cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Taxation in Ethiopia™

🔎 #ታክስ #በ_ኢትዮጵያ 🔍 #Ethiopian #Tax_Law ማክሰኞና ቅዳሜ ምሽት3:00ሰዓት Saturday & Tuesday 9:00PM ጠቃሚ የታክስ 🔖 #መረጃ #Info 🔖 #ጥቆማ 🔖 #ዕውቀት_ሰጪ ለሚጠቅማቸው ያጋሩ Share 4 #friends መረጃ አድራሽ የግል ቻናል ነው። This is a personal channel. ለጥያቄዎ #for_questions 👇 @ConsultTaxEt

Більше
Рекламні дописи
4 418
Підписники
+624 години
+407 днів
+8630 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 1006/2016 VAT Free Directive #መመሪያ_Directive #ቫት_Vat #አማርኛ_English #ጥቆማ_Tip @Taxation_in_Ethiopia
Показати все...
VAT Directive 1006.pdf3.02 KB
2👍 1
የደመወዝ ገቢ ግብር ማሻሻያ የገንዘብ ሚኒስቴር የደመወዝ ገቢ ግብር ለማሻሻል ጥናት መጀመሩ ታወቀ ፅዮን ታደሰ ሰኔ 19/2016 ዝቅተኛ ገቢ ያለውን የኅብረተሰብ ክፍል ለመደገፍ በደመወዝ ገቢ ላይ የሚጣለውን የግብር ምጣኔ ለማሻሻል የገንዘብ ሚኒስቴር ጥናት መጀመሩ ታወቀ፡፡ ማንኛውም ተቀጣሪ የሚያገኘው ጠቅላላ ገቢ ከ600 ብር በላይ ከሆነ አሥር በመቶ የደመወዝ ገቢ ግብር የሚከፍል ሲሆን፣ ከአሥር ሺሕ ብር በላይ ገቢ ያለው ተቀጣሪ ደግሞ 35 በመቶ የግብር ምጣኔ ይጣልበታል፡፡ ይህ የደመወዝ ግብር ምጣኔ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ ጫና እየፈጠረባቸው በመሆኑ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናት መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ጥናቱ በዋናነት ትኩረት ያደረገው ግብር የሚከፈልበት ዝቅተኛ የደመወዝ ጣሪያ የሆነው 600 ብር ስንት ይሁን? የሚለው ሲሆን፣ እንዲሁም ከፍተኛ ግብር ወይም 35 በመቶ የሚከፈልበት ደመወዝ ከአሥር ሺሕ ብር ከፍ እንዲል ታስቦ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ጉባዔው በሰጠው አቅጣጫ መሠረት፣ በቅጥር ግቢ ላይ የሚጣለው የግብር ምጣኔ እንዲቀንስ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትን ጨምሮ ለገንዘብ ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ኢሠማኮ ጥያቄውን ካቀረበ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በአካል በመገናኘት ውይይት አድርጎ ነበር፡፡ ሆኖም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበረው ውይይት ካቀረባቸው ጥያቄዎች መካከል ምላሽ ያገኙ ቢኖሩም፣ አንዳንዶቹ ምላሽ አለማግኘታቸውንና ምላሽ ካልተሰጠባቸው ጥያቄዎች መካከልም የደመወዝ ገቢ ግብር እንዲቀንስ የሚለው ወሳኙና አንደኛው መሆኑን ኢሠማኮ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ይደመጣል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር የጀመረውን የግብር ምጣኔ ማሻሻያ ጥናት እንደማያውቁ ለሪፖርተር የገለጹት የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ የግብር ምጣኔው እንዲቀንስ በተደጋጋሚ ጥያቄ መቅረቡን አስታውሰዋል፡፡ ግብሩ የሚቀንስበት መጠን በዚህን ያህል መጠን መሆን እንዳለበት በአንዴ ለመወሰን ስለሚያስቸግር፣ ጥናት መደረጉ አስፈላጊ መሆኑን፣ ጥናቱ ሲደረግም ከኑሮ ውድነቱ አኳያ መሆን እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን በአዲስ ለመተካት በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ፣ የሕዝብ ውይይት ባካሄደበት ወቅት ማብራሪያ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፣ በገቢ ግብር ላይ አጠቃላይ የማሻሻያ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው ነበር፡፡ የገቢ ግብርን የሚመለከተው አዋጅ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ አካል እንዳልሆነ የገለጹት እዮብ (ዶ/ር)፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ጉዳዩን ትኩረት አድርጎ እየተመለከተውና ሰፊ ጥናት እየተደረገ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ሚኒስቴሩ ሥራውን እንደጨረሰ ለፓርላማው ያቀርባል ብለው ነበር፡፡ ሙሉ መረጃው፥ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ነው🙏🏾 @Taxation_in_Ethiopia
Показати все...
👍 12👏 1
አዲሱ የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ “የሕዝቡን የመክፈል አቅም ታሳቢ ያላደረገ ነው” የሚል ትችት በምክር ቤት አባላት ቀረበበት #ጥቆማ_Tip #ረቂቅ_Draft @Taxation_in_Ethiopia https://www-bbc-com.cdn.ampproject.org/c/s/www.bbc.com/amharic/articles/c6ppekvk030o.amp
Показати все...
አዲሱ የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ “የሕዝቡን የመክፈል አቅም ታሳቢ ያላደረገ ነው” የሚል ትችት በምክር ቤት አባላት ቀረበበት - BBC News አማርኛ

