EECSF
Відкрити в Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
Показати більше508
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
508
🎤ክርስትና ላንተ ምንድነው?
👤 - ክርስትና ማንነት ነው፡፡ አንድ ክርስትያን በኢየሱስ ካመነ በኋላ የሚያገኘው ማንነቱ ነው፡፡ ማንነቱን ይኖረዋል፤ ማንነቱን ያጋራዋል፤ ማንነቱን ጠብቆ ይሞታል፡፡ ሰው በማንነቱ አይደራደርም በህይወቱም እንደዚያው፤ ክርስትና ማንነታችን ሲሆን የማንደራደረው ለዛ ነው፡፡ በመውደቅ መነሳት ውስጥ ሁሉ ይህንን ማንነት ከእኛ እንዳይጠፋ ነው ሁሌ የእግዚአብሔርን ምህረት የምንጠይቀው፡፡ ክርስትናን እኔ እንደዚህ አድርጌ ነው የምረዳው፡፡
🎤የህይወት መርሆችህ ምንድናቸው?
👤- Hahaha… መርህ አልከው? በዋናነት የማምነው የትኛውንም ነገር ስሰራ እግዚአብሔርን ያስደስተዋል ወይ እያልኩኝ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚደሰትበት ነገር ሁሌም ትክክል ነው፡፡ መንፈሳዊ ነገርም ላድርግ፤ በስራም ሆነ በእለት ተእለት ኑሮዬ ያንን ነው ቀድሜ ምጠይቀው፡፡ በሐጥያት መቅደቅም እንኳን ቢያጋጥመኝ እግዚአብሔር አሁን ምን ባደርግ ነው እሺ ደስ የሚለው የሚለውን እጠይቃለሁ፡፡ መርህ ካልነው እንግዲህ ይህ ነው የኔ መርህ፡፡
🎤 ለወጣቱ የምትመክረው ካለህ
👤- ምክር ላይ አባት የሆኑ መሪዎች ስላሉ እነሱ ቢመክሩ ይሻል ነበር በርግጥ፡፡ አብዛኛውን ምክሬን ከላይ ባሉት ሀሳቦች ስለገለጽኩ አንድ የምጨምረው ነገር ቢኖር የግቢ ቆይታችሁን እናንተም እንደምትደሰቱበት እግዚአብሔርም እንደሚደሰትበት አድርጋችሁ አሳልፉት፡፡
🎤 በዩኒቨርስቲ ቆይታህ ገጠመኝ ካለህ
👤- አንድ የማስታውሰውን ገጠመኝ እንኳን ከዚህ በፊት አጫውቻቹሀለሁ፡፡ ነገር ግን ሁሌም እነግራቹሀለሁ ብዬ የምረሳው ነገር ቢኖር መነጽር ሳላደርግ በቀረሁባቸው አንዳንድ ቀናቶች ያላወኳችሁ ልጆች እና ሰላም ሳልል ያለፍኳችሁ እንዲሁም ማንነቴን ሳትለዩ ያለፋችሁኝ ሁሉ ይቅርታ እንድታደርጉልኝ በመነጽሬ ስም እጠይቃለሁ፡፡ ሳታውቁ ሰላም ያላላችሁኝም እኔም ያኔ አይቼ ስላላወኳችሁ ችግር የለውም፡፡
🎤በመጨረሻም
👤- ሁሉን የሚያደርግ እግዚአብሔር ይመስገን እንዲሁም በየትኛውም ሁኔታ የተጀመረው ነገር መጨረሱ አይቀርም እና ከጊዜው አንጻር የሚፈጠረው መስተጓጎል ነገር ሁሉ በጊዜው ሊሆን ስለሆነ በዚህ ሁሉ እግዚአብሔር መንገድ አለው፤ ጊዜውም የእርሱ ነው፡፡ እንዲሁም ይህንን ቃለ-መጠይቅ ያዘጋጁትን የአሁን መሪዎች ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ አንተን አማንን ጨምሮ ማለት ነው፡፡ ሁላችሁም ደግሞ ናፍቃችሁኛል እወዳችኋለሁ፡፡
—---------------------------------------------------------—
🙏እናመሰግናለን🙏
508
ቃለመጠይቅ ከበረከት ጋር 🎤🙍♂️
—------------------------------------------------------------—
🎤ሙሉ ስም
👤- በረከት ፍሬው ዝና እባላለሁ፡፡ ወላጆቼ እንደነገሩኝ ሙሉ ስሜ እንደዚህ ነው፡፡
🎤ዕድሜ
👤- እድሜዬ 23 ነው ፣ ያው እንደጌታ ፍቃድ ከ 50 ቀን በኋላ 24 ይሞላኛል፡፡
🎤 ምን ተማሪ/ተመራቂ?
👤- ከግቢ ተመርቄ የወጣሁት አምና በ2011 ነበር፡፡ እስከዛ ድረስ ግን ለ 5 ዓመታት በ Architecture ግቢ ውስጥ ቆይቻለሁ፡፡ ስለዚህ በዚሁ ትምህርት ነው የተመረኩት ማለት ነው፡፡
🎤 በአንተ ጊዜ የነበረውን የፌሎሺፕ(ህብረት) ህይወት እንዴት ትገልፀዋለህ?
👤- በእኔ ጊዜ የ Fellow ህይወት ደስ የሚል ነበር፡፡ ክ አዲስ ገቢነቴ (Fresh Man) ጀምሮ የኛ ቀደምቶች (Seniors) አቀባበላቸው ፀዴ ነበር፡፡ እኛ ስንገባ ብዙ ስለነበርን ቀደምቶቻችን ዘንድሮ ህብረቱ ሰፋ እያሉ ሲደሰቱ ነበር፡፡ በግምት ሶስቱንም የትምህርት መስኮች(Fields) ጨምሮ ወደ 25 እስከ 30 አካባቢ እንጠጋ ነበር፡፡ በጊዜው መሪ የነበሩት እነ ዋቂ፣ ዞላ፣ ሳሚ ሚባሉ ነበሩ፡፡ አብዛኞቻቹ አልደረሳቹባቸውም ብዬ አስባለሁ፡፡ እነሱ ይከታተሉን ነበር፡፡ ሁሉም የራሳቸው የሆነ ችሎታ ነበራቸው፡፡ ዋቂ ሲቆጣ እና በዛውም Serious ሲሆን ሚችለው አልነበረም፡፡ ዞላ እያሳሳቀ ነበር አናት አናታችንን የሚለን፤ ሳሚ ደግሞ እንደ ጓደኛ በመቅረብም ሆነ አብሮ በመጫወት ነበር የማውቀው፡፡ በኋላም እንደ ይሴ (ይስሀቅ)፣ረዱ እና ጆሽ አይነት መሪዎች መጡ፡፡ እኔ በህብረቱ የበለጠ መጠጋ የጀመርኩት ክ 2nd Year ጀምሮ ነበር፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እንደምናየው መጀመርያ ላይ የገባው ተማሪ ሁሉ በቀረው አመት ሁሉ ከህብረቱ ጋር አብ ይዘልቃል ማለት አይደለም፡፡ ልክ እንደዚያው እኔም መጀመርያ አመት ላይ ብዙም አልነበርኩም፡፡ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ እያለሁ ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ነበር መቅረብ የጀመርኩት፡፡ ፕሮግራማችን እንደተለመደው ማክሰኞ ሲካሄድ ከ Design እና Building እንደወጣ ተማሪ መቀመጥ ሁሉ ያቅተኝ ነበር፡፡ እንደውም አንዳንዴ ጉባዬ መሃል ተቀምጬ መድረክ ላይ የማየው ሰባኪውን ሳይሆን የ Design Course Model Project ነበር፡፡ ግን እንደዚህም ሆኖ ከ ፕሮግራም ግን አልቀርም ነበር፡፡ በአጠቃላይ ህብረቱ ማለት ከግቢው አስጨናቂ አየር አረፍ ምንልበት፤ ደስ የሚሉ ጓደኞቻችንን ምናገኝበት እና አብረን ጌታን ምናከብርበት ነበር፡፡
🎤አገልግሎት የጀመርከው መች ነው?
