cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Deacon Cherinet

ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤አሜን 2ኛ ጴጥ 3፡18 በተዋህዶ እምነታችን ፀንተን እንኑር ! ጥቆማ ወይም ጥያቀ ካላቹ በዚህ የተለግራም ቦት👉🏽https://t.me/Cher2112bot ይጠቀሙ This channel is operated by Deacon Cherinet

Більше
Рекламні дописи
366
Підписники
+824 години
+477 днів
+12130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ከእለታት አንድ ቀን አንድ አባት ወደ አባ መቃርዮስ በኣት ሄደና "አባቴ ሆይ ድኅነትን አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?" ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው። አባታችንም እንዲህ በማለት አሉት። "ወደ መቃብር ሂድና ሙታንን ሰድበሃቸው ና" አሉት። ይህ አባትም የተባለውን አድርጎ ተመለሰ። አባታችንም "ምን አሉህ?" ሲሉ ጠየቁት። ሰውየዉም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "አሁን ደግሞ ሂድና ሙታንን አመስግናቸው" አሉት። ሄዶም አመሰገናቸው። "አሁንስ ምን አሉህ" ሲል በድጋሚ ጠየቁት። ሰውዬም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "ስትሰድባቸው፣ ስታመሰግናቸው እና ስታወድሳቸው ምንም አልመለሱም፤ አንተም ለነፍስህ ድህነትን ከፈለግህ እንደሞተ ሰው ሆነህ ኑር። ሰዎች ክፉ ቢያደርጉብህም፣ ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ" አሉት። @Deaconcherinet @Deaconcherinet @Deaconcherinet
Показати все...
👍 3
"አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል? "ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡ እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው? አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው። እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ @Deaconcherinet @Deaconcherinet @Deaconcherinet
Показати все...
+++ ጸልየህ ልታደርገው ትችላለህ? +++ ማልዶ ቤተ ክርስቲያን ተሳልሞ ወደ ሥራ የሚሄድ አንድ መንፈሳዊ ሰው በጉዞው ከሌላ መንገደኛ ሰው ጋር ይገናኛል። ጥቂት እንደ ተጨዋወቱ ይህ በመንገድ ያገኘው ሰው ከደረት ኪሱ የሲጋራ ፓኮ በማውጣት አንዱን መዝዞ እንዲወስድ ይጋብዘዋል። ያም መንፈሳዊ ሰው "አይ ይቅርብኝ" ሲል እምቢታውን ገለጸ። ባለ ሲጋራውም "ኃጢአት ነው ብለህ ስላሰብህ ነው እምቢ ያልከኝ? ማጨስ እኮ ከአስጨናቂዋ ሕይወት ፋታ ለመውሰድና ራስን ዘና ለማድረግ ይረዳል። ግድ የለህም አንዱን ሞክር" እያለ ሊያግባባው ጣረ።  በመጨረሻም መንፈሳዊው ሰው "ግድ የለም ለእኔ ይቅርብኝ። ባይሆን አንተ ይጠቅመኛል ካልህ በቃ ሲጋራውን ከመለኮስህ በፊት አንድ "አባታችን ሆይ" ጸልይና ጀምር" አለው። በዚህ ጊዜ ያ መንገደኛ ደንግጦ እንዲህ ሲል መለሰ "ጸሎት ጸልዬማ እንዴት እንዲህ አደርጋለሁ?!" በጸሎት ልትጀምር የማትችላቸው ማናቸውም ነገሮች ለአንተ መልካም አይደሉም። በልብህ ኃጢአት እንድታደርግ የሚገፉፉህ ክፉ ሐሳብ ሲመጣ "ይህን ጸልዬ ማድረግ እችላለሁ?" ብለህ ራስህን ጠይቅ። ከጸሎት ጋር የማይጣጣም ከመሰለህ እርሱ ኃጢአት ነውና ተወው። ጸልዮ የሚዘሙት፣ ጸልዮ የሚሰርቅ፣ ጸልዮ ባልንጀራውን የሚሳደብ፣ ጸልዮ በወንድሙ ላይ ክፉ የሚያደርግ ማን ነው? ዲያቆን አቤል ካሳሁን @Deaconcherinet @Deaconcherinet @Deaconcherinet
Показати все...
