cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

🌼 የፊደል ገበታ™ 🌼

መልካምነት ለራስ ነው መልካም ስትሰራ መልሶ ይከፍልሀል። ከልብህ አፍቅር ማፍቀር የራስ ስሜት ነው ፍቅር ሰላም መዋደድ መልካምነት ሁሉም ከፍ ያደርጉሀል። 🇪🇹ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን🇪🇹 🇪🇹አብዝቶ ይባርክ🇪🇹 💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️ . . . Creater - @Bini_dan . . . 4 any comment - @yefidel_gebeta_bot . . .

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
402
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

❤❤❤ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ❤❤❤ 🙏🙏🙏 "ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው"? 🙏🙏🙏 ✍️ የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኝ ዓበይት በዓላት አንዱ የደብረ ታቦር በዓል ነው። በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበረው ይህ በዓል መሠረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ፀሐይ የበራበት፣ ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት፣ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው። ✍️ ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ✍️ ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፡ ተነሡ አትፍሩም አላቸው። ማቴ. ፲፯፡፩-፭ በቤተ ክርስቲያን ደብረታቦር ከቤተክርስቲያን ውጭ አከባበሩ ቡሄ እየተባለ የሚከበረው በዓል በሀገራችን በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወደ መፀው የሚዘለቅበት ወገግታ ፣ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፣ የሚሸጋገርበት ወቅት በመሆኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ በዚህ መሰረት የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይቺ ዕለት 'ቡሄ' የሚለውን ስያሜ አገኘ። ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት፣ ብረሃን የታየበት ድምጸ መለኮት የተሰማበት ስለሆነ፤ ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓልም ይባላል፡፡ ✍️ በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። መነሻ የሆናቸው ትውፊት ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል ፡፡ያንን ለማስታወስ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የሚከበረው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡ የንጋት ወጋገን ሲፈናጠቅ ልጆች በከባድ ድምጽና በጅራፍ ጩኸት የሚታጀብ፣ በገደላገደል ስር እንዲያስተጋባ ተደርጎ ብዛት ባላቸው ህጻናት በከፍተኛ ድምጽ የሚዘመር ነው ቡሄ ። የጅራፉ ጩኸትም እግዚአብሔር አብ “የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት” ሲል ሐዋርያት ራሳቸውን ስተው የወደቁበትን የመለኮት ድምፅ ለማስታወስ ነው፡፡ ✍️ ደብረታቦር ወይም ቡሄ በአብነት ተማሪዎች “ስለ ደብረ ታቦር" እያሉ እህል፣ ፣ ጌሾ ለምነው ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምዕመናን በመጋበዝ በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ ይህ ትውፊት መምህረ ሐዋርያት የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ተማሪዎቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ደብረ ታቦር ይዞ ሄዶ የተገለጠ ምስጢር ስለሆነ ከመምህራቸው ጋር በመሆን በዓለ ደብረ ታቦርን /ቡሄን ያከብራሉ፡፡ ስሙን ይጠራሉ፡፡ 🙏❤ የበዓሉ እረዴት በረከት ይደርብን አሜን Comment ➪ @yefidel_gebeta_bot @yefidel_gebeta @yefidel_gebeta ════════ •✧๑♡๑✧• ════════
Показати все...
