uk
Feedback
EECSF

EECSF

Відкрити в Telegram

ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::

Показати більше
508
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
photo content

photo content

የሁለተኛ ዙር አሸናፊዎች....

ምስል 1: ውጫሌ ትሪቲ 📸 ወዳጄ በ ዘመናት መካከል ብዙ የ ጦር ግንባሮች ተሰልፈህ አሊያም ተዋግተህ ሊሆን ይችላል:: እመነኝ ግን ለቀጠናው ሰላም የእነዚህ መሪዎች ስምምነት እና የደጋፊዎቻቸው ጩኸ
ምስል 1: ውጫሌ ትሪቲ 📸 ወዳጄ በ ዘመናት መካከል ብዙ የ ጦር ግንባሮች ተሰልፈህ አሊያም ተዋግተህ ሊሆን ይችላል:: እመነኝ ግን ለቀጠናው ሰላም የእነዚህ መሪዎች ስምምነት እና የደጋፊዎቻቸው ጩኸት ለ ሁለትዮሽ ግንኙነት ያለው ሚና ይሄ ነው የማይባል ነው 💣 Photo credit : Aman

ምስል 2፡ ሊዲያ(ኪኮ) 📸 ይህ ምስል የተወሰደው በህብረታችን ከምናደርገው አመታዊ የፌሎሺፕ ትሪፕ ላይ ነው። ይህን ምስል ለየት የሚያደርገው የእህታችን ኪኮ ልደት ከ #trip ጋ መገጣጠሙ ነው::
ምስል 2፡ ሊዲያ(ኪኮ) 📸 ይህ ምስል የተወሰደው በህብረታችን ከምናደርገው አመታዊ የፌሎሺፕ ትሪፕ ላይ ነው። ይህን ምስል ለየት የሚያደርገው የእህታችን ኪኮ ልደት ከ #trip ጋ መገጣጠሙ ነው:: እንግዲህ ንጉስ ለሚወደው እንዲህ ይደረግለታል እንዲሉ በወቅቱ የተዘጋጀውን ኬክ በመቋደስ ልዩ ጊዜ አሳልፈናል:: ሊዱ ስለ እውነተኛ አገልግሎትሽ እና ስላሳየሽን ፍቅር ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው:: Photo credit : Josh /Milky

ምስል 3፡ Aman,leul And Ab 📸 እኚህ ዘወትር ማክሰኞ ጥዑም ዜማ ለማቅረብ የሚታትሩ ድንቅ ሙዚቀኞቻችንን ናቸው:: እኛም ለ እነሱ ያለንን ልዩ ፍቅር እና አክብሮት እንገልፃለን:: እጃቹ ይ
ምስል 3፡ Aman,leul And Ab 📸 እኚህ ዘወትር ማክሰኞ ጥዑም ዜማ ለማቅረብ የሚታትሩ ድንቅ ሙዚቀኞቻችንን ናቸው:: እኛም ለ እነሱ ያለንን ልዩ ፍቅር እና አክብሮት እንገልፃለን:: እጃቹ ይባረክ ብለናል Photo credit : unknown

ምስል 4 ፡ ኡዝያን ቦልት 📸 ወገን ምን እንደሚታያችሁ አላውቅም??? - ቆመህ ጠብቀኝ መሳሪያ የያዘ ወታደር ወይስ - ኢላማ መር የተሰኝ መጽሐፉ ያነበበ አንድ ወጣት እኔ ግን በዚህ ሁሉ ወጀብ መካ
ምስል 4 ፡ ኡዝያን ቦልት 📸 ወገን ምን እንደሚታያችሁ አላውቅም??? - ቆመህ ጠብቀኝ መሳሪያ የያዘ ወታደር ወይስ - ኢላማ መር የተሰኝ መጽሐፉ ያነበበ አንድ ወጣት እኔ ግን በዚህ ሁሉ ወጀብ መካከል አንድ ነገር ይታየኛል እሱም ከጀርባቸው ያለው ሐይቅ ነው Photo credit : Josh /Milky

