ስራ ይልሃል ፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ ፡፡ ፡፡ አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል ፡፡ አንተም ትተወዋለህ ፤ ከእነ እዳህ ትሞታህ ፡፡ ፡፡ በአንድ ልወሰን ትላለህ ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል ፡፡ አንተም በዝሙት ትወድቃለህ ፡፡ ፡፡ በመጨረሻም የተወሰነልህ ግዜ ያልቃል ፡፡ ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ ይወስዷታል ፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ፡፡ ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል ፡፡ ያሰክርሃል ፡፡ መስከር ‹ ሰውኛን በአጋንንት መቀየር ነው ፡፡ › ፡፡ ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል ፡፡ ያስጨፍርሃል ፡፡ ፡፡ ልስረቅ ስትል ፤ ስረቅ ይልሃል ፡፡ ያሰርቅሃል ፡፡ ፡፡ ግቦ ልቀበል ስትል ፤ ተቀበል ይልሃል ፡፡ ሙስና ያስደርግሃል ፡፡ ፡፡ ልቅረባት / ልቅረበው ስትል ፤ ቅረብ ይልሃል ፡፡ ያዘሙትሃል ፡፡ ፡፡ ልጣለው ስትል ፤ ተጣላ ይልሃል ፡፡ ያጣላሃል ፡፡ ፡፡ ልዋሽ ስትል ፤ ዋሽ ይልሃል ፡፡ ያስዋሽሃል ፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል ፡፡ ይመችሃል ፡፡ስጋህ ወፍሮ ፣ ቀልቶ ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ ተመቸህ እኮ ! › ያስብልሃል ፡፡ አንተም ደስ ይልሃል ፡፡ በዛው ትገፋበታለህ ፡፡ ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ጅምናዝየም ቤት መሄድ ይሆናል ፡፡ ሃሳብህ ሁሉ የተመጣጠኑ ምግቦችን ፣ ፍርፍሬዎችን …. መመገብ ይሆናል ፡፡ሃሳብህ ሁሉ ሳውና ባዝ ፣ ስቲም ቤት ፣ማሳጅ ቤት …. ሂደህ መታሸት እና መዝናናት ይሆናል ፡፡ እግርህ ሁሉ ወደ ሲኒማ ቤት ፣ ወደ ናይት ክለብ ቤት ፣ ወደ ሆቴል ቤት ፣ ወደ ግሮሰሪ ቤት ፣ ወደ ሱፐር ማርኬት ፣ ወደ ምናምን ቦታ …….. ይሆናል ፡፡ በእነዚህ ሁሉ ስጋህ ሲመቸው ፡- ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል ፣ መስገድ ያቅትሃል ፣ መጾም ይከብድሃል ፣ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል ፡፡ ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል ፡፡ ደም ብዝት አስይዞ ሴት ያዝልሃል ፡፡ ደም ብዛት አሲይዞሽ ወንድ ያዝልሻል ፡፡ የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል ፡፡ ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል ፡፡ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል ፡፡ ኩላሊት አስይዞ እድሜን በማማረር ያስጨርስሃል ፡፡ ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር ያደርጋታል ፡፡ በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል ፡፡ ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ ፤ እንደ አብርሃም ፣እንደ ይስሐቅ እና እንደ ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ ነበር ፡፡ ሰይጣን ክፉ ነው ፡፡ ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ ያደርገዋል ፡፡ እንዲህ …እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል ፡፡ በኃጢአት የዳበረው ስጋችን አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል ፡፡ ነፍስ ግን እያዘነችና እየተጸጸተች ወደ ሲዖል ትወረወራለች ፡፡ ይህ ከሃዲ ስጋችን አብሮን ላይሄድ ነፍሳችንን ሲያቆሽሽ ኑሮ ከምድር ይቀራል ፡፡ አባቶቻችን ‹ ከስጋዊ ፈቃድህ ይልቅ ነፍሳዊ ፍቃድህን አስበልጥ ፡፡ › ይሉናል ፡፡ ግን አይሆንም ፡፡ የምናያቸው ቆንጆ ሴቶች ፣ የምናያቸው ቆንጆ ወንዶች ፣ የምናየው የልኳንዳ ስጋ ፣ የምናየው መጠጥና ምግብ ሁሉ ያምረናል ፡፡ ስጋችን ያሸንፈናል ፡፡ ነፍሳችን ትሸነፋለች ፡፡ ለገነት ተፈጥረን ለሲዖል እንሆናለን ፡፡ ወገኖቼ ይህ ዘመን ከባድ ነው ፡፡ ገዳም ገብተህ እንዳትመን ዓለም እንደ ወለላ ማር ትጣፍጥሃለች ፡፡ በዓለም ሆነህ ስጋህን እንዳታቸንፍ ጓደኞችህ ፣ ቤተሰቦችህ ፣ ጎረቤቶችህ ፣ ዓይኖችህ ፣ ጀሮዎችህ ፣ ምላስህ ፣ እግርህ ፣ እጅህ ፣ ልብህ እንቢ ይሉሃል ፡፡ በምድር ትሸነፋለህ ፤ በሰማይም ትሸነፋለህ ፡፡ መጨረሻህ ገሀነም ይሆናል ፡፡ በመንፈሳዊ ዓይን በየቀኑ ራሳችንን ብንመረምር ባዶ በዶ ባዶ ነን ፡፡ ጽድቅ የሌለን ፣ ስም ብቻ የተሸከምን በኃጢአት የተሞላን አህዛብ ነን ፡፡ እግዚአብሔር ወደቤቱ ይመልሰን ለመቀላቀል👇 💚 @Mezmurtewahido 💛 @Mezmurtewahido ❤️ @Mezmurtewahido
Показати все...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! የተወደዳችሁ አባቶች፣ ወንድሞችና እህቶች እንኳን ለ2013 ዓ.ም ዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ፡፡ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ሀገራችንን፣ ቤተ ክርስቲያናችንንና አገልግሎታችንን በማሰብ የጋራ የጸሎት መርሐግብር ለማድረግ ታስቧል፡፡ በመሆኑም በሁሉም የማኅበሩ መዋቅር በወርሐ ጾሙ የመጀመሪያ ሳምንት ማለትም ከየካቲት 29/2013 ዓ.ም እስከ መጋቢት 5/2013 ዓ.ም ድረስ አባላትን ያሳተፈ የጋራ ጸሎት እንዲደረግ; ከዚሁ ጎን ለጎን ከአባላት በማሰባሰብና ከማኅበሩ ወጪ በማድረግ በጸሎት እንዲያስቡን ለተለያዩ ገዳማትና አድባራት መባዕ እንዲላክ እናሳስባለን፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን:: ማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት @Mezmurtewahido @Mezmurtewahido @Mezmurtewahido
Показати все...
ልባችሁ እንዲጽናና የጥበብን ፍቅር እንዲሰጣችሁ ፤ የእግዚአብሔርን መጻሕፍት መስማት ውደዱ። ሁልጊዜ ቅዱሳት መጻሕፍትን አንብቡ ፤ የሃይማኖት ትምህርት ቃል ሰይጣንን ያቃጥለዋልና። ሐዋርያት በዲድስቅልያ "እግዚአብሔር መንግሥተ ሰማያትን ከአዝርዕት ሁሉ በምታንሰው የሰናፍጭ ፍሬ መስሏታል ፤ እርሷ ሰው በሚቀምሳት ጊዜ እንደምታቃጥል ሁሉ የሃይማኖት ትምህርት ቃልም እንዲሁ ሰይጣንን ታቃጥለዋለችና" በማለት እንደተናገሩት። እንደዚህ ብታደርጉ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ትሆናላችሁ ሰይጣንም ከነክፉ ሥራዎቹ ከእናንተ ይርቃል ሕሊናችሁም ከሌላው ፍሬ ይልቅ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለማወቅ ይሰባሰባል። ቅዱሳት መጻሕፍትን መስማት ፤ ከሰማይም ይሁን ከምድር ወገን ወዳለው በጎ ነገር ያደርሳልና። ስለዚህም ሁሉ ይጨመርላቸኋል
Показати все...
ነገ ሰኞ በ10/05/2013ዓ.ም ጾመ ጋድ ነው። ሼር በማድረግ ላልሰሙ እንድታሰሙ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።
Показати все...
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ
Показати все...