​​​​​​┉✽̶»̶̥🌺የቡሄ ፀሃይ🌺̶̥✽̶┉ ❣:¨·.·¨: ❣ ══════❁✿❁ ══════ """"""""""""""""""""""""""""" አንቺ የሳሎን ጌጥ ቢቆጡሽ አባትሽ ከቤት የማትወጪ እኔ በአመት አንዴ ሆያ ሆዬ እያልኩኝ ከቤታችሁ መጪ በነሀሴ ዝናብ ብቅ የምትይ ፀሀይ ብርሃን አመንጪ ከእናትሽ ጀርባ ሙልሙል ዳቦ ይዘሽ ነይ ውጪ ነይ ውጪ!! አይንሽን እያየሁ "ቡሄ በሉ" እያልኩኝ ስትይ አ.ፈ.ር ቀና ምቱ ተዛባብኝ አፌ ተሳሰረ ግጥሙም ጠፋና። እናትሽ ታዘቡ አባትሽ ተቆጡ ወንድምሽ ደነፋ እኔን ውሀበላኝ የማረገው አጣሁ መላ ቅጤ ጠፋ። ብቻ እዘማምራለሁ "ቡሄ በሉ.....ቡሄ በሉ ይቺን ቆንጆ ለእኔ በሉ እኔም ላቁም መስለምለሙ እሷም ትተው መሽኮርመሙ እዛ ማዶ ጭስ ይጨሳል እዚ ማዶ ልቤ ጨሷል የሷን ፍቅር ይፈልጋል አል'ያ ግን ጨሶ ያልቃል ድምፅዋን ብሰማ ብሩህ ነው ቀኔማ" ብዬ እንኳን ሳልጨርስ መዘማመሬን፤ አባቷ ደቆሱኝ በዱላ ጎኔን። ከቀልብያ ሆኜ ሳልጀምር እሩጫ፤ ዋልጌ ነህ እያለ ይነግረኝ ነበረ የእናቷ ግልምጫ። አቤት የወንድሟ በእኔ ግጥም ስንኝ በብስጭት ናውዞ፤ ካልገደልኩት ይላል በአገላጋዮች ተከቦ ተይዞ። ምን አለ ፈጣሪ ከቤቷ በረንዳ እሷን እያየሁኝ ከሙልሙሉም ዳቦ እየገማመጥኩኝ እሷ ፈገግ ብላ እኔ እየጨፈርኩኝ አመቱን በሙሉ ሆ እያልኩኝ በኖርኩኝ! Comment ➪ @yefidel_gebeta_bot @yefidel_gebeta @yefidel_gebeta ════════ •✧๑♡๑✧• ════════
Показати все...
ቡ ሄ •✦• መጣና መጣና ደጅ ልንጠና መጣና ባመቱ እንዴት ሰነበቱ፣ ክፈት በለው በሩን፣ የጌታዬን፤ ክፈት በለው ተነሳ፣ ያንን አንበሳ፤ መጣሁኝ በዝና ተው ስጠኝ ምዘዝና የኔማ ጌታ የገደለበት ስፍራዉ ጎድጉዶ ዉሃ ሞላበት እንኳን ሰውና ወፍ አይዞርበት ያሞራ ባልቴት ውሃ ትቅዳበት። የኔማ ጌታ የሰጠኝ ካራ ከዚህ ብመዘዉ ጎንደር አበራ፣ የኔማ ጌታ የሰጠኝ ስንዴ ገና ሳልበላዉ አበጠ ክንዴ። ወይ የኔ ጌታ የሰጠኝ ሙክት እግንባሩ ላይ አለው ምልክት፣ መስከረም ጠባ እሱን ሳነክት። ሆያ ሆዬ፣ ሆያ ሆዬ ወይ የኔ ጌታ ዋርካ ነህ ዋርካ ቢጠለሉብህ የማታስነካ። . . . . . የኔማ እመቤት፣ እሜት እሜት፣ ሎሚ ተረከዝ ትርንጎ ባት። የኔማ እመቤት የፈተለችው፣ የሸረሪት ድር አስመሰለችው፣ ሸማኔ ጠፍቶ ማርያም ሰራችው። ለዚያች ለማርያም እዘኑላት፣ አመት ከመንፈቅ ወሰደባት። የኔማ እመቤት መጣንልሽ፣ የቤት ባልትና ልናይልሽ። የኔማ እመቤት ብትሰራ ዶሮ፣ ሽታዉ ይጣራል ገመገም ዞሮ። የኔማ እመቤት የጋገረችው፣ የንብ እንጀራ አስመሰለችው። . . . . . ለቡሄ ጨፋሪዎቹ ህፃናትና ታዳጊዎች እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ ይሰጧቸውና እየገመጡ ጅራፋቸውን ሲያጮሁ ያመሻሉ። የቡሄ ዕለት ለእያንዳንዱ የቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ ልጅ አንዳንድ ሙልሙል ዳቦ በልጆቹ ልክ ይሰጣል። በቆሎ ተማሪዎች ዘንድ ደብረ ታቦር ‘የተማሪዎች በዓል’ ነው። ተማሪዎቹ ቀደም ብለው “ስለ ደብረ ታቦር" እያሉ እህሉንም፣ ብቅሉንም፣ ጌሾውንም ይለምኑና ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምዕመናን ሁሉ ይጋብዛሉ። . . . . . Comment ➪ @yefidel_gebeta_bot @yefidel_gebeta @yefidel_gebeta ════════ •✧๑♡๑✧• ════════
Показати все...
👍 1
❤️ፍቅርና ጊዜ 💛ሁሉም አይነት ስሜቶች የሚኖሩበት አንድ ደሴት ነበር፡፡ የደስታ ስሜት፣የመከፋት ስሜት፣ እውቀት እና ሌሎቹ ስሜቶች ፍቅርን ጨምሮ፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ደሴቱ ሊሰምጥ እንደሆነና ሁላቸውም ስሜቶች ሊያመልጡ የሚችሉበትን ጀልባ መስራት እንዲችሉ አዋጅ ተነገረ፡፡ በዚህም መሠረት ሁሉም ስሜቶች ጀልባቸውን ሲሰሩ ፍቅር ግን ደሴቱ እስኪ ሰምጥ ድረስ ጀልባ አልሰራም ነበርና ከሊሎቹ ስሜቶች እገዛ ለመጠየቅ ወሰነ፡፡ 💙ሀብታምነት የሚባለው ስሜት በፍቅር በኩል ሲያልፍ “ሀብታም ሆይ ከአንተ ጋ ይዘኸኝ ልትሻገር ትችላለህ?” አለው ፍቅር፡፡ “አይሆንም፡፡ አልችልም በጀልባየ ውስጥ በርካታ ወርቅና መዳብ የያዝኩ በመሆኑ ለአንተ የሚሆን ቦታ የለኝም” ሲል ጥሎት ሄደ፡፡ ፍቅር አቶ ስግብግብን ሲያልፍ ተመለከተውና እንዲረዳው ጠየቀው፡፡ “አልችልም አቶ ፍቅር ጀልባየን ታበላሽብኛለህ አይሆንም ብሎ” ትቶት ሄደ፡፡ አቶ መከፋትን በቅርብ አገኘውና አሁንም ፍቅር አብሮ እንዲያሻግረው ጠየቀው፡፡ “ኦው! ፍቅር አዝናለሁ እኔ ብቻየን ነው መሆን የምፈልገው፡፡” ብሎ አሰናበተው፡፡ ደስታም ፍቅርን አልፎት እየሄደ በጣም በፈንጠዝያ ስሜት ላይ ስለነበር ፍቅር ሲጠራውም መስማት አልቻለም፡፡ 💜ፍቅር ትዕግስቱን እያጣ በመከፋት ስሜት እንዳለ ባጋጣሚ “ፍቅር ና እኔ እወስድሃለሁ” የሚል ድምጽ ሰምቶ ሲዞር የተባረከ አዛወንት ነበር፡፡ “ጊዜው ነው” ወዳጀ ፍቅር ሲል እውቀት የተባለው ስሜት መለሰ፡፡ 📍 “ጊዜ ማለት!?” ፍቅር በመደነቅ ጠየቀው “ነገር ግን ለምን ጊዜው ሊረዳኝ ቻለ?” እውቀት ፈገግ እያለ ምክንያቱም “የፍቅርን ዋጋ መረዳት የሚችለው ጊዜ ነው፡፡” ሲል መልስ ሰጠው፡፡ ❤️በዚህ ዓለም ፍቅር ብቻ ነው ሠላምንና ታላቅ ደስታን ሊያመጣ የሚችለው፡፡ ባለጸጎች ስንሆን ፍቅርን ካራቅነው፣ ተፈላጊነታችን ሲጨምር ፍቅርን ከዘነጋን፣ ምናልባትም በደስታና በሀዘን ስሜት ስንሆንም ፍቅር ካጣን የማስተዋል ጊዜው ሲደርስ ነው የፍቅር ጥፍጥና የሚታወቀን፡፡ 💞የልባችን ብርሀን የሚበራው በፍቅር ነውና ሁሌም ፍቅርን እናስቀድም፡፡ ምንጭ፡ Lovely Time.. Or Timely Love ውብ አዳር❤️ Comment ➪ @yefidel_gebeta_bot @yefidel_gebeta @yefidel_gebeta ════════ •✧๑♡๑✧• ════════
Показати все...
