cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

👑 አዳም ረታ 👑

ቀንዎን ያሳምሩ 👉የአዳም ረታ እና ሌሎችም እውቅ ደራሲያን ስራዎች 👉ግጥሞች 👉የአማርኛ መፅሀፍት በ pdf 👉 አዝናኝ እና ቁምነገር አዘል ፅሁፎች 👉ሙዚቃዎች እና ሌሎችም የምትፈልጓቸውን አንድ ላይ በ አዳም ረታ ያግኙ። 👉 የመፃህፍት ጥቆማ @AdamuReta @AdamuReta @AdamuReta For cross promotion contact @isrik @isrik

Більше
Ефіопія7 776Амхарська7 309Книги13 375
Рекламні дописи
571
Підписники
Немає даних24 години
-17 днів
-1430 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

10. ጥያቄዎች ለስብሐት ገብረ እግዚአብሔር **** ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር [...] ኢትዮጵያውያን ደራስያን ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡ ከአርባ ዓመት በፊት የጻፈው " ሌቱም አይነጋልኝ " የተሰኘው ልብ ወለዱ ቀን ወጣለት፤ [...] ያለ ቅድመ ምርመራ (ሳንሱር) ታትሞ ገበያ ላይ ውሏል። በልብ ወለዱ ውስጥ የሚገኙት ለአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ትውፊት እንግዳ የሆኑ ጉዳዮች በአንባብያን ዘንድ አዲስ ክርክር ፈጥረዋል ፡፡ የአዲስ ነገር ዓምደኛ በዕውቀቱ ሥዩም ከስብሐት ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡ በሌቱም አይነጋልኝ መግቢያ ላደ በሕይወት የምታውቃቸው ሰዎች ስማቸው ተለውጦ ገጸ ባሕርይ እንደሆኑህ ገልጸሃል ከዚህ በመነሣት ጽሑፍህ የሚለውን ነገር ኑዛዜ አድርገው የሚወስዱት ይኖራሉ ። በዚህ ላይ አንተ ምን ትላለህ? ►ስሜት አይሰጠኝም፤ የራሳቸው ጉዳይ፡፡ እኔ’ኮ ስለ አንባቢው ሳስብ እንደ እኔ ሰው ነውና የሰው ነገር ይመለከተዋል ብዬ ነው እንጂ ከዚያ በኋላ ሞራሉ ወዴት ይወስደዋል? ወጣቱን ምን ዓይነት አርኣያ እኾነዋለሁ? ብዬ አልጨነቅም :: ወጣቱ ከፈለገ ከወላጆቹ ፣ ከፈለገ ከመጽሐፍ ቅዱስ ራእይ ወይም አርኣያዬ ከሚለው ይውሰድ፣ ከእኔ አይደለም፡፡ ከእኔ ከፈለገ ጨዋታ፣ ልብ ወለድ፣ ተረት መውሰድ ይችላል። እንዳንድ ሰዎች ግለ ታሪካዊ የሆነውን አጻጻፍ(Autobiography) ይቃወማሉ? አንዳንድ ሰዎች ደግሞ አስፈላጊነቱን አብራርተው ይናገራሉ። ►የሚቃወሙት ይቃወሙ !! ... አብራርተው የሚያወሩት ዓላማ ሲኖራቸው ነው፡ ፡ በርናንድ ሾውን ታውቀዋለህ? እርሱ መጀመሪያ መግቢያውን ይናገራል። የእንግሊዝን ሕዝብ በሙሉ ሊያስተምር ስለ ተነሣ ዓላማ አለው። እኔ ዓላማ የለኝም። ልብ ወለድ ማንበብ ስለምወድ ደስ ይለኛል፤መጻፍም ስለምወድ ጻፍኩት፡ ፤ ከዚህ በኋላ የሚወደው ይወደዋል፤ የሚደብረው ሰው ይደበራል። አንዳንዱ ደግሞ እርግማን ያወርዳል፤ ደግሞ እርግማን ሲያወርድ አሪፍ ነው። በነገራችን ላይ አንተ ሌላ ጥያቄ ካለህ ጠይቀኝ ወይም እንደገና ጠይቀኝ በሌላ መልኩ? መጽሐፎችህ ፖርኖግራፊ ናቸው የሚሉ ሰዎች አሉ ፡፡ " ፖርኖግራፊ " ናቸው ሊባሉ ይችላሉን? ►እኔ የሚያናድደኝ ሒስ ምናምን የሚሠሩ ሰዎች ለእንጀራቸው ሲሉ "ፖርኖግራፊ “ ናቸው ይላሉ፡፡ ሕይወት ፖርኖግራፊ አይደለም? የምንወልደው በምንድን ነው? ስለዚህ ተጻፈ፡፡ " ፖርኖግራፊ " ማለት እንዲቆምብህ እና እንድታደርግ የሚያደርግ ማለት ነው፤ ይኼ እኮ ሕይወትን እና እሱን መሰል ጻፍን እንጂ "ፖርኖግራፊ " አይደለም፡፡ አማርኛ ልብ ወለድ ለብዙ ዘመን ያክል የዕርቃንነትን ሚና ረስቶ የቆየ ይመስሰኛል፡፡ ልክ ያንተ ልብ ወለድ ሲመጣ ድንገት የሆነ የሚያስደነግጥ ስሜት ይፈጥራል ብለህ አልገመትክም? ►እኔ የገመትኩት ከዕለታት በአንድ ቀን ከተነበበ " በቃ እንዲህ ነው መጻፍ " ይላል እንባቢው ብዬ ነበር፡፡ ሕይወት ነዋ ! ሕይወትን ደብቀህ "ሶሻል ሪያሊዝም " የሚለውን ፍልስፍና እኔ አላምንበትም:: ሌላ መንገድ አለ ሕዝቡን የምታሳድግበት፡፡ ይህ ደግሞ የተጻፈው ሰውን ለማስደሰት ነው። ኑሮ አሳይተኽው አሪፍ ተደርጎ ተጻፈ ብሎ እንዲያነብ ነው እንጂ ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡ አሁን ሳስበው የገረመኝን ልንገርህ፡፡ ስጽፈው 26 ዓመቴ ነው። ስለ ሕይወት ያኔ ከማውቀው አሁን የጨመርኹት ምንም ነገር የለም፣ አይገርምም? በሕይወት ላይ ያለኝ አመሰካክት አልተለወጠም ነው የምትለኝ? ► "ሌቱም አይነጋልኝ " ፈረንሳይ ነው የተጻፈው፡፡ "ትኩሳት" እዛ ተኑሮ እዚህ ነው የተጻፈው። በሩቁ መጻፍ የበለጠ ያጎላዋል? ►በእርሱ ምክንያት አይደለም፡፡ “ሌቱም አይነጋልኝ ን ፈረንሳይ ባልሄድና ሌላ ኑሮ ውስጥ ባልገባ ኑሮ እዚሁ እጽፈው ነበር :: እንዲቆይ እንዲበስል ያቆየሁት ነገር አይደለም ፤ የአጋጣሚ ጉዳይ ነው ትኩሳትንም እዚያው ብቆይ ኖሮ እና ሌላ ጉዳይ ባይዘኝ እዚያው ይጻፍ ነበር። ስለ ሐሳፊነት እያነሡ የሚጠይቁህ አሉ፤ የሚጽፉም አሉ፤ እንተንም በግንባር ቢያገኙ ሊጠይቁህ ይችላሉ፡፡ እንዴት ነው የምታልፈው? ►እኔ ሐላፊነት ምናምን አለብህ ቢሉኝ አይገባኝም፡፡ ሕግ ሊጠይቅህ ይችላል ? ► ይጠይቀኝ ! ሐላፊነት አለብህ ነው ያልከው? ሂድ... ተነፋ፤ ሐላፊነትህን አንተ ውሰድ፡፡ እኔ ሐላፊነት ያለብኝ ሕግ ሳልጥስ ለመኖር እና ከወለድኩም ልጆቼን ለማሳደግ ነው፡፡ ሌላ ሐላፊነት የለብኝም፡፡ መኖር ነው የኔ ሐላፊነት። የኢትዮጵያ ሕግ የወሲብ ሥነ ጽሑፍን የሚፈቅድ አይመስለኝም ። ከሕጉ ጋርስ እንዴት መጻፍ እና መኖር ይቻላስ? ► ሕጉ ይምጣና ያፋጠኝ :: ምን አልኩ? ተነሡ! መንግሥትን እንገልብጥ አላልኩ፣ ተነሡ! ይኼ እ... መባ… ይቅር በአ … በቂ… ብቻ ይሁን አላልኩ! ብያለሁ? ታድያ ምን ሌላ ነገር አልኩ? ሕዝቡ የሚኖረውን እኔ እንዳየሁት ጻፍኩኝ ደግሞም ለማንም አልጻፍኩም ለራሴ ደስ ስላለኝ ጻፍኩ ስለዚህ እኮ ነው አሪፍ ጸሐፊ የሆንኩት፡፡ እነ ጆይስ እኮ ተሰደዋል። እኔ ግን ዕድለኛ ስለ ሆንኩ ደሞዝ እየተከፈለኝ ነው የጻፍኩት፡፡ “ሌቱም አይነጋልኝ " ወደ ኤስኪሞ ቋንቋ ቢለወጥ እዛ ሙቀትም ምንም የለም፤ ግን በደንብ ነው የሚገባቸው። እኔ ስለ ኤስኪሞዎች ሳነብ እገባለሁ ፣ እየበረደኝ ። ከዚያ ውጭ በዓላማ የሚነሡ ይቅናቸው። ባንተ አመለካከት ፣ ሴተኛ አዳሪነት አንዳንዶች እንደሚሉት የኢኮኖሚ ችግር ነው ወይስ የተፈጥሮ ሕግ ነው? ►እኔን ተወኝና በእንግሊዝኛ ልጥቀስልህ (Prostitution is the oldest profession in the world) እደግመዋለሁ (Prostitution is the oldest profession in the world) አብርሃም ወደ ግብፅ ሲገባ ሚስቱን ሣራን ፈርዖን ሚስቴ እንደ ሆንሽ ካወቀ ይገድለኛል፡፡ ስለሚፈልግሽ እኀቴ ነሽ ብለን እንግባ ብሎ ሚስቱን አላስ. . . ? አዲስ ነገር ጋዜጣ ቅዳሜ ኅዳር 14 ቀን 2000 ዓ.ም የፎቶ ስዕል የበዕውቀቱ ስዩም Swipe Januda ፣ የጋሽ ስብሐትን Ras Habte እንደሆነ ከመድህ ተነግሮኛል , ሁለታችሁንም ከልብ አመስግናለሁ🙏❤️ © Teshale kebede Bedriya
Показати все...
