Tech FaF
Відкрити в Telegram
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ ⚡️We Do All Kinds of Account and Website SPY TASK⚡️ 🚪We Offer Other Kinds of BlackHat Hacking Such As🚪 ⚙️CC and 101+ pins dumps sale ⚙️All Country Proxy Sale ⚙️Telegram Account Hacking ⚙️ Facebook Account with with Ads power sale ⚙️Tr
Показати більше4 882
Підписники
Немає даних24 години
+9257 днів
+1 65430 днів
Архів дописів
4 882
UFO (Unidentified flying object)
ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት)
ክፍል 3
በ 1968 በዩንቨርስቲ ኦፍ ኮሎራዶ የተቋቋመ የጥናት ቡድን ስለ UFO በቀረቡ ሁኔታዎች ላይ ጥናት አካሂዶ ነበር ። ከፊሉ ዘገባዎች ማስረጃ ሊቀርብላቸው ቢችልም ጥቂቶቹ ደግሞ ምንም አይነት ማብራሪያ ሊቀርብላቸው አልቻለም። የ UFO ጥናትና ምርምር ብዙ አወዛጋቢ ሁኔታዎች እየገጠሙት ቢሄድም UFO ግን መታየትቸውን ቀጠሉ።
በተለይ በፍሎሪዳና በባሃማስ መካከል ባለው ክልል የሚታዩት UFO ቁጥር ከሌሎች አካባቢዎች ሁሉ የበዛ ነው። በውሀ ውስጥና በ አየር ላይ ከመታየታቸውም በላይ ከአየር ወደ ባህር ከባህር ወደ አየር ሲመላለሱ ብዙ ጊዜ ተስተውለዋል። አየን ካሉት ሰዎች አብዛኞቹ እምነት የሚጣልባቸው ነበሩ። በእነኚሁ አካባቢ የUFO በብዛት መታየት ቤርሙዳ ትራያንግል ክልል ውስጥ ከሚከሰቱ የመሰወር ሁኔታዎች ጋር የተያያዙ ናቸው የሚል አስተሳሰብ አሳድሯል።እንዲያውም UFO ለዘመናት አውሮፕላኖችንና መርከቦችን ሲጠልፉ ኖረዋል የሚል አስተሳሰብም በብዙዎች ዘንድ አለ።
.
.
.
.
💥ይቀጥላል💥
🔰SHARE🔰
4 882
UFO (Unidentified flying object)
ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት)
ክፍል 3
በ 1968 በዩንቨርስቲ ኦፍ ኮሎራዶ የተቋቋመ የጥናት ቡድን ስለ UFO በቀረቡ ሁኔታዎች ላይ ጥናት አካሂዶ ነበር ። ከፊሉ ዘገባዎች ማስረጃ ሊቀርብላቸው ቢችልም ጥቂቶቹ ደግሞ ምንም አይነት ማብራሪያ ሊቀርብላቸው አልቻለም። የ UFO ጥናትና ምርምር ብዙ አወዛጋቢ ሁኔታዎች እየገጠሙት ቢሄድም UFO ግን መታየትቸውን ቀጠሉ።
በተለይ በፍሎሪዳና በባሃማስ መካከል ባለው ክልል የሚታዩት UFO ቁጥር ከሌሎች አካባቢዎች ሁሉ የበዛ ነው። በውሀ ውስጥና በ አየር ላይ ከመታየታቸውም በላይ ከአየር ወደ ባህር ከባህር ወደ አየር ሲመላለሱ ብዙ ጊዜ ተስተውለዋል። አየን ካሉት ሰዎች አብዛኞቹ እምነት የሚጣልባቸው ነበሩ። በእነኚሁ አካባቢ የUFO በብዛት መታየት ቤርሙዳ ትራያንግል ክልል ውስጥ ከሚከሰቱ የመሰወር ሁኔታዎች ጋር የተያያዙ ናቸው የሚል አስተሳሰብ አሳድሯል።እንዲያውም UFO ለዘመናት አውሮፕላኖችንና መርከቦችን ሲጠልፉ ኖረዋል የሚል አስተሳሰብም በብዙዎች ዘንድ አለ።
.
.
.
.
💥ይቀጥላል💥
🔰SHARE🔰
4 882
🔶UFO (Unidentified flying object)
ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት)
ክፍል 11
💥እነዚህ ላይ መታወስ ያለበት በሰሜን ምስራቅ አሜሪካ በ 1965 እና በማያሚ በ 1973 የኤሌክትሪክ ሃይል መቋረጥ በደረሰበት ወቅት UFO በአካባቢዎቹ መታየታቸው ተመዝግቧል። በሰሜን ምስራቁ የኤሌክትሪክ ሃይል መቋረጥ ጊዜ 100 ጫማ ክብ ስፋት ያለው ቀይ አብረቅራቂ መሰል ነገር ሲራክስ በተባለው ቦታ ታይቷል። ካዩዋቸውም ሰዎች መካከል በወቅቱ የፌዴራል የበረራ ድርጅቱ ም/ኮሚሽነር የነበሩት ሰው ይገኙበታል። ሌሎችም UFO በኒው ዮርክ እና ፊሌዴልፊያ ከመታየታቸውም በላይ በተጨማሪ በማሳቹሴት ፣ ሮድ እይላንድና ኒው ዮርክ ስቴት በበርካታ ስፍራዎች ታይተዋል። አንድ በጣም አስገራሚ ክስተት ደግሞ UFO በታዩባቸው አካባቢዎች በምድር ላይ የነበሩ መኪናዎች ሞተራቸው መበላሸቱ ነው። ይህ ሁኔታ በቤርሙዳ ትራያንግል ክልል በጠፉ አውሮፕላኖችና መርከቦች ላይ ከተከሰተው የሃይል መሟጠጥ ጋር ተመሳሳይ ነው።
በ 1965 የደረሰው ታላቅ የኤሌክትሪክ መቋረጥ የተነሳበት ቦታ በስተኋላ ቢደረስበትም ምክኒያቱ ግን ሊታወቅ አልቻለም። በተደረገው ይፋ ምርመራ የተደረሰበትም ማጠቃለያ እውነትነት ያለው ነው። እንዲህ ይል ነበር።«በሰሜን ምስራቁ የኤለክትሪክ ሃይል ማመንጫ ላይ የተፈጠረው የሃይል መቋረጥ በዘመናዊ ስልጣኔ ታሪክ ታላላቅ ከሆኑ እንቆቅልሾች አንዱን ፈጥሯል።
.
.
.
.
🔰ይቀጥላል🔰
4 882
🔶UFO (Unidentified flying object)
ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት)
ክፍል 9
💥አንድ ጊዜ ማለትም ጥር 10 ቀን 1964 ፓላሪስ የተባለ ሚሳይል የትኮሳ ሙከራ በሚካሄድበት ወቅት አንድ UFO በሚሳይል የጉዞ መስመር ውስጥ ጥልቅ ይላል። ለአስራ አራት ደቂቃ ያህል ምድር ላይ ያለው ራዳር የበራሪ አካሉን ያልተስተካከለ አካሄድ ከተከታተለ በኋላ ወደ ኢላማ ሚሳይሉ ተመለሰ። በወቅቱ በስፍራው የነበሩት ስለሁኔታው ብዙ ቢናገሩም በመገናኛ ዘዴዎች ግን ለህዝብ አልተገለጠም። ጄሰፕ UFO የእኛን የአየር እንቅስቃሴ ማወቅ ይፈልጋሉ ያለው አባባል በቅርብ አመታት በተፈጠሩ ክስተቶች ተጠናክረዋል።
UFO በጠፈር ጉዞ ወቅትም ታይተዋል። በተለይ በጄምኒ 4 እና በጄምኒ 7 የጠፈር መንኮራኩሮች ጉዞ ወቅት ይህ ሁኔታ በደንብ ተስተውሏል በጄምኒ 4 ውስጥ የነበሩ ጠፈርተኞች ከመንኮራኩራቸው ጎን አብሮ ይጓዝ የነበረ አስፈሪ ነገር አይተዋል። በወቅቱም የማምለጥ ሙከራ ለማድረግ አስበው ነበር። ሌላ አስፈሪ ነገር እንዲሁ ጄምኒ 7 መንኮራኩርን ሲከተል መታየቱ በዘገባዎች ሰፍረዋል። የአፖሎ 12 መንኮራኩርም ይኸው ሁኔታ ደርሶበት ነበር። ይህችው መንኮራኩር በ 132‚000 ማይል ርቀት ላይ በነበረችበት ጊዜ ከፊት አንድ ከኋላ አንድ UFO ያጅቧታል። በመንኮራኩሯ ውስጥ ከነበሩት ጠፈርተኞች መሃል ጎርዶን የተባለው «በጣም የሚያበሩና ለኛም በብርሃን ብልጭታ ምልክት የሚሰጡ ይመስሉ ነበር። » ሲል በጊዜው የነበረውን ሁኔታ ጠቅሶታል። ከሂዩስተን የጠፈር መቆጣጠሪያ ጣቢያ ጋር ባደረገው የሬዲዮ ግንኙነትም «እንደሚታየው ከሆነ የማይተናኮሉና ሰላማዊ ይመስላሉ» ብሏል።
.