👤- አገልግሎት የጀመርኩት 3rd Year ሩብ ዓመት አካባቢ ነበር፡፡ ከመሪዎች መካከል ነበር አንድ ሰው ቀርቦ ያዋራኝ ከዛም ያለፈው ህይወቴ እንዴት እንደሆነ፣ የቤተ ክርስትያን እድገቴን ሁሉ ጠይቆ ካወቀ በኋላ መሪዎች አንድ ላይ ተሰብስበው ነበር ያናገሩኝ፡፡ እኔም ሸክሙን ለመቀበል ብዙም አላንገራገርኩም፡፡ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ለ 2 ዓመታት ያህል በመሪነት አገልግያለሁ፡፡
🎤ከክርስቲያን ህብረት አገኘሁት የምትለው ጥቅም ምንድር ነው?
👤- ከክርስትና ህብረት ዋናው አገኘሁት የምለው ጥቅም ወንድም እና እህቶችን ነው፡፡ በተለይ 2ኛ ዓመት መጀመርያ አካባቢ መራቅ ጀም ነበር፡፡ ነገር ግን የህብረቱ አባላት አብረው ከዶርም እየጠሩኝ፤ ግቢ ውስጥም ሲያገኙኝ እንዴት ነህ ብለው መጠየቃቸው ራሱ በጣም የሚያበረታ ነገር ነበር፡፡ አንድ ሰው በግሉ የቱንም ያህል መንፈሳዊ እድገት ቢኖረው ነገር ግን ህብረት ውስጥ ብቻ የሚገኝ ግን ጥቅም እና በረከት ግን አለ፡፡ ለዛም ነው መዝ 133 ላይ ስለ ህብረት በእግዚአብሔር ፊት ስላለው ውበት እና በሰውም ፊት ስላለው ሞገስ የተጻፈው… እኔም ያንን ውበት እና ፍቅር ነው በዚሁ ህብረት ያገኘሁት፡፡
🎤 የመጀመሪያ እና የመጨረሻው የአገልግሎት ጊዜህን እንዴት ትገልፀዋለህ?
👤- የመጀመርያው የአገልግሎት ጊዜዬ ትንሽ ከባህሪዬም አንጻር ከብዶኝ ነበር፡፡ ሰውን መግባባት የሚጠይቀው የመሪነት ቦታ ለኔ ከባድ ነበር፡፡ ቀድሞ እንደ አንድ ክርስትያን ግቢ ውስጥ አግኝቼ ሰላም ምለውን ሰው ኋላ መሪ ከሆንኩ በኋላ ሰላምታ ራሱ እንዴት እንደሆነ ጠፍቶብኝ ያውቃል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲራዳ እና ጸጋውን ሲሰጥ አብሮም የሚጨምረው ችሎታ ስላለ ቀስ በቀስ ተላመድኩት፡፡ የመጀመርያው የአፈልግሎት ጊዜ ላይ ከኔ ሚጠበቀውን ነገር ብቻ በቻልኩት መጠን ለማድረግ ነበር የምጥረው ነገር ግን በመሪነት በገፋሁበት ወቅት እግዚአብሔር ከህብረቱ በመሪነቴ በኩል ሊጠቀም የሚፈልገውን ነገር ማየት ጀመርኩ፡፡ መሪነት የብስለትም ጉዳይ መሆኑን ያየሁበት ጊዜም ነበር፡፡
🎤በአገልግሎትህ ውስጥ ያጋጠመህ challenge ምንድነው?
