cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ድሬደዋና አካባቢዋ የንፅፅር ቻናል

አንብብ፣በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም። ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)። አንብብ፤ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤ያ በብርዕ ያስተማረ፤ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን። [አል ዐለቅ፡1-5]

Більше
Рекламні дописи
337
Підписники
-124 години
-27 днів
+830 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ክፍል 5 የኒቂያና የመጀመሪያው የቁስጥንጥንያ ጉባዔ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ፥ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡       ከላይ እንዳየነው የኒቂያ ጉባዔ በጊዜው የተፈጠረውን ታሪካዊ ሁነቶች ተከትሎ የተካሄደ ነው። ከኢየሱስ እርገት በኋላ ይህ ጉባዔ እስከተካሄደበት 300 ዓመታት ውስጥ በኢየሱስ ማንነት ዙሪያ ላይ አንድ ወጥ የሆነ አስተምህሮት አልነበረም። እናም የባዛንታየኑ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ በአካባቢው የተፈጠረውን የእምነት ክፍፍል አጥብቦ አካባቢውን ለመቆጣጠር መሞከሩ የሚጠበቅም ነበር። እናም ቆስጠንጢኖስ የኒቂያን ጉባዔ በ325 ዓ.ል ቱርክ ላይ ጠራ። ጉባዔው ላይ 318 ጳጳሳት የተሳተፉ ሲሆን ከአንዱ በስተቀር ሁሉም ምስራቃውያን ናቸው ተብሏል። በዚህ ታሪካዊ ጉባዔ ላይ ለቀናት ያህል በመሰረታዊ የኢየሱስ አስተምህሮት ላይ ክርክር ከተካሄደ በኋላ በስተመጨረሻም ጉባዔው ‹‹በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ›› አምላክነት ማመን የክርስትና መሰረት እንዲሆን፤ ይህንንም የማይቀበል እንዲወገዝ ተስማምተው ጉባዔው ሊፈፀም ችሏል።       በጉባዔው ላይ ኢየሱስ ‹‹የአምላክ አምላክ ነው፤ የብርሃን ብርሃን ነው፤ የታላቅም ታላቅ ጌታ ነው፤ ልጅ ነው፤ አልተፈጠረም፤ ከአባላቱም ጋር አንድ ነው።››       የሚል አቋም ይዘው ሊለያዩ ችለዋል። ይሁን እንጅ ጳጳሳቱ ከሥላሴ አንዱ ስለሆነው ‹‹መንፈስ ቅዱስ›› በጥቂቱ እንጅ አልተወያዩም። በጊዜው ‹‹በመንፈስ ቅዱስ አምነናል›› ብለው ጉባዔውን ከመዝጋታቸው ውጭ መንፈስ ቅዱስ ምንድነው? አካል አለው ወይስ የለውም? የሚሉትንና መሰል ጥያቄዎችን በይደር ትተዋቸው ነበር።(1)       አትናቴዎስ በዚህ ጉባዔ ላይ የእስክንድርያውን ጳጳስ ወክሎ የተገኘ ሲሆን ገና የ27 ዓመት ወጣት እንደነበር ተገልጿል። በጉባዔውም የተሳተፉትን ጳጳሳት ተረድቼዋለሁ ያለውን የሥላሴ ቀኖና እንዲቀበሉ ከፍተኛ ግፊት ማድረጉ ይነገርለታል። የኋላኋላ አትናቴዎስ በህይወቱ መጨረሻ አካባቢ መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው አምላክ እንደሆነና ከአብና ከወልድ ጋር እኩል ስልጣን እንዳለው ደንግጎ መሞቱን ቀደም ብለን የጠቀስን ሲሆን ይህም ከኒቂያ ጉባዔ ከ56 ዓመታት በኋላ የመጀመሪው የቁስጥንጥንያ ጉባዔ እንዲጠራ ምክንያት ሆኗል።(2)       እናም የመጀመሪያው የቁስጠንጢንያ ጉባዔ አትናቴዎስ ደንግጎት የሞተውን የመንፈስ ቅዱስን አምላክነት ለማፅደቅ በ381 ዓ.