.
.
.
🔰ይቀጥላል🔰
4 882
🔶(Unidentified flying object)
ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት)
ክፍል 8
💥እሱም ፍሬያ ፣ ሜሪ ሴሌስቴ እና ኤለን ኦስቲንን ጨምሮ በቤርሙዳ ትሪያንግል የደረሱ የመሰወር ክስተቶች በሙሉ ከ UFO እንቅስቃሴ ጋር የተያያዙ ናቸው ባይ ነው። ከቤርሙዳ ትራያንግል ውጪ ርቆ በመሄድ 'ሲ በርድ' የተባለች ትልቅ ጀልባ ላይ ያሉ ሰዎች ስለ ተሰወሩበት ሁኔታም ይጠቅሳል። በ 1850 ሮድ አይላንድ ከሚገኘው ኒውፖርት ወደብ አጠገብ ለአንድ አሣ አጥማጅ ጀልባ ምልክት ካሳዩ በኋላ 'ሲ በርድ' ላይ የነበሩት ሰዎች በሙሉ ተሰወሩ። በደንብ ተዘጋጅቶ የተደረገ እና ያልተነካ ምግብ ጠረቤዛው ላይ ነበር። 'ሲ በርድ' ባዶዋን ወደ ወደቧ ጉዞ ቀጥላ በባህር ዳርቻው ላይ ከፍ ብላ ቆመች። ልክ በግዙፍ እጆች የተነሳች ይመስላል ከዚያም አሸዋ ውስጥ በጥብቅ ከተወሸቀች በኋላ ማታውኑ ተሰወረች። በዛኑ እለት ማታም ማዕበል እንደነበር ተዘግቧል ጄሰፕ እነኚህን ሁኔታዎች በሚገባ ካየ በኋላ ክስተቶችን ማስረዳት የሚቻለው ከወደ ላይ ከሚመጣ ታላቅና ወሳኝ ሃይልና ድንገተኛ እንቅስቃሴ ያለው አንድ ነገር አለ ከሚል አኳያ ነው ብሏል። አከታትሎም በርካታ ጉዳዮችን ካነሳ በኋላ «ሁሉም የሚያመለክተው ከፍተኛ ወደሆነ የአእምሮ ብስለት ነው» ባይ ነው።
ጀሰፕ የኛ የአየር ዘመን መዳበር በጠፈር ለሚኖሩ ጎረቤቶቻችን ትልቅ የማወቅ ፍላጎት ያሳድርባቸዋል ባይ ነው። ይህ ሁይኔታም በተለይ በቤርሙዳ ትራያንግል አካባቢ በፍሎሪዳ ጠረፍና በኬፕ ኬኔዲ አካባቢ UFO በብዛት ለመታየታቸው ምክኒያት ነው ይላል።
.
.
.
🔰ይቀጥላል🔰
4 882
🔶UFO (Unidentified flying object)
ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት)
ክፍል 7
💥በኋላም ተንሳፋፊ ፊኛዎች በተፈለሰፉ ጊዜ እነዚህ በራሪ አካላት ፈረንሳይ ውስጥ እብረቅራቂ የእሳት ፊኛዎች ተብለው ተገልጸዋል። በ አስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ቨርሞንት ውስጥ እነዚህን ነገሮች ያዩዋቸው ሰዎች የዘንግ ቅርፅ ያላቸው የአየር ላይ ተሽከርካሪዎች ብለው ገልጽዋቸዋል።
በሰኔ 30 ቀን 1908 በሳይቤሪያ ውስጥ በባይካል ሃይቅ አጠገብ በዩኒሴይ ወንዝ አካባቢ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ፍንዳታ ደርሶ ነበር። በዚህ ጊዜ ሰው ባይጎዳም በርካታ እንስሳት አልቀዋል። ብዙዎቹ ይህ ፍንዳታ የተፈጠረው ተወርዋሪ ኮከብ ምድር ላይ ሲወድቅ ነው ብለው ነበር። ሆኖም ፍራንክ ኤድዋርድስ የተባለና ለረጅም ጊዜ ማብራሪያ ያልተገኘላቸውን ክስተቶች ያጠና ሰው ግን አንድ የሰማይ በራሪ አካል በሚፈነዳበት ጊዜ የተፈጠረ አቶሚክ ፍንዳታ ነው ይላል። ለዚህም አባባሉ አሌክሳንደር ካትዜኔቭ የተባለ ሩሲያዊ የሳይንስ ፀሃፊ ይጠቅሳል። እርሱ እንደሚለውም የደረሰው ጥፋት በሰው ከሚደረጉ የአቶሚክ ፍንዳታዎች ጋር ተመሳሳይ ነው። ሆኖም ምንም እንኳን መሬት ውስጥ ተቀብረው ሊሆን ቢችልም አንዳችም ስብርባሪ አልተገኘም ኤድዋርድስ ሲያጠቃልል «በ 1908 በዩኔሴ ወንዝ አካባቢ በደረሰው ጥፋት አንድ ከሌላ ዓለም የመጣ እንግዳ አጥተናል» ብሏል።
ኤም. ኬ.ጄሰፕ ስለ UFO እጅግ ሳይንሳዊ የሆኑና የረቀቁ ፅሁፎችን ያቀረበ እውቅ ተመራማሪ ነው። በተጨማሪም ስለክዋክብት ከፍተኛ እውቀት ያለው ከመሆኑም በላይ ጨረቃን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይም ሊቅ ነው። ጄሰፕ 'The Case For UFOs' በሚባለው መጽሃፉ ያሰፈራቸው ነጥቦች አሉ።
.
