cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

አቴር...ግጥም እና ሌሎች❤

💌ደብዳቤዎች💌 ✏️ፅሁፎች✏️ 📚እይታዎች 📖 🌪️ልቦለድ ታሪኮች🌫️ 📝 አስተማሪ ማስታወሻዎች 🗒️ 🔸🔸🔸 … እዚህ ያገኛሉ🔸🔸🔸

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
179
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

# ሀገር - ቤት - ሲታሰብ ያነፈሰን ነፍስ ያቃጠለን ፀሐይ የመሸብን ፅልመት የጋረደን ሰማይ ። በኑራችን መሃል የሰማነዉ አዛን አሜን ያልነዉ ኪዳን ተጋግዘን ያዘነዉ የባልንጀራ ሃዘን ። ፡ ከረመዳን ጧሚ የቀመስነዉ አፍጥር አንጀት ያስጠፈረን የማርያም ለት ዝክር ። ፡ ሰላም ለመሳጣት ካስቀዳሽ ትከሻ ስመን ያነሳነዉ የከርቤ እንክብል ከሩቅ የሰማነዉ ፤ ያድባር ሽማግሌ የሚከረክር ሳል ። ፡ ጣራችን ያረፈ የደመና ቁራጭ ጥቋቁር ጥላሸት በድግግም ብዛት ተቀብለን ያልነዉ መዙማ ማህሌት ። አንድነት ፤ ባንድነት ። በስዉር መዳፍ ፤ እያጨባበጠ ሀገር ከመናፈቅ ፤ የለም ያመለጠ ። ገጣሚ ምግባር ሲራጅ
Показати все...
#ለዚህ_ነው_ማላምንሽ . (እዮብ ዘ ማርያም) . ቃላት አሳምረው፣ ስለ ዝናብ ውበት አድንቀው የፃፉ ዝናብ የመጣ 'ለት፣ ዣንጥላ ዘርግተው ተጠልለው አለፉ ልክ እንደዚህ ሁሉ ንፋስ ነው ዘመዴ ምናምን የሚሉ ንፋሱ ሲነፍስ መስኮት ይዘጋሉ ያንቺም ልብ እንዲህ ነው፣ ይቀበል ይመስል ፍቅር ፍቅር ብሎ ፍቅር ያካፋ ቀን ያልፋል ተጠልሎ
Показати все...
1.25 KB
Repost from የኛ ግጥም
ኤልያስ ሽታኹን ~ ~ ~ ~ ~ አልመካበትም ውጥቅንጥ ነውና የመኖር መንገዱ ባንዱ ጋ ሳበራ ጨለማ ነኝ ባንዱ። : "ያፈራል" ይላሉ "የወደቀ ስንዴ" "ካፈራሁ" እያልኩኝ እወድቃለሁ ስንቴ። : "የሚያዘነብለው ፍሬያማ ነው" ብለው እኔ ሳዘነብል ምነው? እናቃለሁ። : ሰው "ራሱን ዝቅ አርጎ ይኖራል ተባርኮ" የሚለውን ይዤ ዝቅ ስልላቸው ረግጠው የሄዱኝ ቤቴ ይቁጥራቸው።
Показати все...
Repost from የኛ ግጥም
ናፍቆት "አያ ጅቦ" ኤልያስ ሽታኹን ~ ~ ~ ~ ~ የናፈቁትን እየዳሩ የወደዱትን እየሞሸሩ (የምን እሹሩሩ) አንዴ ከሆነ ወዲያ ቢባል ሆዴ ባባ ምን ሊረባ? ያፈቀሩትን እንዲሳም ሌላን ሲታቀፍ ላያድኑት አበባን ከማርገፍ.... እንዲያው መቀበጣጠሩ ላይስተከል ነገሩ (እሱ ነው መለየት ሸሩ) እኔማ እንሆንው ያልኩትን ከሌላ ከሆነሽው "አፈቅርሻለሁን" የትም ካደረግሽው? ሁሉ በነበር ሲቀር ቅጽበትም ሲያስፈራ ህይወት እንደዚህ ናት ያልዘራሽውን ምታፈራ፡፡ አልዘራሁም አንቺን ማጣት (አጨዳለሁኝ ቅጣት) አልዘራሁም አልዘራሁ መለየት (አጨድኩኝ መሸኘት) አልዘራሁ መራራቅ ነገዬ ታየኝ እንደጭራቅ፡፡ እንደልጀነቴ እንደአያጅቦ ማጣት ሲመጣ በሰው አፍ ታጅቦ፡፡ "ይበልሃል" ሲሉኝ ጥቅልል ሽፍን ብዬ እንዲያ ነው ምፈራ መለየት አንቺዬ፡፡ እኔማ ያንን "አያ ጅቦ" ባልፍም ተድበስብሶ መለየት ግን በላኝ ያውም "ከጅብ" ብሶ፡፡ https://t.me/besye_getm
Показати все...
የኛ ግጥም

