cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

እኔ እና ፍቅሬ 😍❤️

ፍቅረኛዋን ማስደሰት 😘 ወይም ይቅርታ መጠየቅ ይፈልጋሉ እንድያውስ ይዬንን ቻናል ይቀላቀሉ @lovebcha. @lovebcha ማለት ምትፈልጉት በዚ ይላኩልን @heyab223 እና @Ab9716 @Maki6307

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
194
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ሙዚቃ የምትወዱ ከሆነና ለጋደኛችሁ ወይም ለፍቅረኛችው መጋበዝ ከፈለጋችሁ ይህንን ቻናል ተቀላቀሉ የተለያዩ የፍቅር ዘፈኖች በትንሽ kb!! 👇👇👇#JOIN👇👇👇
Показати все...
JOIN
​​​​​​​​┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄            ❣:¨·.·¨: ❣ ⇨ሳሮን🌺 ┈┈••◉❖◉●••┈ ✎ ክፍል 1⃣3⃣♥️ ┈••◉ናኦዴ ስልኩን ሳይዘጋው ማሚ ብሎ ጮሀ ናኦድ ስማኝ ስለው ሊሰማኝ አልቻለም ስልኩን ሳይዘጋው እንዴት እንደዚ አይነት ነገር ከኔ ትደብቃላቹ ብሎ እናቱ ላይ ጮሀባት ቀወጠው እንዴት አድርገን እሱን ማረጋጋት እንዳለብን አናውቅም ብቻ በራሱ ጊዜ እንደሚረጋጋ አውቃለው ስልኬን ዘጋሁትና ማሰብ ጀመርኩኝ አልሄድም አልታከምም እንደማይል ተስፋ አደርጋለው ብዬ ስልኩን መጠበቅ ጀመርኩኝ እንደሚደውል እርግጠኛ ነኝ ብቻ ብዙ ብጠብቀውም መደወሉ ግን አልቀረም ነበር ምን አርጌሽ ነው ግን እንዴት ከኔ ይሄንን ነገር ደበቃቹኝ ሲል አንተን እያሳሰበህ ያለው ስለደበቅንህ ብቻ ነው እንዴ?? ስለ ህይወትህስ ምንም አታስብም አልኩት እኔ የምትታከምበትን ገንዘብ አግኝቻለው በቃ ጊዜ የለንም በቶሎ መታከም አለብህ ናኦዴ እባክህን ዛሬውኑ ወደ አዲሳባ ና አልኩት ምንም አላንገራገረም እሺ መጣለው ብሎ ሪፈሩን አፅፎ ጊዜ ሳይፈጅ ወደኔ ጋር መጣ ልክ አዲስ ሲገባ እኔ ሄጄ ተቀበልኩቲኝና ወደ ቤት ይዤው ሄጄ ከቤተሰብ ጋር አስተዋወኩት ጊዜያችን እየሮጠ ስለነበረ ከጊዜ ጋር መፍጠን ነበረብን እና እኔ አባቴ እና ናኦዴ ቀጥታ ወደ አሜሪካን ሀገር አመራን ደሞ ከዶክተሩ የወሰድነው ብር የአሜሪካን ዶላሩ ሲመነዘር 2ሚሊዮን ብር ነበር የሆነው የኢትዮጵያው ደሞ ወደ 700,000 በር ነበረ እና ከተዘረዘረ በኋላ እራሱ አላመንም ነበር . . እና እንደ እግዛቤር መልካም ፈቃድ ሆኖ ለሳምንታት ያህል ታግለን ህክምናውን ጨርሶ ወደ ኢትዮጲያ ተመለስን አሁን ናኦዴ ሙሉ ጤነኛ ነው በጣም ጤነኛ ሆኗል የኔ ልዩ የኔ ፍቅር የኔ ጣፋጭ ሁሌም ቢሆን እኔ ላንቺ ሞታለው እሺ አለ ለምን እንደዛ ትላለህ ማሬ ከሞት አፋፍ ላይኮ ነው የተመለስከው ረሳሀው እንዴ ሁለተኛ የሞትን ስም አትጥራብኝ አንተ ከኔ ጎን ብቻ ነው መሆን ያለብህ አልኩትና አብረን የሚገራርሙ ጊዜያትን ማሳለፍ ጀመርን . እና አሁን እንዴት ነው የምናደርገው አልኩት ሊያ አለች አንተ አለህ ሁለታቹም ስላላቹልኝ በጣም አመሰግናለው እሺ አልኩት አረ ሳሮንዬ ተይ እኛ ነን ማመስገን ያለብን አለና ለምን ፓርቲ አናዘጋጅም ጨፍሬ አላውቅም እቺን ቀን የኛ እናርጋት የደስ ደስ ማለት ነው የኔ ልዑል የዳነበት ቀን ብለን እናዘጋጅ ስለውተስማማ ከዛ አንድ ሆቴል ለአንድ ቀን ብለን እዛ ሆቴል ውስጥ አዘጋጅተን የምናውቃቸውን ሰዎች ጠርተን ጭፈራው ተጀመረ ሌሊቱ እራሱ አበደ ጭፈራው እየቀለጠ እያለ አንድ ሰውዬ ከውጪ ካላስገባቹኝ ብሎ ይጮሃል ልቀቁኝ እገላቸዋለው ብሎ ዛተ ለቀቁት እና ገባ ዶ/ር ሳሚ ነው ሽጉጡን አነጣጥሮ መጣ በጣም ደንግጫለው እንዴት መጣ የት እንዳለንስ እንዴት ሊያውቅ ቻለ የወሰድሽውን ገንዘቤን አንድ በአንድ ትሰጪኛለሽ ወይስ የፍቅረኛሽን ግንባር ሁለት ቦታ ላርገው አለ የናኦድ ግንባር ላይ አነጣጥሮት.....የወሰድሽውን ገንዘቤን አንድ በአንድ ትሰጪኛለሽ ወይስ የፍቅረኛሽን ግምባር ሁለት ቦታ ላርገው? አለ የናኦዴ ግምባር ላይ የያዘውን ሽጉጥ አነጣጥሮት የማደርገው ነገር ጠፋኝ እና ደርቄ ቀረሁኝ ምላሴ ሁሉ ተሳሰረ ምንልታደርግ ነው አልኩት ?? አይታይሽም እንዴ ልገላግልልሽ ወይስ ወይስ ገንዘቤን ትሰጪኛለሽ አለ በጣም መረጋጋት እንደነረብኝ ገባኝና እንደምንም እራሴን አረጋጋሁት እና እኛ ገንዘቡ ከሌለን እና መመለስ ካልቻልን ናኦድን ትገለዋለህ አልኩት አይ ተኩሼበት ወስጄ አክመዋለው! ቆይ ስታስቢው ጨዋታ ናፍቆኝ የመጣው ይመስልሻል አለ አይመስለኝም አልኩት እና አትሰጪኝም አለ........ ✎ ክፍል 1⃣4⃣ ከ20Vote ቡሀላ ይቀጥላል..
Показати все...
