cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

TIKVAH-ETHIOPIA BACKUP

ይህ የቲክቫህ (ተስፍ) ኢትዮጵያ #BACKUP ቻናል ነው (ዋናው ቻናል በማናውቀው ምክንያት #ከተቋረጠ ወይም #ከጠፍ) ሁሉንም የቲክቫህ መረጃ እና መልዕክቶች በዚህ ቻናል ማግኘት ይችላሉ። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Більше
Рекламні дописи
7 579
Підписники
+524 години
+87 днів
-5830 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
" ከ2013 ዓ/ም በፊት በአከባቢው ሰላም እና ፀጥታ ሲያስከብሩ የነበሩ ታጣቂ ተፈናቃዮች ከነትጥቃቸው ይመለሳሉ " - ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌ/ ጀነራል ታደሰ ወረደ ትላንት መግለጫ ሰጥተው ነበር። በመግለጫቸው ፥ " ለአመታት ከቄያቸው ተፈናቅለው በትግራይ የተለያዩ ከተሞች እና በሱዳን የሚገኙ የምዕራብ ትግራይ ነዋሪዎች እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ወደ አከባቢያቸው ለመመለስ የተያዘው የጋራ እቅድ የዘገየው በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተፈጠረ ችግር አይደለም " ብለዋል። " የነበረ ክፍተት ተገምግሞ ተፈናቃዮች ድህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ቄያቸው ለመመለስ እየተሰራ ነው " ሲሉ አክለዋል። ም/ፕሬዜዳንቱ ፥ " የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮችን ወደ አከባቢያቸው የመመለስ ስራ የራያ እና ፀለምቲ ተፈናቃዮች በመመልስ የተገኘው ልምድ መስረት በማድረግ ይፈጸማል " ብለዋል።  " ተፈናቃዮችን የመመለስ ተግባሩን የሚያቆም አካል የለም " ሲሉ ተደምጠዋል። " የምዕራብ ትግራይ የህዝብ ብዛት እና የኢኮኖሚ የበላይነት ለመያዝ ያለመ የሰፈራ ስራ በአማራ መንግስት ተካሂደዋል " ያሉት ሌ/ጀነራሉ " ከሌሎች አከባቢዎች ወደ ምዕራብ ትግራይ ገብተው እንዲሰፍሩ የተደረጉ ታጣቂዎች እንዲወጡ ይሰራል " ብለዋል። " ከ2013 ዓ.ም በፊት በአከባቢው ሰላምና ፀጥታ ሲያስከብሩ የነበሩ ታጣቂ ተፈናቃዮች ከነትጥቃቸው ይመለሳሉ "  በማለትም ተናግረዋል። በሌላ በኩል ፥ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ቀላል እና ከባድ ወንጀሎች በመፈፀም ላይ እንዳሉ ተናግረው በአጭር ጊዜ ወንጀል ፈጻሚዎችን ወደ ተጠያቂነት ለመሸጋገር የሚስችል ስራ መጀመሩን አሳውቀዋል። በከባባድ ወንጀል በተሳተፉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አመልክተዋል። እነማ በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ? የሚለውን በዝርዝር አልተናግሩም። #TikvahEthiopiaFamilyMekelle @thikvahethiopia
Показати все...
👍 1
5.43 MB
4.15 KB
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#DStvEthiopia የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰ ! ከከባድ ትንቅንቅ በኋላ ስፔን እና እንግሊዝ ለፍፃሜ በጀርመን ኦሎምፒያስታዲዮን ይገናኛሉ! እንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ታነሳ ይሆን? ስፔንስ የአሸናፊነት መንገዷን ትቀጥል ይሆን?  ⚽️ Spain vs England ሐምሌ 7 ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት | 10፡00 PM 👉SS Football ቻናል 225 በጎጆ ፓኬጅ 👉SS Euro2024 ቻናል 222 በሜዳ  ፓኬጅ ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ልዩ በቀጥታ ይከታተሉ! የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ! 👇 https://bit.ly/3RFtEvh #Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ ሚያዚያ ወር በተቀሰቀሰው ግጭት ከኮረም፣ ወፍላ፣ ዛታ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ዋግ ኽምራ እና ሰሜን ወሎ ዞን ይገኛሉ። እነዚህ ወገኖች ላለፉት ሶስት ወራት ያለ በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ በመቆየታቸው የከፋ ችግር ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል። አጠቃላይ ተፈናቃዮች ከ22 ሺህ ይልቃሉ። ተፈናቃዮች ምን አሉ ? - አሳሳቢ የምግብ እና የመጠለያ ችግር አለ። - እያንዳንዱ በሰው ቤት ተጠግቶ ነው ያለው። - ቤተዘመድ እያገዛቸው እንጂ ለ3 ወር የከፋ ችግር ላይ ወድቀው ነው የሚገኙት። - በ3 ወር ምንም የተደረገ ድጋፍ የለም። - ዋግኽምራ ዞን የተቻለውን ቢያደርግም ከአቅሙ በላይ ነው። ብዙ ሰው ነው ያለው። - አብዛኛው በረዳ ወቅዷል። - ዘመድ ያለውም ዘመዱ ጋር ተቸግሮ ነው የሚኖረው። - እየለመ የሚበላ አለ፣ ጉልበት ያለውም ተቀጥሮ የሚሰራ አለ። - አንዳንድ እናቶች መጠለያ ተሰጥቷቸው ነበር ግን ልጆቻቸው ሲታመሙ ቤት ተከራይተው ወጥትተዋል። በዚህ ኑሮ ውድነት መኖር አልቻሉም። - ተፈናቃዮቹ በቄያቸው ቤት እና ስራ ነበራቸው። የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ምን አለ ? ° ከ11 ሺህ ተፈናቃዮች ነው ያሉት። ° አሁን ባለንበት ሁኔታ መጠለያ ማዘጋጀት አንችልም። ድንኳንም የለንም። ° የምንመግበውን ተቸግረን በመጡ ጊዜ ለአንድ ሰው 25 ኪ/ግ ነው  የሰጠነው። ከመጠባበቂያ ! ° የሰላሙ ሁኔታ አለ፣ መንገድ ዝግትግት ያለ ነው ሌላ አካል ድጋፍ ላምጣ ቢል እንኳን። ° አካባቢው ዝናብ አጠር ነው። በድርቅ ይጠቃል። የዓምናው ድርቅም ጉዳቱ እንዳለ ነው። ብዙ ሰው ተጎድቷል። አሁን ተፈናቃይ ተጨምሮ ይቅርና በፊትም ብዙ ችግር አለ። ° በህጻናት አድን ድርጅት ካሽ 14 ሺህ በሁለት ዙር ለመስጠት ልየታ እየተደረገ ነው። ° ያሉት ተፈናቃዮች ከኦሮሚያ፣ ከመተማ፣ በሰሜን ጦርነትም ተፈናቅለው ያልሄዱ አሉ። በአሁኑ ወቅት እርሳቸውም ተፈናቃይ መሆናቸውን የገለጹትና ኮረም ከተማን ለሁለት ዓመት በከንቲባነት የመሩት አቶ ብርሃኑ ኀይሉ፣  የተፈናቀለው ሕዝብ ብዛት ከ22 ሺሕ እንደሚበልጥ ገልጸው ፥ የምግብ አቅርቦቱ እጥረት አሳሳቢ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ " እርዳታ ጠይቀናል። ለ3 ወራት ተከታታይ እርዳታ የለም።  ክልሉ የሰጠን ነገር የለም፤ ጭራሽ አላነገረንም " ብለዋል። የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን " መረጃ አለን ፤ ለተፈናቃዮቹ የምግብ አቅርቦት ጥያቄ በቅርቡ ምላሽ ይሰጣል ፤ እርዳታም ይጓጓዛልም " ሲል ገልጸዋል። #ቪኦኤ @thikvahethiopia
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#Internet ትላንት ምሽት በተካሄደ የኢንተርኔት የመመለስ ስራ ለበርካታ ወራት ኢንተርኔት ተቋርጦባቸው የነበሩ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኛታቸው ተሰምቷል። ከሁነኛ ምንጭ በተገኘ መረጃ ኢንተርኔት ተቋርጦ በነበረባቸው 19 ከተሞች አገልግሎት ተመልሷል ተብሏል። የትኞቹ ከተሞች ናቸው ? - ባህር ዳር - ጎንደር - ደሴ - ኮምቦልቻ - ወልዲያ - ሰቆጣ - ደብረ ብርሃን - ደብረ ማርቆስ - ደብረ ታቦር - ፍኖተ ሰላም - ገንደውሃ - ከሚሴ - ጋሸና - ቡሬ - ባቲ - ደጀን - ደባርቅ - ኢንጅባራ - ሁመራ ናቸው። በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎችን ስለ ተለቀቀው የኢንተርኔት አገልግሎት በተመለከተ ጠይቀናቸው ፍጥነቱ ያን ያህል እንደሆነ እንዲሁም መጨናነቅም እንደሚታይ ነገር ግን እንደተለቀቀ አመልክተዋል። #TikvahEthiopia @thikvahethiopia
Показати все...
00:13
Відео недоступнеДивитись в Telegram
#ቪድዮ : የቀድሞ የአሜሪካ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ የግድያው ሙከራ በተደረገባቸው ወቅት እሳቸው ቅስቀሳ ከሚያደርጉበት ስፍራ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣሪያ ላይ የነበሩ የ " ሴክሬት ሰርቪስ " የስናይፐር ተኳሾች የግድያ ሙከራውን ባደረገው ሰው ላይ ምላሽ ሲሰጡ ተይተዋል። አንድ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪድዮ ሁለት የሴክሬት ሰርቪስ ስናይፐር ተኳሾች በፍጥነት ኢላማ አድርገው የግድያ ሙከራውን ባደረገው ግለሰብ ላይ የተኩስ ልውውጥ ሲያደርጉ ታይተዋል። ግለሰቡ የግድያ ሙከራ ባደረገ በሰከንዶች ውስጥ መተገው ገድለውታል። የግድያ ሙከራውን ያደረገው ማነው ? - FBI የግድያ ሙከራውን ያደረገው ቶማስ ማቲው የተባለ #የ20_ዓመት_ወጣት እንደሆነ ገልጿል። - ነዋሪነቱ ምርጫ ቅስቀሳውና የግድያ ሙከራው ከተደረገበት ስፍራ የአንድ ሰዓት ጉዞ የሚፈጅ ቦታ ነው። - በ2022 ነው ቤተል ፓርክ ከተባለ ሀይስኩል የተመረቀው። - ወጣቱ በብሔራዊ የሒሳብ እና ሳይንስ ኢኒሼቲቭ ተሸላሚም ነበር። - የሪፐብሊካን ደጋፊም ጭምር እንደሆነ ተመዝግቧል (የዶናልድ ትራምፕ ፓርቲ ማለት ነው)። - ቅስቀሳው ከሚደረግበት ቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣራ ላይ ሆኖ ነው ዶላንድ ትራምፕን ለመግደል የሞከረው። - ለምን ይህን ለማድረግ እንደፈለገ FBI ምርመራ እያደረገ ነው። #USElection #FBI @tikvahEthiopia
Показати все...
5.62 KB
👍 3
1.90 MB
4.96 KB
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.