በቀጣይ የቀድሞ ፎቶዎችን እያስታወስን እንመለከታለን

አጥጋቢ መልስ እስክናገኝ እንቀጥላለን::

ጥያቄ #3 🤸‍♀️💰💣🏃‍♂

ጥያቄ 3🤔⁉️ ( 100 Mb & 20 sms) መልሶን እዚህ ይላኩ: @Caleb_24 @Caleb_24 @Caleb_24

ለምሳሌ: 👑😱🏃‍♂ 1,ንጉሱ በድንጋጤ ሮጠ or 2,ዛሬ ፈሪ ብትሆንም በ ሂደት አሸናፊ መሆንህ አይቀርም 😂😂 ተዘጋጅ...... ምርጥ ሁለት መልሶች ይሸለማሉ

በመቀጠል "emoji” ተመልክተን አዝናኝ ትርጉም እንሰጣለን🙆 1, "emoji “ ውን በደንብ መመልከት 2, ከዚያም አንድ ወጥ ታሪክ መስጠት 3, በመጨረሻም ምርጥ አስቂኝ አረፍተ ነገር በ መመስረት ውድድሩን ማሸነፍ 👇👇👇👇 @Caleb_24

👇 አሁን ❓❓ የጥያቄ ጊዜ ❔❔ ነው 👆 ተዘጋጅ 👑 መልካም ሰኞ ሾው👑 —EECSF—

የዛሬው ጥያቄ ልዩ የሚያደርገው በየዙሩ ሁለት አሸናፊዎችን መሸለሙ ነው:: 100 mb and 20 sms......

Don’t forget “ Jesus loves you!!!”