‍ ‍ ​​​​​​​​┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄            ❣:¨·.·¨: ❣ ⇨ሳሮን🌺 ┈┈••◉❖◉●••┈ ✎ ክፍል 1⃣4⃣♥️ ✨🍂የመጨረሻ ከፍል✨🍂 ┈••◉አሁን እኔን ስማኝ እኔ እንኳን ሌባ ሆኜ አልነበረም ግን የሰውን ህይወት ላድን ነበር ይሄንን ነገር ያደረኩት ደሞም ከእግዚኣብሄር ጋር አድኜዋለው ቢያንስ ለኔ ለሱ ለቤተሰቤ ለቤተሰቦቹ ደስታን ፈጥሬላቸዋለው አሁን ከስጋት ነፃ ናቸው ግን ይሄንን ያደረኩት ህሊናዬ ከሚወቅሰኝ ማድረግ እየቻልኩኝ ሳላደርግ እጄን አጣጥፌ ብቀመጥ ለዘለዓለም እራሴን ይቅር አልለውም ነበር ደሞ ይሄንን ነገር በማድረጌ ቅንጣት ታክል ህፍረት አልተሰማኝም እራሴን ጀግና እያልኩት ሳይሆን ማድረግ ያለብኝን ነገር ነው ያደረኩት ደሞ ታቀኛለህ ለምወደው ሰው እሞትለታለው አልኩትና በል ላንተ የሰውን ህይወት ማጥፋት ደስታን የሚፈጥርልህ ከሆነ ይሀው ሁለታችንንም ግደለን ለገንዘብ ብለህ እኛን ማጥፋት ካለብህ ይሀው ምን ትጠብቃለህ ግደለን ስለው ይሄ ልበሙሉነትሽ ገዝቶኝ ነበርኮ አለ ተው ተው አንተን ሊገዛህ የሚችለው ነገር ቢኖር ገንዘብ ብቻ ነው ልታታልለኝ እንዳትሞክር አልኩት አንተ ግን ህሊናህ እራሱ አይወቅስህም? ለስሙ ዶክተር ነህ ግን እንዴት ነው ጭንቅላትህ ፈቅዶልህ ሁለት የሚዋደዱ ጓደኛሞችን ለይተህ በመሃል ልትገባ ያሰብከው እስኪ ንገረኝ እኔ እሺ ብልህ ግን ደስተኛ ሆነህ ትኖር ነበር ለዛ ሰውስ ምንም ነገር አታስብም አንተን የሚሰማህን ያህል ለዛ ሰውም እንደሚሰማውስ ማሰብስ እንዴት አቃተህ ስለው ሽጉጡን ቀስስ ብሎ አወረደ እና የሚመልስልኝን ነገር አጥቶ በዝምታ ተዋጠ አየህ መልስ የለህም አሁን ነው ማሰብ የጀመርከው ለገንዘብ እራስህን አሳልፈህ ስትሰጠው እሱ አንተን ያዝሃል አንተ ደሞ የሱ ታዛዥ ትሆናለህ አልኩት ስለዚህ ካሁን በኋላ ከገንዘብ በፊት የሰው ልጅ ይቀድማል እሺ አልኩት መልስም የለም ምንም የለም ፈጣሪዬ ሆይ ሃሳቡን ብቻ እንዳይቀይር አልኩኝ ሽጉጡን አስቀምጦ አጠገቡ ላይ የነበረው ወምበር ላይ ቁጭ አለ እንዳጋጣሚ ሆኖ የአቤል እናትም ነበረች እና መታ አጠገባችን ላይ ቆማ ፈዛ ቀረች እሱም አይቷት ነበር አና እኔ ከተናገርኩትና ከተቀመጠ በኋላ ቀና ብሎ ሲያያት ደርቆ ቀረ እሷም እንደዛው ናኦዴ ምንድነው እየተፈጠረ ያለው ነገር ስለው ምንም ነገር አልገባኝም ብሎ እማዬ ምንድነው ሲላት አይሆንም አይሆንም አለች ምንድነው የማይሆነው ታውቂዋለሽ እንዴ ስላት አዎ አውቀዋለው አለች የት ነው የምታውቂው አላት እዛው ሀዋሳ ነው የማውቀው ብላ ቁጭ ብላ ማልቀስ ጀመረች ሁለቱ የሚያውቁት ነገር አለ ማለት ነው ብለን ግራ በመጋባት አየናቸው ማንም ሊነግረን አልቻለም . . የናኦዴ እናት ትንሽ ከተረጋጋች በኋላ አንተ አውሬ ብላ እየዛተች ወደሱ አመራች እኛም ምን እንደነፈጠረ ለማወቅ ተቻኩለን ተከትለናት ሄድን አንቺ ደሞ እዚ ምን ትሰሪያለሽ አላት አዎ ለነገሩ ለኔ እንደዚ አይነት ቦታ አይመጥነኝም አይደል እንደዛ አሽቀንጥረህ እንዳልጣልከኝ አለችው ጭቅጭቃቸው ጦፈ ነገሩ እንዲህ ነው የሆነው የናኦዴ እናት ድሮ ሳሚ ተማሪ እያለ የሱ ቤት ተመላላሽ ሰራተኛ ነበረች እና ሳሚሻ አምሮት ስለነበረ ሳትፈልግ አስገድዶ ደፈራት ከዛ በተደጋጋሚ ግንኙነት ስላደረጉ ከእለታት አንድ ቀን እንዳረገዘች ስትነግረው 100 ብር ሰቷት አስወጪው እንዳላትና ሁለተኛ አጠገቡ እንዳትደርስ አርጎ ቀጥቅጦ እንዳባረራት ነው ያወራችው እና እሷ ደሞ ህሊናዬ አይፈቅድልኝም ብላ ለልጇ መስዋዕትነት ከፍላ ለዚ ያደረሰችው በእውነት በጣም ይቅርታ ይቅር በይኝ በድዬሻለው ይሄንን ነገር ደሞ በምንም ልክስሽ አልችልም አለ ፈጣሪ የእጄን ይስጠኝ አለ አፈር ብላ እንደው ይሄ ልጅ ዘላለም እንዳያይህ ነበር የፈለኩት ግን ምን ያረጋል እያለች ፎከረች ናኦዴ እና እሱ ነው የኔ አባት አለ??? አዎ ይሄን ሁሉ ጊዜ ስትጨቀጭቀኝ የነበርክለት ጨዋው አባትህ ይሀው አለችው ይሄ ነገር ህልም እየመሰለኝ ነው አልኩኝ እኔም እያመንኩኝ አይደለም አለ ናኦዴ ሁሉም ግራ ተጋባ የሚንጫጫው ተንጫጫ የሚያለቅሰው አለቀሰ የሚያ ዝነውም እንደዛው አዘነ ሰዎች አሁን እንደዚ ስለሆንን ምንም ምንም የሚቀየር ነገር የለም አልኳቸውና ሁሉንም አረጋግቼ ፓርቲው ቀርቶ ቤት ቀይረን ከአባቴ ጋር ሁሉንም ሰው አስታርቀን ናኦዴም በግርግር አባቱን አገኘ በአባቱም ብር ታከመ ያቺ ቀን በእንደዚህ አለፈች ከ አንድ አመት በኋላ ሊያም ወልዳ ልጁንም ቤተሰቦቿ ተቀበሉን አብሬያት ሄጄ ሁሉንም ነገር አስረድቼቻው እነሱም የልጅ ልጃቸውን ተቀብለውን ያቋረጥነውን ትምህርታችንን ቀጠልን የኔ እና የናኦድ ፍቅርም ከንደገና ጀመረ ህይወት ግን ትቀጥላለች። ─────✦ ተፈፀመ ✦───── ➟ እነሆ ሳሮን♥️ የተሰኘው አስተማሪና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ💟💟 ዛሬ በዚህ መልኩ ➟ ተፈፀመ ➟ ከታሪኩ♥️ ብዙ እንደ ተማራቹበት ተስፋ አደርጋለሁ በሌላ ታሪክ እስከምንገናኝ ሰላም ሁኑልኝ ስለተከታተላችሁን ከልብ እናመሰግናለን🙏🙏 አስተያየታችሁን📬 አድርሱን እንቀበላለን እና ➟ ሼር ➟ ማድረጋችሁን እንዳትረሱhttps://t.me/joinchat/VRpADeIZBjsLy6lk 🌹✨▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️✨🌹 @Yefker_Liboch @Yefker_Liboch
Показати все...