.
.
.
🔰ይቀጥላል🔰
4 882
💥UFO (Unidentified flying object)
ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት)
ክፍል 6
🚀ንጉሰም ሰላምን ለመመለስ ጥሩ መአዛ ያለው እጣን እንዲጨስ አድርገው በሂይወት ቤት የታሪክ ማህደር ውስጥም ሁኔታው ተጽፎ እንዲቀመጥ አዘዙ . . . ለዘለዓለም ሲታወስ እንዲኖር።
ባለፉት ብዙ ምእተ ዓመታት UFO አየን የሚሉት ሰዎች የሚያቀርቧቸው ስእላዊ ገለጻዎች በጣም ይራራቁ ነበር። እነዚሁ ባእድ አካላት በተለያዩ እንስሳትም የተመሰሉበት ጊዜ አለ።
በውጊያ ስልት ከፍተኛ ልምድ የነበራቸው የታላቁ እስክንድር ወታደሮች ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 329 ዓመተ ዓለም የግሪክ ጦር የጃክሳርቱስ ወንዝን አልፎ ወደ ህንድ ሲገባ መንገዳቸውን ያቋረጠውን የUFO ስብስብ "ትላልቅ ብርማ ተብረቅራቂ ጋሻዎች" ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ 384--322 ዓመተ ዓለም የኖረው አርስቶትል የግሪክ ስፖርተኞች የሚወረውሩትን ዲስክ ያውቅ ስለነበር እነዚህን ባእድ አካላት "የሰማይ ዲስኮች" ብሏቸዋል። ሮማውያን ልክ እንደታላቁ እስክንድር እንደጋሻዎች ወይም የእሳት ጦሮች ወይም የመርከቦች ስባስብ አድርገው ያዩአቸው ነበር። ፕሊኒ የተባለው ጸሃፊ 'ናቹራል ሂስትሪ' በተባለው መጽሃፉ ሁለተኛው ቅጽ ላይ እንደሚከተለው ጽፏል። «በሉሲየስ ቫሌሪየስ እና በጊየስ ቫሌሪየስ እማኝነት የእሳት ፍንጥቅጣቂ በሁሉም አቅጣጫ ይረጭ የነበረ የሚነድ ጋሻ በፀሃይ መጥለቂያ ጊዜ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ በሰማዩ ላይ እየትወረወረ ሄደ»።
በአዳዲስ ነገሮች መፈልሰፊያና በዓለማት ፍለጋ ዘመን እነዚህን በራሪ አካላት ያዩ ሰዎች ከመርከቦች ጋር አመሳስለዋቸው ነበር።
.
.
.
.
