cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ልብ ወለድ❤ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮች❤

#በቻናሉ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪኮችን + እዉነተኛ የፍቅር ታሪኮችን + የፍቅር ደብዳቤዎችን + ግጥሞች + የፍቅር ጥቅሶችን + ሞቲቬሽናል ስፒቻች እና latest ፊልሞችን ያገኙበታል !!!

Більше
Ефіопія3 351Амхарська2 626Книги4 805
Рекламні дописи
5 104
Підписники
+2024 години
+717 днів
+41030 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

..ልጄ ፍፀም ልዩ ሰው ሆኖ ነበር የመጣው.ያው ታውቃለህ የእምሮ በሽተኛ ስለሆነ ሁኔታው ሁሉ ወሰድ መለስ ነበር የሚያደርገው...በዛን ቀን ግን እንደዛ አልነበረም….መልኩ ጥርት ያለ …አለባበሱ ጠርት ያለ…ንግግሩ ጥርት ያለ ነበር…፡፡ተደሰትኩ፤ተስፋ አደረኩ፤ጓጓው…በውስጤ ለአንድ ሺ ጊዜ ደጋግሜ ፈጣሪን አመሰገንኩ…ልጄ ሙሉ በሙሉ እየዳነልኝ ነው አልኩ….በደስታ እየተጫወተንና እየተቃለድን ቁርስ በላን..እማዬ ጸጉርሽ ተንጨብርሯል አለና ፀጉሬን ፈቶ ሲያበጥርልኝ ..መልሶ እየጎነጎነ ሲሰራልኝ …አቤት የተደሰትኩት መደሰት.ለካ እሱ እየተሰናናተኝ ነበር.ለመቸረrሻ ጊዘዜ ሰውነቴን እዳበሰኝ ነበር…የልጅ እጅ ሰውነትህ ላይ ሲያርፍ የሚሰማህን ስሜት ታውቀዋለህ…?በምንም ሊገለፅ የማይችል ልዩ ነው....እንደዚህ እንደዚህ እያልን አምስት ሰዓት ተኩል ሆነ፡፡ ‹‹.ከዛ በቃ እማዬ ክፍሌ ናፍቆኛል ››አለኝ ‹‹እሺ ግባ እኔም እስከዛ ቆንጆ ምሳ በራሴ እጅ ሰራልሀለው›› አልኩና እሱን ወደክፈሉ ሸኝቼ ወደኪችን ገባው፡፡ ከዛ ሚወደውን ምግብ ሁሉ አንድ ሳላስቀር ሰርቼ ጠረጳዛውን ሞላውና ወደክፍሉ ሄጄ አንኳኳው መልስ የለም…እስኪደክመኝ አንኳኳው ‹እንቅልፍ ወስዷት ይሆን?› የሚል ጥርጣሬ ገባኝ…‹‹እንደለመደው ወጥቶ በመሄድ ጠፈቶብኝ ይሆን? ›ስልም ተጠራጠረርኩ…ቁልፍ አስመጣውና ከፍተን ስንገባ ..ልጄ በሰማያዊ ሲባጎ እራሱን አንጠልጥሎ በድኑ በአየር ላይ እየተሸከረከረ ነበር፡፡ ማንኛዋም እናት በእኔ የደረሰው ሀዘን አይድረስባት…ያው አሁን እኔም በህይወት መኖሬን እርግጠኛ አይደለውም…ውስጤ ደክሟል..ተስፋዬ መክኗል…ለህይወት ያለኝ ጉጉተት ጠፍቷል..የምበላው ምግብ ጨው ይኑረው አይኑረው እራሱ መለየት ትቼያለው…የምጠጣው ውሀ ይሁን በረኪና ግድ አይሰጠኝም…የዩኒቨርሲተ አስተማሪ ልሁን የፅዳት ሰራተኛ እርግጠኛ አይደለውም…ፕሮፌሰር ብለው ሲጠሩኝ እራሱ ማንነው? ብዬ መደንገጥ ጀምሬያለው..እኔ ይሄ ሁሉ ቀርቶብኝ እናት ብቻ ነበር መሆን የምፈልገው… የቢላል እናት መሆን…፡የቢላል እናት በሚል በፀጋ በተሞላ አስደናቂ ስም መጠራት.፡፡ ፖሊሱ ራሱ የሁሉቱ ሴቶች ሀዘን በጥልቀት ተጋባበት….ምንአይነት የተለየ ሰው ቢሆን ነው በዚህ መጠን ይወዱት የነበረ…?ሲል በውስጡ አሰበ….ከመሳቢያው ኪስ ውስጥ አንድ ወረቀት አወጣና ጠረጳዛ ላይ አሰቀመጠ….እና በሁለቱ መካከል ገፋ አደረገና አስጠጋላቸው.ሁለቱም እርስ በርስ ተያዩ ‹‹…ምንድነው ኢንስፔክተር?›ሲፈን ነች ጠያቂዋ የቢላልን ክፍል ስንመረምር ያገኘነው ነው…ለሁለታችሁ ከመሞቱ በፊተ የተወላቸሁ መልዕክት ነው.፡ ሲፈን በፍጥነት አፈፍ አድርጋ አነሳችው….ድምፃን ከፍ አድርጋ ማንበብ ጀመረች፡፡ I hope you are blessed With a heart like a wildflower Strong enough to rise again After being trampled on Tough enough to weather The worst of the summer and even able to grow and flowrish In the most broken of places // ማን ነበር እነዚህን የሀዘንና የተሰፍ እንጉርጉሮ ያንጎራጎረው.?.እኔ እንጃ ተረሳኝ/እማዬ….አንቺ የአለሞ ቁጥር አንድ እናት ነሽ...በጣም ነው የምወድሸ….ጤነኛም ስሆንም እዕምሮዬም በተቃወሰ ጊዜም ጭመር አንቺን ባለመቋረጥ እወድሻለው…እናም ደግሞ ከሞትኩ ቡኃላም እንደምወድሽ እንዳትጠራጠሪ፡፡ደምፅሽ እያወራሽኝ ሁሉ ይናፍቀኝ ነበር፤.ጠረንሽ ጉያሽ ተሸጉጬ እራሱ እራበዋለው…እማዬ ጥዬሽ ስለሞትኩ በጣም አዝናለው….ግን የግድ ማድረግ ስላላብኝ ነው፡፡አዎ በፍጥነት ውሳኔ ወስኜ እራሴን ካላጠፋው የምወዳትን ልጅ አጠፋለው….እሷን ገድዬም ደግሞ ብተርፍ አንድ ነገር ነበር …..ከገደልኮት ቡኃላ ደግሞ እራሴን ማጥፋቴ የማይቀር ነው..ሁለት ኪሳራ.፡፡..እና እማዬ ይቅር በይኝ… ሲፈን ….አንቺ በነፍሴ የማፈቅራት ልዩ ሴት ነሽ….በጣም ልዩ ሴት..፡፡በንግግርሽ በጣም ከመደንዜ የተነሳ የእውነትም አንቺን ስለማግባት እያሰብኩ ነበር…ቃል እንደገባሽልኝ ገነት መሳይ በተፈጥሮ ያሸበረቀች ልዩ የብቻችን ቦታ ወስደሺኝ .እዛ ጎጆችንን ቀልሰን ..ልጆቻችንን ወልደን….ብርቱካንና መንጎ ከጎሮ እየቀነጠስና…ጥልል ባለ የወንዝ ውሀ ገላችንን እየታጠብን …በዝሆንና ቀጪኔ ጀርባ ላይ ሰርከስ እየሰራን..