attach 📎

​​​​​​​​ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄            ❣:¨·.·¨: ❣ ⇨ሳሮን🌺 ┈┈••◉❖◉●••┈ ✎ ክፍል አስር♥️ ┈••◉ተይው በቃ እኔ አንቺን ላስጨንቅሽ አልፈልግም አለኝ ምንድነው ምን ማለት ነው ላስጨንቅሽ አልፈልግም ማለት? እንደዚህ ከሰውነት ተራ ያወጣህን ነገርማ ማወቅ አለብኝ ንገረኝ አልኩት ተይው ይቅርብሽ በቃ ዝም ብለሽ ካጠገቤ ሁኚ አለኝ ኡኡኡፍፍፍፍ ናኦዴ አታድክመኝ በናትህ ስለው እሺ በቃ ተረጋጊ እነግርሻለው ግን አንቺን ማስጨነቅ ፈልጌ ሳይሆን ብቻ ላንቺ ብነግርሽ ይቀለኝ ይሆናል ብዬ ነው አለኝ እሺ ምንድነው የሆንከው ስለው አይን አይኔን እያየ በጣም ከፍቶታል ግን በኔ ፊት ደስተኛ የሆነ እያስመሰለ ሳሮንዬ አንቺ በጣም ጥሩ ልጅ ነሽ ከሚገባው በላይ ምርጥ ልጅ ነሽ እኔ አንቺን አስደስቼሽ አላውቅም በአግባቡ እንኳን ካጠገብሽ ሆኜ አላውቅም አንቺ ግን ለራስሽ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ህዝብ ሁሉ ልትተርፊ የምትችይ ልጅ ነሽ አለ ናኦድ ስለሆንከው ነገር ንገረኝ ስለው በርግጥ ካንቺ ጋር ስሆን ደስተኛ ነኝ ካንቺ ጋር ስሆን በጣም ደስተኛ ሆናለው ምክንያቱም አንቺ የኔ ደስታ ምንጭ ነሽ አለኝ እና በህይወታችን ውስጥ በምን እንደምንፈተን አናውቀውም ግን ሁሉም ሰው በህይወቱ ይፈተናል ግን እኔም ይሄንን ነገር ፈተና ብዬ እቀበለዋለው አሁን ላይ አንዱ ኩላሊቴ ፌል አርጎዋል አለኝ ምን????? ናኦዴ የምርህን ነው አልኩት አዎ ግን አትደንግጪ ምንም ነገር እንዲሰማሽ አልፈልግም እሺ አለኝ በስመዓብ እንዴት ነው ይሄንን ነገር እስካሁን ለኔ ያልነገርከኝ ስለው ምንም አይጠቅምሽም ብዬ ነው አሁን እራሱ ስለገርኩሽ እንድፀፀት እያረግሽኝ ነው አለኝ ምንም አላልኩም ተነስቼ እቅፍ አርጌው ናኦድዬ ምንም ነገር አትሁንብኝ እሺ እኔ ካላንተ የትም አልደርስም ባክኜ ነው የምቀረው አልኩት ፈጣሪ እንግዲ ከረዳን በህክምና እድናለሁ አለ ከጎኔ ሁን እሺ መቼም ቢሆን ከኔ አትለይ ናኦዴ አፈቅርሃለው እሺ ብዬ ከንደገና እቅፍ አርጌው በጣም እንዳላጣው እየፈራሁ ፈጣሪዬ ሆይ ምነው መከራዬን አበዛሀውሳ እባክልነህን ናኦዴን አድንልኝ ብዬ መማፀን ጀፈርኩኝ ደሞ እንዳይጨንቀው ብዬ ነው እንጂ እምባዬን መቆጣጠር አቅቶኛል . . አልቻልኩም ናኦድ ታሞዋል በነጋታው ሆስፒታል ሊታከም ሄደ ለኔም ተነግሮኛል እኔም ምንም አይነት ጊዜ ሳላጠፋ በርሬ ሄድኩኝ እዛ ስደርስ ግን ቀጠሮ ስለነበረው ውስጥ ምርመራ እያደረጉለት ነበር በር ላይ ቁጭ ብለው የነበሩት እናቱ እና የእንጀራ አባቱ ብቻ ናቸው። ዶክተሩ ከክፍሉ ሲወጣ ሁላችንም ወደ ዶክተሩ በመጠጋት ምን እንደተፈጠረ ለመስማት ጓግተን ወደሱ ሄደን ንገረን ምንድነው ደና ነው ብላ ጠየቀችው እናትየው ዶክተሩም በጣም ይቅርታ ግን መበርታት አለባችሁ ግን ናኦድ በቶሎ ህክምና ካላገኘ ሁለቱም ኩላሊቶቹ ስራቸውን ያቆማሉ ስለዚ በሁለት ሳምንት ውስጥ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ መታከም አለበት ካለበለዚያ ግን በህይወት የመቆየት አቅም አይኖረውም አስቡበት አለና ሄደ እናትየው ዶክተሩን ተከትላ ሄደችና ቢሮ ውስጥ ማውራት ጀመሩ ስንት ብር ነው ለህክምና የሚያስፈልገን ብላ ጠየቀችው ባጠቃላይ ወደ 800,000ሺ ብር ያስፈልጋችሁዋል አላት እናትየው ምንም ነገር ሳትል ለቃ ወጣችና መጣች ወደኛ መጥታ ነገረችን እኔ በጣም ነው የደነገጥኩት እራሴን አመመኝ ማመን አልቻልኩም 800,000 ብር ማለት እኮ በጣም ብዙ ነው አልኩኝ ድምፄ ከፍ አድርጌ ሳይታወቀኝ የናኦድ እናት አውቃኛለች ስለኔ ናኦዴ ነግሯታል መሰለኝ ሁላችንም በሀዘን ተክዘን ሳለ አሁን ገብታችሁ ማየት ትችላላቹ ስንባል መጀመሪያ ዘልዬ የገባሁት እኔ ነበርኩኝ ናኦዴ ደና ነህ ስለው እኔ በጣም ደና ነኝኮ አንቺ እራስሽን አረጋጊው አለኝ አንተኮ የመኖሬ ሚስጥር ነህ ካላንተ አልችልም አልኩት እባክህን ጠንከር በልልኝ እሺ አልኩት እሺ እበረታልሻለው አለኝ የናኦዴ ቤተሰቦችም ገቡ እኔ እነሱ ሲገቡ ክፍሉን ለቅቄ ወጣሁኝ . . እጄን አጣጥፍማ አልቀመጥም መፍትሔ መፈለግ አለብኝ ብዬ ተነሳሁኝ ቀጥታ ወዳረፍንበት የዶ/ር ሳሚ ቤት አመራሁኝ እዛ ስደርስ ሊያም በጣም እየታመመች ነው እርግዝናው አልተስማማትም ጉዴ ፈላ አልኩኝ ማንም ሰው አጠገቤ ላይ የለም ብቻዬን የሁለት ሰው ነፍስ ማዳን አለብኝ ብዬ አሰብኩኝ እና ወደ ማታ ዶ/ሳሚ ሲመጣ አናገርኩት ሳሚም ይሄ ነገር በጣም ይከብዳል ግን አንቺ የጠየቅሽኝ 500,000 ሺ ብር አልችልም ግን አንቺ የኔ የምትሆኚ ከሆነ ላንቺ ስል የማላደርገው ነገር የለም አለኝ አሁን ስለሱ የሚወራበት ጊዜ ነው ስለው ነገርኩሽኮ እኔ ብወድሽ ነውኮ ቤቴን ክፍት ያደረኩልሽ ማን ይሄንን ያደርጋል እኔ በጣም እወድሻለው ጥያቄዬን ተቀበይኝ ሲለኝ ሊያ ሰማች እንዴት ናኦድን የመሰለ ልጅ ትተሽ ከዚ ሰውዬ ጋር ስለ ፍቅር ምናምን የምታወሪው ብላ ቁጣ ወይ ጣጣ ለስንቱ ላስረዳ ብዬ ግሪ በመጋባት ሳያት አታፍጪ በናትሽ ብላ ወደ ክፍሏ ገብታ በሯን ዘግታ ቁጭ........ ✎ ክፍል 1⃣1⃣ ከ40Vote ቡሀላ ይቀጥላል አንብበው ሲጨርሱ Like እና Sher ያድርጉ
Показати все...