ፍቅር እስከ መቃብር ሰብለ ሰብለ ሰብለ ወዳጄ እመቤቴ የመአልት ምርኩዜ የሌሊት መብራቴ ስራብ እንጀራዬ ስጠማ ወተቴ ሳዝን መጽናኛዬ ስደክም ጉልበቴ ሳጣ አለኝታዬ ስጠቃ ኩራቴ የስጋ የመንፈስ ያለሽኝ አንድ ሀብቴ ቁርጥ ከሆነማ እኔ አንችን ማጣቴ ምን ዋጋ ሊኖረዉ ከእንግዲህ ሂወቴ የለም ህይወት በቃኝ ይገላግለኝ ሞቴ ተቀማሁ ወይኔ ድሃ በመሆኔ ጥየሽ የሄድኩለት ወንዝ ተሻግሬ የደም እምባ አልቅሼ በድሌ አማርሬ የሁዋሊት ስጎተት በፍቅርሽ ታስሬ ወደ ፊት መራመድ እያቃተዉ እግሬ አሁንም አሁንም ቆሜ እያየሁ ዞሬ ምን ልቤ ቢፈራ ባይቀር መጠርጠሬ በተስፋ ነበረ የወጣሁ ካገሬ እስከ ዛሬም ድረስ በህይወት መኖሬ ተስፋ ሆኖኝ ነበር ፍቅርሽና ፍቅሬ ግን እዉነት ከሆነ የነገሩኝ ወሬ ሊያገባሽ ነዉ ብለዉ ባለብዙ በቅሎ ባለብዙበሬ በፍቅር ለሞተ መታሰቢያ ሆኖ እንዲቀር መቃብሬ መኖር አልፈልግም ሞቼ ልደር ዛሬ Comment ➪ @yefidel_gebeta_bot @yefidel_gebeta @yefidel_gebeta ════════ •✧๑♡๑✧• ════════
Показати все...
