EECSF
Відкрити в Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
Показати більше508
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
508
ዳንኤል 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ ዳንኤልም ተናገረ እንዲህም አለ፦ ጥበብና ኃይል ለእርሱ ነውና የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይባረክ፤
²¹ ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን ያፈልሳል፥ ነገሥታትንም ያስነሣል፤ ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል።
508
2ኛ ተሰሎንቄ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ እኛ ግን፥ በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፥ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና፤
¹⁴ ለዚህም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር ለማግኘት በወንጌላችን ጠራችሁ።
¹⁵ እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ።
¹⁶-¹⁷ ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን ልባችሁን ያጽናኑት በበጎም ሥራና በቃል ሁሉ ያጽኑአችሁ።
♨️♨️♨️ ጳጉሜን 4♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️
508
ኖረ ኖረ እና ብዙ ዘመን ሞተ፣
በምድር ህይወት ላይ እንዲሁ ዋተተ፣
ቀባሪ እንዳጣ ሰው፣
ገናዥ የሌለው ሰው፣
ከእንቅልፉ ሳይነቃ ጊዜውን ጨረሰው።
መኝታው ላይ ሆኖ ዘመናት አልፈዋል ፣
ያያቸው ህልሞቹ በቁሙ ከስመዋል፣
እሱም ተንተርሶ ሗላ በቁም ሳይሞት፣
ንቃ በለው ጎበዝ ጊዜው ሳያልፍበት።
❤️❤️❤️❤️ እግዚአብሔር ይርዳን!!
ሮሜ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።
¹² ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።
♨️♨️♨️ ጳጉሜን 3♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️
508
ፊልጵስዩስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።
⁷ አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
♨️♨️♨️♨️ ጳጉሜን 2♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️
508
ጊዜ ጊዜን ተካ እልፍ ጊዜያት አለፉ፣
አመታት ትሻግረው ወራት አሰለፉ።
ወራትም ቀናትን አጀብ አሰኝተው፣
በሰአታት ጀማ ደቂቃ አስቆጥረው፣
ሰከንድ ማይክሮ ሰከንድ ከሚሊ እስከ ናኖ፣
በውስጣቸው ሲታይ የሚታየው ገኖ፣
የእግዚአብሔር ምህረት ነው የእግዚአብሔር ጥበቃ በላያቸው ሆኖ።
❤️❤️❤️❤️❤️
❤️❤️❤️❤️❤️
ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና።
— ሰቆ. 3፥22
♨️♨️♨️ጳጉሜን 1♨️♨️♨️♨️
♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️♨️
508
I wanna say congratulation🎉 to Sami,Debo,Keri,Mercy,Kali,Bety,Misikir,Dave,Yara,Masse,Efi and Simon. Am Pleased to see you guys succeed; praise be to God! A head another blessing is coming! Congratulations Again!
508
🎇 CONGRATULATIONS
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
🎈 🎈 🎈 🎈 🎈 🎈
ለተወደዳችሁ የEiABC fellowship ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን እግዚአብሄር ረዳችሁ ማለት እንወዳለን ። ላለፉት ዓመታት የዘራችሁትን እንዲሁም የለፋችሁበትን የምታጭዱበት በቀጣይ ላሉት አመታት ደግሞ ስንቅ ለምትሰንቁብት ለዚች የተወደደች ቀን እንኳን እግዚአብሔር በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።👏👏👏👏👏🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
💢“እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።”
— መዝሙር 118፥24
508
📌 የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን ፕሮግራማችን ይህን ይመስል ነበር!
🤗 Lidu, Jire እና Dagi ጸጋ ይብዛላችሁ! 🙌
ፕሮግራማችን ሳምንትም ይቀጥላል። ☺️
መልካም ምሽት! 🤗
508
📖 ዮሐንስ 14 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ “ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ።
² በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ ይህ ባይሆንማ ኖሮ እነግራችሁ ነበር፤ የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው።
³ ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም ከእኔ ጋር እንድትሆኑ ልወስዳችሁ ዳግመኛ እመጣለሁ።
⁴ እኔ ወደምሄድበትም ስፍራ የሚያደርሰውን መንገድ ታውቃላችሁ።”
508
📌 በመቀጠል ከተወደደ ወንድማችን ከ Dagi ጋር አብረን የእግዚአብሔርን ቃል የምንካፈልበት ጊዜ ይሆናል! 📖
ሁላችንም መጽሐፍ ቅዱሶቻችንን ከፍተን ቃሉን እየተካፈልን አብረን እንቆያለን!
🙌 ተባረኩ!
508
📖 ኢሳይያስ 38
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ሂድ፥ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ በዕድሜህ ላይ አሥራ አምስት ዓመት አጨምራለሁ።
⁶ አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፥ ይህችንም ከተማ እጋርዳታለሁ።
⁷ እግዚአብሔርም የተገረውን ነገር እንዲፈጽመው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክቱ ይህ ይሆንልሃል።
⁸ እነሆ፥ በአካዝ የጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ ከፀሐይ ጋር የወረደውን በደረጃዎች ያለውን ጥላ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ። ፀሐይም በጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ የወረደበት አሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ።
