cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

Рекламні дописи
4 451
Підписники
Немає даних24 години
+17 днів
+930 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

በትግራይ ክልል ከነበሩት 6378 ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ወደ ስራ የገቡት 227 ብቻ መሆናቸው ተገለጸ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ከ2013 ጥቅምት ወር ጀምሮ የተቀሰቀሰው ጦርነት በርካታ ማህበራዊ፣ ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራን አድርሷል፡፡ የትግራይ ክልል ኢንዱስትሪ ቢሮ ኮምኒኬሽን ዳይሬክተር ዳዊት ገብረጻዲቅ ለአል ዐይን አማርኛ እንደተናገሩት፤ ከጦርነቱ በፊት በክልሉ 6378 ኢንዱስትሪዎች ነበሩ፤ ነገር ግን  ከነዚህ ውስጥ አሁን ወደ ስራ የገቡት 227 ብቻ ናቸው። ዳይሬክተሩ በክልሉ ቁጥጥር ስር በሚገኙ 57 ወረዳዎች ወደ ስራ ተመልሰዋል ከተባሉ 227 ኢንዱስትሪዎች መካከል 200 አነስተኛ፣ 15 መካከለኛና 12 ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙበት ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ ለውጭ ገበያ የሚሆን ምርት የሚያቀርቡት ሁለት ብቻ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ኢንዱስትሪዎቹ ጦርነቱ ከመቀስቀሱ በፊት ለውጭ ገበያ የሚሆኑ ምርቶችን የሚያመርቱ፣ ለሀገር ውስጥ ፋብሪካዎች የሚቀርቡ ግብአቶችን በማቅረብ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ አበርክቶ የነበራቸው ናቸው ብለዋል፤ አቶ ዳዊት፡፡ ከዚህ ባለፈም ከፍተኛ ፋብሪካዎችን ሳይጨምር በመካከለኛና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ቁጥራቸው ከ10ሺ የሚልቁ ዜጎች ተቀጥረው ይሰሩ ነበር፡፡  በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የኢንዱስትሪ ሰራተኛና ባለሙያ ተበታትኖ ያገኛል ያሉት አቶ ዳዊት፤ በህይወት የሚገኙ ሰራተኞችን ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ አዳዲሶችንም ለማሳተፍ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። በፋብሪካዎች ላይ የደረሰው አጠቃላይ የጉዳት መጠን ምን ያህል ነው ተብለው የተጠየቁት ዳይሬክተሩ፤ሙሉ ለሙሉ ጉዳት የደረሰባቸውና ወደ ስራ የማይመለሱ፣ በከፊል የወደሙና ጥቂት ጉዳት ያስተናገዱ ሲሉ ከፍለዋቸዋል፤ የደረሰባቸውን የገንዘብ ኪሳራ በተመለከተ ገና ጥናት በመከናወን ላይ በመሆኑ በቁጥር ማስቀመጥ አይቻልም ነው ያሉት፡፡ የወደሙ ፋብሪካዎችን ስራ ለማስጀመር በሚደረገው ጥረት ከፌደራል መንግስት የሚደረገው ድጋፍ በቂ የሚባል አይደለም ያለው ቢሮው፤ ተነቅለው የተወሰዱና ውድመት የደረሰባቸውን ማሽነሪዎች ለመተካት የውጭ ምንዛሬና የበጀት እጥረት ፈተና ሆኖብኛል ብሏል፡፡ አቶ ዳዊት፤ ኢንዱስትሪዎች ላይ የሚኖረውን የፋይናንስ ጫና ለማርገብ የሥራ ማስኬጃ ካፒታል ብድሮችን፣ የቀድሞ ብድሮችን የመክፈያ ጊዜ ማራዘምንና የውጭ ምንዛሪ ማኔጅመንት እርምጃዎችን ጨምሮ - የፋይናንስ እገዛ ላይ ከፍተኛ ክፍተት መኖሩን ተናግረዋል፡፡ አቶ ዳዊት አክለውም፤ ባንኮች ኢንዱስትሪዎች ስራ ያልሰሩባቸውን የጦርነት አመታት ጭምር የብድር ወለድ እንዲከፍሉ እየጠየቁ ነው ብለዋል፡፡ ክልሉ ካሳለፈው የግጭት ግዜ አንጻር ፋብሪካዎቹም ከሚያንቀሳቅሱት የሰው ሀይልና ኢኮኖሚ አኳያ፣ በፋይናንስና በውጭ ምንዛሬ ዙርያ ያለባቸውን ችግር ለመቅረፍ መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በዓለም ባንክና በልማት አጋሮች የቴክኒክ ድጋፍ በመታገዝ የትግራይ ክልሉን ጨምሮ በሀገሪቱ ግጭቶች ያደረሷቸውን ውድመቶችና ጥፋቶች እንዲሁም የፈጠሯቸውን ፍላጎቶች በተመለከተ አካታች መረጃ ለመስጠት፣ የጉዳትና የፍላጎት ግምገማ ወይም Damage and Needs Assessment (DaNA) ይፋ አድርጎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የጉዳትና የፍላጎት ዳሰሳ ግምገማው ከፌደራልና ከክልል የመንግስት ተቋማት፣ ከልማት አጋር ድርጅቶች፣ ከሲቪክ ማኅበረሰብ አካላትና ከግሉ ዘርፍ ግጭቶች በተከሰተባቸው ቦታዎች ላይ በመገኘትም ሆነ በርቀት በተገኙ መረጃዎች ላይ የተደረጉ ትንታኔዎችን መሠረት በማድረግ፣ ግጭቶቹ ከኅዳር 2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 2014 ዓ.ም ያደረሷቸውን ጉዳቶች ይተነትናል። ግምገማው በአፋር፣አማራ፣ቤኒሻንጉል ጉሙዝና ትግራይ በኢንዱስትሪ ዘርፍ (በትላልቅና መካከለኛ ደረጃ አምራቾች፣ በጥቃቅንና አነስተኛ አንተርፕራይዞችና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ) 1 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት አጠቃላይ ጉዳት መድረሱን አስቀምጧል፡፡ በፕሪቶርያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት  ሲያደራድሩ ከነበሩ አካላት መካከል አንዱ የሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጎን ኦባሳንጆ፣ ሴማፎር በተባለ አንድ ድረ-ገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ መልሶ ግንባታ ለማከናወን 25 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ማለታቸው ይታወሳል። Via አዲስ አድማስ @Tikfahethiopia
Показати все...
😢 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የዛሬው daily combo 🥂 ያልጀመራችሁ ለመጀመር Hamster combat Daily 5millions combo 👇 https://t.me/hamster_kombaT_bot/start?startapp=kentId5503782284 React and share 🥂
Показати все...
የአማራና የኦሮሚያ ክልሎች በሚዋሰኑበት የሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱባቸውና በርካቶች እየተፈናቀሉ እንደኾነ ነዋሪዎች ለዋዜማ ሪፖርተር ተናግረዋል። በተለይ ሰረርኩላ እና ቱቲን የመሳሰሉ ቀበሌዎች ነዋሪዎች፣ የትምህርትና ጤና አገልግሎቶችን ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል። ነዋሪዎች ጥቃቱን የሚያደርሱባቸው፣ ከአማራ ክልል ተሻግረው የሚመጡ የፋኖ ታጣቂዎች እንደኾኑ ዋዜማ ሰምታለች። ግንቦት 14 ቀን፣ እነዚሁ  “የደራ ማንነት አስመላሽ ኃይል” የሚል ስያሜ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በሰረርኩላ፣ ቱቲ፣ ብርጄ፣ ሰንቀሌ እና አባዶን በተባሉ ቀበሌዎች በተመሳሳይ ሰዓት በፈጸሙት ጥቃት፣ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን የዐይን እማኞች ተናግረዋል። የፋኖ እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎችን አፍኖ በመውሰድ ገንዘብ እንደሚጠይቁም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። @Tikfahethiopia
Показати все...