ብዙ ብዙ ነገር እንዳልም አድርገሺኛል…. ግን አንዳንዴ መራር ቢሆን እውነታን መጋፈጥ የጀግኖች ባህሪ ነው.እና እኔም ጀግና መሆን ወሰንኩ…፡፡ለአንቺ ህይወት የሚበጀውን ዘላቂ ነገር ማስብ እንዳለብኝ ወሰንኩ…አንቺን አንቄ ከመግደሌ በፊት እራሴን ማንጠልጠል እንዳብኝ ወሰንኩ…፡፡.እንደዛ ያደረኩት ለአንቺ አስቤ አይደለም፡፡.ጥዬሽም ለመሄድ አንጀቴ ጨካኝ ሆኖ አይደለም…አብረን ብንሞት እና አንድ መቃብር ብንቀበር ደስ ይለኝ ነበር…ግን እንደዛ ማደርረግ አልቻልኩም .፡፡ለምን? ለልጃችን ስል፡›› .ማንበቧን አቋረጠችና አንዴ ፕሮፌሰሯን አንዴ ኢንስፔክሩን እያፈራረቀች ተመለከተች‹‹..የምን ልጁ?›› ፕሮፌሰሯ ትከሻዋን በመነቅነቅ ‹እኔ ምን አውቄ ›የሚል መልስ ሰጠች.. እንስፔክተሩ ‹‹ማንበብሽን ቀጥይ ›› አለት ማንበብ ቀጠለች… ‹እማዬ እና ሲፈን…እድለኛ ከሆንኩ አንድ የምስራች ልንገራችሁ…ማለቴ ይሄን ደብዳቤ ከማንባችሁ በፊት በሌላ መንገድ ዜናውን ካልሰማችሁ ማለቴ ነው፤እማዬ ልጅ ትቼልሽ ነው የሞትኩት…የልጅ ልጅ ሊኖርሽ ነው..ሲፈን እርጉዝ ነች የእኔ .ል..ጅ…..አርግዛ..ለች.› ሲፈን ከመቀመጫዋ ተነሳች..ሆዷን በእጆቾ ዳበሰች.. ‹‹ምን ማለት ነው.?››ማርገዜን እንዴት ነው ያወቀው…?እንዴት እንደዛ ሊሆን ይችላል?›› ‹‹ምነው? ግንኘነት አልፈፀማችሁም እንዴ…?››ኢንስፔክሩ ነው የጠየቃት ‹‹አይ.. እሱማ ፈፅመናል..አዎ በደንብ ፈፅመናል..ግን ያልገባኝ እኔ ማርገዜን ሳላውቅ እሱ እንዴት..?ደሞ እኮ ምንም አይነነት የእርግዝና ምልክት እየታየብኝ አይደለም›› ‹ኢንስፔክተር ይቅርታ አድርግልን ከፈለከን በሚመችህ ሰዓት ተመልሰን መምጣት እንችላለን ..አሁን ሆስፒታል ሄደን ይህንን ተአምር ማረጋገጥ አለብን.››ከመቀመጫዋ ተነስታ ሲፈንን እየጎተተች የኢንስፔክተሩንም ይሁንታ ሳትጠብቅ ይዛት ወጣች፡፡ወደ ሆስፒታል፡ /// አለም በምንም ጉዳይ ላይ ሚዛን የምትጠብቅበት የራስዋ የሆነ ስውር ቀመር አላት…፡፡ገፍትራ ከገደል አፍፍ ላይ ብትጥለንም ስንወድቅ ግን አስከመጨረሻው ተሰባብረን እንዳንደቅ ማረፊያችንን በተደላደለ የሰንበሌጥ ሳር አልብሰሳ ትጠብቀናለች ፡፡ድንገት ሳናስበው በአስፈሪ የአዞ አፍ ተሰልቅጠን ብንዋጥም ሆዱን ሰንጥቀን አረሳችን ነፃ የምናወጣበት ጩቤ ከጎናቸን እናገኛለን፡፡ ቢላለ በምን አይነት ተአምር እንዳወቀ ለሁለቱም እንቆቅልሽ ቢሆንባቸውም በምርመራ እንዳረጋገጡት ሲፈን የሶስት ሳምንት እርጉዝ ነች፡፡አዎ ከጭለማ ቡኃላ ብርሀን ይፈነጥቃል..ከምሽት ብሃል ንጊት አይቀሬ ነው….ከስቅለት ቡኃላ ትንሳኤም የሚጠበቅ ነው…በሁለቱ ሴቶች በሀዘን የደቀቀ ልብ ውስጥ የሆነች ብጣቂ ተስፋ ለመነቃቃት ስትንፈራገጥ ትታያለች፡፡ ይቀጥላል... #ሊጠናቀቅ አንድ ክፍል ብቻ ቀረዉ!!
Показати все...
😘ነፍስ ስታፈቅር😘 🔥ክፍል 43 . . #ሊጠናቀቅ አንድ ክፍል ብቻ ቀረዉ!! . . ፀሀይ በደመቀ ብርሀኗ እና ለብ ባለው ሙቀቷ በፈገግታሽ ብትወጣም ሰዓቷን ጠብቃ መክሰሟና መጥለቋ አይቀሬ የተፈጥሮ ግዴታ ነው..ጨረቃም ምሽቱን ጠብቃ በዝግታ እየተሳበች በመውጣት ሰማዩ ላይ በመገማሸር ብርሀኗንም ውበቷንም ብተረጭም ንጊት ሲቃረብ መጥፋቷ የሚጠበቅና የግድ የሆነ የተፈጥሮ ግዴታ ነው፡፡ደጅ ላይ የተተከለ አበባም ፈንድቶ በማዓዛውም በውበቱም አካባቢውን አድምቆ ለንቦችም ለቢራቢሮዎችም የሚገባቸውን ምግብ ያለስስት ለግሶ የማታ ማታ ወይ በአንድ አድናቂው ተቀንጥሶ ወይ ደግሞ በራሱ የተፈጥሮ ኡደት ጊዜው ደርሶ መድረቁና መርገፉ የማይቀር ነው፡፡ ሰውም እንደዛ ነው፡፡ከተወለደ..መቼም ይሁን መቼ የሞት ዕጣ እንዳለበተ ቅንጣት የማያጠራጥር ንፅህ እውነት ነው፡፡እንደውም ለሰው መለቀስ ካለበት ተክክለኛው ወቅት ሲወለድ ነው፡፡ብልሁ ሰው ለሞት ቀለብነት እየተፈጠረ ነውና፡፡ዳሩ ሰው ሰው የሚሆነው ምንአልባት ለእናት ካልሆነ በስተቀር ለሌላው ሰው ቅርፅ የሚመዘን ውበት የሚኖረው ከተወለደ ብኃላ በእድገቱ እና በኑሮ ውጣ ውረዱ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር በሚፈጥረው መስተጋብር ፤በእያንዳንዱ ነጠላ ገጠመኝ በየግለሰቦቹ ልብ ውስጥ ባለው ግዛት የሚገነባቸው የትዝታ ግንባታዎች አይነት ነው ፡፡ አንዳንዱ እድሜ ልክ አጠገባችን ኖሮ በውስጣችን ያለው ትዝታ ከእጅ መዳፍ የማይበልጥ ይሆናል...ሌላው ደግሞ ሶስት ቀን ስራችን ቆይቶ ሀገር የሚያህል ግዛት በልባችን ተመርቶ በደግነት ጡብ የታነፁ በፍቅር ልስን ያማሩ ለዘመነት የሚበቁ የትዝታ ግንብ ገንብቶ እናገኘዋለን፡፡ ቢላል በሲፈን ልብ ውስጥ የፈጠረው እንደዛ አይነት ታአምር ነው፡፡እንደውም ከዛም በላይ ነው.፡፡ለሰው ሊያስረድት ከሚችሉት በላይ...ለራስም አስበው ሀሳቡን ለመቋቋም ከሚችሉት በላይ…በመኖር እና ባለመኖር መካከል ያለች የሳሳች በጣም ቀጭን የህይወት ክር ላይ አንጠልጠሎ የሚያላጋ ስሜት ላይ የሚያስቀምጥ፡፡ ሙሉ በሙሉ ጥቁር ለብሳለች….