በዚህ #የህይወት ምስክርነት እንደተባረካችሁ ተስፍ እናደርጋለን

#. መልካም እንግዳ #. ግንቦት 3-2012 ቃለመጠይቅ: ከ አርኪቴክት ብሩክይሁን ጋር 🎤 ---------------------------------- ------------------------------ 🎤ሙሉ ስም 👤 ብሩክይሁን ሽጉጤ 🎤ዕድሜ 👤 ፳፯ 🎤 ምን ተማሪ/ተመራቂ? 👤አርክቴክቸር እና አርክቴክቸራል ኢንጂነሪግ 🎤 በአንተ ጊዜ የነበረውን የፌሎሺፕ(ህብረት) ህይወት እንዴት ትገልፀዋለህ? 👤 በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን። ሮሜ 12:4-6 እንደሚል ቃሉ መያያዝ፡ መተባበር፡ ፍቅር፡ አንድነት፡ መተናነፅ፡ የነበረው ህብረት እንደነበር ትዝ ይለኛል ግን…ግን.. “እርስ በእርስ እና በግል በውስጡ የበረታ ህብረት ቢሆንም ለሌላው ብርሃን የሆነ ህብረት ነበር ወይ?” የሚል ጥያቄ ነበረኝ:: 🎤አገልግሎት የጀመርከው መች ነው? 👤 ሁለተኛ ዓመት መሰለኝ ስለቆየ ዘነጋውት፡ አብዛኛውን በእኛው ባች ህብረት ላይ እና Academic ህብርት 🎤ከክርስቲያን ህብረት አገኘሁት የምትለው ጥቅም ምንድር ነው? 👤 የክርስቲያን ህብረት በዋናነት ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድነቃቃ: እንድተያይ; እርስ በርሳችንም እንድንመካከር በደንብ ጠቅሞናል፡ ዕብ 10:24-25 በዋናነትም በህብረት በክርስቶስ አንድ አካል ሆነን በአንድነት ጌታን እንድናሳይ ሮሜ 12: 4-6 እና በአንድነት እንድንበረታ ጠቅሞናል ማቴ 18:19-20; በዚህ ሁሉ ውስጥ በክርስትና ህይወቴ ለማደግ ትልቅ አስተዋፆ ነበረው 1 ቆሮ 14፡26 🎤 የመጀመሪያ እና የመጨረሻው የአገልግሎት ጊዜህን እንዴት ትገልፀዋለህ? 👤የመጀመሪያ አገልግሎት ጊዜ ያው የጊቢው ትምህርት ሁኔታ፡ በደንብ ያልተለመደ አከባቢ፡በደንብ ያልተግባባዋቸው ተማሪዎች፡ ከራሴም ሁኔታ ጋር ተደማምረው ትንሽ ከበድ ቢልም ቶሎ ለመልመድ አልከበደኝም ነገር ግን መጨረሻ አከባቢ ጊቢ ውስጥ ከነበረኝ የስራ ጫና የተነሳ እንዳሰብኩት እንዳልጨረስኩ ትዝ ይለኛል፡፡ በአጠቃላይ ግን “ብቅ ጥልቅ እያልክ ጨርሰክ ወጣክ” ያለኝ የአንድ ወንድም አስተያየት በደንብ ሚገልፀኝ መሰለኝ 🎤በአገልግሎትህ ውስጥ ያጋጠመህ challenge ምንድነው? 👤 አገልግሎት ሲባል ያው በchallenge የተሞላ ነው ግን ይሄን ያህል በጣም ከባድ ነው ብዬ የማወራው የለኝም ሲገጥመንም ሮሜ 8፡ 35-39 እንደሚል ፍቅሩን ስናስብ እንበረታለን፡ ግን ከመሪዎች ጋር ፌሎ ላይ ስንወያይ sound system: በፕሮግራም ሰዓት የተማሪው ማርፈድ፡ መቅረት: መጥፋት: ገንዘብ.. ዋና ሚባሉ እንደነበሩ አስታውሳለሁ:: 🎤የምትወደው ወይም አርዓያ የሆነህ ሰው 👤 ይስሐቅ ዘውገ እና ቲታ (ተመስገን ኤልያስ) ለእኔ ልዩ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ከህይወት ልምዳቸው እሰከ ቀን በቀን ማለት ሁሌም ባላቸው ህይወት ክርስቶስን በእነርሱ በደንብ አይቻለው፡፡ ጳውሎስ በፊል 3፡17 “ወንድሞች ሆይ፥ እኔን የምትመስሉ ሁኑ፥ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ፥ እንዲሁ የሚመላለሱትን ተመልከቱ።” እንደሚል የክርስቶስ ምሳሌ የሆኑኝ ወንድሞች ናቸው:: ሚገርመው ነገር ግን ሁሌም አጠገቤ ስላሉ ዛሬ ነገ እያልኩ ነግርያቸው አላውቅም፡፡😊 🎤ዩኒቨርሲቲን ከሌላው ህይወት የሚለየው ምንድር ነው? 