አንድ #የቆሎ_ተማሪ ነበር ይህ ተማሪ ከሌሎች እሱን መሰል ተማሪዎች የሚለየው ስለ ማርያም ስለ እመብርሃን ብሎ ከለመነ በኋላ ያገሬው ሰው ሲሰጡት " ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ " ብሎ መርቆ ይሄዳል፡፡ እናም ይህ የቆሎ ተማሪ ትምህርቱን እየተማረ የተዘከሩትንም ' ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ' እያለ ሲኖር ባንድወቅት ወደ አንዷ ሴትዮ ቤት ገብቶ "ስለ ማርያም ስለ ወላዲተ አምላክ ተዘከሩኝ" ብሎ ሲለምን የቤቱ ባለቤት ቁራሽ እንጀራ አውጥታ ተዘከረችው እሱም የለመደው ነውና "ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ" ብሎ መርቆ ይሄዳል በዚህ ግዜ ሴትዮዋ "እንዴት ስዘከረው እግዚአብሔር ይስጥልኝ ብሎ መመረቅ ሲገባው 'ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ' ይለኛል" ብላ ትናደዳለች፡፡ "እንዲህ ከሆነማ ጥሩ ብላ ነገ ሲመጣ አሳየዋለሁ" ብላ ትፎክርበታለች በነገታውም ወደ አመሻሹ ለእራት የሚሆነውን ሊለምን ወደ መንደሮቹ እንደለመደው "ስለ ማርያም" እያለ ሲሄድ ሴትዮዋም በጎማ ጠላ አዘጋጅታ ጠላው ውስጥ መርዝ ጨምራ ጠበቀችው ተማሪውም እሷ ቤት እንደደረሰ ስለ ማርያም ስለ እመብርሃን ብሎ ደምፁን እንዳሰማት ወዲያውኑ ያዘጋጀችውን ጠላ የያዘውን ጎማ አውጥታ ሰጠችውና ከዛው ቁጭ ብሎ ከጠጣው መርዙ ሊገለው ስለሚችል "በል እዚህ ቁጭ ብለህ ከጠጣኸው ስለሚመሽብህ ከቤትህ ሄደህ አረፍ እንዳልክ ጠጣት፡፡ እንዴት ያለች ጠላ መሰለችህ" ብላ ትልከዋለች፡፡ "እሱም ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ " ብሏት ይሄዳል "እስኪ ደግም ሆነ ክፋት ለራስ ከሆነ እናያለን" ብላ በውስጧ ሞቱን አስባ ተሳለቀችበት፡፡ እሱም የተዘከሩትን ምግብም ሆነ መጠጥ ይዞ ወደ ማደርያው ጉዞውን ጀመረ በመንገድ ላይ የሴትዮዋ ልጆች በረሃ ቆይተው በጣም ደከሟቸው ከተማሪው ጋር ተገናኙ ወደ ተማሪው ቀረብ ብለው "እባክህን በርሃ ቆይተን በጣም ደክሞን መግባታችን ነውና እቤት እስክንደርስ የውሃ ጥማችንን ቢያስታግስልን ከያዝከው መጠጥ ትንሽም ቢሆን አጠጣን" ብለው ሲለምኑት "እኔም ለምኜው ነው ደግነትም ለራስ ነው" ብሎ ከያዘት ጎማ እንዲጠጡ ፈቀደላቸው ሁለቱም ልጆች ከጎማዋ እንደጠጡ ወደያው ይሞታሉ ይህን ጊዜ እሪታው ቀልጦ ⚂የመንደሩ ሰው በሙሉ ይሰበሰቡና ግማሹ ዱላ ይዞ ደብድበን ካልገደልነው ⚂ገሚሱም በድንጋይ መወገር አለበት ⚂የተቀሩት ደግሞ ለህግ መቅረብ አለበት ሲባባሉ ሴትዮዋ የመንደሩን ግርግር ሰምታ ስትመጣ ሁለቱም ልጆቿ ሞተው መርዝ ከጠላ ጋር ቀላቅላ የሰጠችውም ተማሪ ሰዎች እያመናጨቁ ይዘውት ወደ ህግ እናቅርበው ብለው ሲወስዱት ታያለች ይሄኔ ነበር 'ደግም ለራሱ ክፉም ለራሱ' የሚለው ነገሩ ትዝ ያላት ሴትዮዋም "በሉ የያዛችሁትን ተማሪ ልቀቁት የዚህ ሁሉ ችግር ምክንያት እኔው እራሴው ነኝ" በማለት የሆነውን ነገር ሁሉ ተናግራ "በገዛ ክፋቴ የገዛ ልጆቼን የገደልኩት እኔው እራሴው ነኝ እናም ይሄ ሰው ንፁህ ሰው ነው ልቀቁት" ብላ እራሷን ለህግ ሰጠች፡፡ እውነትም ደግም ሆነ ክፉ መሆን ለራስ ነው ክፉ መሆን በቅድሚያ የሚጎዳው እራስን ነውና ደግ እንሁን ከደግነት በላይ መልካም ነገር የለምና Comment ➪ @yefidel_gebeta_bot @yefidel_gebeta @yefidel_gebeta ════════ •✧๑♡๑✧• ════════
Показати все...