✝✝✝ይህችን ዓመት ተወኝ!✝✝ 🌿💚ከዓመት እስከ ዓመት - ፍሬን ሳላፈራ - ደረቅ እንደሆንኩኝ በራድ ወይም ትኩስ - ሁለቱንም ሳልሆን - እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ አለሁኝ በቤትህ - ለሙን መሬትህን - እያጎሳቆልኩኝ አውቃለሁ አምላኬ - ፍሬዬን ለመልቀም - እንዳመላለስኩህ ዛሬም ሳላፈራ - እሾህን አብቅዬ - ደርቄ ጠበቅሁህ ያልተደረገልኝ - ያላፈሰሰክብኝ - ያልሰጠኸኝ የለም ነገር ግን ይህ ሁሉ - አላርምህ አለኝ - አልለየኝም ከዓለም የማትሰለቸኝ ሆይ - ተነሥቼ እስክቆም - እባክህ ታገሠኝ የእኔን ክፋት ተወው - መልአክህን ሰምተህ - ይህችን ዓመት ተወኝ! 🌿💚አውቃለሁ ታውቃለህ - ቀጠሮን ሰጥቼ - እንደማላከብር ብዙ ጊዜ አቅጄ - ብዙ ጊዜ ዝቼ - በወሬ እንደምቀር ‹ዘንድሮስ…!› እንዳልኩኝ - አምና ይሄን ጊዜ - ሰምተኸኝ ነበረ ምንም ሳልለወጥ - ‹ዘንድሮዬ› አልፎ - በአዲስ ተቀየረ ፍሬ የማይወጣኝ - እኔን በመኮትኮት - እጆችህ ደከሙ እኔ ግን አለሁኝ - ዛሬም አልበቃኝም - በኃጢአት መታመሙ የቃልህን ውኃ - በድንጋይ ልጅህ ላይ - ሳትታክት ስታፈስስ - ዘመን ተቆጠረ ወደ ልቤ ሳይሰርግ - ሕይወቴን ሳይለውጥ - እንዲያው ፈስሶ ቀረ ቃልህን ጠግቤ - እያገሳሁት ነው - ሌሎች እስኪሰሙ በቃልህ መኖር ግን - አልያዝህ አለኝ - ከበደኝ ቀለሙ ብዙ ጥቅስ አገኘሁ - ከቅዱስ መጽሐፍህ - ገልጬ አይቼ ከራሴ ላይ ብቻ - አንድ ጥቅስ አጣሁኝ - በበደል ተኝቼ ውጤቴ ደካማ - ትምህርት የማይሠርጸኝ - ተማሪ ብሆንም ይህችን ዓመት ተወኝ - ደግሞ ትንሽ ልማር - ታገሠኝ አሁንም! 🌿💚እባክህ አልቆረጥ - በቅዱስ መሬትህ - ልቆይ ፍቀድልኝ ያፈሩት ቅዱሳን - የፍሬያቸው ሽታ - መዓዛ እንዲደርሰኝ የተሸከምከኝ ሆይ - ዛሬም ተሸከመኝ - አትሰልቸኝ አደራ ማን ይታገሠኛል - ጠላት እየሆንኩት - አይሠሩ ስሠራ! አታውጣኝ ከቤትህ - ብዙ ቦታ አልይዝም - ፍሬ ስለሌለኝ ስፍራ የማያሻኝ - ቤት የማላጣብብ - ፍሬ አልባ በለስ ነኝ! ቦታስ የሚይዙት - ባለ ምግባሮቹ - ቅዱሳንህ ናቸው ልክ እንደ ዘንባባ - የተንዠረገገ - ተጋድሎ ጽድቃቸው! ከሊባኖስ ዝግባ - እጅጉን የበዛ - ገድል ትሩፋታቸው! እኔ አይደለሁም - ቦታስ የምትይዘው - የአንተው እናት ናት ሥሮቿ በምድር - ጫፎቿ በሰማይ - ሲደርሱ ያየናት ይህችን ዓመት ተወኝ - ከሥርዋ እሆናለሁ - ባፈራ ምናልባት!.. 🌿💚ይህችን ዓመት ተወኝ - እባክህ አምላኬ - አንድ ዓመት ምንህ ናት ሺህ ዓመት አንድ ቀን - አይደለም ወይ ለአንተ - ዓመት ኢምንት ናት! ይሄ ዓመት አልፎ - ዳግም ‹ዓመት ሥጠኝ› - እስከምልህ ድረስ እባክህን ጌታ - ይህችን ዓመት ተወኝ - የወጉን እንዳደርስ! በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
Показати все...
ለዝች አጭር እድሜ ለዚህ ከንቱ አለም እድሜያችን ተመዞ ላንኖር ዘላለም በድንገት ተጠርተን ላይቀር መሄዳችን መልካም ጥሩ ይሁን ሁል ግዜ ስራችን
Показати все...