ል ተጠራ። በጊዜው በተለያዩ አብያተክርስቲያናት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ የተለያየ ትርጉምና ፍች ሲሰጠው የኖረና አንዳንዶች መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር የሚወጣ እስትንፋስ ነው፤ ሌሎች ደግሞ አምላክ ነው ይሉትም ነበር። አርዮስ ደግሞ ከመላዕክት አንዱ ሊሆን ይችላል ሲል አስተያየት መስጠታቸው ይታወሳል።       በመጨረሻም በጥንቷ ‹‹ቁስጥንጥኒያ›› በአሁኗ ቱርክ ዋና ከተማ ‹‹ኢስታንቡል›› የተሰባሰቡት ጳጳሳት አትናቴዎስ በቀመረው ፅንሰ ሃሳብ ላይ ተመስርተው የመንፈስ ቅዱስን አምላክነት አወጁ። አትናቴዎስንም ‹‹የክርስትና አባት›› አሰኙት።(3)       እነዚህ ከላይ በጥቂቱ ለማየት የሞከርናቸው የቀደምት ክርስትና ክፍሎችና የሥላሴ አመጣጥ ታሪኮች አስተምህሮቱ እንደዛሬው አንድ ወጥ አቋም ከመያዙ በፊት የነበረውን ሂደት ያሳዩናል ባዬ አስባለሁ። በጊዜው በእምነት አባቶች መካከል የተፈጠረው ውዝግብ የኋላኋላ በኒቂያና በቁስጥንጥንያ ጉባዔ ለፀደቀው የሥላሴ አስተምህሮት መመስረት ምክንያት እንደሆነም እንረዳለን። በአጠቃላይ የሥላሴ ታሪካዊ አመጣጥ በመጠኑ ይህን የሚመስል ሲሆን በቀጣዮቹ ርዕሶች ደግሞ አስተምህሮቱ በመጽሐፍ ቅዱስ በብሉይና በአዲስ ኪዳናት ውስጥ ያለውን ቦታ እንዳስሳለን። __ (1) Donald Fairbairn (2009). “Life in the Trinity: An Introduction to Theology with the Help of the Church Fathers”, pp. 46–47 (2) Philip Schaff “Nicene and Post-Nicene Fathers”, Book 2, disc 41 (3) Philip Schaff, Henry Wace (1893). Nicene and Post-Nicene Fathers of the Christian Church. 477 ------------------------------Ω-------------------------------------- https://t.me/muhammed6964 ወሠላሙ ዐለይኩም
Показати все...
አስፈላጊ ቻሌንጅ ለሁሉም ይሄ ፅሁፍ ይሰራጭ!!! አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ በተለያየ ሀገር የምትገኙ ሙስሊም ወንድምና እህቶቼ እዲሁም ክርስቲያን ወገኖች ሰላም ብያለው ኢንሻአላህ ኢስላምን በደንብ ለማወቅና ለመረዳት ይጠማል ብዬ የኢስላም መሰረታዊ ነገሮች የሚባሉትን አብረን እድንማማር አስቤ ነበር በዛውም ልክ አላህ ካለ ለክርስቲያኖች ሰበበል ሂዳያ እንሆናለን ብዬ አስባለው ስለዚህ የሚለቀቀውን ትምህርት ሼር በማድርገ ክርስቲያኖች ወደ ዲነል ኢስላም እዲመጡ መንገድ እንድንሆን ስል እጠይቃቹሀለው ይሄን ፅሁፍ ሼር በማድረግ ቻናሌን እናሳድገው 2000 ተከታይ ስንገባ ኢንሻአላህ እንጀምራለን ሼር ማድረግ ካሁኑ ይጀመር የሚሰጡት ትምህርቶች ምዕራፍ አንድ የኢስላም መሰረታዊ ነገሮች 1•ኢስላም ማለት ምን ማለት ነው? 2•ተውሂድ ማለት ምን ማለት ነው? 3•አላህ ማነው ምድነው? 4•ለምን አላማ ተፈጠርን? 5•በእስልምና መድብል አምልኮ ( ስላሴ) እዴት ይታያል? ምዕራፍ ሁለት ስለ ነቢያቶች 6•ነብዩ ሙሀመድ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ማናቸው? 7•ነብዩን ማን ላካቸው? 8•ነቢያቶች በአጠቃላይ እምነታቸው ምን ነበረ ? 9•ነብዩ ኢሳ ( ኢየሱስ) በእስልምና ያለው ደረጃ እዴት ነው? 9•የነብያት ደረጃ በሌሎች እምነት? ምዕራፍ ሶስት ቅዱሳን መፅሀፍት 10•ቁርአን የማን ቃል ነው? 11•ቁርአን እዴት ወረደ? 12ቁርአን እዴት ተሰበሰበ? 13•ከቁርአን በፊት ለነቢያቶች የወረዱት መፅሀፍት ነበሩን? 14•ከቁርአን በፊት የወረዱት መፅሀፍቶች ማን በረዛቸው? 15•አላህ ለምድነው ለእነዛ መፅሀፍት ሀላፍትነትን ያልወሰደው? ምዕራፍ አራት ስለ ግድያ በእስልምና እዴት ይታያል 16•ጂሀድ ማለት ምን ማለት ነው ? 