ከለቅሶ ብዛት አይኗቹ ከተገቢው በላይ ማበጣቸው ካደረገችው ግዙፍ ጥቁር መነፅር እንኳን ሙሉ በሙሉ ሊከልላቸው አልቻለም፡፡ከሁለት ቀን እራስን የመሳትና የሆስፒታል ቆይታ ቡኃላ ነው እንደምንም ተደግፋ ቀብር ላይ የተገኘችው፡፡የፕሮፈሰሯ ሆነ የእሷ ቤተሰቦችና ወዳጇች በብዛት ተገኝተዋል፡፡ከዛም በላይ ወሬ ቃራሚ የሚዲያ ሰዎች ከለቀስተኛው ጋር በመመሳሰል ፤ አንዳንዱ መንነታቸውን የሚለይ ባጅ አንገታቸውን አንጠልጥለው በግልጽም ተገኝተዋል፡፡ የቀብር ፕሮግራሙ ብዙ ሀሜቶችና ጉረምርማተዎች የታጀበ ነበር....የአልቃሹ ቁጥር የአንድ ሰው የእጅ ጣት አይበልጥም…በሀዛን የተሰበሩት ፤.ከልባቸው በመንሰፍሰፍ የሚያለቅሱት ደግሞ ፕሮፌሰሯና ሲፈን ብቻ ናቸው….እርስ በርስ የእየተቃቀፉ..እርስ በርስ እየተደጋገፉ…እርስ በርስ እየተፅናኑ ይህንን የጨለማ ቀን ግዙፍ ተራራን ለመግፋት እየጣሩ ነው….ከገቡበት ጥቅጥ የብቸኝነት ጨለማ ዋሻ በእንዴት አይት ፅናት ገብተው ሳይፈራርሱና ማንነታቸውን ሳያጡ ከዚህ ክፉ ፈተና እንዴት ማገገም እንደሚችሉ በየልባቸው እየተማከሩ ነው፡፡ ቀብሩ ከተጠናቀ ብኃላ ያው በደንቡ መሰረት ቀጥታ ወደፕሮፌሰሯ ቤት ነው ያመሩት ፡፡ቤተሰቦቾም ሆኑ ሄኖክ ከሚከታተሏት ሰዎች ጋር የነበራቸውን ውል ሙሉ በሙሉ አቋርጠዋል፡፡እናም አሷ ግድ ባይኖራትም አሁን በየሄደችበት እየሄደ የሚከታተላት ሰው ከጀርባዋም ሆነ ከፊቷ የለም፡፡ /// ..ቀብሩ ከተጠናቀ በሶስተኛው ቀን ቡኃላ ፕሮፌሰሯ እና ሲፈን ፖሊስ ጣቢያ ተጠሩና ሁለቱም በአንድላይ መርማሪ ፖሊስ ፊት ለፊት ቀረቡ፡፡ ‹‹ከቢላል ጋር ያላችሁን ዝምድና ወይም ግንኙነት?››የፖሊሱ ጥያቄ ነበር ‹‹ሁለቱም ተራ በተራ አብራሩ›› ‹‹ሲፈን ..ቢላልን ለመጨረሻ ጊዜ ያየሽው መቼ ነው?›› ‹‹ከሞቱ ከስድሰት ወይም ከሰባት ሰዓት በፊት›› ‹‹የት ?›› ‹‹እቤቴ ማለት አባቴ ቤት እኔ ክፍል›› ‹‹ምን ሊሰራ ነበር የመጣው ..?›› ‹‹ያው እደነገርኩህ ቤላል ጓደኛዬ ነው…ድንገት ከተሰወረ ከ22 ቀን ቡኃላ ለሊት ላይ የቤታችን ጣሪያ ቀዶ ነበር የገባው…እና ያንን በማደረጉ በነፍሴ ጭምር ነበር የተደሰትኩት፡፡ ከዛ ቡኃላ በተከታታይ ሀያ ለሚሆኑ ቀናት ከዛ ክፍል አልወጣም ነበር.›› ‹‹ሀያ ቀን ሙሉ›› አዎ …ብዙ ነው እንዴ …?.ለእኛ ግን የሁለት ቀን ያህልም ርዝመት አልነበረውም….እንዴት መሽቶ እንዴት እንደሚነጋ አናውቅም ነበር…ዋናው ጭንቀታችን የእሱን እዛ መኖር እቤተሰቦቼ ወይም ሌላ ሰው እናዳያውቅ ማማረግ ነበር.ያም ተሳክቶልና.፡፡.በህይወቴ ትልቅ ትርጉም ያለው የሚገርም ጊዜ ነበር ያሳለፍነው….እድሜ ልኬን ከእዛ ክፍል የመውጣት እቅዱም ፍላጎቱም አልነበረኝም…የውጩን አለም ጠቅላላ ዘንግቼው ነበር..ምንም የሚናፍቀኝ ነገር አልነበረም…ስራዬ..ሀብቴ ሰሜ ..በእቅፌ ከነበረው ቢላል ጋ ሲነፃፀሩ ምንም ትርጉም አልነበራቸውም፡፡››ረጅም ትንፋሽ ወሰደችና በጉንጮቾ ላይ ያለከልካይ የሚፈሰውን እንባ በሶፍት መጠራረግ ጀመረች…ከዛ ፀጥ አለች ‹‹ቀጥይ ..እየሰማውሽ ነው››አንስፔክተሩ ነው በገለፃዋ እንድትቀጥላ ያበረታታት.ፕሮፌሰሯ በእንባ ከማገዝ ውጭ በዝምታ እንደተዋጠች ነው፡ ‹‹ወደዋናው ነጥብ ልምጣልህና የሞተ ቀን ማለቴ አሁድ አብረን በደስታ አደርን ጥወታ በማለዳ ነቃንና ….ብዙ የደስታ ወሬዎች አወራን...ሳቅን.. .ተላፋን…..የምንወደውን ሙዚቃ በአንድ ኤሮፎን አዳመጠን….ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ ልክ እንደሌሎቹ ቀናት የምንበላውን ቁርስ ለማምጣት በውጭ ቆለፍኩበትና ወደኪችን ሄድኩ፡፡ ብዙም አልቆየውም .. ከ10 ወይም ከ12 ደቂቃ ቡኃላ የምንበላውን ቁርስ ይዤ ስመጣ ክፍሉ ባዶ ነበር…ሻወር ቤት ፈልኩ ..አልጋ ስር ሳይቅር ፈለኩ…በጣም ደንገጥኩ.. ልጮህ ሁሉ ነበር፣.ቡኃላ ጠረጳዛ ላይ መልዕክት ትቶልኝ ነበር› ‹‹ምን ይላል መልዕክቱ?›› ‹‹እማዬ ናፍቃኛለች…እሷ ጋር ሄጄያለው…በተለመደው መልክ ማታ ተመልሼ መጣለው…በጣም እወድሻለው›› ይላል፡ ከዛ ተረጋጋው.‹. ቢሆንም መንገድ ላይ አደጋ ያጋጥመው ይሆን…?› የሚል ስጋት ስላለብኝ ከአንድ ሰዓት ቡኃላ መሰለኝ ለፖሮፌሰር ደወልኩና ጠየቅኳት ..በደስታ እሷ ጋር እንዳለ ነገረችኝ..፡፡ ከዛ ቡኃላ በቃ ሰባት ሰዓት ላይ ተደውሎልኝ እራሱን አጥፈቷል ተባልኩ…መአት ነው የወረደብኝ…ከከረምኩበት ገነት የሆነ ክፉ አጋንንት በእንዴት አይነት ፍጥነት አሽቀንንሮ ሲኦል እንደጨመረኝ አልገባኝም…አለም ግን እንዴተ አስቀያሚ ነች….ጠንካራ አለት ነው ብዬ የቆምኩበት አፈር ነው ድንገት ተደርምሶ እንጦሮጦስ ወስዶ ያሰመጠኝ፡፡››በእንባዋ እየታጣበች በመሪር ሀዘን የነበረውን ነገር አስረዳችው፡፡ ‹‹እሺ ፕሮፌሰርስ?›› ‹‹እሷ እንዳለቸው ነው.ሶስት ሰዓት ሲሆን ሳሎን ቁጭ ብለን ቁርስ አየበላን ሳለ . በሩ በዝግታ ተከፈተ… አይኔን ወደዛ ስልክ የእኔ ምስኪን ልጅ ነበር..፡፡ብታይ አምሮበታል…እነዛ ሰማያዊ አይኖቹን እላዬ ላይ ሲያንከባልላቸው የተሰማኝ የደስታ ስሜት ልግልፃልህ አልችልም...ከአርባ ምናምን የጭንቅ ቀን ቡኃላ ነበር ልጄን ያቀፍኩት …እቤቱን በጪኸት አስነካውት፤ ግቢው ውስጥ ያሉት ሰዎች ሁሉ ተሰበሰቡ ፡፡
Показати все...
ሰላም ለእናንተ ይሁን። የተወሰኑ ችግሮች ስለገጠሙኝ ነዉ የተጠፋፋነዉ። ፈልጌዉ ባልጠፋም ይቅርታ እጠይቃለሁ🙏 ታሪኩን ሰሞኑን የምፅፍላችሁ ይሆናል። ሁላችሁንም ከመጥፎ ሰዎች ይጠብቃችሁ!!
Показати все...
