EECSF
Відкрити в Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
Показати більше508
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
508
ምስል 1 : ከማለዳ ፀሎት መልስ
📸 ወንድሞች በህብረት ቢሆኑ መልካም ነው::
ስለ ጉንጫቸው ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን በሰብሳቢው ወንበር ላይ የተሰየመው ወንድም ዋቄ: በወቅቱ በተክለ ሰውነቱ 💪እና በግርማ ሞገሱ 😜 ወደር ያልተገኘለት ነበር::
Photo credit : Unknown
508
ምስል 3 : ናዝራዊ ባሳ
📸 ዘወትር በአምልኮ የጌታን ፊት እንድንፈልግ እንዲሁም በተሰጠው ግሩም ድምፅ እግዚአብሔርን ያለ ስስት የሚያገለግለው ወንድማችን ናዚ ጌታ ዘመንህን ሁሉ ይባርክ::
ለብዙዎችም መልካም ዐርዓያ በመሆንህ እናመሰግናለን::
Photo credit : unknown
508
ምስል 4 : የ እግር ኳስ ፍልሚያ
📸 ይህ ምስል የተወሰደው በህብረታችን በየዓመቱ ከሚካሄደው የአቋም መፈተሻ(የወዳጅነት ጨዋታ) ላይ ነው::
እንግዲህ ከእነዚህ ውስጥ ማን እንደተሳተፈ ለማወቅ ????????
ወዝ አልባ ግንባር መፈለግ ብቻ ነው
(😂😂😂😂😂😂😂.😂😂😂)
Photo credit : Natan
508
ቃለመጠይቅ 🎤🙍♂
----------------------------------------------------------------
🎤ሙሉ ስም
👤 ቡዙአየው ሠላሙ
🎤ዕድሜ
👤25
🎤 ምን ተማሪ/ተመራቂ?
👤 የconstruction technology and management (COTM) engineering ተመራቂ (2011 EC Graduate)
🎤 ከየት ዩኒቨርስቲ?
👤 አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ(ህንፃ ኮሌጅ)
🎤 በአንተ ጊዜ የነበረውን የፌሎሺፕ(ህብረት) ህይወት እንዴት ትገልፀዋለህ?
👤 ለኔ ፌሎሺፕ አዲስ ነበር
ጊቢ ሳልገባ በተማሪዎች ህብረት አልሳተፈም ነበር ፡ጊቢ በነበረኝ ህብረት በጣም፥ በጣም ደስተኛ ነበርኩኝ::
ከቤተ ክርሰትያን ህብረት በላቀ ፡ግብዝነት የሌለበት ፍቅር፣አንድነት፣መተሳሰብ፣አንዱ የሌላውን ሸክም የመሸከም ነገር ነበር በፌሎሺፕ፤እናም ሁላችንም በክርስቶስ አንድ መሆናችንን ያየውበት ቦታ ነበር ፌሎሽፕ፡:
ገላ 2:28
🎤አገልግሎት የጀመርከው መች ነው?
👤 አገልግሎት የጀመርኩት ሁለተኛ አመት አንደኛ ሴምስተር
🎤ከክርስቲያን ህብረት አገኘሁት የምትለው ጥቅም ምንድር ነው?
👤ጊቢ ውስጥ የነበረኝን እና አሁን ያለኝን መንፈሳዊ ነገር ሁሉ ፣ መፅሐፍ ቅዱስ ማንበብ ፣መጸለይ በህብረት ውስጥ ከነበሩት ወንድሞቼ አና እህቶቼ ነበር የተማርኩት፡ በጌታ ጸጋ ፤ባጠቃላይ ለመንፈሳዊ ህይወቴ እድገት የምያስፈልገኝን ሁሉ ጥቅም አግኝቻለው ከ ህብረት።
🎤 የመጀመሪያ እና የመጨረሻው የአገልግሎት ጊዜህን እንዴት ትገልፀዋለህ?
👤 ቲታ እና ዋቂ በጣም የተወደዱ ወንድሞቼ እነሡ ነበር አገልግሎት ያስጀመሩኝ::
ስጀምር በጣም ፈራ ነበር፣ ትንሽ ስቆይ ግን ፍራቱ ወደ ጥንካሬ ተለወጠ፣ እናም በነበረኝ ጊዜ ሁሉ ጌታን የማገልገል ረሀብ ነበረኝ ፣በመጨረሻ ጊዜ በመጀመሪያ የነበረኝ ቅናት እና ትጋት ትንሽ የቀነሰ ይመስለኛል ሆኖም መጀመሪው እና መጨረሻው ለእኔ ጥሩ ነበር ጌታ ይመስገን።
🎤በአገልግሎትህ ውስጥ ያጋጠመህ challenge ምንድነው?