መሸ-ጋ-ገር (ልዑል ሀይሌ) ስታልፍ ዝንፍል ፥ዝንፍል፤ ሳያት ግንፍል ፥ግንፍል፤ ልቤን እንደ ሙሴ ለሁለት ፥ ስትከፍል፤ ባሳብ ተሻግሬ ወደ ተስፋ ምድር ህልሜ ላይ አምጥቻት፤ ስተኛ እቅፌ ውስጥ ነግቶ ጎኔ አጥቻት፤ አወይ በትር አይኗ አወይ በትር ልቧ አወይ በትር ጥርሷ፤ ልቤን ከፍላ አሻግራ ኋላ መመለሷ፤ በትሯን ንጠቃት እያልኩኝ ስከሳት፤ እኔን በትር ሰጥቶ የሷን ልብ ከፍሎ ወደ'ኔ መለሳት፤ . [አወይ በትር አይኔ አወይ በትር ጥርሴ አወይ በትር ልቤ፤ ከፍዬው ተመለስኩ የትላንት ምግባሯን ሐጢያቷን አስቤ፤ . ተራዬ ደረሰ!.. ብድሬን በምድር ኖሬ መለስኩላት፤ መቼ ተረዳችኝ መች አሻገረችኝ በምነት ስከተላት፤] . መቼም!.. [ሕልም አይጠገብም ተኝቼ ታየችኝ፤ ሳንገላታት አደርኩ እንዳንገላታችኝ፤] . ነቃሁ!.. በየት አልፋ ይሆን?!.. ሐምሌ 21,2015 ዓ.ም. @getem @getem @getem
Показати все...
አዳም በገጸ-ባህሪያቱ ለምን ይወቀሳል ? *** "በነገራችን ላይ አዳሙ ስለተባለ አውቃለሁ ባይ፣ ድራሸ ቢስ የዘመኑ ደብተራ ላወራ አልፈልግም" (የስንብት ቀለማት፣165) የድህረዘመናዊነት (Postmodernism) ማዕከላዊ ዕሳቤ የሚያርፈው ተፈጥሮኣዊ አድርገን የተቀበልናቸው ገናን እውቀቶችን፣ እሳቤዎችን፣ ብያኔዎችን…ተፈጥሮኣዊ እንዳልሆኑ በማሳየት ነው ትላለች፤Linda Hutcheon፣ 'The Politics of Postmodernism' በተሰኘው መጽሃፏ፡፡The postmodern initial concern is to de-naturalize some of the dominant features of our way of life... እነዚህን ገናን ብያኔዎችና የሕይወት ዘይቤዎች የባህል ስሪት (social construction) በመሆናቸው ነው፤ እንደተፈጥሮአዊ፣ የማይለወጡና ዘላለማዊ እውነት አድርገን እንዳንወሳደቸው አሳብያኑ የሚያሳስቡን፡፡ አዳምም ልክ እንደ ድህረዘመናዊ ከያኒያን ሥነጽሁፋችን ውስጥ ቀኖናዊ የሚመስሉ ልማዶችና ብያኔዎችን በመሻር አዳዲስ ስልቶችን በድርሰቶቹ ውስጥ አስተዋውቆናል፡፡ ይኼ ማለት ግን አዳም የድህረዘመናዊነት እሳቤ አራማጅ ወይም አቀንቃኝ ደራሲ ነው ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን የድህረዘመናዊነት እሳቤዎችና ቴክኒኮችን በጥንቃቄ እየወሰደ በድርሰቶቹ ውስጥ በስፋት ይጠቀማል፡፡ በሃገራችን ያልተሞከሩ የአከያየን ዘይቤዎችን ሞክሮ የተሳካለትም ጥንቁቅ አንባቢና ያነበበውን አውዳዊ አድርጎ በማምጣት የተካነ ደራሲ በመሆኑ ነው፡፡ በድህረዘመናዊ ልብወለዶች ውስጥ እንደሚስተዋለው፣ አዳም የገጸ-ባህርያቱ ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን ራሱን እንደአንድ ገጸባህሪ አድርጎ በ'የስንብት ቀለማት' ውስጥ ሚና ወስዶ ተጫወቷል፡፡ ተጫውቶም ተሳክቶለታል፡፡ አዳም በዚህ ልብወለዱ ውስጥ መንታ ማንነትን ተላብሶ ሲተውን እናገኘዋለን፡፡ በደራሲነቱ የምናውቀው አዳምና አስረግዞ የጠፋው… አዳ(ሙ)ም፡፡ በሁለቱም ማንነቱ ገጸ-ባህሪያቱ አጥብቀው ይነቅፉታል፣ ያንጓጥጡታል፣ ያሙታል፡፡ ያቺ ሰዎችን በሴራና በተንኮል ጠልፎ መጣል 'ሆቢዋ' የሆነው በ'የስንብት ቀለማት' ውስጥ የምንተዋወቃት ሳላይሽ ምናልባት የምታፈቅረው አዳሙ የተባለ "የዘመኑ ደብተራ" ጥሏት ስለሄደ ይሆን? ባህሪዋ የከፋው! ማን ያውቃል?... እስኪ ከሳላይሽ አንደበት፤ "ከለይኩን ጋር ከተቀራረብን በሁዋላ አንድ ቀን በጨዋታ መሃል ባልጠበቅሁት ጊዜ የአዳሙ ወዳጅ ('ወዳጅ' የሚለው ቃል አያስቅም? በነገራችን ላይ አዳሙ ስለተባለ አውቃለሁ ባይ፣ ድራሸ ቢስ የዘመኑ ደብተራ ላወራ አልፈልግም) አልነበርሽም እንዴ? አለኝ ሳቅ እያለ፡፡ ምናልባት ስለአንቺ ሁሉን ነገር አውቃለሁ ሊለኝ እንደሆነ ይገባኛል፡፡ "እንዴት አወቅህ አንተዬ? ምናምን አልኩት የተገረመ መስዬ፡፡… "'በደንብ አውቅሻለሁ' ሊለኝ የቅርብ ጓደኛዬ ኅብስት አዲስአባ ኤዞፕ የተባለ አንድ የግሪክ መድሃኒት ቤት እንደምትሰራ፣…ወዳጄ የነበረው ደራሲ አዳም (የብዕር ስሙ ነው፣ ሌላ ስም ጠፋ እንዴ?) በጥጋብ አገሩን ከድቶ እንደሸሸ፣ ብቻ ሌላም ሌላም የረባ ያልረባውን ዘርዝሮ ነገረኝ፡፡" አዳም ዲሞክራት ደራሲ ነው፡፡ የመለመላቸው ገጸ-ባህሪያት ሚና-ሚናቸው ሰጥቷቸው ሲጫወቱ ከላይ ሆኖ መመልከትን አልፈቀደም፡፡ እሱም የእነሱ አካል ሆኖ ቀረበ እንጂ፡፡ ለነገሩ ሁሉም ነገር ታስቦና ታቅዶ የተዋቀረና የተሰራ ነው ካልን፣ እኛም በሆነ መንገድ ገጸ-ባህሪ ነን፤የሆነ ሚና ተሰጥቶን የምንጫወት፡፡ ስለዚህ እውንና ቅዠት የሚሉ ዳይኮቶሚዎች ብዙም አያስኬዱንም፡፡ "ሰቨን ዶርስ ሁለት ቀን አደርኩ፡፡ ከማን ጋር መሰለህ የተደበቅነው ከአዳሙ ጋር፡፡ የሚያውቃት ልጅ ነበረች እዛ የምትሰራ ስሟ ጠፋኝ የሆነ የወፍ ሥም ነገር [የቹቹ እናት ላስታ ነች]፡፡… አዳሙ አለ እባክህ? አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ አካባቢ ከአንድ ሚጢጢ ቀይ ልጅ ጋር [ሳላይሽ] አንዳንዴ አየው ነበር፡፡ ሆላንድ ተተከለ አይደለ እንዴ? ሆላንድ ሄደ? ፎጋሪ ነበር አቦ፡፡ ለምን? ለትምህርት ወይስ አቀጣጠነ? አንዳንዱ ድምጹን እያጠፋ ይሰወራል፡፡" (ስ.ቀ፣319) አዳም በዚህ ውድ ልብወለዱ ውስጥ ፍዝ ገጸ-ባህሪ ሆኖ ነው የተከሰተው፡፡ ሌሎች ገጸ-ባህሪያት ናቸው ስለሱ የሚነግሩን፡፡ በገጸ-ባህሪያቱ ስለአዳም የሚተረክልን አንዳንድ ነገሮች ግነት አያጣቸውም፡፡ እንደቹቹ ያለች ሴት የምታቀርበው ወቀሳ ግን ቸል የሚባል አይደለም፡፡ በሚያምረው 'ኮልታፋ' አንደበቷ ቹቹ ትናገራለች፤ "እማ አፍ አውጥታ ̍እኔ እናትሽ ሸልሙጣ ነኝ ብላኝ አታውክም፡፡ ኩላቷ ያሳዝናል፡፡…አባት የለኝም፣ ማለቴ አባቴን አላውከውም፡፡ ካላሳደገኝ ̍አለኝ̍ ማለት እችላለሁ? ድልክና ይሆናል አይደለ?...በክልብ ደሞ አባትሽ ̍አዳሙ̍ ይባላል እና ልጅ ከእኔ እንደወለደ አያውክም፡፡ አሁን የት እንዳለ እንጃ አለችኝ፡፡ እማ ሃያ አይሞላትም ስትወልደኝ…ይገልምሻል እስከዛሌ አዳሙን ትወደዋለች፡፡አምልጧት ስትምል 'አድዬ ድለስ' ትላለች፡፡ሺት ነች አይደለ፡፡እንደዛ ስትል ይደብለኛል፡፡ ማነው ይሄ ደግሞ አድዬ?̍ ምናምን እላታለሁ፡፡̍ዝምበይ̍ ትለኛለች፡፡…ሃንድለድ ፐልሰንት እልግጠኛ ነኝ ከሴተኛ አዳሊ በመውለዱ ነው የጠፋው" (ስ.ቀ፣387) አንድ ማሳያ ላክል፤በ'የስንብት ቀለማት' ውስጥ በገጣሚነቱና በሰዓሊነቱ የሚታወቀው የወርቁ ዕንቁባህርይ ስራዎች ከአዳም ረታ ስራዎች ጋር ይመሳሰላሉ በሚል ለሚቀርበው ̍ትችት̍ ዮሃንስ ወላይሶ የተባለ የባህል ሃያሲ የሰነዘረውን ትችት እንመልከት፡፡ "በስራ ውጤታቸው ብቻ ሳይሆን (ዱካው ቀርቶ) በከያኒነት ማንነታቸው ወርቁና አዳም ይለያያሉ፡፡ ደራሲ አዳም በአሁን ጊዜ ሆላንድ ይኖራል ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ በስደት ይሁን በጥጋብ፣ በስራ ይሁን በልመና አይገባኝም፡፡ እንዴት ደራሲ እዛ አውሮፓ እየኖረ ስለዚህ አገር ወጣ ገባ ይጽፋል?...ከሃገሩ ለምን ይሸሻል? በሽሽቱ ምን ሊያገኝ? ካላገኘ ደግሞ ምን ሊፈጥር?" በነገራችን ላይ የአዳም የልጅነት ስም አጠራሩ "አዳሙ" ነው፡፡ በአዳምና በአዳሙ፤ በደራሲው አዳምና በንፋስ ስልክ ወዳጆቹ በተደጋጋሚ ስሙ በሚነሳው አዳም መካከል የተሰመረው መስመር ገጥሞ ይቀላቀላል፡፡ ልክ እንደዚሁ በምናብ የተፈጠረችው የሻገር ሆቴል ባለቤቷ በትግስት (ቲጊ) እና በወዳጅዋ በታዋቂው ሙዚቀኛ ካሳ ተሰማ መካከል የተሰመረው መስመር ሲደበዝዝ በልብወለዱ ውስጥ እንደምናነበው፡፡ ለዚህ ነው 'እውናዊ የትኛው ነው?'፣ 'ምናባዊውስ ? '...የሚለው በልብወለዱ ውስጥ የሚምታታብን፡፡ መግቢያዬ ላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት በድህረዘመናውያኑ እሳቤ ውስጥ እውናዊና ምናባዊ፤ ተፈጥሮኣዊና ሰው ሰራሽ የሚባሉ ወሰኖች ይፈርሳሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ እያንዳንዳችን "እኔ" ወይም "ሰው" ብለን የያዝነው አረዳድና ግንዛቤ ሳይቀር ማህበረሰብ ሰራሽ እንጂ ተፈጥሮኣዊ አይደሉም፡፡ በዚህም እውኑ ልብወለዳዊ፣ ልብወለዳዊው ደግሞ እውናዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ፈረንሳያዊ ፈላስፋ Gilles Deleuze የኪነት (ሥነጽሁፍን ጨምሮ ሌሎች ምናባዊ የፈጠራ ሥራዎች) ዋነኛ ተግባር ማስተማሰልና የወል የሕይወት ልምድ ወይም ዘይቤ ማስተጋባት አይደለም ይለናል፡፡ ከዚያ ይልቅ ተቀብለነው የምንኖረው የሕይወት ልማድና ብያኔ በሃሳብ መነቅነቅ ነው የኪነት ተግባር፡፡ ከዚህ ከተነቀነቀው ወይም እንዲታወክ ከተደረገው ልማድ ውስጥ ከያኒው ሌላ አይነት የሕይወት መንገድ እንዳለ የማሳየት፣ አማራጭ ዓለማትን የመስራት ግዴታ ይወድቅበታል፡፡ "Literature would not be based
Показати все...
on representing or expressing some common worldview or shared experience; literature Should shock, shatter and provoke experience." አዳምም በድርሰቶቹ ውስጥ አዳዲስ የሕይወት መንገዶችን በመቀየስ፣ ለሃገራችን እንግዳ የሆኑ አዳዲስ ስልቶችን በማስተዋወቅ፣ ከምንም በላይ ደግሞ ከዚህ ለዛዛና ድግግሞሻዊ ዓለም አውጥቶ በፈጠራቸው ኪናዊ ዓለማትን ውስጥ ገብተን እንድንደሰት ማድረግ ችሏል፡፡ ለዚህ እኮ ነው አዳም ኹነኛ ደራሲና ፈላስፋ ነው የምለው ! *** መልካም ልደት "የእኛ አዳም " ፤ ብዙ ፍቅርና ስስት !🎂🎂🎂