👤- ያጋጠመኝ አስቸጋሪ ጊዜ ብዬ የማስበው 4ኛ ዓመት እያለሁ በመሪነት 1 ዓመት ያህል ካገለገልኩ በኋላ ያጋጠመኝ ጊዜ ነበር፡፡ በጊዜው ከአቅም በላይ በሆኑ ችግሮች አብረውን የነበሩ መሪዎች ባለመኖራቸው ለ 2 ወራት ያክል እኔ እና አማን ብቻ ለመሆን ተገደን ነበር፡፡ በተጨማሪም እኔ ደግሞ Internship ላይ ስለነበርኩ እንደሚፈለገው መንቀሳቀስ ተቸግሬ ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ሁሌም አማራጭ ስለነበረው መሪ ሳይሆኑ እንደ መሪ የሚያገለግሉ ልጆች አብውን ነበሩ፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ሊሰራ ያሰበው ነገር ካለ በየትኛውም መንገድ እንደሚፈጽመው ያወኩበት ጊዜ ነበር፡፡ እናም ያ ጊዜ ለኔ በመሪነት ህይወቴ አስቸጋሪው ጊዜ ነበር፡፡
🎤የምትወደው ወይም አርዓያ የሆነሽ ሰው
👤- በግቢ ቆይታዬ አርዓያ ብዬ የማነሳቸው 2 ሰዎች ናቸው፡፡ የመጀመርያዋ ሊዲያ(ኪኮ) ናት፡፡ የመጀመርያ ዓመት ተማ በነበርኩበት ሰዓት የ Bible Study አስተማሪዬ ነበረች፡፡ ስለ ግቢ ቆይታዋ፤ ስለ Academics ህይወቷ እና አጠቃላይ ስለ ክርስትና ህይወት የምትነግረኝ ነገር በጣም ነበር የጠቀመኝ፡፡ በዚያ በጣም ነው ማመሰግናት፡፡ ሌላው አርዓያ ብዬ የምለው ደግሞ የእኔው Batch ተማሪ እና አብሮኝ የተመረቀው ብዙአየሁ (ቡዜ) ነበር፡፡ ከእሱ ደግሞ ትጋቱ እና መንፈሳዊ ህይወት ላይ የነበረው አቋም በጣም ነበር የሚያስገርመኝ፡፡ በመሪነት ጊዜዬ ጭምር ከእሱ ብዙ ነገር ተምሬያለሁ፡፡ በዚህም ሁለቱንም እግዚአብሔር ይባርካችሁ ልላቸው ፈልጋለሁ፡፡
🎤ዩኒቨርሲቲን ከሌላው ህይወት የሚለየው ምንድር ነው?
👤- ዩኒቨርስቲ ከሌላው የሚለየው ሚለው ነገር አብዛኞቻችን የምናውቀው እና በቆይታችን የተለማመድነው ነገር ነው፡፡ ብቻ ከመሆን አንስቶ እስከ ገንዘብ አያያዝ፤ ከ ጊዜ አጠቃቀም ጀምሮ እስከ ክርስትና ህይወት፤ የትምህርት ሁኔታ እና የዶርም ህይወት ሁሉ ነገር ውጪ ከምናውቀው ለየት ያለ ነገር ነው፡፡ ህይወታችን ክፍሎች ቢኖሩት ይህ ህይወት አንዱ እና በኋላም የማንረሳው ክፍላችን ነው፡፡
🎤የምትወደው የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅስ
👤- በጣም የምወደው የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ዕንባቆም 3፡17-19 ያለው ክፍል በጣም ነው የምወደው፡፡ ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ላይ ታምኖ ስለመኖር እና በየትኛውም ሁኔታ ስለማይጠፋ ደስታ የሚያወራ ክፍል ነው፡፡
508
መልስ 1 😊🤰
🔓 “ማንም በእርሱ እኖራለሁ የሚል፣ ኢየሱስ እንደ ተመላለሰ ሊመላለስ ይገባዋል።”
1ኛ ዮሐንስ 2፥6 (አዲሱ መ.ት)
🙏 ስለተሳትፎአችሁ ተመስገኑ