🔰ይቀጥላል🔰
4 882
💥UFO (Unidentified flying object)
ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት)
ክፍል 5
🚀 አውሮፕላን ከመፈልሰፉ በፊት ታዩ ስለተባሉ UFO የቀረቡት ዘገባዎች ምናልባት መሬት ለረጅም ጊዘ በሌሎች አለማት ስልጣኔዎች ክትትል ይደረግባት ነበር የሚል አመለካከት ፈጥሯል። ሆኖም የሰው ልጅ በታሪክ ውስጥ ሁሉ ለምልክቶች ወደ ሰማይ ይመለከት ስለነበረ ከትክክለኛ UFO እና እሳት መሰል ምልክቶች መሃል ያለውን ልዩነት ማወቅ አስቸጋሪ ነው። እነዚህ ምልክቶች እንደማስጠንቀቂያዎች ማበረታቻዎችና ትንቢቶች ሆነው ይቆጠሩ ነበር። በቫቲካን የግብጽ ሚዩዚየም ውስጥ በአስራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ስለ ነበረ ቱትሞስ ሶስተኛ የተባለ ንጉስ ታሪክ ላይ የተጻፈ አንድ ክፍል ስለ UFO ሳይሆን አይቀርም ተብሎ ይገመታል። ከዛ ቡሃላ ባሉ ምዕተ ዓመታት ከቀረቡ የእይታ ዘገባዎች ጋር ፍጹም በተለየ ሁኔታ እዚሁ እተጠቀሰው ጽሁፍ ላይ የሚከተለው ሰፍሯል።
"በ 22 ዓ.ም በክረምት ሶስተኛ ወር በቀኑ ስድስተኛ ሰአት የህይወት ቤት ጽሁፎች . . . የእሳት ቀለበት ከሰማይ ሲመጣ ተመለከቱ . . . መጠኑ አንድ ሮድ ርዝመትና አንድ ሮድ ስፋት ነበረው . . . እነሱም በሆዳቸው ተኙ . . . ከዚያም ያዩትን ለመናገር ወደ ንጉሱ ሄዱ ። ንጉሱ በዛ ጊዜ ስለተፈጠረው ሁኔታ በጣም እያሰበ ነበር . . . እነዚህ ነገሮች በፊት ከነበሩት ይበልጥ በሰማይ ውስጥ በጣም እየበረከቱ ሄዱ ከጸሃይም ብርሃን በበለጠ ሃይል እያብረቀረቁ እስከ ሰማይ ሰማያት አራቱ ድጋፎች ድረስ ተንሰራፉ።
የንጉሱ ጦር ሃይሎች በትኩረት ተመለከቱ ንጉሱም መሃላቸው ነበሩ። በምሽቱ ከእራት በኋላ ነው የእሳት ቀለበቶቹ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወደ ሰማይ በጣም የወጡት።
.
.
.
.
🔰ይቀጥላል🔰
4 882
🔶UFO (Unidentified flying object)
ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት)
ክፍል 10
💥ምንም እንኳን የሂዩስተን የጠፈር መቆጣጠሪያ ጣቢያና የአሜሪካ ጠፈር ድርጅት በወቅቱ ማረጋገጫ ያልሰጡ ቢሆንም እነዚህ ብርሃን ለበስ ነገሮች አውሮፓ ውስጥ ባሉ በርካታ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎችም ታይተዋል። ከጊዜ በኋላ በዚቹ መንኮራኩር በረራ ወቅት ጠፈርተኞች 'ቬነስን የሚያክል' ብለው የገለጹት ሃይለኛ ብርሃን ከመንኮራኩሯና ከመሬት መሃል ለአስር ደቂቃ ያህል ከታየ በኋላ ተሰወረ።
በጠፈርተኞች ታዩ ስለተባሉት UFO ዶክተር ፍራንክሊን ሮች 'ኮንደን ሪፖርት' ብለው ባቀረቡት ዘገባ ላይ የራሳቸውን አመለካከት በዚህ አይነት አስፍረውታል። «ጠፈርተኞቹ ብርሃኖችን ያዩባቸው ሁኔታዎች ልክ የጎንና የኋላ መስታወት በሌላትና የፊት መስታወቷ በከፊል በተሸፈነ ትንሽ መኪና የፊት ወንበር የተቀመጡ አንድ ወይም ሁለት ሰዎች የሚታያቸው አይነት ነው» ብለውታል። ይህ የዶክተር ሮች አባባል የሚያመራው ጠፈርተኞች አየን የሚሉዋቸው እንግዳ ሁኔታዎች መጀመሪያውኑ አልተፈጠሩ ይሆናል ወደሚል መደምደሚያ ነው።
እነዚህ ባዕድ አካላት እኛ ላይ ማድረግ የሚችሉትን ነገር ስናስብ እስካሁን ድረስ እንቅስቃሴያቸው የረጋና መልካም መሆኑ እድለኞች ነን። ሆኖም ግን እነዚህ ባእድ አካላት ሁሉም የሚመጡት ከአንድ የተወሰነ አካባቢ ላይሆን ይችላል። በመሆኑም መሬትንና ነዋሪዎቿን እንዳለ ጠብቆ ለማቆየት ያላቸው አስተሳሰብም ተመሳሳይ ላይሆን ይችላል።
እነዚህ በራሪ አካላት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለደረሱብን የኤሌክትሪክ ሃይል መቋረጥ ክስተቶች ምክኒያት ሆነው ከሆነ በወቅቱ ምንም አይነት አደጋ ወይም አካላዊ ጉዳት አለመደረሱ የሚገርም ነው።
.