👤challenge ነበር ብየ ማስባው ፡ የማለዳ ጸሎት ላይ የብዙ ልጆች አለመገኘት (ጌታ ይመስገን ልወጣ አከባቢ ጥሩ ነበር) እና ማክሰኞ ፌሎሺፕ የብዙ ሰው በጊዜ ባለመገኘት የ program late መሆን ለእኔ ትንሽ challenge ነበር
🎤የምትወደው ወይም አርዓያ የሆነህ ሰው?
👤 እወነት ለመናገር ሁሉም ልዩ ነበሩ ለእኔ በህብረቱ የነበሩ፤ አሁንም ያሉት። ስም መጥቀስ ካለብኝ ገና ጊቢ ስገባ ያገኘዋቸው መልካም ሰዎች ፡ ቲታ፡ዋቂ፡ bible study mam( ብሩ እና በጣም የምወደው ወንድሜ አብነት ያቆብ ጥሩ ምሣሌ ነበሩ ለእኔ።
🎤ዩኒቨርሲቲን ከሌላው ህይወት የሚለየው ምንድር ነው?
👤ዩንቨርስቲ ብዙ ወጣ ፡ውረድ ያለበት ፤ከተለያዪ አከባቢ የመጡ እና የተለያየ የሕይወት ፍልስፍና ያላቸው ሰዋች ያሉበት ቦታ ነው።
ካወቅንበት በብዙ አቅጫጫ የምናድግበት እና የምንለወጥበት ሲሆን ከፈለግን ደግሞ የምንጠፋበት ስፍራ ነው።
የዩኒቨርሲቲ ፡ቆይታ በነጌው ህይወታችን ላይ በጎም ሆነ መጥፎ ተፅእኖ ስላለው አስተውለን መልካሙን እንያዝ እላለው ::
🎤የምትወደው የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅስ?
👤ዕንባቆም 3:18 -19
🎤ክርስትና ላንተ ምንድነው?
👤 ክርስትና ለእኔ፡ በእኔ ሕይወት የክርስቶስ መገለጥ፤እኔ ሞቼ ክርስቶስ በእኔ እንዲኖር መፍቀድ።
በአጠቃላይ ክርስትና ክርስቶስን በመምሠል ህይወት፡ በመኖር ፡እግዚአብሔርን ማስደሰት ነው።
🎤የህይወት መርሆችህ ምንድናቸው?
👤 በ ሮሜ 14:28 ጳውሎስ እንደገለጸው ለጌታ ኖሮ ፣ ለጌታ መሞት ፤ በሁሉ ነገር ጌታን ማክበር ነው።
🎤 ለወጣቱ የምትመክረው ካለህ?
👤ወጣትነታችንን፣ዕውቀታችንን ፣ጊዚያችንን፡ ለጌታ መስዋት አድርገን ሰጥተን ለእኛ ክብር እና ደስታ ሣይሆን ለጌታ ክብር ና ደስታ እንኑር፤ በሁሉ ነገር ፡ክርስቶስን በመምሰል እንደግ እላለውኝ ።
🎤 በዩኒቨርስቲ ቆይታህ ገጠመኝ ካለህ?
👤ትዝ የሚለኝ ፡ገጠመኝ አንደኛ እና ሁለተኛ አመት ይመሠለኛል በጣም ቴንሽናም ነበርኩ::
ብዙ project submit ምናደርገው ነበር እና ህመምም ተጨምሮበት ሁለት ጊዜ ራሴን ስቼ ወድቄ ነበር::
ሁለተኛ አመት ላይ "material exam"
ለመፈተን ለሊቱን ሙሉ ሳጠና አድሬ ጥዋት ቁርሴን ሳልበላ exam ገባሁ: ከነበራው ድካም እና ቴንሽን የተነሳ የለበስኩትን ጃኬት "exam room"
ውስጥ ረስቼ ጥየ ወጣሁ::
የሚገርመው ደግሞ ማታ church ለመሄድ ስነሳ ሎከሩ እስኪናጥ ድረስ መበርበሬ ነው :: ዶርም ውስጥ በጣም ነበር የሳቅነው
EIABC እና ቴንሽን የሁል ጊዜ ትውስታዬ ናቸው።
🎤በመጨረሻም
👤በመጨረሻም ይህን እድል ስለሠጣቹኝ አመሠግናለው፡
የጌታ ጸጋ እና ሠላም ይብዛላቹ ፡እወዳቹዋለው ተባረኩ!!!
-------------------------------------------------------------
🙏እናመሰግናለን🙏