👤 ለመጀመሪያ ጊዜ ለአብዛኞቻችን የሙሉ ቀንናችን / የ24 ሰዓት ጌቶች ሆነን (ከቤተሰብ/ ታላቅ ቁጥር ወተን) ህይወታችንን ምንመራበት፤ እንዲሁም ለብዙ ነገር ከብዙ አቅጣጫ አዲስ ሆነን (በእኛ ጊዜ😊) ምንጀምርበት ቦታ ነው፡፡ እግዚአብሔር በግላችን በተግባር ብዙ ነገር ከብዙ አቅጣጫ ሚያስተምረን ስፍራ ነው፡፡ በዛዉ መጠን ለክፋትም በደንብ ምንጋለጥበትም ነው። ከሁሉ በላይ እግዚአብሔርን ፈርተን መኖር ያለብን ስፍራ ነዉ። 🎤የምትወደው የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅስ 👤“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።” — ኢሳይያስ 40፥31 🎤ክርስትና ላንተ ምንድነው? 👤 እውነትን(ክርስቶስን) መኖር 🎤የህይወት መርሆችህ ምንድናቸው? 👤 ከክርስቶስ ህይወት ውጪ ምንም ሊያስተምረኝ፡ ሊመክረኝ፡ ሊገፅፀኝ፡ ሊመራኝ እና ሊቀርፀኝ አይችልም፡፡ ማደጌም ክርስቶስን በመምስል ውስጥ እና በመኖር ብቻ ነው፡፡ 🎤 ለወጣቱ የምትመክረው ካለህ 👤 ራዕይ ይኑረን (ያው ለራሴም ጭምር ነው)፡ ምንም ከባድ ነገር ቢገጥመን ራዕያችን ላይ ትኩረት እናድርግ፤ ኃይልን በሚሰጠን በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ፤እንወጠዋለን፡፡ challengeኦችን ለመልካም አጋጣሚዎች እንጠቀማቸው እንጂ እምነታችን አይዛል፡፡ በዋናነት በዐይናች እና ጆሮችን የሚገቡ ነገሮች ላይ እንጠንቀቅ፤ ዐይን እና ጆሮ ለምድራዊው ኑሮ(እንቅስቃሴ) ቢጠቅሙንም መንፈሳዊ ህይወትን በጣም ይጎዳሉ፡፡ በመጨረሻም We occasionally need to shed off old habits & items that burden us without adding to our lives. 🎤 በዩኒቨርስቲ ቆይታህ ገጠመኝ ካለህ 👤 እ እ እ የሚያስቅ ገጠመኝ የለኝም ይቅርታ🙏🙏…፤ ሚያሳዝን እንጂ፤…… የመጨረሻ መመረቂያ ፁፍ ልናቀርብ 15 -20 ቀን ሲቀረን Laptopአችን ተሰረቀ፤ የእኔ እና ይሳቅ፤ ጌታ ግን ረዳን በድል አሻገርን፡፡ 🎤በመጨረሻም 👤 እድሉን ካገኝው አይቀር ይቅርታ መጠየቅ ፈልጋለው፡፡ ለክርስቶስ መስቀል ጠላት ሆኜ የተመላለስኩበት ጊዜ ፡ ምሳሌ ባልሆንኩበት ሁሉ ያሳዘንኩዋቹ ፡ ያሰናከልኩዋቹ፡ ሁላቹንም ይቅርታ ማለት ፈልጋለው፡፡ በእኔም ሆነ አብረውኝ በነበሩ ወንድም እና እህቶች (ከአንዳንዶቻቹ ጋር ስናወራ ስለእነሱም ስሞታ ያቀረባቹ ስለነበራችሁ) የተስናከላቹ ይቅር በሉን፡፡ በመጨረሻም ንፁ/መልካም አስተሳሰብ ይኑረን፡ እግዚአብሔርን እንታመን፡ ክርስቶስን እንምሰል፤ እንኑረው …… ያው እስካውን ባብራራውት/በመለስኩት ግድፈት አይጠፋውምና በቅንነት እንድትረዱኝ እጠይቃለሁ…ተባረኩ፡፡ አናቴማ 1ኛ ቆሮ 16፡22 ------------------------------------------------------------- 🙏እናመሰግናለን🙏

🎙 መልካም እንግዳ የዛሬው እንግዳችን አርኪቴክት ብሩክይሁን ሽጉጤ ነው። የህይወት ልምዱን አካፍሎናል በጥሞና ተከታተሉ👇👇👇👇👇 @EECSF @EECSF
🎙 መልካም እንግዳ የዛሬው እንግዳችን አርኪቴክት ብሩክይሁን ሽጉጤ ነው። የህይወት ልምዱን አካፍሎናል በጥሞና ተከታተሉ👇👇👇👇👇 @EECSF @EECSF

አሁን የሳምንቱ #መልካም እንግዳ....