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄            ❣:¨·.·¨: ❣ ⇨ሳሮን🌺 ┈┈••◉❖◉●••┈ ✎ ክፍል ስምን♥️ ┈••◉እንዴት እንዴት ነው የምታአሪው አለኝ እንደምታየው ነዋ አልኩት ሴቶችኮ ምላሳችሁ ከሚረዝም ቀሚሳችሁ ቢረዝም ነው የሚሻለው አለ አሁን ያንተ ምላስ ነው የረዘመው ባክ ስለው ማነኝ አልሽ ግን? አለ ለምን እንደተፈለኩኝ ማወቅ እችላለው? አለ? ሳሮን እባላለው የሊያ ጓደኛ ነኝ እህቷ በለኝ በቃ አትቸኩል በሚገባ ትሰማዋለህ አልኩት እሺ ቶሎ ንገሪኝ አለ አሁን እኔ የፈለኩህ እንኳን ደስ አለህ ልበልህ? ወይስ አዝናለው ምን እንደምልህ እራሱ አላውቅም!¡¡! ግን ሊያ እርጉዝ ነች አልኩት . . ምን ውሸት ነው አለ ተቁነጠነጠ ሊሆን አይችልም እንዴት ነው እንደዚህ ሊሆን የቻለው ብሎ የተገናኘንበት አካባቢ ያልረገጠው ቦታ የለም እሱ ብቻ ሳይሆን ከ ሁለት ወር በላይ ስመሆነ ማስወረድ እራሱ አትችልም ልትሞት ስለምትችል አልኩት ጭራሽ አበደ እኔ አላምንም አለ እሺ እንዳረጋግጥልህ ነው የምትፈልገው ብዬ ሊያን ሄጄ ከዶርም ይዤለት ሄድኩኝ አያት በፍጥነት ሆዷን ነካክቶ ሲያያት አመነ ቆይ እንኳን አረገሽልኝ ብዬ አቅፌ የኔ ሚስት እንዳንቺ አይነት ሚስት አለም ላይኮ የለም ምናምን እንድልሽ ነበር የጠበቅሽው? አላት እሷም እና የት እንድሄድ ነበር የፈለከው ቤተሰቦቼ ጋር አይስ ያንተ ቤተሰቦች ጋር አለችው አይመለከተኝም ካሁን በኋላ አላውቅሽም አታውቂኝም ግን ለፖሊስ እንናገራለን እንከሰዋለን ምናምን ብትሉ ውርድ ከራሴ በናንተ ምክንያት አይደለም አንድ ሳምንት አንድ ቀን እንኳን ትምህርቴን ባቋርጥ ደግሜ ትምህርቱን አልማረውም ጠላታቹ ነው የምሆነው ዘላለም አሰቃያቹዋለው አለን እና አስፈራራን አሁን አንተም ከወንዶች እኩል ትጠራለህ ምን አይነት ሰው ነህ በጣም ነው የምትቀፈው እሺ ገደል ግባ እኛ ይሄንን ልጅ እናሳድገዋለን ግን ልጄ ምናምን ብለህ ብትመጣ እኔ ሳሮንን አያርገኝ አልኩት እሺ ብሎ ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ አለና ሳቀብን . . ሊያን አንጠልጥያት ወደ ዶርም ተመለስን በቃ ሊያም ቆርጦላታል አልቅሳም ወቶላታል ጊዜውም ነጎደ እኔም ቤተሰብ እያስቸገርኩኝም ቢሆን እሷን መንከባከብ አላቆምኩም ነበር ጊዜው እየሄደ ሲመጣ ቤተሰቦቼም እየተሰላቹ መጡ በሆነው ባልሆነው ላኩልኝ ብዬ ሳስቸግር ናኦዴም እንደዛው በጣም መስዋትነት ከፍለዋል በዙሪያዬ ያሉት ሁሉ የዚ ችግር ሰለባ ሆነዋል . . 5ወር ሞላትና ሆዷም ስለገፋ ይበልጥ እየተጨነቅን መጣን ግራ ገባን ጊቢ ውስጥ እንደዚ ሆና መታየት የለባትም ብዬ አሰብኩኝና ለናኦዴ ስለ ዶክተሩ ነገርኩትና በጣም ጥሩ ሰው ነው አለኝ በቃ ሊረዳን የሚችለው እሱ ብቻ እንደሆነ ነገርኩት ከረዳቹማ አሪፍ ነው ግን እኔ አለሁልሽ እሺ ብቻሽን አይደለሽም የኔ ቆንጆ አለኝ እሺ ናኦድዬ የኔ ፍቅር አመሰግናለው አልኩት እና ከናኦዴ ጋር ትንሽ እንዳወራን ተለያይተን ዶርም ሄጄ ለ ዶ/ር ሳሙኤል ደወልኩለት እና ስልኩን አንሳ ዶክተር አስታወስከኝ ሳሮን ነኝ አልኩት ኦኬ አዎ እንዴ አንቺን እንዴት ረሳሻለው አለ አመሰግናለው ዶክተር ግን ልናገኝህ ፈልገን ነበር አልኩት ወደ ማታ እንጂ አሁን አልችልም አለ እሺ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት ሊያ ምን ታስቢያለሽ የሆነ መፍትሔ ከሱ አናጣም አልኳት አዎ እናግኘው አለችኝ ወደ ማታ ላይ ደውለንለት ሄደን አገኘነው እና ትምህርት ጥሩ ነው አለን አዎ አሪፍ ነው ብለነው ስለ ወራቱም ነገርኩትኝ እና እንዴ አምስት ወር ሞላት? አለ አዎ አልኩት በጣም ይገርማል ጊዜው በጣም ይሮጣል አለና እኔ አሁን ላይ የመጣልኝ ነገር ምንድነው ዊዝድሮው ትሙላና እኔ ጋር መሆን ትችላለች አለ አረ እሷንማ ብቻዋን አልተዋትም ብዬ እኔም እሞላለው አልኩት መልካም እሺ ሁለታቹም ሙሉና ነገ በማንኛውም ሰዓት ደውሉልኝ አለን እኛ አንድ አመት አቋርጠን በሚቀጥለው አመት ልንማር ነው የወሰነው ትምህርቱን . . እሺ ብለነው በነጋታው ዊዝድሮው ሞልተን ሁለታችንም አመሻሽ ላይ ደወልንለት እቃችንን ሁሉንም ነገር ይዘን ከጊቢ ወጣን እና ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ መጣና በራሱ መኪና ቤቱ ወሰደን ጊቢው ሲያምር በጣም ሰፊና በአበባ ያጌጠ ጊቢ ነው የጊቢው ሳይገርመን ቤቱ ስንገባ ሳሎኑ መኝታ ቤቶቹ የተንጣለለ ቪላ ቤት ነው ያለው እናመሰግናለን በእውነት በጣም ጥሩ ሰው ነህ አልኩት አረ ችግር የለውም አለና እንግዲ ቤት ቤት አስመስሉት አለና ሻወር ሊወስድ ገባ እኛም ቡና አፍልተን ጠጥተን ምናምን የሆነ መድኃኒት አመጣና ይሄ ለእርግዝናሽ ጥሩ ነው ብሎ መድኃኒቱን ሰጣት ሊያም መድኃኒቱን ጠጥታ ትንሽ እንኳን ሳትቆይ ተኛች እኔም በቃ ሳሚ ደና ደር ልንተኛ ነው አልኩት እሺ ግን ከይቅርታ ጋር መኝታዬን ታስተካክይልኝ አለ አረ ችግር የለውም ብዬ መኝታውን አነጣጥፌለት ጨርሼ ዞር ስል ፎጣ ብቻ ለብሶ ከኋላዬ ቆሟል.... ✎ ክፍል 9 ከ50Vote💙 ቡሀላ ይቀጥላል ቶሎ ቶሎ Vote💙 አድርጉ
Показати все...