👍 3 3😢 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ትራምፕ በተከሰሱባቸው 34 ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታሪካዊ በሆነ የክስ ሂደት በጠቅላላ ጥፋተኛ ተብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ከንግድ መዝገቦች ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በቀረቡባቸው 34 ክሶች በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል። በአሜሪካ ታሪክ በሥልጣን ላይ ያለም ይሁን ከሥልጣን የወረደ ፕሬዝዳንት በወንጀል ክስ ጥፋተኛ ሲባል ትራምፕ የመጀመሪያው ናቸው። የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው ትራምፕ ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም. የቅጣት ፍርድ ይተላለፍባቸዋል ተብሏል። ፍርድ ቤቱ ስድስት ሳምንታት በዘለቀው ችሎት ላይ ከ22 ሰዎች ምስክርነትን ሰምቷል። ከእነዚህ መካከል የቀድሞ የልቅ ወሲብ ተዋናይት ስቶርሚ ዳንኤልስ ትገኝበታለች ሲል ሮይተርስ ዘግቧል። @Tikfahethiopia
Показати все...
👍 6
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ቤተክርስቲያኗ የውስጥ ፈተናዎቼ በዝተውብኛል አለች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የውስጥ ፈተናዎቼ በዝተውብኛል ብላለች፡፡ ቤተክርስቲያኗ ይህንን ያለችው ዛሬ በተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ የጉባኤውን መጀመር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እንደተናገሩት በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች ብለዋል፡፡ ቤተክርስቲያኗ የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋልም ብለዋል፡፡ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጎደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ Via EOTC @Tikfahethiopia
Показати все...
👍 3
00:21
Відео недоступнеДивитись в Telegram
We call to our Investors! Just one step: From purchasing NFTs to creating and co-founding the bank of the future: TLVD Trusty Bank! Closed listing by founders from May 9, 2024! Open sale of NFTs on the DeFi marketplace OpenSea begins on June 10, 2024! UNION IS STRENGTH! +372 5837 7377 https://tlvd.uk https://opensea.io/collection/tlvd https://t.me/nftttbank
Показати все...
20240528-42674-crtikx4.49 MB
እስራኤል በራፍህ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላይ በፈፀመችው ጥቃት ቢያንስ 35 ፍልስጥኤማውያን ተገደሉ የእስራኤል ወታደሮች በራፋህ ደህንነቱ  በተጠበቀ ዞን ውስጥ ተፈናቃዮች የሚገኙበትን የድንኳን ካምፕ በቦምብ በመምታት ቢያንስ 35 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የፍልስጥኤም ባለሥልጣናት ገልጸዋል። ከተጎጂዎቹ መካከል አብዛኛዎቸ ሴቶች እና ህጻናት ናቸው። የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ማህበር በድንኳኑ ውስጥ ከነበሩት ሰዎች መካከል ብዙሃኑ "በሕይወት እያሉ ተቃጥለዋል" ሲል አስታውቋል። በተጨማሪም በአካባቢው ያሉ ሆስፒታሎችን ሆን ብሎ የጤና ስርዓቱን በማናጋት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውብ ተጎጂዎች ማስተናገድ አልተቻለም ሲል የቀይ ጨረቃ ማህበር ይፋ አድርጓል። በታል አስ-ሱልጣን አካባቢ ከተፈፀመው ጥቃት በተጨማሪ የእስራኤል ወታደሮች በጃባሊያ፣ ኑሴራት እና ጋዛ ከተማን ጨምሮ በተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን መጠለያዎች ላይ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በፈፀሙት የቦንብ ጥቃት ቢያንስ 160 ሰዎች መገደላቸውንን የፍልስጤም ባለስልጣናት ገልጸዋል። የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ቃል አቀባይ እስራኤል በታላ ሱልጣን ላይ ያደረሰችውን ጥቃት "ከድንበር በላይ የሆነ እልቂት" ሲሉ አውግዘዋል በማለት ዋፋ የዜና ወኪል ዘግቧል። ናቢል አቡ ሩዲነህ “በፍልስጤም ህዝብ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በአፋጣኝ ለማስቆም አስቸኳይ ጣልቃገብነት እንደሚያስፈልግ በመግለፅ  “አስከፊው እልቂት” ለዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት ግልጽ ውሳኔን ጨምሮ ለአለም አቀፍ ትዕዛዝ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል ብሏል። የዓለም የፍትህ ፍርድ ቤት እስራኤል በራፋህ ከተማ የምታደርገውን ወታደራዊ ጥቃት እንድታቆም እና ለፍልስጤም ህዝብ ከለላ እንድትሰጥ አዟል። አቡ ሩዲነህ ለእስራኤል ወንጀሎች የዩናይትድ ስቴርስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን አስተዳደር ተጠያቂ አድርገው ዋሽንግተን "እስራኤል በጋዛ ላይ እየፈፀመች ያለውን እልቂት እና የዘር ማጥፋት እንድታቆም ሊያስገድድ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል ። @Tikfahethiopia
Показати все...
4👍 2
የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገለፀ። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው ይህ የተገለፀው። በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በተሠራው የተቋማት ኦዲት ሪፖርት የ2014 በጀት ዓመት ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጣቸው 24 መሥሪያ ቤቶች ውስጥ 13 ተቋማት ላይ አስተደደራዊ ዕርምጃ መወሰዱን ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ለቋሚ ኮሚቴው ገልጸዋል፡፡ በዚህም የወላይታ ሶዶ፣ ጋምቤላ እና ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉን ተናግረዋል። ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ እና ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መሠጠቱም ተገልጿል። @Tikfahethiopia
Показати все...
👍 8🥰 3 1🔥 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የታሪካዊው አልነጃሺ መስጅድ ጥገና ስራ ከቀናት በሁዋላ ይጀመራል:: የቱሪዝም ሚንስቴር ከቱርክ አምባሳደር በርክ ባራን ጋር ባደረገው ተከታታይ ውይይት የ አልነጃሺን መስጅድ ለመጠገን የቱርክ መንግስት አስፈላጊውን የገንዘብ እና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሷል:: በመሆኑም ደረጃውን የጠበቀ የጥገና ስራ ለማድረግ የሚያስችል ቅድመዝግጅት ተጠናቋል:: በቀጣይ ሳምንትም የጥገና ስራው በይፋ ይጀመራል:: በአፍሪካ የመጀመሪያው መስጅድ እንደሆነ የሚነገርለት የአልነጃሺ መስጅድ የጥገና ስራው ታሪካዊ ይዘቱን ለትውልድ ጠብቆ ማስተላለፍ በሚያስችል መልኩ የሚከናወን ይሆናል:: @Tikfahethiopia
Показати все...
👍 8 1🥰 1
00:00
Відео недоступнеДивитись в Telegram
‼️ በዙሪያዎ እየተከናወኑ ስላሉ ጉዳዮች የራስዎን አስተያየት ይያዙ። ምልከታዎችን አንጭንም፣ እውነት አናዛባም፣ ሃስተኛ ዜናዎችን እናሰራጭም፤ የተሟላና ትክከለኛ መረጃ ብቻ። 🌍 ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም ዙሪያ የተሰሙ ዜናዎች፤ በጉምቱ ተንታኞች የሚቀርቡ ሙያዊ አስተያየቶች እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች። ስፑትኒክ አማርኛ፤ ያልተነገረዎትን መንገር  ጀምሯል! 👉 https://t.me/+8tQ6L6wQ2k8wNTQy
Показати все...
20240522-22890-1lpv9x411.53 MB
👍 5