አዳዲስ እና ቆየት ያሉ ግጥሞች ለማግኘት የኛ ግጥም another channel @appandtech

ድርሻዬን ጠባቂ እንደሌለው ክዳን አልባ ቁና ክፍት ሆኜ ቢያገኘኝ እጁን ሰደደና ከቀኔ ከሌቴ እየቆየጠረ ከድሜው ጋ ደርቦ የኔን ድርሻ ናኖረ ከመፅሀፍ የተወሰደ ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም @babilon124
Показати все...
# ባህላዊ # ምክሮች # ሀሜት ፦ ያለ መሳርያ ሰዉን መግደል ነዉ ። # ማጉረምረም ፦ ባገኙት በቃኝ ብሎ አለ ማመስገን ። # ቁጣ ፦ ከስድብ የሚያደርስ የክፉ አድራጎት መሰረት ነዉ ። # ብስጭት ፦ የተበሳጩበትን ነገር ሳይሆን ተመልሶ እራስን የሚጎዳ መርዝ ከክህደት የሚያደርስ የሀጥያት ምንጭ ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነዉ ። # መርገም ፦ አቅም ሲያንስ ወደ ላይ የሚወር የደካማ ሰዎች ቀስት ነዉ ። # መሳደብ ፦ ህሊናን የሚያቆስል ቁስሉ ቶሎ የማይድን አቅም የሌላቸዉ ሰዎች ዱላ ነዉ ። # ዋዛ # ፈዛዛ ፦ በስልት የሚቃኙት የስራ ፈቶች በገና ነዉ ። # ዘፈን ፦ ለዝሙት የሚያነቃ ልብ የሚወጋ ፍላፃ ነዉ ። # ድንፍታ ፦ የጀግኖች ባልትና የሰነፎች ጫጫታ ነዉ ። # በክፉ # ማንሾካሾክ ፦ ቀስ ብለዉ ሰዉን የሚገድልበት የአሳባቂዎች ጩሀት ነዉ ። # ነገር ፦ ማመላለስ የሚወዱትን የሚለያዩበት የዲያቢሎስ የግብር ልጆች መሳሪያ ነዉ ። # የአደራ # ገንዘብ # መብላት ፦ሳይጥሩ ሳይግሩ የሰዉ ላብ ሲበሉ የሚኖሩበት የሰነፍ ሰዎች መሳሪያቸዉ ነዉ ። # ሰዉን # ማስነወር ፦ሰዉ የወደደዉን የተከበረዉን ስም ለማጥፍት የሚቀቡት የምቀኞች ቀለም ነዉ ። # መሳለቅ ፦ የማይታይ የቀናተኞች ጦር ነዉ ። # ተስፍ ፦ ከማጣት ወደ ማግኘት ለመሸጋገር የሚያገለግል ድልድይ ነዉ ። # ጠብ ፦ እሳት ለማንደድ የሚጭር የነገረኞች የኪስ ክብሪት ነዉ ። # ችኮላ ፦ የትግስት ጠላት የፀፀት አባት ነዉ ልጁም ወይኔ ይባላል ። # ሙከራ ፦ የስራ ጥልቀትን መለኪያና መመጠኛ ነዉ ።
Показати все...
ሉላዊነት የጋራችን አለም የጋራችን ሰማይ የብቻችን ህመም የብቻችን ስቃይ ከመፅሀፍ የተወሰደ
Показати все...
Repost from Yoni Arts
👍 ከፈላስፋዎች ጉያለሚጠቅም ነገር ጊዜን ማባከን ስኬት ነው! 👉 አንድ ሠው መጥቶ ሶቅራጦስን ‹‹እገሌ ስለተባለው ወዳጅህ የሰማሁት ደስ አይልም›› አለው። ሶቅራጦስ ግን ዝም አለ፡፡ ሰውየውም እንደገና ‹‹ይገርማል ከእርሱ አይጠበቅም፤ በጣም ገርሞኛል›› አለው፡፡ ሶቅራጦስም እንደማይለቀው ስለተረዳ ‹‹ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የፈለግከውን ልሰማው የምችለው ሶስት ጥያቄዎች አሉኝ፤ እነርሱን ስትመልስልኝ ብቻ ነው›› አለው፡፡ ሰውየውም ተስማማ 👉 የመጀመሪያው ጥያቄዬ የእውነት ጥያቄ ነው፡፡ ስለወዳጄ የሰማኸው መቶ በመቶ እውነት ነው ወይ? ሰውየውም መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን አልችልም አለው፡፡ ሶቅራጦስም ‹‹ልትነግረኝ የፈለግከው እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው፡፡ ሁለተኛው ጥያቄዬ የምትነግረኝ መልካም ነገር ነው ወይ?