7🙏 3
#ንስሐ እንዴትና ለማን እንገባለን? ንስሐ ገብተን፣ የኃጢአትን ስርየት አግኝተን፣ ከሰውና ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀን በጽድቅ ጎዳና ለመራመድና በደህንነት ጸጋ ለመኖር እንድንችል ቢያንስ ሦስት ነገሮችን መፈጸም አለብን:: #የመጀመሪያው የንስሐ ሐዘን ማለትም እውነተኛና ልባዊ ጸጸት በቅድሚያ እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡ #ሁለተኛው ኑዛዜ ሲሆን #ሦስተኛው ደግሞ ስለኃጢአታችን የሚሰጠንን የንስሐ ቅጣት የሚያመለክት የቀኖናን ሥርዓት መፈጸምና እንደዚሁም በካህኑ በኩል የምናገኘው የፍትሐት ጸጋ ነው:: #የንስሐ ሐዘን /ጸጸት/ ንስሐ የሚገባ ሰው በመጀመሪያ ኃጢአቱን እያስታወሰ ሰውና ፈጣሪውን መበደሉን እያሰበ የሚያደርግው ሐዘን ወደ ንስሐ የሚወስድ እውነተኛ ሐዘን ስለሆነ ሃዘኑን እግዚአብሔር ይቆጥርለታል፡፡ ብፁዓን ናቸው፣መጽናናትን ያገኛሉና» /ማቴ. ፭፥፬/ የተባለው የራሳቸውንና የሌላውን ኃጢአት እያሰቡ የሚያዝኑትን ተነሳሒያን ያመለክታል፡፡ #ንስሐ ማለት ጸጸትን የሚያመለክት ቢሆንም ቁጭትና ቅንዓት የሞላበት የዓለማዊ ጸጸት ሳይሆን እውነተኛው ሐዘንና መመለስ መሆኑን በቅድሚያ መገንዘብ ይኖርብናል:: ስለ እውነተኛው ሐዘን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚከተለው ያስተምረናል፡፡ « አሁን ስለ ንስሐ ስላዘናችሁ ደስ ብሎኛል እንጂ ስላዘናችሁ አይደለም ፤በምንም ከእኛ የተነሳ እንዳትጎዱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አዝናችኋልና፡፡ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን ጸጸት የሌለበትን፣ወደ መዳንን የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ሐዘን ግን ሞትን ያመጣል።» /፪ኛቆሮ. ፯፥፱-፲/:: እንግዲህ እውነተኛውን ሐዘን ከእንባ ጋር አድርጎ በንጹህ ልቦናና ጸሎት ለእግዚአብሔር በማቅረብ ተነሳሒው እንደገና ላለመበደል መወሰን ይኖርበታል። ውሳኔውንም ለመፈጸም የሚያስችለውን የመንፈስ ቅዱስን ረድኤት በማግኘት ሁልጊዜ ተግቶ መጸለይ አለበት። @deaconcherinet @deaconcherinet @deaconcherinet
Показати все...
👍 2🙏 2
+++ እግዚአብሔር ሲቀጣን ... +++ "[አንድ] ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡ "#እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡" © ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ፥ ገ. 36 @deaconcherinet @deaconcherinet @deaconcherinet
Показати все...
🥰 4👍 2
+ #ዝም_ብለን_የምንጠላው_ሰው + ከሩቅ የምናውቀው አንዳንድ ሰው የለም? ብዙም አናውቀውም:: ቀርበን አውርተነው አናውቅም:: ስናየው ግን እንዲሁ ደስ የማይለንና ያለ ምክንያት የምንጠላው ሰው የለም? "እሱን ሰውዬ ጥሎብኝ አልወደውም" "አይ እሱን ልጅ ቀልቤ ትከሻዬ አልወደደውም" "እኔ እንጃ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አልወዳትም:: ምክንያቴን አትጠይቀኝ ግን በቃ እንዲሁ አልወዳትም" ምንም ምክንያት ሳይኖረን እንዲሁ የምንጠላው ሰው አለ:: እግዚአብሔር ግን "አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል" (ዮሐ 3:16) የሚያሳዝነው ያለ ምክንያት የጠላናቸውን ሰዎች የበለጠ ለመጥላት በልባችን እስር ቤት ውስጥ በጥላቻ ሰንሰለት እናስራቸውና የበለጠ ለመጥላት ስለእነርሱ ክፉ ክፉ ማስረጃ ለመስማት እንተጋለን:: ጥሩ ነገራቸውን ለመስማት አንፈልግም:: ክፉ ስንሰማ ግን "እኮ እኔ እኮ ዝም ብሎ ትከሻዬ ይነግረኝ ነበር" ብለን በደስታ እንፈነድቃለን:: እንዲሁ የጠላነውን ሰው በምክንያት ለመጥላት በመቻላችን ደስ ይለናል:: እኛ ሰውን ለመጥላት ምክንያት የምንፈልገውን ያህል እንዲሁ የወደደን እግዚአብሔር ግን እኛን ለመማር ሰበብ ይፈልጋል:: ትንሽ በጎነት ቅንጣት ቅንነት ሲያገኝ እጅግ ይደሰታል:: ባለቅኔው "እግዚአብሔር መንግሥቱን በርካሽ ዋጋ ሸጠው:: በቀዝቃዛ ውኃ በዘለላ ዕንባ እና ማረኝ በሚል የወንበዴ ጩኸት!" እንዳሉት እሱ እኛን ይቅር ለማለት የሚታይ በጎነት ቢያጣ ልባችን ውስጥ ገብቶ ትንሽ መጸጸት ካለ ይፈልጋል:: እንዲሁ ወዶናልና እንዲሁ ሊተወን አይፈልግም:: @deaconcherinet @deaconcherinet @deaconcherinet
Показати все...