.
.
.
🔰ይቀጥላል🔰
4 882
🚀UFO (Unidentified flying object)
ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት)
ክፍል 4
የዚህ መላ ምት ዋነኛ ደጋፊዎች ከሆኑት አንዱ 'ሊምቦ ኦፍ ዘ ሎስት' የተባለው መጽሐፍ ደራሲ ጆን ስፔንሰር ነው። ስፔንሰር በአየር ሃይል ውስጥ ለአስር አመታት ያህል ያገለገለ በመሆኑ ስለአውሮፕላኖች በሚገባ ያውቅ ነበር በተጨማሪም ስለ UFO ክስተቶች የቅርብ ተከታታይ ነበር። ስፔንሰር ባሁን ዘመንም ሆነ ታሪክ በጽሁፍ መስፈር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ስለ UFO የቀረቡትን መረጃዎች ከመረመረ በኋላ እነኚህ ያልታውቁ በራሪ አካላት 2 አይነት ናቸው ይላል። አንደኛው ዓይነት 'በራሪ ሳህን' ሲሆን የዙሪት ስፋቱ 80 ጫማ ይሆናል። ሌላው ደግሞ በውስጡ በርካታ 'በራሪ ሳህኖችን' ወይም ምድራችን ላይ ያሉ ትላልቅ መርከቦችን የሚይዝና ግዙፍ የሆነ 'እናት መርከብ'(mother ship) አይነት ነው። ይህ ትልቅ በራሪ አካል አልፎ አልፎ ታየ ከሚባለው የሲጋራ ቅርጽ ያለው አካል ጋር ይመሳሰላል። ሆኖም እንደበራሪ ሳህኖቹ ብዙ ጊዜ አይታይም። ከኛ ክልል ውጪ በሆኑ አለማት ለሎች በጣም የተራቀቁ ስልጣኔዎች ሊኖሩ ይችላሉ ይላል ስፔንሰር።
.
.
.
.
🔰ይቀጥላል🔰
4 882
🖐 ሰላም ውድ የETHIO Termux ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ
ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ ሲፅፉ ምን ያክል ይፈጥናሉ?
🔥ለዛሬ ኮምፒውተር ላይ እንዴት እንደምንፅፍ የአማርኛ ፊደሎች ከላቲን Keyboard ጋር ያላቸውን የፊደል መስተጋብ እናያለን
⩩በነገራችን ላይ Computer ላይ ለመፃፍ (Power Geez,Keyman ወይንም win 10 Jun Updated ያስፈልገናል)
📌H>>ሀ
📌Hu>>ሁ
📌Hi>>ሂ
📌Ha>>ሃ
📌Hy>>ሄ
📌He>>ህ
📌Ho>>ሆ
👆በዚህ አፃፃፍ ስልት የሚፃፉ ፊደላት
📌ለ-L 📌ተ-T📌ቸ-C📌ነ-N
📌ከ-K📌አ-X📌መ-M 📌ረ-R
📌ሰ-S📌ቀ-Q 📌በ-B 📌ወ-W
📌ዘ-Z 📌ፈ-F 📌ፐ-P 📌ገ-G
📌ደ-D 📌ጀ-J 📌ቨ-V
️ሐ>>Shift+h
️ሑ>>Shift+hu
ሒ>>Shift+hi
ሓ>>Shift+ha
ሔ>>Shift+hy
ሕ>>Shift+he
️ሖ>>Shift+ho
👆በዚህ የአፃፃፍ ዘዴ ማለትም " shift+ፊደል " የሚፃፉ ፊደላት
️ሠ>>Shift+s ብሎ ይጀምራል
️ሰ>>Shift+S ብሎ ይጀምራል
️ኘ>>Shift+n ብሎ ይጀምራል
️ዐ>>Shift+x ብሎ ይጀምራል
️ዠ>>Shift+Z ብሎ ይጀምራል
️ጠ>>Shift+t ብሎ ይጀምራል
️ጨ>>Shift+c ብሎ ይጀምራል
ኸ>>capslock + Shift + h
ኹ>>capslock + Shift + hu
ኺ>>capslock + Shift + hi
ኻ>>Capslock + Shift + ha
ኼ>>Capslock + Shift + hy
ኽ>>Capslock + Shift + he
ኾ>>Capslock + Shift + ho
👆በዚህ የአፃፃፍ ዘዴ ማለትም " Capslock shift+ፊደል " የሚፃፉ ፊደላት
ኀ>>Capslock + Shift + H ብሎ ይጀምራል
ጸ>>Capslock + Shift + t ብሎ ይጀምራል
ፀ>>Capslock + Shift + T ብሎ ይጀምራል
📝ሌሎች ተጨማሪ ማለትም ዲቃላ ፊደላት የሚባሉት በKeyboard ሲፃፉ
ቋ>>Capslock+qwa
ቧ>>Capslock+bwa
ቷ>>Capslock+twa
ኟ>>Capslock +Shift+nwa
