EECSF
Відкрити в Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
Показати більше508
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
508
Isaiah 41:10
10 So do not fear,for I am with you; do not be dismayed, for I am your God.
I will strengthen you and help you.
I will uphold you with my righteous right hand.
508
ራእይ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ እነሆ፥ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።
¹² ድል የነሣው በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፥ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።
508
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 121)
----------
1፤ ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ?
2፤ ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
3፤ እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም።
4፤ እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም።
5፤ እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል።
6፤ ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት።
7፤ እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል።
8፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል።
508
ሰላም 👋 እንዴት ናችሁ?
የማክሰኞ የሕብረት ጊዜያችን በተለመደው ሰዓት
እንደሚቀጥል ልናሳስባችሁ እንወዳለን።
ስለዚህ በጊዜ በመገኘት አብረን ወደ ጌታ ፊት እንቅረብ። ተባረኩ!😊
508
በጌታ የተወደዳችሁ!! ሠላም! ዛሬ (ሮቡዕ) በሻካሂና ቤተ/ክርስቲያን fresh welcome! ስላለ ሁላችሁም በጊዜ 11:30 እድትገኙ በጌታ ፍቅር አሳስባችኋለው!
508
Tuesday, January 12
👇
•Restoration/ ተሀድሶ
( pastor Daniel )
👆
📝 2ኛ ዜና 29 : 3-11
📌 ህዝቅያስ ቤተመቅደሱን አፀዳ
ህዝቅያስ በ አባቱ አካዝ መንገድ አልሄደም::
አካዝ:
📌 የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃዎች ሁሉ ሰባበራቸው::
📌 የእግዚአብሔርንም ቤት ደጅ ቈለፈ::
📌 በኢየሩሳሌምም ማዕዘን ሁሉ መሠዊያ ሠራ።
📌 ለበኣሊም ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችን ሠራ።
📌 በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ዐጠነ::
📌 እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳሳደዳቸው እንደ አሕዛብም ክፉ ልማድ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ።
📌 በተጨነቀ ጊዜ እግዚአብሔርን መበደል አበዛ።
ህዝቅያስ:
📌 የእግዚአብሔርን ቤት ደጆች ከፈተ፥ አደሳቸውም።
📌 ካህናቱንና ሌዋውያኑንም አስመጣ::
📌 ይቀደሱም ዘንድ ሌዋውያንን አዘዘ
📌 ርኩሱን ነገር ሁሉ ከመቅደሱ አስወገደ።
📌 ከእግዚአብሔር ጋር ቃልኪዳን አደረገ::
📌 ቤተመቅደሱ እንደገና ለእግዚአብሔር የተለየ ሆነ::
4 key points
• observation/ ህዝቅያስ ያለበትን ሁኔታ በሚገባ ተረድቶታል::
• የጥያቄው መልስ እራሱ እግዚአብሔር መሆኑን አምኗል::
• ለስራው የሚሆኑ ተገቢ ሰዎችን በተገቢ ቦታ አስቀምጧል::
• ለእግዚአብሔር ይሰዋ ነበር
( የአምልኮ ህይወት)
508
=========================
Tuesday?🤔....Yea It's Tuesday😱
📖 Restoration to God
👤 pastor Daniel
Jan 12, 2021
⏱ 11:30 - 1:30 LT
@ Assembly of God church
EECSF
=========================508
"ሕፃን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።"
ኢሳይያስ 9:6
508
ሰላም ቅዱሳን🤗....ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ማክሰኞ ዕለት(በቀን 27) የመጀመሪያውን የ2013 የሕብረት ጊዜያችንን በጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን (ልደታ አጥቢያ) እናደርጋለን። ፀሎት፣ ዝማሬና የቃል ጊዜ ስለሚኖረን ራሳችንን አዘጋጅተን እንምጣ። የሕብረት ጊዜያችን 11:30 ላይ ይጀምራል።