#የማይለወጥ ርዕስ! "መድረክ ላይ የሰበ'ከውን ጌታ ቤት ስትገባ አትጣለው" “ዕለት ዕለትም #በመቅደስና #በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር ። /ሐዋ 5፥42/ በማንኛውም የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ የማይለወጥ የዘላለም አጀንዳ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ክርስቲያን የምጣድ ባህሪ ሊኖረው አይገባም። ሲጣድ የሚግል፣ ሲወርድ የሚቀዘቅዝ ሊሆን አይገባም። ክርስትና በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ግለቱ እየጨመረ የሚሄድ ሕይወት ነው። ወገኖቼ ከላይ በጠቀስነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ስናነብ የሐዋርያቱን የሚደንቅ የየዕለት ሕይወትና የማይለወጥ ርዕሳቸውን እንመለከታለን። አገልጋይ በመቅደስ የሰበከውን ኢየሱስን ቤቱ ሲገባ ሊረሳው አይገባም። "ኢየሱስ ጌታ ነው" የሚለው ስብከት የመድረክ ማድመቂያ ሳይሆን የቤታችንም ውበት ነው። ኢየሱስ ሕይወታችን ይሁን! በመቅደስ፣ በአትሮንስ ላይ የገነነው ጌታ በሕይወታችንና በቤታችን ሊገንና ሊደምቅ ይገ'ባል። "ዕለት ዕለትም #በመቅደስና #በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ መስበክን አልተውም ነበር።" የሚደንቅ ነው! በመቅደስ ያስተማሩትን ርዕስ እቤታቸው ሲገቡ አልረሱትም። ዕለት ዕለት በዘላለማዊው ርዕስ ይተጉ ነበር። የዳነ፣የተነካ፣ የተለወጠ፣ ቅዱሱን መንፈስ የተሞላ፣ ለጥሪው የታመነ በየትኛውም ሁኔታና ስፍራ የማይለወጥ ርዕሱ "ኢየሱስ ክርስቶስ " ነው። የየዕለት ስብከታችን፣ ዝማሬአችን፣ ውይይታችን ....ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን! ይህ ከሆነ አንበርድም፣ አንቀልም፣ አንወርድም። የማይታፈርበት ክብራችን ኢየሱስ ነው። የመድረክ ላይ ሕይወታችንን የቤት ውስጥ ሕይወታችን ተቃውሞብን ይሆን!? ወገኖቼ ቅድስና ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላለም አምላክ ነው! ወሰበሐት ለእግዚአብሔር !!!! Share @deaconcherinet @deaconcherinet @deaconcherinet
Показати все...
🥰 3 1
#ዳግማይ ትንሳኤ ማለት ዳግም መነሳት (ሁለተኛ መነሳት) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ #ዳግማይ\ትንሳኤ ተብሏል። ሁለተኛ ለምን ተገለጠ? #ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጉኔን ዳስስ ብሎታል። ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑ በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል ።ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው ።ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች (የዳሰሰች)እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች ።እስካሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ። #ሰንበትን ሊያጸናልን የአይሁድ ሰንበት፣እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም(ቅዳሜ)ናት ።በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ከሙታን መካከል የተነሳባት፣አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት(ዳግማይ ትንሳኤ)፣መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች ።ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች ።ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት ።እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን)የምናሳልፈው ማለት አይደለም ።እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ 👉 ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል ።በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ። "ብጹዓን እለ እንዘ ኢይሬእዩ የአምኑ" (ዮሐ20:29) @Deaconcherinet @Deaconcherinet @Deaconcherinet
Показати все...
4
ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ ክርስቶስ ተነሳ እሰይ እሰይ እኛንም ከሞት ሊያስነሳ ክርስቶስ ከሙታን ተነሳ ሰላም ሰላም ለሰው ልጆች በምድር ኾነ ሰላም . . ዘማሪት ማርታ ኃ/ሥላሴ
Показати все...
4_5771593789852354821.mp34.24 MB
ልደታ ለማርያም በግንቦት አንድ ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች። እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት፡፡ ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ። በዚያ ወራት የመካኖች መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና፡፡ እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር፡፡ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሐሳባቸውን ተመለከተ፡፡ ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው፡፡ በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ፤ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት። ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች። ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች፡፡ ከዚህም በኋላ ይህችን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች። ስሟንም ‹ማርያም› ብላ ሰየመቻት። ትርጓሜውም ‹እመቤት› ነው። ‹ደግሞም ሀብታና ስጦታ› ማለት ነው፡፡ በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት ናትና። የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ለዘለዓለሙ ይኑር፤ አሜን፡፡ ከመጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት 👉@Deaconcherinet 👉@Deaconcherinet 👉@Deaconcherinet
Показати все...