😘ነፍስ ስታፈቅር😘 🔥ክፍል 42 . . /// ሁለቱም ነጭ ፎጣ ከወገባቸው በታች አገልድመው ጣጣቸውን ጨርሰው   ከሻወር ወጡ..አልጋው ጠርዝ ላይ  ጎን ለጎን ተቀመጡ.. ‹‹እርቦሀል?›› አለችው:: ‹‹በጣም….መቼ ምግብ እንደበለው አላስታውስም››መለሰላት፡፡ ‹‹እንግዲያው እንብላ .እኔም እራቴን እስክጠግብ የበላው ቢሆንም አሁን ሆዴ ውስጥ አውሬ እንደታሰረ እየቧጠጠኝ ነው›››አለችና ከመቀመጫዋ  በመነሳት ምግብና መጠጥ የተደረደረበትን አነስተኛ ጠረጳዛ ቢላል ወደ ተቀመጠበት ቦታ እያስጠጋች፡፡ ‹‹ቡዙ ኃይል ስላወጣሽ ነዋ….›› ‹‹ቀላል ኃይል…ሙጥጥ ነው ያደረከኝ.›› /// ቀላል ጫወታ እየተጫወቱና እየተጎራረሱ ምግብን በሉ…ከሚጠጠውም ጠጡ. // ‹‹አሁን ብንተኛ ምን ይመስልሀል.?››. ‹‹ደስ ይለኛል›› ‹‹ቢጃማ ልስጥሀ?›› ‹‹…አንቺን ማረብሽሽ ከሆነ…እንዲሁ ብተኛ ደስ ይለኛል›› ‹‹ግድ የለህም በእንደዚህ አይነት ሁኔታ መረበሽ እራሱ የራሱ የሆነ  ጣፋጭ ጣእም አለው.›› ‹‹እንግዲያው አጣጥሚው …››.አለና ያገለደመውን ፎጣ ከላዩ ላይ ተርትሮ አነሳና ጠረጵዛ ላይ አስቀመጠ…መለመላውን  ወደ አልጋው ወጣ ….ገልጦ ከውስጥ ገባ….እሷም ልክ እንደእሱ አደረገች…አዎ ይህቺን ቀን በተደጋጋሚ በህልሟ  አይታታለች….ህልሟ ህልም ሆኖ ይቀራል የሚል ጠንካራ ጥርጣሬ ነበራት….አሁን ግን ይሄው ባላሰበችው ተአምራዊ መንገድ ህልሟን እየኖረችው ነው..…የነፋሷን ጌታ በስጋዋ እቅፍ ከታ..በትንፋሹ ውስጧን እያሞቀች ….በሙቀቱ እየቀለጠች…በደስታ ስካር ላይ ነቸ….ይህ ተአምር ነው፡፡ደረቱ ላይ ልጥፍ አለች…እጆቹን በአንገቷ ስር  አሸግሮ አቀፋታ አንዱን እግሯን አነሰችና እግሮቹ ላይ ጫነች..አንደኛው  እጇን ደረቱ ላይ አሳረፈችና የደረቱን  ጸጉሮች ማፍተልተል  ጀመረች….. ‹‹ግን  ይሄን ሁሉ ቀናት የት ሄደህ ነበር?››ካገኘችው ደቂቃ ጀምሮ ለመጠየቅ ፈልጋ ግን ደግሞ እስኪረጋጋ በሚል የማዘን ስሜት አፍናው  የነበረውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡ ‹‹እንዲህ በነፍሴ ጭምር ስጨናነቅ የምሄድበት ቦታ›› ‹‹እኮ ያ ቦታ የት ነው?›› ‹‹እሱን አሁን አልነግርሽም›› ‹‹እሺ እንዳሰብከው መሄድህ ጠቀመህ?›› ‹‹አንቺ ምን  ይመስልሻል?›› ‹‹እሱማ  እንደማይህ በጣም ጠቅሞሀል….ካሰብኩት  በላይ ተረጋግተህል…. ፍፅም ጤነኛ ሆነህ ነው የመጣሀው›› ‹‹ፍፅም ጤነኛ አልሽ..ፍፅም ጤነኛ እና ፍፅም በሽተኛ የሚባል ሰው የለም…ሁላቸንም ጤነኝነት እና በሸተኝነትን በደባልነት  አዝለን ነው የምንዞረው …. ልዩነቱ  የመጠን ጉዳይ ነው.እንዳልሺው ግን መሄዴ ጠቅሞኛል….ቢያንስ እስከዛሬ አንቺን አልገደልኩሸም…›› ‹‹ለእኔ  ግን  ዝም ብለህ አድራሻህ ሳታሳውቅ እንደዛ ጠፍተህ በፍለጋ ከምታሰቃየኝ ..ብትገድለኝ ይሻለኝ ነበር›› ‹‹አዎ እኔም ለብዙ ቀን  በነገሩ ላይ ካሰላሰልኩበት  ቡኃላ‹ ….እስከመቼ ገና ለገና ልገድላት እችላለው በሚል ስጋት  ከእሷም ሆነ ከእናቴ እሸሻለው…?ወደእሷው ተመለሼ እውነታውን መጋፈጥ አልብኝ..ደግሞ እጣፈንታን   ይጋፈጡታል  እናጂ ሸሽተው አያመለልጡትም ›  ብዬ  ወሰንኩ እናም እንደምታይው መጣው..›› ‹‹ከግድያ  ወሬ እንውጠና ሌላ ጥያቄ ልጠይቅህ?›› ‹‹ያንቺው ነኝ.. .እንደፈለግሽ›› ‹‹ስለቤተሰቦችህ›› ‹‹ስለቤተሰቦችህ ምን.?›› ‹‹ፕሮፌሰር ወላጅ እናትህ እንዳልሆነች አውቄያለው›› ‹‹ለእኔ ግን  እንዳዛ አይሰማኝም› ‹‹እሱ ጥሩ ነው…ግን ስለወላጆችህ ምን ታውቃለህ?›› ‹‹ምነው አንቺ ስለቤተሰቦቼ የምታውቂው ነገር አለእንዴ ?›› ‹‹በፍጽም›› ‹‹እንግዲህ እኔም ምንም አላውቅም…እናት፤ አባተ የለኝም፡፡ልጅነቴ ትዝ አይለኝም፡፡የሞለ ህፃናት ቆይታዬ እንዴት እንደነበር አላውቅም…ትምህር ቤት የት ሀገር እንደተማርኩ እንኳን  አላውቅም፡፡.ከአስተማሪዎቼ መካከል አንዱ እንኳን   ትዝ አይለኝም…ግን እንደተማርክ  አውቃለው… በከፍተኛ ደረጃ እውቅ የተባሉ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተምሬያለው….የት ? እኔ እንጃ……ስለ እነዚህ ነገሮች ምንም የማስታውሰው ነገር የለውም..ከልጅነቴ  ጀምሬ ለረጅም  አመት የሆነ ግዙፍ ዋርካ ስር በጥላው ተመስጬ  በመተኛት ወጣትነቴን ካጋመስኩ ቡኃላ ድንገት የነቃውና ስነቃ ደግሞ የፕሮፌሰሯሮ  እጅ ላይ እራሴን ያገኘው ነው የሚመስለኝ፡፡አዎ ያንን ብቻ ነው በግልፅ የማስታውሰው፡፡ ‹‹ስለእኔ ምን  ታስባለህ?››ሌላ ጥያቄ ‹‹ስለአንቺ ምን?›› ‹‹እንዴት ልታፈቅረኝ ቻልክ….?መቼስ እንደሌላው ገንዘቤ ላንተ ትርጉም እንደማይሰጥህ አምናለው…መልኬ …?ንግግሬ…  ?ምኔ..? ‹‹ከዚህ በፊት የነገርኩሽ መስሎኝ..› ‹‹ለእኔ?›› ‹‹አዎ ለአንቺ…የማፈቅረው ነፍስሽን ነው ብየሽ ነበር›› ‹‹አዎ አስታውሳለው….እሱ ግን   አገላለፅ እኮ ነው…ነፍስ ተጨባጭና ተዳሳሽ አይደለችም›› ‹‹ፍቅርም ተጨባጭና ተዳሳሽ ቁስ አይደለም..ግን ግልፅ ለማድረግ በነፍሴ ነው ያፈቀርኩሽ ሰል ላስረዳሽ የፈለኩት  ያወቅኩሽ ወይም ያፈቀርኩሽ በአካል ያገኘውሽ ቀን እንዳልሆነ ለመግለፅ ፈልጌ  ነው›› ወደምትፈልገው መስመር እየገባላት ሰለሆን በአድናቆት ከደረቱ ቀና በማለት  ተንከባላይ አይኖቹን በፍቅርና በጉጉት እያች‹‹ይበልጥ አብራራልኝ.››ስትል ጠየቀችው፡፡ ‹‹እብድ ባልሆን ኖሮ ይሄንን ማስረዳት ይከብደኝ  ነበር…ግን ምንም አይነት ወጣ ያለ ነገር ብናገር ወይም ያልሆነ ነገር ብሰራ እብድ ስለሆነ ነው ስለሚባል ብዙም አያስገረምም. .እኔ አንቺን ከማግኘቴ በፊት፤ እቤትሽ ከመምጣቴ በፊት፤ ከፕሮፌሰሯ እናቴ ከመገናኜቴም በፊት፤ ምን አልባትም ከመወለዴም በፊት ይመስለኛል የማውቅሽ…..አማዬ  አልነገረችሸም እንዴ አንቺን ከማግኘቴ በፊት ገና ሆስፒታል በሰንሰለት ታስሬ ስታከም እራሱ ያንቺን ስዕል እየሳልኩ አሳያት ነበር…እሷ እንደውም ወላጅ እናቴ ወይም  እህቴን የምስል ይመስላት ነበር…አሁን ነው ነገሩ የገባት….›› ‹‹ስለዚህ መጀመሪያ እቤቴ መጥተህ ሻወር ፈልጋለው ብለህ ያስደመምከኝ  ሆነ ብለህ ነበር ማለት ነው፡፡›› ‹‹በፍጽም …ለምን እንደዛ  አልሽ..?›› ‹‹በወቅቱ ሰታየኝ ብዙም የተለየ ነገር አላሳየህማ…የዛን ቀን በአካል ያገኘኸኝ የመጀመሪያ ቀን ቢሆን ኖሮ ያሰታውቅብህ ነበር.›› ‹‹እውነትሽን ነው….በአካል ሳይሽ ያ የመጀመሪያ ቀኔ አልነበረም…ለመጀመሪያ ጊዜ የዛሬ አመት አካባቢ ስለካማፓኒሽ በቲቪ  መግለጫ ስትሰጪ  ነበር ያየሁሽ.. ‹‹እና ምን አደረክ?›› ‹‹ምንም አላደረኩም….በወቅቱ  ሰውነትን በጠቅላላ የሚነዝር የደስታ ስሜት ነበር የተሰማኝ….ሙሉ እብድ እንዳልሆንኩ ያወቅኩት የዛን ቀን ነው…..ምክንያቱም ተጨባጭ ነገሮችንም በአዕምሮዬ  አለማለው ማለት ነው የሚለውን የአንቺ የሆነ ቦታ በአካል እውን ሆኖ መገኘት ማረጋገጨ ሆነኝ .ይሁን እንጂ  እኔ በነፍሴ አፍቅሬያት በእየእለቱ እያለምኳት የነበረችው ሴት ተራና  ንፅህ   የመንደር ሴት እንድትሆን ነበር ፍላጎቴ…ከተቻለ ጭልጥ ያለ ገጠር የምትኖር . ‹‹አና እኔ ንፅህ አይደለውም ማለት ነው.?.›› https://t.me/ethiofilm2adey_drama
Показати все...