አርምሞ በክፉም በደጉም ያለፈውን ጊዜ በሰከነ መንፈስ በኋሎሽ ትካዜ በቀናት መካከል በወር ባመታቱ ስንት መልካም መጥቶ ከፍቶ አለፈ ስንቱ አባጣ ጎርባጣ የህይወት ስንክ ሳር ፍቅር ያጠቃ ጦር የመልካም ጥፍ ነበር ለዚያ ነው ... ዝም ያልኩት ፀጥ ያልኩት አክብጄ በዝምታዬ ውስጥ አርምሞን ወድጄ ራሴን አሳልፌ ስሰጥ ለፀጥታ የኮልኮሌ ዓለም ቅብርጥስ ጋጋታ ልረሳው ብወስን ፍቅር የነሳኝን ውስጤን የረበሸው ክፉ ጥብርብርታን እሱን ልረሳ ስል ከብዷል ዝምታዬ ከቶ ላላሸንፍ በነበር ውሎዬ እናም እሮዝ አለም መገፋት ክፋቱ ፍቅር አደብዝዞ ሲባረር እውነቱ አንቺም በዚህ መሀል በነበረሽ ሚና አንዱ ክፍል ሆኖል ያርምሞዬ ዜና እናም ውዴ ፍቅር ዝምታዬ ቢከብድ ስትረሽኝ ስተዊኝ ብታገል ለመልመድ መቆዘም አበዛሁ ፍቅር አሳዘነኝ ከልብ መዝገብ ውስጥም ስረዛሽ አመመኝ ግናም ሁሉም ይሁን ... ብታለል በቃልሽ ልቤ አንቺን አምኖ ፁፍሽን ብጠብቅ ባይመጣ ጉም ሆኖ በሰው አፍ ብናገር ምላሹ ቢከፋ በራሴ ብሞክር ባጣ ትንሽ ተስፋ አርምሞ መረጥኩኝ በተሰረኩት ልብ በእሮዟ ውብ መዓዛ በትካዜ ቅንብብ አፍቃሪሽ! Comment ➪ @yefidel_gebeta_bot @yefidel_gebeta @yefidel_gebeta ════════ •✧๑♡๑✧• ════════
Показати все...
➳"በሕይወት ትምህርት እንጅ ስህተት የለም። የሚለመልሙ መልካም ዕድሎች ፣ እንጂ አጓጉል ገጠመኞች የሉም ። ....ትግል ያበረታል። ሕመም እንኳን ሳይቀር ድንቅ መምህር ነው።" Comment ➪ @yefidel_gebeta_bot @yefidel_gebeta @yefidel_gebeta ════════ •✧๑♡๑✧• ════════
Показати все...
ለኔ... ከድብልቅልቁ አለም ሰዉ ከሞላባት ከጉዲቱ ምድር ወከባ ካለባት ውሸቱ ከእውነቱ ከተዳቀለባት ወዳጅ ከጠላቱ ከተዋዋለባት አስመሳይ ማንነት ከተንሰራፋባት አዋቂ ነን ባዮች ከሚያጫርሱባት የእውነት አዋቂዎች አላዋቂ ተብለው ከተገለሉባት ከዚች ጉደኛ አለም ተገነጠልኩና ውስጤ ውስጥ ዘልቄ "ማን አለልሽ ?" ብላት ከአንድ ራሴ ውጭ አንድም አጣሁላት ። Comment ➪ @yefidel_gebeta_bot @yefidel_gebeta @yefidel_gebeta ════════ •✧๑♡๑✧• ════════
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.