የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
Відкрити в Telegram
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Показати більше2 794
Підписники
Немає даних24 години
+17 днів
+2030 днів
Архів дописів
በደብራችን እየተከናወነ ያለው የነነዌ የሶስት ቀን ጉባኤ ተጠናቀቀ ጉባኤው ሶስቱንም ቀን በጸሎተ ምሕላ የተጀመረ ሲሆን ትምህርተ ወንጌል በመጋቤ ሃይማኖት ኢዮብ ይመኑ የተሰጠ ሲሆን ያሬዳዊ ዝማሬ በዘማሪት ማርታ ኃይለሥላሴ እና በመላከ ሰላም ቀሲስ እስክንድር የቀበረ ሲሆን ቅኔ በደብራችን የቅኔ መምህር የኔታ ኮከበ ጽባሕ ቀርቦ
የሶስተኛና የመጨረሻ ቀን ጉባኤ በደብራችን ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት አዕምሮ ምስጋናቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ በጸሎት ተጠናቅቋል።
ይህ ጉባኤ እንደሚታወቀው በየዓመቱ የጾመ ነነዌን ሶስት ቀናት ምክንያት በማድረግ በየዓመቱ ከረጅም ዓመታት በፊት ጀምሮ የሚከናወን ሲሆን እንደ ቅዱስ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በሰላም ቢያደርሰን በቀጣዩ ዓመት ይቀጥላል አምላካችን እድሜና ጤና ሰጥቶ ያድርሰን ሐገራችንን ይጠብቅልን!!
+9
በደብራችን እየተከናወነ ያለው የነነዌ የሶስት ቀን ጉባኤ ሁለተኛ ቀን በጸሎተ ምሕላ የተጀመረ ሲሆን ትምህርተ ወንጌል በ አባ ቃለጽድቅ (ዶ/ር) የተሰጠ ሲሆን ያሬዳዊ ዝማሬ በማኅበረ ሰላም ማኅበር እና በዲ/ን ሚኪያስ ቀርቦ የሁለተኛ ቀን ጉባኤ ተጠናቅቋል
የሶስተኛ ቀን ማጠቃለያ ጉባኤ ይቀጥላል
+9
በደብራችን በዛሬው እለት የተጀመረው የነነዌ የሶስት ቀን ጉባኤ በጸሎተ ምሕላ የተጀመረ ሲሆን ትምህርተ ወንጌል በቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል(ፕሮፌሰር) የተሰጠ ሲሆን ያሬዳዊ ዝማሬ በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ጎልማሶች ማኅበር እና በበኩረ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደ ቂርቆስ ቀርቦ የመጀመሪያ ቀን ጉባኤ ተጠናቅቋል
ነገ ሁለተኛ ቀን ጉባኤ ይቀጥላል
ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡
በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው መሆኑን እንዲነግራቸውና ቸርነትና ምሕረት ወደማያልቅበት ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ንስሐ እንዲገቡ እንዲነግራቸው ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው።
ነቢዩ ዮናስ ግን ‹‹አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎችም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ
ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይሆንም›› አሉ፡፡ ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡
ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ከላይ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል ።
የጾሙ በረከት በሁላችንም ይደር!!
+6
የተልዕኮ ተማሪዎች ጉባኤ ተከናወነ የዕለቱ ትምህርት በመ/ር አቤል ካሣሁን የተሰጠ ሲሆን የበገና ዝማሬ ቀርቦ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።
+1
ጥር ሃያ አራት በዚህች ዕለት ''ሐዲስ ሐዋርያ'' ብሎ የሾማቸው የኢትዮጵያ ብርሃኗ የሆኑ የደብረ ሊባኖሱ ጻድቅ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በጸሎት ብዛት አንዲቱ የእግራቸው አገዳ የተሰበረበትን (ስብረተ አፅማቸው) መታሰቢያ ይከበራል።
ጻድቁ አባታችን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ሃይማኖት ስለመለሱት በዚህም የተነሣ ብርሃን ዘኢትዮጵያ ተብለዋል፡፡
አባ ተክለሃይማኖት ከበዓታቸው ሳይወጡ በጸሎት ተጠምደው ሌሊትና ቀን ይቆሙ ነበር። ከተጋድሎ የተነሳ ቁመትንም ካበዙ ወዲህ አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰበረች ደቀ መዛሙርቱ አንሥተው አክብረው በሰበን ጠቅልለው ከመንበሩ እግር በታች ቀበሯት። ከዚህም ባንዲት እግራቸው ሰባት ዓመትን ቆሙ። በዚህ ቀንም ቤተክርስቲያን በጸሎት ብዛት አንዲቱ የእግራቸው አገዳ የተሰበረበትን (ለስብረተ አፅማቸው) መታሰቢያ ታከብራለች።
የጻድቁ አባታችን በረከታቸው ይደርብን!!