›› አለው። ሰውየውም ‹‹እርሱማ መልካም አይደለም›› አለው፡፡ ሶቅራጦስም ‹‹አንደኛ እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ ሁለተኛ መልካም ያልሆነ ነገር ልትነግረኝ ፈልገሃል፡፡ ሶስተኛ ጥያቄ አለኝ?›› አለው፡፡ ሰውየውም ‹‹እሺ›› አለ 👉 ሶቅራጦስም ለእኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለው ወይ? አለው። ሰውየውም ‹‹የለም›› ብሎ መለሰ፡፡ ሶቅራጦስም በመጨረሻ ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ መልካም ያልሆነ፤ ለእኔ የማይጠቅም ነገር አልሰማም›› አለው ይባላል፡፡ 👌 ወዳጆቼ እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፣ መልካም ያልሆነ እና በሕይወታችን ላይ ጉልህ ሚና የሌለው ነገር ላይ ጊዜን ማጥፋት ትልቅ ብክነት ነው፡፡ 👌 አንዳንድ ሰዎች በማይመለከታቸው ነገር እድሜአቸውን ይገፋሉ በዚህም መልሰው ማግኘት የማይችሉትን ውዱን ጊዜአቸውን መና ሲያደርጉት ማየት አሳዛኝ ነው። ☑️ ታላቁ ፈላስፋ ሶቅራጦስም ይህን እውነት በሚደንቅ መልሱ አሳይቶናል ስለሆነም በጎ ዓላማ በሌለው፣ ሐቅነቱ ባልተረጋገጠና አንዳች ፋይዳ በሌለው እንቶፈንቶ ሳንባዝን ለሚጠቅም ነገር፣ ለሠናይ ተግባር እና ለእውነት እንትጋ፡፡ 👍 ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ @yemaledabisrat @yemaledabisrat @yemaledabisrat
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ያኔ_እኔን_አያርገኝ አንቺ ፥ ረሳውሽ ስል ማስታውስሽ፣ ብናፍቅሽ ናይልኝ ብል ማልመልስሽ። አንቺ ፥ ደስታ ሳቄን ቀምተሽኝ ፣ ከንቱ ፍጡር አደረግሽኝ፣ #አዎ ስናፍቅሽ መቼ መጣሽ! ከሀሳቤስ መቼ ወጣሽ? #ብቻ ናፍቄሽ ሳትመጪ ፥ ጠብቄሽ ስትቀሪ፣ ሁኛለሁ አለሜ ፥ ተስፋ ቢስ በራሪ፣ #አየሽ በመሄድሽ ብስራት ፥ ሲናወጥ መንፈሴ፣ ሲንቀጠቀጥልሽ ፥ አካልና ነብሴ፣ #አንቺ_ግን? ህመሜም አልገባሽ፣ ጭራሽ በኔ አነባሽ። #ብቻ ጭካኔሽ አይሎ ፥ እርቀሽ ብትሄጂ፣ የኔን ገላ ረስተሽ ፥ ከሌላ ብትለምጂ፣ ያኔ እኔን አያርገኝ አፈር ያርገኝ እንጂ። #ገጣሚ ሮቤል አለማየው #ዝምተኛው_ሲርሎስ 2014 ዓ.ም በደሌ
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.