በዛሬው ዕለት ሰኔ 13/2016 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው አዲሱ የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ፤ “ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ላይ ጫና የሚፈጥር ነው” የሚል ትችት ከምክር ቤት አባላት ቀረበበት።

👍 6
1004-THE EXCISE STAMP MANAGEMENT DIRECTIVE No. 1004-2024.pdf2.37 KB
1004_የኤክሳይዝ_ቴምብር_አስተዳደር_ስርዓትን_ለመወሰን_የወጣ_መመሪያ_ቁጥር_1004_2016_.pdf2.48 KB
Показати все...
Taxation in Ethiopia™

🔎ታክስ በኢትዮጵያ 🔖 #አዋጅ 🔖 #ታክስ_ህግ ጥያቄዎን ያቅርቡ መረጃ አድራሽ የግል ግሩፕ ነው። 🔍Ethiopian #Tax_Laws 🔖 #Proclamations 🔖 #Regulations 🔖 #Directives A personal group! No Advertisement contact us @ConsultTaxEt Visit Our channel @Taxation_in_Ethiopia

Показати все...
Taxation in Ethiopia | LinkedIn

Taxation in Ethiopia | 293 followers on LinkedIn. Tax in Ethiopia | Your go-to resource for clear and comprehensive explanations of Ethiopian tax rules. Simplifying the complexities of taxation in Ethiopia to help individuals and businesses make informed financial decisions. Follow us for expert insights and guidance on navigating the Ethiopian tax landscape.