‹‹እሱ ብቻ አደለም ችግሩ በአንቺ ደረጃ ያሉ ሰዎች እርቴፌሻል ህይወትና  ነው  ያላቸው..እያንዳንዷን በእለት ውሎቸው የሚከውኗቸው  ነገሮችን  እቅድ በሚል ስም መጀመሪያ በወረቀት ላይ እስክሪፒቱን  ይጻፍና   ከዛ ሳያዛንፉ ሲተውኑ ይውላሉ.. ንግረግራቸው በተመረጠና የሆነ ውጤት እንዲያመጣ በተሰላ መንገድ የሚነገር…አለባበሳቸው የሆነ መልዕክት የሚያስተላልፍ …አበላላቸው.አጠጣጣቸው..ሁለነገራቸው አርቴፊሻል ነው..እና ባለሽበት ተውኩሽ››.. ‹‹በነፈስ ማፍቀር እንዲህ ለመተው ቀላል ነው እንዴ?››ሞጋች ጥያቄ ጠየቀችው፡ ‹‹አዎ ..አልከበደኝም.፡፡ምክንያቱም እኔ ማስባትን አይነት እንደሆንሽና የሆነ በደን በተከበበ   የአራዊት ማጎራት በቅርብ በሚሰማበት.፤የወፎች ዝማሬ መንፈስን በሚያድስበት፤ ፎፎቴ  ከተራራው አናት ከሚከነበልበት፤ ልዩና ንፅህ ቦታ ልክ እንደሄዋን በቅጠል እፍረትስጋዋን ብቻ ሸፍና ከእንጨት ተጠርቦ የተሰራና በሀረግ የተጠቀለ ጫማ አድርጋ፤ ፀጉሯና ከወዲህ ወዲያ ንፋስ እየተበተነባት፤ ከበለስ ግንድ ላይ የበሰለውን ስትቀነጥስ በምናቤ እያየውና  እየጎመዣው እችለዋለው፡›› ‹‹ስለገኘኸን እና እንዲህ ስለሆነ ቅር ብሎሀል?››አለችው ቅር በተሰኘ የስጋት ድምፅ ‹‹አላለኝም ..ምክንያቱም የዛን ጊዜ ስለአንቺ  የወሰድኩት  ግምቴ ላይ  ግማሽ  ሰህተትም ነበረበት›› ‹‹እንዴት?›› ‹‹…አንቺን  ፍጽም አርቴፊሸል ሴት እንደሆንሽ መገመቴ  የእኔ  ስህተት ነበር  ፡፡ያንን ስህተን ደግሞ የተረዳውት አሁን ባልሽው ለመጀመሪያ ቀን ሻወር ፍለጋ እቤቴሽ መጥቼ ዘበኛሽ  አበሻቅጦ ሲመልሰኝ አንቺ ተቀበለሽ በሳተናገድሺኝ ቀን ነው፡፡በአንቺ ቦታ እና ደረጃ ያለች ሴት የፈለገ በውስጧ ብትፈልግ እንኳን  እንደእኔ አይነት ሰውን ወደቤቷ አታስገባም…›› ‹‹እና የመጀመሪያውን ፈተና በመጀመሪያው ቀን አልፍኩ ማለት ነው›› ‹‹አዎ…..እስከአሁንም ያልተቀየረ ፅናት ነው ያለሽ….ከልብሽ ለሚፈልቀው  እውነት በዓለም ፊት በድፍረት የመቆም ፅናት . ..›› ‹‹እሺ ትክክል የሆንከውስ?›› ‹‹….አነቺ ተራ ሰው ባለመሆንሽ በዙሪያሽ ብዙ ጣጣ እንዳለ መገመቴ ትክክል ነበርኩ፡፡እንቺ ባትፈልጊም በዙሪያሽ ብዙ ኮተትና  እና ግሳንግስ መኖሩን አይቀሬ ነው…ለምሳሌ ልታገቢው ቀለበት ያሰርሽለት ሰው...›› ‹‹ሄኖክ ..እሱ ምን  ሆነ?›› ‹‹ያፈቅርሻል አውቃለው….ግን  ካንቺ በላይ ንብረትሽንና ዝናሽን ነው የሚያፈቅረው..ያንንም የማሳጣው ስለመሰለው ሊያስገድለኝ አራት ሰው ቀጥሯል…›› ‹‹እንዴ !!!አንተ ይሄንን እንዴት ልታውቅ ቻልክ..?›› ‹‹ይሄንንም አልነግርሽም…ደግሞ ቤተሰብ የለኝም እንጂ ጓደኞች የሉኝም አላልኩሽም… በመጀመሪያ እኔን መስሎቸው ለገደሉትና ከዚህ አለም መከራ ለገላገሉት ሰው 1 ሚሊየን ብር ከፍሎቸው ከስሯል…አሁንም ሁለተኛ ስመምነት በስድስት መቶ ሺ ተስማምተው ቅድመ ክፍያ 150 ሺ ብር ከፍሏቸዋል.ከአንቺ ከመገናኘቴ  በፊተአግኝተው ሊገድለኝ መከራቸውን እየበሉ ነው ›› ‹‹ምንድነው የምታወራው…?›› ‹‹ከፈለግሽ  ግድያውን የመራውን ግለሰብ ስም ..የተጻፈለትን ቼክ እና ቼኩን የመነዘረበትን የባንክ ቅርንጫፍ ሁሉ ልነግርሽ እችላለው..ከዛ አንቺ ደግሞ ባለሽ ተፅዕኖ በቀላሉ ማረጋገጥ ትችያለሽ፡፡እናም ደግሞ ትዕዛዙን ሲያስተላልፍ ገዳዩ ቀድቶታል….እኔ ደግመ ሞባይሉን በሆነ መንገድ ተቀብየዋለው..ከፈለግሽው ጃኬቴ ኪሴ ውሰጥ አለልሽ..›› ከመኝታዋ ተስፈንጥራ ተነሳች….ጃኬቱ ወደተንጠለጠለበት የልብስ መስቀያ አመራች…ደልደል ያለ ሰውነቷንና  የሚገለባበጥ መቀመጫዋን በተኛበት በስስት እያየ ነው…እጇን በጃኬቱ ኪስ ውስጥ ከተተች..ለመጀመሪ ጊዜ እጇ  ላይ የገባላትን አወጣች...አብረቅራቂና ስል ጩቤ ነው.አገላብጣ አያችው..አይኗን ወደቢላል ላከች…መልሳ እጇን ወደጃኬቱ  ኪስ  ሰደች…አሁንም ያገኘችውን ነገር ይዛ ወጣች...በግምት 10 ሜትር  የሚረዝም ጠንካራና መካከለኛ ውፍረት ያለው  ሲባጎ ገመድ ነው…ዝግንን አላት…፡፡ይህን ጩቤም ሆነ በእጇ  የያዘችውን  ገምድ ታውቀዋለች…ቢላል በጠፋ ቀን ጥሎላት በሄደው ስዕል ላይ ጩቤው እሷ የታረደችበት አይነት ሲሆን ገመዱ ደግሞ እሱ የተሰቀለበት ጋር ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ ነው›› ‹‹ምንድነው ይሄ››አለችው ሁለቱንም እጇን ወድሱ እየዘረጋች ‹‹አጥር ዘልዬ ጣሪያቸሁን  ቀድጄ እኮ ነው እዚህ ስርሽ የተገኘው…ይሄን ሁሉ ደግሞ ባዶ እጄ ብቻ ላደርገው አልችልም…በዛ ላይ..›› ‹‹በዛ ላይ ምን?›› ‹‹ተይው …ስልኩ በደረት ኪስ ውስጥ መሰለኝ ያለው ››. የያዘችውን ጩቤና ገመድ ጠረጳዛው ላይ  አስቀመጠችና ወደጠቆማት ኪስ እጇን ሰደደች .. .ዘመናዊ ሳምሰንግ ስልክ አገኘች፣ይዛ ወደአልጋው ተመለሰች… .ከፍቶ  እንዲያሰማት አቀበለችው.. የሶስት ደቂቃ ቆይታ ያለውና ሌላ ደግሞ የ5 ደቂቃ ቆይታ ያለው የስልክ ልውውጥ ነው…እሷን እየተከታተሏት መሆኑን..ቢላል እንዲገደል የተሰጠ ትዕዛዝ..የልጁ በስህተት መገደል….ሁሉን በግልፅ ያሰርዳል፡፡ ‹‹ወይኔ ምኗ  ጅል ኖሬያለው…ወደስልኬ ላክልኝ፡፡›› ‹‹አረ እኔ ምን  ያደርግልኛል.ስልኩን እኮ ለአንቺ ነው ያመጣውት..ከፈለገሺው ማለቴ ነው፡፡›› ‹‹አረ በጣም  ነው የምፈልገው…..በል አሁን ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሆነ እኮ… ትንሽ እንተኛና ምን እንደምናደርግ ሲነጋ እናወራለን›› ‹እሺ እንዳልሽ….›› ማብራን ተንጠራርታ አጠፋችና እቅፉ ውስጥ ተሸጎጠች…ለተወሰነ ጊዜ እንቅልፍ እንዲወስዳት በመፈለግ ተገለባበጠች ..ግን ሊወስዳት አልቻለም‹ቢላሌ›በለሆሳሳ ድምፅ ተጣራች፡ ‹‹አቤት የእኔ ፍቅር›› ‹‹ብንጋባ ምን ይመስልሀል?