​​​​​​​​┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄            ❣:¨·.·¨: ❣ ⇨ሳሮን🌺 ┈┈••◉❖◉●••┈ ✎ ክፍል 1⃣1⃣♥️ ┈••◉ሊያ እንዴት ናኦድን የመሰለ ልጅ ትተሽ ከዚ ሰውዬ ጋር ስለ ፍቅር ምናምን ታወሪያለሽ ብላ ተቆጣችኝና ክፍሏ ገብታ በሩን ዘግታ ቁጭ አለች እኔን ቢያንስ አንድ የሚረዳኝ ሰው እንኳን አጠገቤ የለም?? ብዬ በጣም ተሰማኝ ጭንቅላቴ እራሱ ደንዝዞብኝ የማስበው ነገር ሁሉ ትክክል አይደለም በቃ ናኦዴን ህይወቱን ማዳን አለብኝ ብዬ ወሰንኩኝ እና ለሊያ ላስረዳት ሞከርኩኝ ግን ምንም ልትረዳኝ አልቻለችም ካላመንሽኝ ይሀው እኛ ስናወራ መስማት ትችያለሽ ብያት ወደ ሳሚ ክፍል ገባሁኝ እና እሷ ደሞ በሩ ስር ቆማ እኛን መስማት ጀመረች ሳሚዬ በጣም እየጨነቀኝኮ ነው አረ የሆነ ነገር በለኝ ናኦድን ማዳን አለብን ያለሀኝ ብቸኛ ሰው ደሞ አንተና አንተ ብቻ ነህ እባክህን ሳሚዬ አልኩት ይሀውልሽ የኔ ቆንጆ እኔ በህይወት እያለሁኝ አንቺ ምንም መቸገር የለብሽም አለኝ ስለዚ የታለ ታድያ እርዳታህ ስለው ወደራሱ ጎትቶኝ እራሱ ላይ አስቀምጦኝ ጉንጬን እየሳመ ቀላል ነው ብሎ ሊያስተኛኝ ሲል አይሆንም ብዬ ዘልዬ ተነስቼ ወጣሁኝ አየሽልኝ አይደል አልኳት ለ ሊያ በጣም ይቅርታ የኔ ቆንጆ ለካ ወደሽ አይደለም አለችኝ ስለዚህ ናኦድን ለማዳን ምንም ነገር እናደርጋለን አይደል ስላት አዎ ጓደኛዬ በርቺ አለሁልሽ አለችኝ ከዛ ለሊያ አንድ ሚስጥር ነግሬያት ወደ ሳሚ ክፍል ገባሁኝና እና ሳሚ እቺን ልጅ እንዴት እናርጋት ስለው ቀላል ነው ብሎ የእንቅልፍ መድሃኒቱን በጁስ አርጎ ሰጠኝ እኔም ወድጄ ሳይሆን በግዴ ሄጄ ለሊያ ጁሱን ሰጥቻት ቀጥታ ወደ ሳሚ ክፍል ገባሁ ሳሚ ተኛች እንዴ አለ አዎ ስለው አላመነም ሄዶ ሲያያት ጦሽ ብላ ተኝታለች አንቺ ከመቼው ተኛች አንቺ ግን ጎበዝ ነሽ እሺ አለኝ አመሰግናለው ግን ሳሚ አንተኮ . . ትልቅ ሰው ነህ እንዴት አድርጌ ይሄንን ነገር እንደማደርገው አላውቅም አልኩት ታደርጊዋለሽ በጣም ቀላል ነው አለኝና በፍጥነት ልብሱን አወላልቆ የኔን ልብስ ከላይ የለበስኩትን ጃኬት አወለቀው ሳሚ በጣም ፈርቻለው አልኩት አትፍሪ የኔ ቆንጆ ምንም የሚያስፈራ ነገር የለም አለ አልገባህም ማለት ነው አልኩት ምኑ ነው ያልገባኝ አለ እኔኮ ድንግል ነኝ አልኩት አትዋሺ እኔ አላምንሽም አለኝ እውነቴን ነው ስለው በደስታ ጦዞ የኔን ልብስ ለማውለቅ ታገለኝ ቆይ እንጂ ተረጋጋ ስለው ምንም መረጋጋት አያስፈምግም ብሎ በስሜት ትንፋሹ ተቆራርጦዋል ለምን ታስለፊኛለሽ የኔ ቆንጆ እኔኮ እወድሻለው አለና ከላይ የለበስኩትን ቦዲ በግድ አወለቀው እና ወደሱሪዬ ሲመጣ ጮኩኝ ግዴታ መጮህ ነበረብኝ ከዛ ምን ያስጮህሻል ሳልነካሽ አለ እንዴ አልኩኝ ድምፄን ከፍ አድርጌ አረ አታካብጂ ይላል በስሜት ጦዞ ሊያ በሩን ቀስስ ብላ ከፍታ በዘነዘና አናቱን አለችው አንቺ ግን አብደሻል እንዴ አልኳት ምነው ስትለኝ ለምን ቆየሽ አልኳት ፈራሁኝ አለችኝ መጀመሪያ ተነጋግረን የገባሁት ልክ እሱ በስሜት ሲጦዝ እሷ መታ እድትገላግለኝ ነበር የእንቅልፍ መድኃኒቱ ማለትም ጁሱን አልሰጠኋትም አውቃ እንድታስመስል ነበር ያደረግነው ምን ሆነሽ ነው ይሄን ያህል የቆየሽው አንድ ነገር ቢያደርገኝስ ብዬ ጮኩባት እና ይቅርታ አለችኝ እሺ ግን በደምብ ነው . . የመታሽው ስላት አዎ አለች እንደማይነቃ እንዴት እርግጠኛ ነን ስላት ደግሜ ልምታው እንዴ አለችኝ ሃሃሃሃ ቅርጫ ልታረጊው ነው እንዴ አሁን መፍጠን አለብን ብዬ ቀጥታ ወደ ካዝናው አመራን እኔ ከዚህ በፊት ሲከፍተው ስላየሁኝ የካዝናውን የሚስጥር ቁጥር አውቀዋለው እና ልክ ስከፍተው ያገር የአሜሪካን ዶላር አለበት የኢትዮጵያ ብር እራሱ ተቆጥሮ የማያልቅ ገንዘብ ነው ያለው በቶሎ አንድ ሻንጣ አቀበለችኝና ከዶላሩም ከኢትዮጲያም ብር ግማሽ ግማሹን ይዘን ሻንጣውን ሞልተን በቶሎ ከዛ ቤት ወጣን ይሄ ሁሉ ነገር ሲፈጠር ከሌሊቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነበር ከዚ ከተማ ወተን መሄድ አለብን ብያት ቀጥታ ወደ መናሃሪያው አመራን መናሃሪያ ውስጥ ምንም የለም ግዴታ ሌሊት በሚበረው መሄድ አለብን ብለን እየተጠባበቅን እያለን የታባታችሁ ልቴዱ ነው አለን አለቀልን በቃ ብለን ተፋጠጥን....የታባታችሁ ልቴዱ ነው ነው አለን አለቀልን በቃ ብለን ተፋጠጥን ሊያ ወይኔ ምን ሊያደርገን ነው አለች አይዞሽ አትፍሪ እንጋፈጠዋለን አልኳት ቦርሳችንን ወደኃላ አርገነው ሊያ የያዘችውን ስልክ አይኑ ላይ ስታበራበት ለካ አንዱ ሰካራም ነው ኡኡኡፍፍፍፍ ፈጣሪዬ ሆይ ተመስገን ብለን እኛን የመሰለን ዶ/ር ሳሚ ነበር ምን ፈለክ ስንለው እገላቹዋለው አለ አረ ባክ ምናምን አለችው ሊያ ተይው እኔ ለሱ እበቃዋለው ብያት ረጋግጬው ትሄዳለህ ወይስ ድጋሚ ላጋጭህ ስለው ሄዳለው ሄዳለው አለና ነካው..... ✎ ክፍል 1⃣2⃣ ከ30Vote ቡበላ ይቀጥላል...
Показати все...
​​​​​​​​┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄            ❣:¨·.·¨: ❣ ⇨ሳሮን🌺 ┈┈••◉❖◉●••┈ ✎ ክፍል ዘጠኝ♥️ ┈••◉መኝታውን አነጣጥፌለት ዞር ስል ፎጣ ብቻ ለብሶ ከኋላዬ ቆሟል ሳሚ ጨርሼያለው አልኩት እና ይሄን የመሰለ አልጋ ላይ ብቻዬን ልታሳድሪኝ ነው እንዴ አለና እኔን ያዘኝ እጁን ከላዬ ላይ አንሰስቼ የጓዳውን በር ልከፍት ስቿኮል በቁልፍ ቆልፎታል አይዞሽ ጓደኛሽ አትሰማንም ቅድም የእንቅልፍ መድሃኒት ነው የሰጠሁዋት ግን ፅንሷ ላይ ምንም አይነት ኢፌክት አይፈጥርባትም አለ እና ዶክተር አንተኮ ትልቅ ሰው ነህ እንዴት እንደዚህ አይነት ነገር ከኔ ትጠብቃለህ ስለው ምንምኮ ችግር የለውም ብሎ ወደኔ ተጠጋ ዶክተር እኔ ምንም ነገር ማድረግ አልፈልግም ለራሴ ያለብኝ ችግር ይበቃኛል ስለው አሁን ለችግሮቹ እኔ አለው አለና ሰውነቴን ሲደባብስ እሾክ ነገር እላዬ ላይ የተጎተተ ያህል ነው የተሰማኝ እጁን ከላዬ ላይ አንስቼ አልችልም አልኩት ትዝ ይልሻል ሊያን ይዘሻት የመጣሽ ጊዜ ያላረገዘች መስሎሽ ዘለሽ ያቀፍሽኝ ጊዜ ጡቶችሽ ደረቴን ወጋ ወጋ ሲያደርጉት የተሰማኝን ደስታ ልነግሽ አልችልም አለ . . ለዛ በጣም ድቅርታ እንደዛ እንዲሰማህ ፈልጌ አልነበረም ሳላስበው ነው አሁን ልሂድ አልኩት ጓደኛሽን አስቢያት አለኝ ያ ማለት ግዴታ ይሄንን ነገር ማድረግ አለብሽ አለበለዚያ አውጥቼ እጥላቹዋለው ማለቱ ነው ብዬ ግንኮ ፍቅረኛ አለኝ በጣም የምወደው