የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
Відкрити в Telegram
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Показати більше2 610
Підписники
+524 години
+127 днів
+3030 день
Архів дописів
አባታችን ተክለ ሃይማኖት ‹‹…ከዚህ በኋላ መልአኩ ወደ ሰማይ አውጥቶ ከመጋረጃው ውስጥ አስገብቶ ከሥላሴ ዙፋን ፊት አቆመኝና ሰገድኩለት፡፡ ከዚያ አስቀድሞ በማላውቀው በሌላ ምስጋና አመሰገንኩት፡፡ ‛‛ተክለ ሃይማኖት ክፍልህ ከ24ቱ ካህናቶቼ ጋር ይሁን’’ የሚል ቃል ከዙፋኑ ውስጥ ወጣ፡፡
የወርቅ ጽና አምጥተው ሰጡኝና ከእነርሱ ጋር አንድነት አጠንሁ፡፡ ምስጋናዬ ከምስጋናቸው ጋር ልብሴም እንደልብሳቸው ሆነ፡፡ ፈጣሪዬንም በሦስትነቱ ተገልጦ አየሁት፡፡
የጻድቁ የአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ጸሎትና በረከት በሁላችንም ላይ ይደር!!
ገድለ ተክለሃይማኖት
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ወርሐዊ የባለትዳር አባላት ጉባኤ
''መንፈሳዊና ሕይወትና የጠባይ ለውጥ''
እሑድ ኅዳር 28/2018 ዓ.ም
ከ5:00- 7:00
ጉባኤው በወር አንድ ቀን ብቻ የሚከናወን በመሆኑ በእለቱ ተገኝተው ቃለ እግዚአብሔርን ይመገቡ።
የባለትዳር ጉባኤ
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
+2
ዜና እረፍት!
ዐራት ዐይና ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ የትርጓሜ መጻሕፍት፣ የአቡሻኽር፣ የፍትሐ ነገሥት እና የቅኔ መምህር፤ የክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም አበምኔት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተሰምቷል ።
በየኔታ ይባቤ በላይ እረፍተ ሥጋ የተሰማንን ኃዘን እየገለጽን ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው፣ ለገዳሙ መነኮሳትና መነኮሳይት መጽናናትን እንመኛለን።
© የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብራችን በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ ።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብራችን በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ የደብራችን ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን አዕምሮ ምስጋናው እና ሌሎችም የቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት፣ የሰንበት ት/ት ቤት አገልጋዮችና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብራችን በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ ።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብራችን በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ የደብራችን ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን አዕምሮ ምስጋናው እና ሌሎችም የቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት፣ የሰንበት ት/ት ቤት አገልጋዮችና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ቅድስት ጽዮን ድንግል ማርያም
ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው።
"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።
እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በኋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር፣ ሞገስ፣ አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል። (ዘጸ. 31፥18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች።
ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች። እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው። ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን።
ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን። ግን አንጨነቅም። ምክንያቱም የመጣችውም የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም። በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም። ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም።
ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን፣ ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች። "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው። "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው።
"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው። ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል። ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው።
ኅዳር ሃያ አንድ የምናስብበት ምክንያት
✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።
✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።
✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።
✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤
✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤
✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤
✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤
✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤
✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤
✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤
በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።
ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን!!
ናርዶስ ዲጂታል መጽሔት ልዩ እትም
ኅዳር 2018 ዓ.ም
እስመ ሐረያ እግዚአብሔር ለጽዮን
ወአብደራ ከመትኩኖ ማህደሮ
ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም
እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና
ማደርያውም ትሆነው ዘንድ
ወዷታልና እንዲህም ብሎ
ይህች የዘለዓለም ማረፊያዬ ናት
መዝ.131÷13
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የኅዳር ጽዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል ታቦታተ ሕጉ ወጥተው በታላቅ ድምቀት ይከበራል!!
እስመ ሐረያ እግዚአብሔር ለጽዮን
ወአብደራ ከመትኩኖ ማህደሮ
ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም
እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና
ማደርያውም ትሆነው ዘንድ
ወዷታልና እንዲህም ብሎ
ይህች የዘለዓለም ማረፊያዬ ናት
መዝ.131÷13
Вже доступно! Дослідження Telegram за 2025 — головні інсайти року 