›› ‹‹እየቃዠሽ ነው እንዴ?›› ‹‹አይ እውቴን ነው….›› ‹‹እብድ አግብተሸ አንዴት እንዴት ልትሆኚ ነው..?በዛ ላይ ከእብድ መውለድ አለ…ነው ወይስ አሁን ጤና ስለሆንኩ  ሁልጊዜ እንደዚሁ የሚቀጥል መሰለሽ› ‹‹ግድ የለህም ..ከእኔ ጋር ከተጋባህ ለዘላለም ጤነኛ ትሆናለህ…ባትሆንም ደግሞ ከጎኔ እስካለህ ድረሰ ግድ የለኝም…›› ‹‹አይ ሚሆን አይመስለኝም…..ቅድም እኮ ነገርኩሽ .አንቺ ብዙ ጣጣ ያለብሽ የአደባባይ ሴት ነሽ› ‹‹ለአንተ ስል ሁሉን ነገር ተዋለው.በእዕምሮህ ያለችውን አይነት ሴት ሆንልሀለው…እልም ያለ ገጠር እንገበለን በደን የተሸፈነ ፤እንስሳት የሚተረማመሱበት፤ ወፎች የሚደንሱበት ፤የሰው  ግርግር የሌለበት አንድ አነስተኛ ገነት መሳይ  ደሴት እንገዛና እዛ እንኖራለን….› ‹‹ወይ .ለዚህ እኮ ነው በነፍሴ የማፈቅርሽ..እና ደግሞ በጣም ነው ያስጎመዠሺኝ ….ግን ሌላ  ሁለት ችግር አለ›› ‹‹ምንና ምን?›› ‹‹አንደኛው የአባትሽ ጉዳይ ነው…ጋብቻሽን በተመለከተ ስለተፈራረምሽው ውል አውቀለው›› ‹‹አሱን  ለእኔ ተወው የሆነ መፍትሄ አገኝለታለው…ሁለተኛውን ችግር ንገረኝ›› ‹‹ሁለተኛው እረሴው ነኝ…እስከዛው ካልገደልኩሽ….› ‹‹ከገደልከኝማ ተገላገልን …ሁሉ ነገረ እዛ ላይ ይገባደዳል›› ‹‹እንደዛ ከሆነ እሺ…ምን አልባት ልንጋባ እንችላለን…አሁን ደህ እደሪ›› ‹‹ደህና አደርልኝ.›› ‹‹ጭኑ መካከል  አስገባትና ቅልፍልፍ ብለው ተኙ…ሁለቱም በደቂቃዎች ውስጥ ነበር ጭልጥ ያለ ሰላማዊ እንቅልፍ  የወሰዳቸው፡፡ ይቀጥላል .... ┈┈┈••✿ Share ┈┈┈••✿                   💗 https://t.me/ethiofilm2adey_drama https://t.me/ethiofilm2adey_drama https://t.me/ethiofilm2adey_drama                    💗
Показати все...
ታሪኩን መልቀቅ እንዳለብኝ ለመወሰን እንዲረዳኝ ነዉ። ምን ያህሎቻችሁ ቴሌግራም እየሰራላችሁ ነዉ? Like በማድረግ አሳዉቁኝ ።
Показати все...
😘ነፍስ ስታፈቅር😘 🔥ክፍል 41 . . // ሄኖክ ነገሮች ሁሉ ከእቅድና ከቁጥጥሩ ውጭ እያፈተለኩ ተቸግሯል።‹‹ፊት ለፊት ተቃጥረውና ተዘጋጅተው የሚገጥሙት ጠላት እንዴት የተባረከ ነው›› አለ.‹‹.እኔ ነኝ እንጂ ከመንፈስ ጋር ድብብቆሽ የምጫወት"ሲል ተማረረ......አሁን ቢላል እስኪገኝና በቀጠራቸው ሰዎች እስኪያስገድለው ድረስ ዝም ብሎ እያማረረ ከሚቀመጥ መስራት የሚችለው አንድ ነገር እንዳለ ተሠማው....ከሲፈን ጋር ያለውን የሻከረ ግንኙነት ማለስለስ...አዎ ይሄ ሁሉ ፈተናና ውጣ ውረድ እሷን የራሱ ለማድረግ ነው...ከሰሞኑ ደግሞ በመካከላቸው በተፈጠረ ተደጋጋሚ ግጭት እና መፋተግ የተነሳ በጣም እንደተራራቁ ይሰመዋል ..ደግሞም ተራርቀዋል፡፡:ስልኩን እንኳን ማንሳት ካቆመች ቀናቶች አልፈዋል...፡፡ይሄም ቢሆን ግን በህይወቱ ሌላ ጥሩ ዜና አልጠፋም. …ከእሷ አባት ጋር ተዋውቀዋል..ከዛም አልፈው እሷን በተመለከተ ሊመካከሩና መፍትሄ ሊያበጅ ከሶስት ጊዜ በላይ በአካል ተገናኝተው አውርተዋል...በእሷ ላይም ዶልተዋል።ይሄንን ጉዳይ እሷ ፈፅሞ አታውቅም። እና ለሄኖክ ከሲፈን ጋር ቀለበት ካሠረበት ቀን ብኃላ የገጠመው አንድ መልካም ነገር ከአባትዬው ጋር የፈጠረው መግባባትና በመተባበር ለአንድ አላማ አብሮ መስራት መቻሉ ብቻ ነው፡፡..እና አሁን ከሲፈን ጋር የተፈጠረውን መሻከር ለማለዘብ ሽማግሌ በሚቀጥለው እሁድ መላክ አለበት ..ይሄ የእሱ ብቻ እቅድ አይደለም የሲፈን አባትም ምክር አለበት...ክፍሉን ለቀቀና ወደ አባቱ ክፍል አመራ...አንኳክቶ ገባና ቀጥታ ወደጉዳዩ ገባ "አባዬ በዚህኛው እሁድ ሌላ ኘሮግራም እንዳይዙ ለሽማግሌዎቹ ደውልና ቀድመህ አሳውቃቸው" ‹‹እሺ..እደውልላቸዋለው..አንተ አታስብ" ‹‹እሺ አባዬ አመሰግናለው"አለና እንደአመጣጡ በፍጥነት ፊቱን አዙሮ ሊሄድ ሲል "ሄኖኬ"ጠሩት ‹‹አቤት አባዬ›› አንድ ነጭ ፓስታ አቀበሉት‹‹ምንድነው አባዬ?›› ‹‹አላወቅኩም...ሲፈን ነች የላከችልህ" የሲፈንን ስም ሲሰማ ጊዜ አላጠፋም …ተስገብግባ የመንጠቅ ያህል ከአባቱ እጅ ፓስታውን ተቀበለና ወደክፍሉ ተንደረደረ….ገባና መቀመጥ እንኳን ሳይሞክር ፓስታውን ከፈተው..ውስጡ ያለውን ወረቀት ሲያወጣ የሆነ ነገር ተስፈንጥሮ ወለሉ ላይ ወደቀ...አይኑን የወደቀው ነገር ምንነት ለማወቅ አንከራተተ..ኪሊሊሊሊሊ እያለ የሚሽከረከረው ጥቂት አንፀባራቂ ብረት ነው..ጎንበስ ብሎ አነሳው. ቀና ማለት ከበደው ፡፡ከወገብ ላይ የሆነ ደም ስር ጧ ብሎ የተበጠሰ መሠለው...፡፡እጅ ላይ ያለው ቀለበት ነው..፡፡ሲፈን ጣቶች ላይ በደስታ በሰከረ መንፈስ ውስጥ ሆኖ በኩራት ያጠለቀላት ውድ ባለ አልማዝ ፈርጥ ቀለበት.. ‹‹.እስከወዲያኛው አልፈልግህም እያለቺኝ ነው"ሲል ድምፅ አውጥቶ ጨኸ.."እገድላታለው...የእኔ ካልሆነች የማንም አትሆንም...መሞት አለባት….ቢላል የተባለው ጂል ተሳክቶለት ባይገድላት እንኳን እኔ አለቃትም"...ወሰነ /// ሲፈን በመከራ ስትገላበጥ ቆይታ ነው እንቅልፍ የወሰዳት...‹‹ ከመቼው ነጋና ነው የሚቀሰቅሱኝ...?ደግሞስ ለምን ይቀሰቅሱኛል..?.ምን ተፈጠረ.?.›ስትል አጉተመተመች፡፡እንደምንም ተንጠራራችና አይኖቾን አጨንቁራ ከፈተች..... እባብ እንደተጠመጠመበት ሰው ጆሮ ሰንጣቂ ጩኸቷን ለቀቅችው…. ከአ ልጋው ተስፈንጥራ በመውረድ ወለሉ ላይ በባዶ እግሯ ቆመች….በአንድ ሜትር ርቀት ፊት ለፊቷ ተገትሮ ቆሟል...ጩኸቷን የሠሙት እናቷና ሰራተኛዎ እየተጋፍ መጥተው በራፍን በማንኳኳት ላይ ናቸው፡፡ "ልጄ ሰላም ነሽ..?" "በራፍን ክፈቺ" ሲፈን በቆመችበት ወደበራፍ አይኖቾን ላከች. ….