ቿ>>Capslock+cwa
ሟ>>Capslock+mwa
ቷ>>Capslock+twa
ጓ>>Capslock+gwa
ፏ>>Capslock+fwa
ሯ>>Capslock +rwa
ዷ>>Capslock+dwa
ቯ>>Capslock+vwa
ኋ>>Capslock+hwa
ዟ>>Capslock+zwa
ዧ>>Capslock+Shift+zwa
ኗ>>Capslock+nwa
ሏ>>Capslock+lwa
ኳ>>Capslock+kwa
ሷ>>Capslock+swa
ጇ>>Capslock+jwa
ጧ>>Capslock+twa
4 882
🔶UFO (Unidentified flying object)
ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት)
ክፍል 2
ዶክተር ጄ አለን ሀይኒክ የተባሉ የ UFO ተመራማሪ እንደሚሉት " UFO አየን የሚሉ የብዙ ሰዎች የአእምሮ ብስለት መሃከለኛ የጥቂቶች ደግሞ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው። እነዚህ አካላት በተለያየ የጥራት መጠን ፈቶ ተነስተዋል። ከአውሮፕላኖች ጎን ሲበሩ መታየታቸውም ተወስቷል። በርካታ የምርምር ዘገባዎች እነዚህን ነገሮች ከብዙ ሁነታዎች ጋር አያይዘዋቸዋል። ለምሳሌ ከጨረቃ ፣ ተወርዋሪ ኮከብ ፣ ፊኛዎች ፣ ብሩህ መብራቶች ፣ የሰሜን ብርሃኖች ፣ የእሳት ኳሶችና የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላሉ እሚል ግምት አለ።
ሌሎች በርካታ መላምቶች ቢኖሩም ሁሉንም የሚያስማማ መላ ምት አለ ማለት ግን አዳጋች ነው። በምድር ላይ ያሉ ሃያላን መንግስታት የሰሯቸው የሚስጥር መሳሪያዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚለው መላ ምት ግን በሁሉም ዘንድ ተቀባይነትን አጥቷል። (በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት እነዚህ ከተዋጊ አውሮፕላኖች አካባቢ ያንዣብቡ የነበሩ ብርሃናማ አካላት ተፋላሚ ወገኖች አንዱ የሌላውን ሚስጥር መሳሪያዎች ናቸው የሚል ጥርጣሬ ነበራቸው።) ግን እነኚህ UFO የሚስጥር መሳሪያዎች ቢሆኑ ኖሮ ሁኔታው በመገናኛ መሳሪያዎችና በመሳሰሉት መጋለጡ አይቀርም ነበር። የአሜሪካ አየር ሃይል "UFO ማብራሪያ ሊገግኝላቸው አይችልም። ስለዚህም የሉም" እሚል አቋም አለው። የሚገርመው ግን የአየር ሀይሉ የውስጥ ህግ አንዱ ክፍል አውሮፕላን አብራሪዎች UFO ቢገጥማቸው መውሰድ የሚገባቸውን እርምጃዎች ይጠቅሳል።
.
.
.
.
💥ይቀጥላል💥
🔰SHARE🔰
4 882
🔶UFO (Unidentified flying object)
ያበአ (ያልታወቁ በራሪ አካላት)
ክፍል 1
ከስሙ እንደምንመለከተው UFO (Unidentified flying object) በሰማይ ላይ ከተለምዶ የበረራ ህግ ውጪ ወይንም ከ Aerodynamic ህግ ውጪ የሚንቀሳቀሱ በራሪ አካላት ማለት ነው።
ለመጀመሪያ ጊዜ ሰላም በሰፈነበት ወቅት እ.ኤ.አ በ1947 ዓ.ም ታዩ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ UFO በ አሜሪካ ውስጥ ለብዙ ሺህ ዘገባዎችና ምርምሮች ምክንያት ሆነዋል። በተቀረው ዓለምም ስለ UFO መታየት ብዙ ሺህ ዘገባዎች ቀርበዋል። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በ አሜሪካና በሌሎች አገሮች UFO ማየታቸውን ተናግረዋል እነዚህ በራሪ አካላት የጠለቀ የሳይንስ እውቀት ባላቸው ሰዎችም በስዕላዊ መግለጫ መልክ ቀርበዋል።
ዶክተር ጄ አለን ሀይኒክ የተባሉ የUFO ተመራማሪ እንደሚሉት "
.