አልኩት እና እኔን ትጠይኛለሽ ማለት ነው አለኝ እንደዛ ማለቴ አይደለም ዶክተር እያስጨነከኝ ነውኮ ስለው ነይ እስቲ እንደውም አልጋ ላይ ቁጭ እንበል አለና ሁለታችንም አልጋው ላይ ቁጭ አልን የማትፈልጊ ከሆነ አላስጨንቅሽም ግን አንድ ቀን ትፈልጊኛለሽ አለ አመሰግናለው ዶ/ር ሳሚ አሁን በሩን ክፈትልኝና ሊያ ጋር ልተኛ አልኩት እዛ ጋር አለልሽ ቁልፉ አለ እሺ ደና ደር ብዬው በሩን ከፍቼ ሊያ ጋር ተኛሁኝ እና በነጋታው ተነስቶ እንዳይደብራቹ እሺ በቃ እንደቤታቹ አርጋቹ ቁጠሩት አለና ሄደ እኛም እዛ ቤት ውስጥ ውሎ ማደሩን ጀመርነው እና በሁለተኛው ቀን ለ ናኦዴ ደውዬለት ከጊቢ እንደወጣን ነገርኩት እና ዶክተሩ ጋር እንደሆንንም ነገርኩት በጣም ተናደደ ምን ጊቢውን ለቀሽ መሄድሽ ሳያንስ ወንድ ቤት ለሁለት ተያይዘን ሄድን ስትይ ትንሽ እንኳን አታፍሪም አለ ለምን አፍራለው ናኦዴ ሁሉንም ነገር እያወከው ስለው ባክሽ ይሄንን የማይረባ ወሬ ተይና ከዛ ቤት ለቀሽ ውጪ ልጅቷን ለቤተሰቦቿ እንልካታለን ሲለኝ ሁለታችንምኮ ዊዝድሮው ሞልተናል ስለው አብደሻል እንዴ አንቺ ምን ልቶኚ ነው ዊዝድሮው የሞላሽው ሲል እኔ ወስኜ አምኜ ላደረኩት ነገር እንድታጣጥልብኝ አልፈልግም ደሞ ከጎንሽ ነኝ አላልክም ነበር እንደዚ ነው ከጎኔ የምቶነው ስለው በርቺ ግን ዶክተሮች ሁሌም ቢሆን በሴቶች ላይ አይታመኑም እሺ አለኝ እሺ እራሴን ጠብቃለው አልኩት እሺ ቻው ብሎ በመጨቃጨቅ ብቻ ሳንግባባ ስልኩ ተዘጋ በጣም ተበሳጭቶብኛል ግን እኔ ለራሴ ትክክል እንደሆንኩኝ ነው የሚሰማኝ ፈጣሪዬ ሆይ አንተ እርዳኝ ብዬ ትግሉን ቀጠልኩኝ . . ቤት ውስጥ ሁሉም ነገር አለ ሊያንም በደምብ እየተንከባከብኳት ነው ግን ይሄ ሰውዬ እንደዛ ካለኝ በኋላ ምንም እያመንኩት አይደለም ሌላ ነገር ማሰብ ጀመርኩኝ ከሱ ውጪ ሊረዳን ወደ ሚችል ሰው ግን ምንም ነገር ሊመጣልኝ አልቻለም እንደድንገት ናኦዴ ደወለልኝ ምን ሊለኝ ይሆን ብዬ ስልኩን ሳነሳው ሳሮንዬ ጮኩብሽ አይደል በጣም ይቅርታ እሺ አለኝ ችግር የለውም የኔ ጌታ አልኩት ላገኝሽ እችላለው አለኝ አዎ ምን ጥያቄ አለው የኔ ውድ ስለው ወሳኝ ነገር ልነግርሽ ነው አለኝ እሺ ብዬ ሊያን እንዳይደብርሽ ብዬ በቶሎ ከቤት ወጥቼ ስሄድ አዝኖ ጉስቁል ብሎ ቁጭ ብሏል ናኦድ ምንድነው ሰላም እንኳን አትለኝም እንዴ ስለው እሺ ብሎ እየደበረው ሰላም አለኝ ምንም ነገር ደስ ያለው አይመስልም ችግር አለ ናኦድዬ አሞል እንዴ ስለው ደና ነኝ ግን ተይው በቃ ላስጨንቅሽ አልፈልግም አለ ናኦድ ንገረኝ ብዬ አስጨነቅኩት..... ✎ ክፍል 🔟 ከ20Vote ቡሀላ ይቀጥላል
Показати все...
​​​​​​​​┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄            ❣:¨·.·¨: ❣ ⇨ሳሮን🌺 ┈┈••◉❖◉●••┈ ✎ ክፍል 1⃣2⃣♥️ ┈••◉እኛ ከዛ ከተማ መውጣት አለብን ብለን እስከወሰንን ድረስ በቶሎ ካልወጣን አለቀልን ብለን አሰብን ለምን መንገድ ላይ ወተሽ ሌላ መኪና ካገኘሽ አትፈልጊም አለችኝ እሺ ብዬ ወደ መንገዱ በጥንቃቄ ወጣ አልኩኝ የሆነ አጠገቤ ላይ ከመች መች መቶ ይዘኛል የሚል ፍራቻ አንቀጥቅጦኝ ልሞት ነው ሳስቆማቸው አይቆሙልኝም በጣም ከታገስኩኝ በኋላ አንዱ መቶ ምነው እናት በዚ ሰዓት ሲለኝ የት ነህ ስለው እኔ እንኳን ወደ አዳማ ነኝ አለ በግዛቤር አብረን እንሂድ ስለው እሺ አለና ጊቢ አለኝ ጓደኛዬ አለች አልኩት እሺ ይዘሻት ነይ አለና በሩጫ ወደ ሊያ ሩጬ ሊያን ይዣት ወደ ሰውዬው ሄድኩኝ እና ፈጣሪ ረድቶን ከዛ ከተማ ወጣን እና ለምንድነው ወደ አዳማ የምቴዱት አለን ወደ አዳማ እንኳን አይደለንም ወደ አዲስ አበባ ነን ችግር የለውም ሞጆ ላይ እንወርድ ወደ አዲስ አበባ እንሳፈራለን አልኩት አሺ ግን ምን አጋጥሞዋችሁ ነው አለን አይ ተከራይተን ነበር የምንኖረው እና አከራያችን ጋር ተጣልተን የምንሄድበት የለንም እና ለዛ ነው አልነው ሊያ ከኋላ ቁጭ ብላ ሊሊዬ ተኚ በቃ እሺ አልኳትና ተኛች እኔና ሹፌሩ በዛች ሌሊት ስንቀደድ ስንቀደድ ጉዞዋችንን ቀጠልን ከሌሊቱ 6:30 አካባቢ ሆነ እና ቦርሳውስ ሲል ክው አልኩኝ የምን ቦርሳ ማለቴ ምን ስለው ምነው ደነጥሽ ሲለኝ አይ ሌላ ነገር እያሰብኩኝ ነበር የምን ቦርሳ ነው ያልከኝ ስለው ይሄ ብቻ ነው ወይ የናንተ ቦርሳ ማለቴ ነው አለ አዎ የተወሰኑ እቃዎች ነበሩን ግን ትውሰዳቸው ከጠቀማት ብለን ተውንላት አልኩት ፈጣሪዬ ሆይ ይሄ ሰውዬ ቦርሳቹን ልፈትሽ ብቻ እንዳይል አልኩኝ ወረኛ የሆነ ሰው ነው እንደዚ አይነት ወረኛ ወንድ አጋጥሞኝ አያውቅም እንዴ ሰው ለደቂቃ አያርፍም አስተበተበኝኮ ብቻ ቀስ እያለ ስለነዳ ወደ 10:30 አካባቢ ሞጆ ደረስን እና በጣም እናመሰግናለን የምር ጥሩ ሰው ነክ ብለን መቶ 200ብር ስሰጠው እምቢ አለ እንዴ የሆነ ነገርማ ውሰድ ስለው አረ እንደውም እኔ የትራንስፖርት ልስጣችሁ ብሎ ብር አላወጣም አይሆንም እኛ ትራንስፖርት አለን አልኩት እሺ ስልካችሁን ስጡኝና ልደውልላችሁ ሲል አረ እኛ ነን የምንደውልልህ ብለነው ስልኩን ተቀብለነው ሄድን አንድ ዜና ሰምቶ ደሞ ጉድ ያርገን እንዴ ብለን እሺ ብሎ ያዢ ብሎ ስልአኩን ሰጠን እሺ ቻው ብለን ተሰናበትነው እና ሞጆ ላይ ለ አንድ ሰዓት ያህል ቁጭ ብለን ጠበቅን ደግነቱ ወደ አዲስ የሚሄዱ ሰዎች ብዙ ስለነበሩ አልፈራንም ነበር 11:00 ሰዓት አካባቢ ተሳፈርንና አዲስ 01:00 ላይ ሸገር ተገባ ኡፍዮ አልኩኝ በቃ ወደ ቤት መሄድ ነበረብኝና ቀጥታ ሊያንና ብሩን ይዤ ቤት ሄድኩኝ ልክ ስደርስ ሳሮን ሳሮን የሰፈር ልጆች ሁሉ ፒስ ነዋ ብዬ ትቻቸው ገባሁ ስሚ ሊያ ደሞ ኬት ነው አስጭነሻት የመጣሽክ አሉ ዝም በሉ እናንተ አዛ ሁላ ብዬ ቤት ስንገባ አንቺ አለች እናቴ በጣም ነበር የናፈቀችኝ መጣሁ ተብሎ እንኳን አይደወልም አለች አባቴም ስሚ አንቺ ጦጣ መች መተሽ ነው ቆይ እንደዚ የዘጋሺኝ አለኝ አባዬ ብዬ እቅፍ አርጌ ሰላም ብዬ ስሞኝ ሊያንም አስተዋውቄያቸው እንዴት መጣሽ ለምን መጣሽ የሚል ጥያቄ ከግራ ከቀኝ ጆሮዬን ሊበሱኝ ምንም አልቀራቸውም እና እሺ እነግራቹዋለው ግን ከሁለታቹ ወጪ እዚ ቤት ማንም መኖር የለበትም አልኳቸው እሺ ብለው ልጆቹን አባረዋቸው ወሬውን ጀመርኩላቸው የተፈጠረውን እያንዳንዷን ነገርኳቸው ምንም ነገር ሳላስቀር አባቴ ግን አንቺ የኔ ልጅ ነሽ?? አለ አዋ ለዛውም የዘነጥኩኝ አልኩት ለካ እቺ ናት ባለፈው Hand out in out ምናምን ብለሽ ሳንቲም ስትቀባበይ የነበርሽው አንቺ ጉደኛ አለኝ አዎ አልኩት ግን ያንን የማይረባ ዶ/ር እንኳን ሰራሽለት ይሄ ልክስክስ አለ ሌላው ህይወቱን ሊያጣ ከነፍስ ጋር ይታገላል እሱ መልከስከስ ያምረዋል አለ አዎ አባዬ ብለን እየተሳሳቅን አሁን ጊዜ የለንም አባዬ ብዬው አንድ ስምንት ከ 4 ቀን ብቻ ነው የቀረን አልኩት እሺ የኔ ልጅ ብዙም ጊዜ የለንም ግን የቲኬቱን ነገር እኔ ልጨርስ አለ አይ ቆይ መጀመሪያ ለናኦዴ ደውዬ ልንገረው አልኩት እሺ አለ ለናኦዴ ደውዬለት ናኦዴ የኔ ጌታ የኔ ፍቅር የምስራች ስለው አተር ብይ የኔ ቆንጆ ምን ተገኘ አለ አረ አሁኑኑ ወደ ሸገር ትመጣለክ አልኩት ለምን ሲል መፍትሔ ተገኘያ የኔ ልዑል አሁኑኑ ናልኝ ከሆስፒታል ሪፈሩን ይዘክ አሁኑኑ ና ከፈለክ እናትህን ይዘሃት ና አልኩት ግን ብሩን ኬት አመጣሽው ደሞ ከመቼው ሄድሽ ይሄን ያህልስ መቸኮሉ ለምን አስፈለገ አለ ለካ ደሞ ትንሽ ጊዜ እንዳለውም ማንም አልነገረውም ናኦድ በቃ ያለህ ጊዜ በጣት የሚቆጠር ጊዜ ነው አልኩት ምን ብሎ ስልኩን ሳይዘጋ ማሚ ብሎ ጮሀ ወይኔ ጉዴ ናኦድ ናኦድ ስለው ማልቀስ ጀመረ.... ✎ ክፍል 13 ከ20 Vote❤️ ቡሀላ ይቀጥላል...
Показати все...
​​​​​​​​┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄            ❣:¨·.·¨: ❣ ⇨ሳሮን🌺 ┈┈••◉❖◉●••┈ ✎ ክፍል ስድስት♥️ ┈••◉ከሴቶች ዶርም ምንድነው የምትሰራው አሉት ምን ይመልስ? ግራ ገባው! እኛን ጠየቁን ለምንድነው ያስገባቹት ብለው ሲጠይቁን አረ አላስገባነውም በሩን ሲያንኳኳ ምንድነው ስንለው አያወራም ዱዳ ነው መሰለኝ አልኳት ከዛ እናንተ መጣቹ ያዛቹት አልናቸው እነሱም ወደ ቢሮ ወሰዱት እኛ ዱዳ ነው ያልነው ነገር የሚገርም አጋጣሚ ነበር ጠቀመው የጊቢው ፕሬዝዳንት ጋር ተወስዶ ለአራት ቢያፋጥጡት ቢያወሩት ቢለምኑት ፈርም ቢሉት አይሰማም . . ቀጥታ ወደኛ ዶርም ይዘውት መጡ ፕሬዝዳንቱ እኔን ጠየቀኝ መጀመሪያ ሲመጣ ምን አልሽው አለኝ በሩን አንኳኳ ስከፍትለት ሊገባ ሲል መግባት አትችልም አልኩት ዝም አለ ሂድ ስለውም ምንም አልሰማ ሲል በሩን ልዘጋበት ስል ፕሮክተሮቹ መጡ ይዘውት ሄዱ ሳስበው ማውራት አይችልም ሲያሳዝን አልኩኝ! ዝም በይ አንቺን ማን አዛኝ አደረገሽ አለኝ ፕሬዝዳንቱ እሺ ዝም እላለው ብዬ ናኦድን በሙድ ዝጋ ትንፍሽ እንዳትል አልኩት . . ከዚህ በፊት ማውራት አለማውራቱን ለማረጋገጥ መታወቂያውን ከኪሱ ውስጥ አውጥተው ዶርሙን አውቀውት ቀጥታ ወደ ዶርሙ አመሩ ዶርሙ ሲደርሱ የዶርሙ ጓደኞቹ ሁላቸውም ዶርም ውስጥ ነበሩ በሩን አንኳክተው ገቡና ይሄንን ልጅ ታቁታላቹ አለ ፕሬዝዳንቱ እንዴ ናኦዴን በጣም እንጂ ምርጥ ሰው ነችኮ ምናምን ሲሉ የተጠየቃቹትን ብቻ መልሱ አለ ፕሬዝዳንቱ እሺ ብለው ለጥያቄ ተዘጋጁ ከዚህ በፊት ያወራል ብሎ ጠየቃቸው አንድ በአንድ መልሱልኝ አላቸው ሚኪ : አዎ ግን አንዳንዴ ሲደብረው እኔ ነኝ የማወራለት አለ ፕሬዝዳንት ፡ ቀልድ አልፈልግም ያሬድ : አይናገርም ፕሬዝዳንት ፡ እንዴት ጓደኛክ ያወራል አለኮ ያሬድ ፡ ከኔ ጋር ስለተጣላ ሰምቼው አላውቅም ድምፁ ራሱ ናፍቆኛል ፕሬዝዳንት ፡ ባትቀልዱ ይሻላችሁዋል ብሎ ሌላኛውን ሲጠይቀው ቢኒ ፡ ያወራ ነበር ግን ሰሞኑን አናግሮኝ አያውቅም ይመስለኛል አይመስለኝም ዬትኛው ይሻላቿል አላቸው? ፕሬዝዳንት ፡ አሁን ቁምነገር ብቻ ነው የምፈልገው አለበለዚያ የማደርገውን እኔ ነኝ የማውቀው አለ አንድ ሚስኪን ተማሪ አለ ቁምነገረኛ ብቻ የማይገልፀው አብነት : ወንድሜ እኔ ናኦድን ሳውቀው በጣም ምርጥና ፀባየኛ ልጅ ነው . . ምን እንደሆነ ባላውቅም ስለዚ አሁን አለማውራቱ ለምን አሳሰባቹ? ጤንነቱ ነው ሊያሳስባቹ የሚገባው ወደ መፍትሔ ብትሄዱ ነው የሚሻላቹ አለ ፕሬዝዳንት ፡ እሺ እናመሰግናለን ብሎ ይዘውት ሄዱ እና ምንም መፍትሄ ሲያጡበት ወደ አንድ ድምዳሜ ደረሱ ጊቢ ውስጥ በተለምዶ ደም የለመደ ቦታ ተብሎ የሚጠራበት ቦታ አለ ማለት እርኩስ መንፈስ አለ ተብሎ የሚታወቀው የመጨረሻ ብሎክ ማለት ነው በአመት አንድ ተማሪ ያብዳል ወይም ይሞታል እኛ ደሞ እዛ አካባቢ ነን እሱን ግምት ውስጥ በማስገባት እንደዛ አይነት ነገር ይሆናል ምንም ነገር ማድረግ አንችልም ብለው ለቀቁት . . ሲለቁት ቀጥታ ወደ ዶርሙ አቀና ወዲ ወዲያ ሳይል እቺን ቀን እንደዛ አለፍናት ወደ ከሰዓት አካባቢ ተገናኝተን እያወራን በነገራችን ላይ አድናቆቴን ሳልገልፅልህ አላልፍም አንተ ዱዳውን ቁጭ አይደል እንዴ ያደረግከው በስመዓብ ትወና የግልህ ነው አልኩት አዎ እንግዲ ፈጠሪ በዚ መንገድ አምልጥ ሲለኝ ነው እኔ ሳቄ የመጣው የዶርማችንን ተማሪዎች ሲጠይቃቸው ነው ደረቆች ናቸው አለ ወሬያችንን እያጧጧፍን እያለ ሊያ እያለቀሰች መጣች ከውጪ ሊያ ምን ሆነሽ ነው እንደዚህ የምታለቅሺው አልናት ፀምንም አትመልስም ናኦዴን ትቼው ሊያ ጋር ሄድኩኝ ወደ ዶርም ገባንና ምን እንደሆነች ስጠይቃት ወይኔ ሳሮንዬ ጉድ ሆንኩልሽ አለች ምን ሆነሽ ነው የምን ጉድ ሊያ ንገሪኝ አልኳት አለቀልኝ በቃ አለችኝ አረ ሊያ ስላት አትጠይቂኝ ሳሮንዬ አለችኝ ..... ✎ ክፍል 7⃣ ከ30Vote❤️ቡሀላ ይቀጥላል አንብበው ሲጨርሱ Vote እና Sher ማድረግ አይርሱ
Показати все...