እንደተቀረቀረ ነው ‹‹...ታዲያ በየት ገባ?›እራሷን ነው ምትጠይቀው "እማዬ ሰላም ነኝ ...ቃዠቼ ነው።" "እኔን ልጄ..ምነው አመመሽ እንዴ?" "ደህና ነኝ እማዬ" "ክፈቺልኝና አብሬሽ ልተኛ" "እማዬ...ሠላም ነኝ አልኩሽ እኮ..አሁን ሂጂና ተኚ ..እኔም ልተኛበት" "እሺ ካልሽ ልጅ ..ደህና እደሪ ...ከፈለግሺኝ ጥሪኝ ወይም ደውይልኝ" "እሺ እማዬ.." .የእግራቸው ኮቴ እየራቀ ሲሄድ ሰማች….ዘላ ተጠመጠመችበት...እያገላበጠች ሳመችው..ግንባሩን ..ጉንጩን ..ከንፈሩን ምንም አልቀራትም...አዎ ህልም አይደለም ሰውነቱን እየዳበሰችው ነው..ጠረኑን ወደውስጧ እየማገችው ነው፡፡ከራሷ አራቀችውና መላ ቁመናውን መረመረችው ...ድባይ ወይም አውስትራሊያ ለእረፍት ሰነባብቶ የመጣ ነው የሚመስለው።ጉንጮቹ ሞልተዋል ..ፊቱ ጠርቷል...ጥርሶቹ እንደበፊቱ ፍፅም ነጭ ናቸው...አለባበሱ ዝንጥ እንዳለ ነው፡፡ "እዚህ ክፍል እንዴት ገባህ...?ዘበኛቹን በምን አስማት አለፍካቸው?የሳሎኑን በር ማን ከፈተልህ?ይሄንንስ ክፍል እንዴት?"ማለቂያ የሌለው ግትልትል ጥያቄ፡፡ ወደ ላይ አይኑን አንጋጠጠ..ወደኮርኒሱ እሱን ተከትላ እሷም አንጋጠጠች"ዉይ በፈጣሪ ...አንተ ማፍያ ነበርክ እንዴ ?" ከበላዩ ያለው ኮርኒስ ሆነ ከእሱ በላይ ያለው ቆርቆሮ ሰው ሊያሾልክ በሚችል መጠን በክብ ተቀርፎ ወጥቷል..ቀጥታ ሰማዩ ላይ የተንጠባጠብት ደማቅና ደብዛዛ ኮከቦች ጭምር በጥራት ይታያሉ። እስከአሁን እራሷም ቆማ እሱንም አቁማ መሆኑን ስታስታውስ ጎተተችና አልጋው ጠርዝ ላይ አስቀመጠችው... ‹‹ሰላም ነህ ግን..?.ውዴ አንተን ለመፈለግ እኮ ያላስበረበርኩት የአዲስአባ ጥግ አልነበረም...ምነው እንዲህ ጨከንክብኝ..?.እኔስ ይሁን እንዴት በእናትህ እንዲህ ልትጨክን ቻልክ....?በጣም ነው አኮ ውስጤን ያሰቃየኸኝ...፡፡ልቤ እስኪደክማት ድረስ...አእምሮዬ እንዴት እንደሚታሰብ ግራ እስኪገባው ድረስ....ማን መሆኔ ሁሉ እስኪጠፋኝ ድረስ ነው የተሰቃየውብህ...››ከአንጀቷ ያለምንም ይሉኝታ የውስጧን አውጥታ ተናዘዘችለት፡፡ "እንግዲያው ባለውለታሽ ነኛ" ‹‹እንዴት ማለት የእኔ ውድ?" ‹‹እንዲህ ከስርሽ ርቄ ባልጠፋ ስለእኔ እንዲህ አይነት ስሜት እንደሚሰማሽ ማወቅ አትቺይም ነበር" "እሱስ እውነትህን ነው....በጣም እንደማፈቅርህ አሁን መናዘዝ አለብኝ" "ግን እኮ ሌላ ሰው ልታገቢ ነው?" "እሱን አሁን እርሳው....ደግሞም እኮ አንተም ልትገድለኝ እቅድ አለህ?" "ያ እቅድ የእኔ አይደለም ...የአማልክቱ ነው....እስከአሁንም የውሳኔ ለውጥ መኖሩን አላውቅም"ኮስተር ብሎ ነው እንዲህ ሚላት። "ጉዳዬ አይደለም...አንተ የሌለህበት ኑሮም ያው ከሞት አንደማይለይ በሰሞኑ ሁኔታዬ አረጋግጬያለው... ለማንኛውም ስትገባ ዘበኞቹ እንዳላዩህ እርግጠኛ መሆን አለብኝ..በራፍን ከውጭ ቆልፌብህ ሄዳለው ...እስከዛ ሻወር መውሰድ ትችላለህ" "አዎ መታጠብ ፈልጋለው..ለራስሽ እርግጠኛ ለመሆን ሂጂ....ስገባ ማንም ሊያየኝ እንደማይችል ግን እርግጠኛ ነኝ" "እንደዛ ከሆነ ደስ ይለኛል...ለማንኛውም መጣው"አለችና በለበሰችው ስስ ቢጃማ ላይ ወፈር ያለ ጋወን ደርባበት እንዳለችውም ክፍሉን ከውጭ ቆለፈችና በዝግታ እየተራመደች ወደሳሎን አመራች...ከውስጥ እንደተቆለፈ ነው… ቀስ ብላ ከፈተችውና ወደውጭ ወጣች...ሁሉ ነገር ፀጥ ብሏል..ዘበኞቹ በንቃት የበራፍን ግራና ቀኝ ይዘው ሁለቱም ዘመናዊ ክላሻቸውን ሰድረው ከወዲህ ወዲያ ይንጎራደዳሉ፡፡
Показати все...
በረንዳውን ለቃ ወደእነሱ ተጠጋች..በውድቅት ለሊት ባልተለመደ ሁኔታ ግቢ ውስጥ ሲያዬት ሁለቱም ግራ በመጋባት እርስ በርስ ተያዪ...አንደኛው ወደእሷ ተራመደ "እመቤቴ እባክሽ ወደመኝታሽ ተመለሺ...እንድትወጪ እንደማንፈቅድልሽ ታውቂያለሽ..ለዛውም በዚህ ሰዓት?" "እኔ መች ልውጣ አልኩ?" "ይቅርታ አድርጊልኝ እንደዛ መስሎኝ ነው...ታዲያ ምን እንርዳሽ?" ‹‹አይ የሆነ የመንጓገጓት ድምፅ ግቢው ውስጥ የሠማው መስሎኝ ነው..!ሁሉ ነገር ሰላም ነው ግን?" ….ፈገግ አለ ‹‹<ምነው ጥያቄዬ ያስቃል እንዴ?›› "አረ በፍፁም...ግን ይሄው በግልፅ እንደምትመለከቺው ስራችንን በንቃት እየሠራን ነው ...ወፍ እንኳን ብትሆን ከእይታችን ተሠውራ ወደዚህ ግቢ ዘልቃ መግባት አትችልም..እና ምን አልባት በእንቅልፍ ልብሽ ድምጽ የሠማሽ መስሎሽ ነው... አሁን እኔ የምመክርሽ ልክ እንደወላጆችሽ በእኛ ላይ እምነትሽን ጥለሽ ያለምንም ስጋት የሠላም እንቅልፍሽን እንድትተኚ ነው።›› በተራዋ እሷ ፈገግ አለች "ምነው አላመንሺኝም?" ‹‹አረ በደንብ አምኜሀለው..በሉ ደህና እደሩ›› አለችና ፊቷን አዙራ ወደ ቤት ተመለሰች..‹‹እንዴት አድሮጎ ነው ከእይታቸው ተሰውሮ ሊገባ የቻለው?ይሄን ያህል እንዳጃጅላቸው ቢሰሙ ምን ይሰማቸዋል?››እነዚህንና መሠል ገራሚ ጥያቄዎችን በምናቧ እያብሠለሠለች የሳሎኑን በራፍ እንደነበረ መልሳ በመቀርቀር ድምፅ ላለማሠማት እየተጠነቀቀች ወደ ኪችን ሄደች‹‹...ምን አልባት ምግብ ከቀመሠ ረጅም ጊዜው ይሆናል ..ሊረብ በው ይችላል›› በማለት የተወሰነ ምግብና የሚጠጣ ነገር ይዛ ወደ ክፍሏ ተመለሰች .፡፡ ከፍታ ስትገባ ክፍል ውስጥ የለም ፡፡ አመዷ ብን አለ"ተመልሶ ሄደ እንዴ?"አንገቷን ወደላይ ቀስራ ተመለከተች …በሽንቁሩ ወደላይ ስታማትር ከሰማዩና ሰማዪ ላይ ከተንጠባጠብት ከዋክብት ውጭ የሚታይ ምንም ነገር የለም።የያዘችውን ምግብና መጠጥ ጠረጰዛ ላይ አስቀምጣ በራፍን መልሳ ቀረቀረችና ተንደርድራ ወደ ሻወር ቤት በመሄድ በራፍን በልቅጣ ከፈተችው ..ረጂም የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈሰች..."አለህ?"አለችው፡፡ መለመላውን ቆሞ ከላይ በሚፈሰው ውሀ ሰውነቱን በማስገረፍ ላይ ያለውን ጉብል ወጣት የሻወሩን ውሀ ዘጋና"ምነው እንድሄድ ጠብቀሽ ነበር እንዴ?" ‹‹አረ በፍፅም "አለችው ልስልስ ባለ ሰርሳሪ ድምፅ.... .ወደ እሷ ተንቀሳቀሰ...ወደኃላዋ ለመንቀሳቀስ አሰበች… ግን ደግሞ ልክ በእጆቾ ከያዘቻቸው የሻወር በራፍ ጋር አቆራኝተው እንዳሰሯት ነገር ምንም ማድረግ አልቻለችም..ቀኝ እጇን ያዘና እየጎተተ ወደ ውስጥ አስገባት‹‹...ምን ሊያደርገኝ ይሆን?››የልቧ ምት በእጥፍ ጨመረ"በቃ ሊገድለኝ ነው..."ብርክ ያዛት ...ምንም ለመታገል አልሞከረችም...ከእሱ የሚመጣውን ማንኛውንም ነገር ሁሉ በፀጋ ለመቀበል ከወሰነች ቆይታለች...ይሁንና አሁን እንዲህ የቁርጡ ቀን ሲመጣ በፍራቻ ጣር ከመቃተት ልታመልጥ አልቻለችም..አይን አይኑን እያየች በሚለማመጥ አንደበት"እስቲ ምን አስቸኮለህ?" አለችው፡፡ "ለምን አልቸኩል...በጣም እኮ ናፍቀሺኛል" "ሰው የናፈቀውን ለመግደል እንዲህ አይቸኩልም" "የምን መግደል...?ዛሬ የማፈቀር እንጂ የመግደል ሙድ ላይ አይደለውም።" ወደራሱ ጎተታትና ከራቁት ሠውነቱ ጋር አጣበቃት ...ትንፋሽ እስኪያጥራት ከንፈሮቾን መጠጣቸው...ከዛ ከራሱ አራቃትና የለበሰችውን ጋወን ከላዬ አውልቆ ወለሉ ላይ ወረወረው...ላመል ያህል ሰውነቷ ላይ በተጣለ ስስ ቢጃማ ብቻ ቀረች.. …መልሶ ወደራሱ ጎተታትና ከጠንካራ ደረቱ ላይ ለጠፋት...ጠቅላላ የሠውነቱ ልስላሴ ሲመቻት ከታች ግን ቆረቆራት .."".አፍቅረኝ...በጣም እንድታፈቅረኝ እፈልጋለው"አለችው..፡፡ "በዛ ጥርጣሬ አይግባሽ...በነፍሴ ጭምር ነው የማፈቅርሽ...እሱን ደግሞ በደንብ ታውቂያለሽ"አያለ ሻወሩን ከፈተው..ሿሿሿዋዋዋዋዋ...እንዳቀፋት በቀጥታ ቆሙ..ከሻወሩ ጭንቅላት እየተበታተነ ወደታች እየተስፈነጠረ የሚረግፈው ውሀ በሁለቱ ጭንቅላት ጋር እየተላተመ መላ ሰውነታቸውን ያረሰርስ ጀመር ...ቀኝ እጅን በወገቧ አሽከርክሮ እንዳቀፋት በግራ እጅ ቢጃማውን ከታች ጀምሮ ወደላይ መሠብሠበብ ጀመረ..ከዛ ወደላይ ሰበሰበ..በሁለት እጅ ወደላይ በመሳብ በጭንቅላቷ ሞሽልቆ በማውለቅ ልክ እንደ ጋወኑ ወለሉ ላይ ወረወረው...ቀኝ እጅን መልሳ በወገቧ ዙሪያ አሽከረከረና አቀፋት ..ከሰውነቱ ጋር ያለርህራሄ በኃይል አጣበቃት ..ጡቶቾ ተጨፈለቁ....ቃተተች....ግራ እጅን በፓንቷ እና በመቀመጫዋ መካከል ሰነቀረቸው........የሆነ ህልም ውስጥ ያለች ነው የመሠላት...ለመጀመሪያ ጊዜ ድንግልናዋን ባስወሰደች ቀን የተሠማት አይነት ውጥረት ውስጥ ነው የገባችው..ጉጉት...ፍር ሀት...ደስታ...ዝብርቅ ያለ የሚያንሳፍፍ ስሜት....ይሄ ስሜት ለቢላል ካላት የተለየ ፍቅር ይሁን ወይስ ከወንድ ጋር መተኛት ካቆመች አመት በላይ ስለሆናት አልገባትም....ከንፈሯን በረጅሙ ሲመጣቸው..ከጠንካራ ደረቱ ጋር አጣብቆ ጡቶቾን ሲጨፈልቃቸው..ቀኝ ቂጧን በግራ እጅ ጭምቅ ሲያደርጋት..እና እንትኑ ጭኗ መካከል ድንገት ገብቶ ሲርመሠመስ...እነዚህን ሁሉም ልክ እንደሙሉ ባንድ ህብራቸውን ጠብቀው በተመሳሳይ ጊዜ ሲፈፀሙ....ሲፈን በዛው መጥፋት ማለት ነው የተመኘችው....ሳትነቃ ለዘላለም በዛ ስሜት ውስጥ መቆየት..፡፡ ይቀጥላል.....
Показати все...
ከሶስቱ ባለትዳሮች አንዷ ደወለችልኝ ፤ በቅንነት አነሳሁት ፤ ቤት ስለምፈልግህ ቶሎ ና አለችኝ ፤ በቅንነት እየከነፍኩ ወደ ቤቷ ሄድኩኝ ፤ ባሌ ጅቡቲ ስለሄደ ቤት ውስጥ ብቻዬን ፈርቻለሁና ለዛሬ አስተዳድረኝ አለችኝ ፤ በቅንነት እሺ አልኩኝ። እራት አቀረበች ፤ በቅንነት በላሁ ፤ አጎረሰችኝ ፤ አጎረስኳት ፤ ሌሊት ሆነ ፤ አንተ ሶፋ ላይ ተኛ እኔ መኝታ ቤት ተኛለሁ አለችኝ ፤ እሺ ብዬ በቅንነት ሶፋ ላይ ወጣሁ ፤ ተመልሳ መጥታ ሳሎን ውስጥ ቢንቢ ስለማያስተኛህ መኝታ ቤት እንግባና አንተ ፍራሽ ላይ እኔ አልጋ ላይ እተኛለሁ አለችኝ ፤ በቅንነት እሺ አልኳት። መኝታ ቤት ገባን ፤ አልጋ ላይ ተኛች ፍራሽ ላይ ተኛሁ ፤ መብራቱን አጠፋችው ፤ ከብዙ ሰአት በኋላ ተነስታ የመኝታ ቤቱን መብራት አበራችው ፤ ሰውነቷን የሚያሳይ ስስ ፒጃማ ለብሳለች ፤ አንተ ቀዝቃዛ መሬት ላይ ተኝተህ እኔ አልጋ ላይ መተኛት ከብዶኛልና አልጋው ስለሚበቃን አልጋ ላይ ተኛ አለችኝ ፤ በቅንነት እሺ አልኳት ፤ አልጋ ላይ ወጣሁ ፤ እቀፈኝ አለችኝ ፤ በቅንነት አቀፍኳት ፤ ሳመኝ አለችኝ ፤ በቅንነት አፀፋውን መለስኩላት ፤ አልጋው መነቃነቅ ጀመረ። ተሳቢ መኪናውን እየጎተተ ጅቡቲ የሄደው ባሏ ትውስ ብሎኝ ለስራ ያለውን ፍቅር አስቤ አደነቅኩት ፤ በረዥሙሙሙ ተነፈሰች ፤ በቅንነት የጀመርኩት ነገር በቅንነት ተፈፀመ። ሁላችንም ቅን እንሁን! ቅንነት መልሶ ይከፍላልና!😉😄 ┈┈┈••✿ Share ┈┈┈••✿                   💗 https://t.me/ethiofilm2adey_drama https://t.me/ethiofilm2adey_drama https://t.me/ethiofilm2adey_drama                    💗
Показати все...
👆👆ክፍል 40 ተለቋል!! #ያዉ 176 ግሩፑ ላይ add ስላደረጋችሁ በቃሌ መሰረት ክፍል 40 ተለቋል። 200 ሰዉ add ግሩፑ ላይ ካደረጋችሁ ዛሬዉኑ ምሽት 3 ሰአት ቀጣዮቹን ሁለት ክፍሎች በተከታታይ እለቅላችኋለሁ።🔥 ከስር ተቀመጠዉን ሊንክ በመጫን ግሩፑን እየተቀላቀላችሁ Add አርጉ🙏 🔥Join Join👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇Join https://t.me/lovestorey23 https://t.me/lovestorey23 https://t.me/lovestorey23
Показати все...