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሕፅናዊነት - አጭር የግል ማስታወሻ፦ “ሕፅናዊት” አዳም ረታ የፈጠረው አዲስ የአጻጻፍ ስልት (Method) ነው። ከአዳም በኋላ የሚነሡ ጸሐፍያን አዋጭ ሆኖ እስካገኙት ድረስ የአከያየን ስልቱን በድርሰት ሥራቸው ቢከስቱት የሚያስኮንን፣ የሥራቸውንም ዋጋ (credit) የሚያሳጣ አይደለም። እንዲያውም ሕፅናዊነትን እንደ አንድ የትረካ አማራጭ መንገድ በመገልገላቸው ሊበረታቱ ይገባል። “ሕፅናዊነት” በራሱ ተረክ (story) ሳይሆን የድርሰት አጻጻፍ መሣሪያ (literary device or instrument) ነው። አዳም ረታ “ሕፅናዊነትን” ለመዘየድ ረዥም ርቀት ለመጓዝ የተገደደው ያለንበትን የዘመን ጠባይ፣ መረባዊ ግንኙነታችንን፣ ውስብስብ ሕይወታችንን፣ ለውጦችን ሳያጓድል ለመግለጽና ለመወከል የሚያስችል ሁነኛ ቴክኒክ ስላጣ ነው። ወደ “ሕፅናዊነት” ያመጡት ገፊ ምክንያቶች አሉ። ምናልባትም አዳም ረታ ከአንጋፋዎቹ የሀገሩ ከያኒያን ዘንድ ነባራዊውን ዘመንና ግንኙነታችንን በመግለጽ ረገድ የሰመረ የአጻጻፍ ስልት ንድፍ ለማግኘት ቢታደል ኖሮ ድካሙና ኀሰሳው ይቀልለት ነበር። የእነርሱ ፈለግ ላይ የራሱን እሴት ጨምሮ ከመከተል ወደ ኋላ የሚል አይመስለኝም። እኛ ሀገር ሲሆን እንደ እንግዳ ነገር ከተቆጠረ አላውቅም። የሥነ ጽሑፍ ባሕላቸው በዳበረ ሀገራት ውስጥ ይህ የተለመደ ነው። “ሕፅናዊነት”ን የሚገለገሉ ወጣት ከያኒያንን በግልብ ኂስ ማግለል፣ “ሕፅናዊነት” አዳም ረታ እንደማንኛውም ሰው ኖሮ ሲያልፍ አብሮት ሊሞትና ሊዘነጋ የሚችል የአጻጻፍ ስልት እንደሆነ ያለመገንዘብ ውጤት እንዳመጣው አስባለሁ። ሌሎች ጸሐፊያን ስልቱን አጎልብተው ባይገለገሉበት “ሕፅናዊት” በአዳም ረታ ሥራዎች ብቻ ተወስኖ ይቀራል። ያ ማለት የአጻጻፍ ስልቱ በሌሎች ደራሲያን የሚዳብርበትን፣ የሚያድግበትን ዕድል አያገኝም ማለት ነው። ደራሲ ሙሉጌታ አለባቸውም በ“መሐረቤን ያያችሁ” መጽሐፉ መግቢያ ከአዳም ረታ የሕፅናዊነትን የአጻጻፍ ስልት የተዋሰበትን ምክንያት ሲያስረዳ “ታሪኮቹ የተዋቀሩበት ዘዴ የአቶ አዳም ረታ “ሕፅናዊነት” የተሰኘ የአጻጻፍ ስልት ነው። እነዚህን ታሪኮችን ለመንገር ተመራጩ ዘዴ ሆኖ ስላገኘሁት አመስግኜ ወስጄዋለሁ። ሕፅናዊነትን የማስቀጠል ደፋር ሙከራዬም ነው!” ሲል የገለጸውም፣ ይህንኑ በመረዳቱ ነው። አዳም ረታም በ“አብርሆት” መጽሔት ቃለ ምልልሱ ላይ ኮስታራ ከሆነ ወይም የተባ የሥነ ጽሑፍ፣ የባሕል ኂስ ካለበት ኅብረተሰብ እና ልብ ወለዱ እንኳን ንዑስ ዘውጎች ካልተሰየሙለት ዘመናዊ ከተባለ የሥነ ጽሑፍ ባሕል ስለመመዘዙ ያወሳል። ይሄ እጥረት በሆነ መልክ ድጋፍ ያጣ ደራሲ እንደሚያደርገው፤ የራሱን ፍልስፍና ሲናገር በአገራችን የመጻፍ ካርታ ላይ ከማንና የት ጋር እንደምናስቀምጠው ግራ ሊያጋባን እንደሚችልም አልሸሸገም። ይሄ ባይተዋርነት ሆነ ተብሎ ከሚሰነዘር አግላይነት ጋር ሲደመር ሕፅናዊነት የሚለው ቃል ገቺ ወይም አጋጅነት እንደሚኖረውም ገልጿል። “ሕፅናዊነት”ን ያገኘው በብዙ ኅሰሳና ምርምር ውስጥ አልፎ ነው። በ“ሕፅናዊነት” (በእንጀራና ኢንጆሪ፣ በሥግር ልብ ወለድ) የአጻጻፍ ስልት ላይ የዲበ-አካላዊና አእምሮአዊ ኑባሬ (Metaphysiclal and Ontological) ጥናቶችን በማድረግ መግለጫ (ማኒፌስት) ያቀረበውም አጽንዖት እንዲሰጥለት ስለፈለገ ነው። ከእርሱ በኋላ የሚመጡ ጸሐፊያን፣ እንደ እርሱ እንዳይዳክሩ “ሕፅናዊነት”ን አዋጭ ሆኖ እስካገኙት ድረስ አጎልብተው እንዲጠቀሙት መነሻ ዳና እና ተሻጋሪ አበርክቶ ለመተው መሞከሩም ነበር። “ሕፅናዊነት”ን እንደ አንድ የአጻጻፍ ስልት ከመገልገል ባለፈ በተጽዕኖ ያመለጡ ተወራራሽ ጽሑፎች (texts)፣ የገጸ ባሕርያት ምስስሎሾችና ቅጂዎች (imitations) ከአዳም ረታ በሥራዎቹ የተገኙበት ሌላ ከያኒ ሲኖር በአደባባይ መጽሐፍ ገልጦ፣ ገጽ ጠቅሶ መሞገት፣ በተጨባጭ መረጃ አስደግፎ መተቸት ይገባል። እንዲህ ዓይነቱ ልማድ ደራሲውም ለተጠየቅ ራሱን እንዲያሰናዳ ያደርገዋል። ይህ ካልሆነ ግን በደፈናው የሚነሡ ግልብ አስተያየቶች እርባና አይኖራቸውም። ዘላቂ እሴትንም አይጨምሩም። ከዚህ ውጪ “በጎ ተጽዕኖ” እንዳለም ልብ ማለት ያስፈልጋል። ልክ ሁሉም የዓለማችን ደራሲ ፍጹም ራሱን በራሱ እንደፈጠረ አድርጎ የመውሰድ ዝንባሌ ስሕተት ነው። ከተጽዕኖ የሚያመልጥ ከያኒ አለ ለማለት ይቸግራል። እንዲያውም በዓለም የተደነቁ ጸሐፊያን አንዳቸው ከአንዳቸው የተዋረሱት የተለያየ “ተጽዕኖ” አለ። ማን ማን ላይ በምን መልኩ ተጽዕኖ እንዳሳደረ የሚያሳዩ ካርታዎችም በጥናት ተደግፈው ይቀርባሉ። ራሳቸው ከያኒያኑም ያለመሸፋፈን ማን ተጽዕኖ እንዳሳደረባቸው ይናገራሉ። እናም “ተጽዕኖን” በደፈናው የማነወር አካሄድም አላዋቂነት አለው። በመጨረሻም Adam Reta የሚነበቡ፣ የሚጠኑ፣ የሚተነተኑና የሚያወያዩ ኪናዊ ድርሳናትን ስለሰጠኸን እናመሰግናለን። መልካም ልደት!
Показати все...
ጊታሮቻችን ከጣቶቻችን የረዘመ እድሜ ይኖራቸዋል። ምን አልባት። ድምጾቻችንም እኛ ዝም ባልንበት ይጮኻሉ። ምንአልባት። ፎቶዎቻችን በእጥፍ ይሸጡም ይሆናል። ምን አልባት። ንግግራችን ወይ በግርምት ወይ በእርምት ይነሳ ይሆናል። ምን አልባት። አይጠፋም ሞታችንን ጠብቆ "ተረዳዋችሁ" የሚለን:: ምን አልባት። አይጠፋም አይቶን የማያውቅ ቀጣፊ "አታውቁትም" ብሎ ይዋሽብንም ይሆናል:: ምን አልባት። ግና ምናችን ነው ያኔ? ያን ጊዜ ንግግራችን "አይመጣም" ካልነው የሩቅ ዘመድ ከመሰለን ጣዕረ ሞት ጋ ነው። ያቺ ሰዓት ምነኛ ታስፈራለች? የምናውቀውንም የማናውቀውንም ጥለን የምንሄድባት ቅጽበት። የነበረው እንዳልነበር የሚሆንበት ቅጽበት። የተፏከርንበት ጉልበት የሚሽመደመድበት የተዳራንበት ስጋ በትል የሚወረርበት። ያፈርነውንም የኮራነውንም እኩል የምንጥልበት። ወገብ ይዘን የሰደብነው ወገን ለይተን ያሞገስነውንም እኩል የምንረሳበት። የበለጠንን ሁሉ ያብጠለጠለው ቃላችን ወደምንምነት የሚቀየርበት። ያኔ እንደአውሎ ነፋስ የፈጠነው ሰውነት በገመድ ይጎተታል! ያኔ ሀገር ያጨበለጨበለት ውበት በሳምንቱ ይሸታል! ያኔ በኩንታል የተናገረ ምላሳችን አፈር ሲጭኑበት ዝም ይላል! የተነሳናቸው ፎቶዎች = ምንም የገጠመናቸው ግጥሞች = ምንም የጻፍናቸው ሙዚቃዎች = ምንም Interview እና internet ወደሌለበት። ምንም የማናስበበት። ግን ምንም ወደምንሆንበት ሰዓት መሄዳችን አይቀርም። ያኔ የሚወዱንም የሚጠሉንም አይታወሱንም። አብቅቷልና። ያኔ የምንጠላቸውም የምንወዳቸውም አይታሰቡንም። አብቅቷልና። የጠረጠርነው ወይም ያመንነው "እግዚአብሔር" ብቻ ይቀራል። ኤልያስ ሽታኹን
Показати все...
አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን? እሱባለው አበራ እንደትላንት ተወልደን ዛሬ ላይ እድሜያችን ስንት ደረሰ? ወጣትነታችን ወደ ፊት የሚያራምደን መስሎን ተሞኘን። ዕቃቃችንን ስንጥል፥ ጨዋታችንን አልጠገብንም ነበር። ድክ፥ ድክ ያልነው በወጉ ዳዴ ሳንል ነው። ልባችን ላይ የሚነደው የጉርምስና እሳት ደረታችንን ሲፋጅ ሰፊ መንገድ ያለ መስሎን ነበር። አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን? ከአባታችን ወገብ የተከፈለው ዘር፥ በእናታችን ማኅጸን እንቁላል ሳይመታ፤ ፅንስ ሳንሆን፥ ሥጋችን ሳይቦካ፥  አጥንታችን ሼር ሳይሰድ፥ ጅማታችን ሳይዘረጋ፥ ሽል ሳንሆን በፊት. . . ክፉ ዕጣ ቀድሞናል። አንዳችን ለአንዳችን ጠላት ተደርገናል። ለሞትም ታጭተናል። ሳንመርጥ ወግነናል። ደርሰን ባልበደልነው፥ ባልሠራነው ታሪክ. . . አክ እንትፍ ተብለናል። አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን? እኔና አንተ ምንም እንኳ ወደ ፊት መጓዝ ብንፈልግም፤ ይሄ ሀገር የሚሄደው ወደ ኋላ ነው። ዳገቱን ወጣን፥ አቀበቱን አሸነፍን፥ ተራራውን ረታን ስንል. . . እየተንሸራተተ መቀመቅ ይዞን ይወርዳል። በየቀኑ ትርጉም አልባነትን እንድናንከባልል ተፈርዶብናል። አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን? አናምንም። ግን ዕውቀት የማይዘልቀው የድንቁርና እና የአረመኔነት ዘረመል ሥጋ ለብሶ ያለው እዚህ ሀገር ነው። ኅዘንተኞች ሳለን መጽናኛ የለንም። ፍርፋሪ እሴት ሳይቀር ነጠቁን። ረክሰው አረከሱን። የሤራ ፖለቲካው ጉንጉን ፈጣሪ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበብ በላይ ሳይረቅቅ አይቀርም። እግዚዖ! አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን? ከተወለድን ጀምሮ አላስተኙንም። ታዲያ  ሕይወታችን ስለምን ቅዠት በቅዠት ሆነ? ማለት  መቼ አስተኝተውን? መቼስ ተደላድለን? እስከ መች እንደምንኖር አናውቅም። ሕይወት አጭር ናት፤ እዚህ ሀገር ደግሞ እጅግ በጣም አጭር ናት። ሕልውናችን ከእኛ ቁጥጥር ውጪ ነው። ብንነቃም፥ ብናንቀላፋም ሕይወት ጭራቅ መልኳን ለአፍታ አትቀይርም። የቸገረ ነገር! አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን? እንዴት እንደሆነ ባናውቅም እንደ ትውልድ አምክነውናል። ሳንወለድ ገድለውናል። የእናት ጡት ሳንጠባ አስረጅተውናል። ቆምረውብናል። ቅያሜውን ሳናውቅ፥ ጦርም ሳንገጥማቸው፥ ያለ ወግ ድል አድርገውናል። ያረፈብን የጀግናም አይደለ፥ የፈሪ ዱላ ነው! አየህ ወንድሜ ካልጠፋ ሀገር የት እንደተፈጠርን? ዳሩ ምርጫ አልነበረንም። @EsubalewAberaN @Human_Intelligence @Human_Intelligence
Показати все...
«እንጋባ» ሲል ጠየቃት፣ አሳምነው። አልተቀበለችውም አስማሩ። «ወንድምና እህትነቱ ይበልጣል» አለችው። ተስማሙ። ቤቷ እየመጣ ይጠይቃታል። ቡና ታፈላለች ይጠጣሉ፣ካላት ታቀርባለች – ይበላሉ። አውግተው ይለያያሉ። የትዳር ነገር ዳግም አለተነሳም። አሳምነው አንድ ቀን በጠራራ ፀሐይ መጣ። እንደመጣ የደረበውን ሹራብ አውልቆ አስቀመጠ።ስለሙቀቱ ብዙ አውርተው ተለያዩ። አስማሩ አሳምነው ረስቶት የሄደውን ሹራብ ልብሷን ስታጥብ አጠበችለት። ዳግም ሲመጣ ደርቦ ደራርቦ ነበርና የሚያወልቀው እንጂ የሚደርበው ልብስ አላስፈለገውም። ጃኬቱን አውልቆ ሄደ። አስማሩ እሱንም አጥባ አኖረችው። ሱሪውን ደርቦ መጣ «ወበቀኝ» አወለቀው። አስማሩ አጥባ አኖረችው፣ ካፖርቱን ጥሎ ሄደ፣ አጥባ አኖረችው። አንድ ቀን በጠራራ ፀሐይ ብርድ ልብሱን ለብሶ መጣ፣ አስማሩ «ምነው?» አለቸው። «በጠራራ ፀሐይ ብርድ ሆዴ ገባ» አላት። «ምች ይሆናል፣ አለችው። የምች መድኃኒት ብታሽለት ተሻለው። ሲሻለው ብርድ ልብሱ አላስፈለገውም ጥሎት ሄደ። አስማሩ አጥባ አኖረችው። ትንሽ ቆይቶ፣ ፈራሹን ተሸክሞ መጣ። «ምነው?» አለችው። «ላሳድሰው መሄዴ ነው።አይቼሽ ልለፍ ብዬ ነው» አላት። አመነችው። ጨዋታው ደራ፣ ፍራሹን እረስቶት ሄዶ ኖሮ እኩለ ሌሊት ቢመጣ አስማሩ ቦታ ስላጣች ፍራሹን ላይ ደርባው ደረሰ። ያኔ «ተነሽ» ከማለት «ጠጋ በይ» ማለት ቀልሎ ተገኘ። 📚አለማየሁ ገላጋይ ኩርቢት @frombooks1234 📖📚 📚꧁༻༒༺꧂📚‌‌
Показати все...