.
.
.
💥ይቀጥላል💥
🔰SHARE🔰
4 882
ውድና የተከበራቹ የቻናሌ ቤተሰቦች እንደሚታወቀ በዚህ ቻናል አዳዲስ የ ቴክኖሎጂ ትምህርቶች ይለቀቃል በመሆኑም አውን ደሞ የመወያያ ግሩብ እንድን ከፍት የብዙዎች ጥያቄ እየመጣነው ስለዚህ እናንተ
በዚህ ጉዳይ ምን ትላላቹ ከተመቻቹ👍ካልተመቻቹ👎 የምትለውን button በመጫን ሀሳብ እንድትሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን
4 882
#Laptop_ስንገዛ_core_i3_core_i5_core_i7_core_i9 ሲባል ምን ማለት ናቸው?
እነዚህ ነገሮች ስለ ላፕቶፑ ምን ይነግሩናል?
ኮምፒውተር ላይ ከሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች መካከል #CPU ወይም #processor የሚባለው የኮምፒውተሩ #አእምሮ ማለት ነው።
ይህ #CPU ወይም #processor የተለያዩ ክንዋኔዎችን(Tasks) ተራ በተራ ማከናወን የሚያስችል የኮምፒውተሩ ዋና ክፍል ነው።
በሌላ አነጋገር #CPU ወይም #processor ላፕቶፓችን በአንድ ግዜ ብዙ ስራዎችን በከፍተኛ ፍጥነት እንዲሰራ የሚያስችለው የላፕቶፑ ዋና ክፍል ነው።
ታስታውሱ እንደሆነ የመጀመሪያዎቹ ኮምፒውተሮች በአንድ ግዜ አንድ ሰራ ብቻ ነበር መስራት የሚችሉት።ለምሳሌ #Word ከፍታችሁ እየሰራችሁ ከሆነ ጎን ለጎን excel ወይም ሌላ ሶፍትዌር ከፍታችሁ መስራት አትችሉም ነበር።
እዚህ ጋር #Core የሚለው ቃል ይመጣል ።#Core ማት #አንድ ትንሽ አእምሮ ማለት ነው።#CPU ወይም #processor የኮምፒውተሩ ትልቅ አእምሮ ብትሉት፤ #Core ማለት ትልቁ አእምሮ ውስጥ ያለ #አንድ_ትንሽ አእምሮ ማለት ነው።
እንደምታውቁት የዘንድሮ ዘመናዊ #ላፕቶፖች በአንድ ግዜ ብዙ ስራዎች በከፍተኛ ፍጥነት ማከናወን ይችላሉ ።ለምሳሌ #Word ላይ እየሰራን ጎንለጎን #Excel ላይም ልንሰራ እንችላለን፤እንዲሁም ዩቲዩብ ከፍተን ልናይ እንችላለን።....ባጭሩ ብዙ ስራዎችን በአንድ ግዜ ማከናወን ይችላሉ ።
ታድያ #አንድ_core ሜለት #አንድ_አእምሮ ነው ካልን እና #አንድ_አእምሮ ደሞ በአንድ ግዜ አንድ ስራ ብቻ ከሆነ የሚያከናውነው፤የዘመኑ ላፕቶፖች በአንድ ግዜ ብዙ ስራዎችን ማከናወን እንዴት ቻሉ?
አሁን #corei3፣ #corei5 #corei7፣#corei9 የተባሉት ነገሮች ይመጣሉ።
🍭 Corei3 ማለት 3 #processors ወይም 3 አእምሮች ማለት ነው።
🍭 Corei5 ማለት 5 #processors ወይም 5 አእምሮች ማለት ነው።
🍭Corei7 ማለት 7 #processors ወይም 7 አእምሮች ማለት ነው።
🍭 Corei9 ማለት 9 #processors ወይም 9 አእምሮች ማለት ነው።
የ #core ቁጥር እያደገ ሲመጣ ላፕቶፑ በአንድ ግዜ የሚያከናውናቸው ሰራዎች ከፍ እያሉ ይሄዳል ማለት።ፍጥነቱን ሳይቀንስ።እንደውም በከፍተኛ ፍጥነት።
በሌላ አነጋገር የ4ኛ ክፍል ተማሪ አእምሮ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪ አእምሮ አንድ ነው? አይደለም።
#