👍 2
ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) እና የአክሲዮን ማህበር (SC) ተመሳሳይነትና ልዩነት በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ዉስጥ ካሉት የንግድ ማህበራት መካከል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) እና የአክሲዮን ማህበር (SC) ይገኙበታል ። ሁለቱም ማህበራት አክሲዮን ያላቸዉ ወይም ካምፓኒዎች ሲሆኑ ተመሳሳይነትና ልዩነት አላቸዉ። ተመሳሳይነታቸዉ • ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ መሆኑ ፣ • የራሳቸዉ ንብረት ያላቸዉ መሆኑ፣ • የራሳቸዉን ትርፍና ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባቸዉ መሆኑ፣ • ሁለቱም ትንሹ የአባላት ብዛትና የመነሻ ካፒታል ያላቸዉ መሆኑ፣ • ሁለቱም በቦርድና በማናጀር መመራት የሚችሉ መሆኑ ነገር ግን ለ PLC አሰገዳጅ አለመሆኑ፣ • የሁለቱም ተጠያቂ በተዋጣዉ የገንዘብ መጠን (አክሲዮን ) መሆኑ ፣ • ሁለቱም የሙያ መዋጮን የማይቀበሉ መሆኑ • በሁለቱም ካፒታል ማሳደግና መቀነስ የሚቻል መሆኑ ፣ • በሁለቱም አክሲዮኖች በመያዣ /በዋስትና / መያዝ ሚችሉ መሆኑ። ልዩነታቸዉ አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር / PLC/ private Limited Company/ ለማቋቋም የአባላት ብዛት ከሁለት ማነስ የማይችሉ መሆኑ እንዲሁም ከሀምሳ መብለጥ እንደማይችሉ በንግድ ህጉ ተገልጿል። የአክሲዮን ማህበርን (share company ) በተመለከተ ለማቋቋም ከ5 አባላት ማነስ የማይችል ሲሆን ብዛት ግን ገደብ የሌለዉ መሆኑን በንግድ ህጉ ላይ ይገኛል። • ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መነሻ ካፒታል 15000 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋም በኢትዮጵያ ብር አንድ በመቶ ማነስ አይችልም • አክሲዮን ማህበር መነሻ ካፒታል 50000 ሺህ እና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በታች መሆን አይችልም • ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታሉ ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ግን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የሚከፈል አይደለም ነገር ግን ከተፈረሙ አክሲዮኖች ቢያንስ 1/4 (25%) መከፈል አለበት የቀረዉ በሂደት የሚከፈል ይሆናል። • ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአክሲዮኖች ሽያጭ ለህዝብ ክፍት የሚደርግ አይደለም ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት የሚደረግ ነዉ • ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (PLC) ላይ አክሲዮን ማህበር ዉስጥ ያለ ሰዉ አክሲዮኑን ለሶስተኛ ሰዉ ማስተላለፍ አይችልም ምክንያቱም መተዳደሪያ ደንቡ ላይ አባላት ይህን እስካልፈቀዱ ድረስ በህጉ መሰረት sale freely transferable አይደለም። ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ላይ አክሲዮን ማስተላለፍን በተመለከተ አክሲዮን የገዛ ሰዉ አክሲየኑን ለሌላ አባል ላልሆነ ሰዉ በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላል ። ስለዚህ አክሲዮን ማስተላለፍ ከተፈለገ በቀላሉ የአክሲዮን ማህበርን መምረጥ ያስፈልጋል ማለት ነዉ። • አስተዳደራዊ አካል (ቦርድ) ን በተመለከተ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ከ3-12 ሰዉ የሚይዝ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተር ሲቋቋም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (plc) ዉስጥ የቦርድ መዋቅር ግዴታ አይደለም። ** ምንጭ: አማራ ክልል ገቢዎች🙏🏾 #ጠቅላላ_General #ጥቆማ_Tip @Taxation_in_Ethiopia
Показати все...
👍 15
563 ነጥብ 6 ቢሊዮን ታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ለመሰብሰብ ታቅዷል:: ሰኔ 4/10/2016 የገቢዎች ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 31ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያደረገ ሲሆን ረቂቅ በጀቱ ከ2016 በጀት አንጻር የ21 ነጥብ 1 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል። ምንጭ፥ የገቢዎች ሚኒስቴር ገፅ #ዜና_News @Taxation_in_Ethiopia
Показати все...
🤔 5👍 3
Показати все...
Taxation in Ethiopia™

🔎ታክስ በኢትዮጵያ 🔖 #አዋጅ 🔖 #ታክስ_ህግ ጥያቄዎን ያቅርቡ መረጃ አድራሽ የግል ግሩፕ ነው። 🔍Ethiopian #Tax_Laws 🔖 #Proclamations 🔖 #Regulations 🔖 #Directives A personal group! No Advertisement contact us @ConsultTaxEt Visit Our channel @Taxation_in_Ethiopia

Показати все...
Taxation in Ethiopia™

🔎ታክስ በኢትዮጵያ 🔖 #አዋጅ 🔖 #ታክስ_ህግ ጥያቄዎን ያቅርቡ መረጃ አድራሽ የግል ግሩፕ ነው። 🔍Ethiopian #Tax_Laws 🔖 #Proclamations 🔖 #Regulations 🔖 #Directives A personal group! No Advertisement contact us @ConsultTaxEt Visit Our channel @Taxation_in_Ethiopia

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.