           ❣:¨·.·¨: ❣ ⇨ሳሮን🌺 ┈┈••◉❖◉●••┈❤️ ክፍል አራት♥️ ┈••◉አንገቴን አንቃ ያዘችኝ መተንፈስ አቃተኝ ለሁለት ስለሆነ የያዙኝ ደንግጫለው ግን በደምብ ከነቃሁ በኋላ እንደምንም እጇን ከአንገቴ ላይ አስለቅቄ ሁለታቸውንም ከራሴ ላይ አንስቼ መብራቱን ላበራው ወደ መብራቱ ስሮጥ ከኋላዬ እብድ በሚያክል ዱላ አናቴን መታችኝ ከዛ ሰዓት ጀምሮ እራሴን ሳላውቅ ነጋ እራሴን ሳውቅ ሆስፒታል ውስጥ መሆኔን ብቻ ነው የማውቀው ለነርሷ ምን ሆኜ ነው እዚህ የመጣሁት ብዬ ጠየኳት የድብደባ ጥቃት ደርሶብሽ ነው አይዞሽ እሺ ይሻልሻል አለችኝ ሁሉም ነገር ትዝ አለኝ ጭንቅላቴን ስደባብሰው የተሰፋ ነገር እንዳለ ተሰማኝ . . በጣም ተናደድኩኝ ማንም አጠገቤ የለም አንድ ሰው እንኳን አጠገቤ የለም ብዬ እያማረርኩኝ እያለ ሳሮንስ ሳሮንስ የሚል ድምፅ ከውጪው ሰማሁኝ መግባት አትችልም ምናምን ብላ ትጨቀጭቀዋመች ነርሷ ናኦድ ነበር እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ መግባት ይችላል አልኩኝ አሞኝ የጮኩኝ መስሏት ወደኔ ስትመጣ ተከትሏት ገባ ደና ነሽ ሳሮን አለች ለምንድነው የምትከለክይው እሱኮ ከፈጣሪ በታች ሰላሜ ነውኮ እባክሽን ከኔ ጋር ይሁን አልኳት ግንኮ ሳሮን ማውራት የለብሽም አሁን አለችኝ ችግር የለውም እኔ በምልክት ቋንቋ አወራዋለው አንቺ ብቻ ውጪልን አልኳት ሆ ብላ እሺ በቃ አንተ እንዳታዋራት እሺ አለችው እሺ አላትና ነርሷ ወጣች ማነው እንደዚህ ያደረገሽ ጊቢ ውስጥ ወሬው ሲጧጧፍኮ ጭራሽ አንቺ አልመሰልሽኝም ነበርኮ የኔ ቆንጆ እኔን እሺ አለ አረ ጠላትህ የኔ ቆንጆ አንተማ ምንም አትሁንብኝ አልኩት አንድ ነገር ብቶኚ መቼም ለራሴ ይቅርታ አላደርግለትም ነበር አለ አንተ ምን አጠፋህ ውዴ ስለው እያለቀሰ ማታ ከኔ ጋር ቆመሽ እንደቀኑብሽ ሲያወሩ ሰምቼ ነው እዛ ጋር ላስቆምሽ አይገባም ነበር ይቅርታ ሳሮንዬ እያለ አለቀሰ አረ ናኦዴ ይሄኮ ተራ ነገር ነው በጭራሽ ቦታ ልትሰጠው አይገባም እንጂ እንዴ??? ብዬ አባበልኩት እና እሱ እንዳይጨነቅ ብዬ በጣም ደና ነኝኮ ያው የነርሶቹን ፀባይ ታውቅ የለ ትንሽዬ ክባድ ይጨምሩበታል ብዬ እንደምንም አረጋጋሁት እና ወደ ራሱ መለስኩት ይልቅ ናፍቀሀኛል ና ሳመኝ አልኩት አረ እስምሻለው የኔ ቆንጆ ብሎ እየሳመኝ እያለ . . ተርሷ ኬት መጣች ሳይባል ከች አለች አንተ ምን እያደረክ ነው አሟታልኮ አለች ውይይ እኔ ከዚህ ሆስፒታል አስወጡኝ ብዬ ቀወጥኩት ለምን ስትል ሌላ በሽታ እየጨመርሽብኝኮ ነው አይታይሽም እንዴ እሱ እኔን እያከመኝ ነው በቃ ወይ ሌላ ነርስ ይቀየርልኝ አልኩኝ እሺ እንደፈለግሽ ብላ እየተመነቃቀረች ወጣች ናኦድ ለምን እንደዛ አልሻት የኔ ቆንጆ አለ አረ ተዋት አለኩትና ይልቅ ና አውራኝ አልኩት እሺ በቃ የኔ እብድ ብሎ ከወሬው በፊብ ግን አንዴ አለ የት ነህ ስለው 2ደቂቃ ብቻ አለና ያገር ጁስ ኬክ ዳቦ ያላመጣው ነገር የለም ውይ የኔ ነፍስ በጣም ርቦኝ ነበር እሺ ብዬ የሚገርም ቁርስ አብሮኝ በላ መጣች አዴ ነርስ እንዴት ነሽ ሳሮን አለችኝ የኔ ቆንጆ አሁን ናኦዴ ከመጣ በኋላ በጣም ደና ነኝ አንቺ ግን ናኦድን ባታስገቢው ኖሮ አልቆልኝ ነበር እኔ የሚጠይቀኝን ሳይሆን የሚንከባከበኝ ነው የምፈልገው አልኳት አቤት አቤት አቤት ምላሳቸው የዘመኑ ልጆች ብላ ፈጣሪ ይማርሽ ብላ ወጣች እኔም ሆነ ብዬ ነው የጨቀጨኳት እንድትወጣልን አንቺ ግን የሴቶቹን ፀባይ ጠንቅቀሽ ታውቂ የለ እንዴ ፐፐፐፐ አለ ናኦዴ አረ የናንተንም ጠንቅቄ ነው የማውቀው አልኩት እንደዛ እየተጫወትን እየተሳሳቅን ነርሷንም እያዛግናት ቀኑን አሳለፍነው ወደ ማታ መውጣት ትችያለሽ ተባለ ውይይይ ተረስገን ብዬ ከሆስፒታሉ ወጣን ሆስፒታሉ እዛው ጊቢ ውስጥ ስለሆነ አሁን ከዚህ ጊቢ መውጣት አለብን አለ ናኦድ ማለት ስለው ማለቴ እናቴ ጋር ማረፍ አለብሽ እነዚያ ልጆች ጋር ተመልሰሽ አትሂጂ አለኝ አይሆንም ምንም ነገር አይፈጠርም አታስብ የኔ ልዑል አልኩት አንቺኮ ምርጥ ደረቅ ነሽ የኔ ልዕልት አለ አሁን ልግባ በቃ Telegram አውራኝ አልኩትእሺ የኔ ውድ ብሎ ስሞኝ ተለያየን ልክ ዶርም ገብቼ ገና ከማረፌ ወይዘሪት ሊያ በጣም ይቅርታ አለችኝ! ምን አልኳት?..... ይ ቀ ጥ ላ ል.............. @Yefker_Liboch ✎ ክፍል 5⃣ ከ30Vote❤️ ቡሀላ ይቀጥላል አንብበው ሲጨርሱ Vote እና Sher ማድረግ አይርሱ
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.