17•አላህ ከእስልምና ውጪ ያሉ እምነቶችን ግዶሉ ብሎ አዙአልን? 18•አላህ ምናይነት ሰዎችን ይወዳል? 19•በእስልምና በመግደል መፅደቅ አለን?? 20•ነብዩ ሙሀመድ ( ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያለምክንያት ይገድሉ ነበርን? 21•ስለ ጦርነት በሌሎች እምነቶች እዴት ነው? ምዕራፍ አምስት ስለ ትዳር ጉዳዮች 22•በእስልምና ለወንድ 4 ለምን ተፈቀደ? 23•በሌሎች እምነት ከአንድ በላይ አታግቡ ተብሉአልን? 24•ነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለምን ብዙ ሚስት አገቡ? 25•ሌሎች ነብያቶች አግብተዋልን ወይስ አላገቡም? 26•ነብዮ አይሻን (ረዲየላሁ አንሀ)በስንት አመቱአ አገቡአት? 27•በላሎች እምነት ያገቡ ነበሩ ወይስ የሉም? ምዕራፍ ስድስት ጀነትና ሽልማቶቹአ እና የገሀነም ቅጣት 28•በጀነት ውስጥ 72 ደናግል (ሁረል አይኖች)የሚባሉት አሉ ወይስ የሉም? 29•በጀነት ሴትና ወድን እኩል ናቸው ወይስ አይደሉም? 30•ለአማኞች በጀነት ሽልማታቸው ምድነው? 31•አማኝ ያልሆኑት በገሀነምስ ቅጣታቸው ምድነው ? ምእራፍ ሰባት የህሊናችን ጥያቄዎች ትምህርቱ ይሄን ይመስላል የሚጨመርበት ነገር ካለ እና በሚሰጠው ትምህርት ዙሪያ ሀሳብ አስተያየት እዲሁም ጥያቄ ካላቹ በሀሳብ መስጫው ላይ መወያየት ይቻላል 👇 በተረፈ ትምህርቱን 2000 ሰው ስንገባ እንጀምራለን ኢንሻአላህ ይሄን ፅሁፍ ቶሎ ቶሎ ሼር አድርገን ቻናሉን እናሳድገው ቻናላችን ችንን ይቀላቀሉ👉 @eslmnan_teqebelu ✍ከዐቃቢ ኢስላም ወንድም ነጃ @eslmnan_teqebelu ወሠላሙ ዐለይኩም
Показати все...
👍 1
ባለ 15 ገፁ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለት አዲሱ ረቂቅ አዋጅ! ትናንት ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት አጋርቻችሁ ነበር። በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/nhwdr/19721 ነገር ግን ይህ ረቂቅ አዋጅ አንዳንድ ሃሳቦቹ ከቀረበው ጥናት በተቃራኒ የሰፈሩ አዋጆችን አካቷል። ለምሳሌ፦ አንቀፅ 17 በግልፅ ሶላትን ለመከልከል የታሰበበት ሸፍጥ ያለው ሲሆን፣ አንቀፅ 19 ደግሞ በደፈናው የሙስሊም ሴቶችን አለባበስ ከሌላው ጋር በማነፃፀር ኒቃብ መልበስን «ማንነትን ለመለየት የማያስችል» በሚል ሽፋን ለመከልከል ታልሞበት ነው። ምክንያታቸው ሙስሊም ጠልነት ስለሆነ እንጂ የእውነት ማንነትን መለየት ቢሆን ኖሮ፤ ልክ ባንክና መሰል ቢዝነስ ላይ በሴት ጥበቃ ማንነትን እንደሚፈትሹት መለየት ይችሉ ነበር። ይህ አዋጅ ከመፅደቁ በፊት ሁሉም ሙስሊም እንዲስተካከል ማድረግ አለበት። እስከዛሬ ባልተጻፈ ህግ የጨቆኑን አንሶ፤ ዛሬ ጽፈው ሊጨቁኑን ሲመክሩ ዝም ብለን መመልከት የለብንም። ለነገው ትውልድ ነፃነትን እንጂ በኛ ዘመን የተመሰረተን ጭቆና አናወርስም። ሲቀጥል ገና ከረቂቅ አዋጁ ጥናት ጀምሮ ከ50% በላይ የሆነውን የሃገሪቱን ሙስሊም የወከለው አንድ ግለሰብ ነው። ይህ ግለሰብ ሃሳብ ቢያቀርብ እንኳ «በድምፅ ብልጫ» በሚሉት የዙልም ፍርድ ሃሳቡን ውድቅ ያደርጉበታል። ከ10 በላይ የአዋጁ ጥናት አዘጋጆች መካከል 50%+ ህዝብ ውክልናው 10% ብቻ ነበር። ይህ እጅግ አሳፋሪና በተደጋጋሚ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ የምናስተውለው ነው። ልክ እንደዚሁ የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽንም በወረዳ ደረጃ ሳይቀር ተወካዮችን ሲመርጥ፤ የሙስሊሙን ቁጥር ታሳቢ ባላደረገ መልኩ ነው። ታዲያ እንዲህ ሆኖ ምን የተሻለ ውጤት ይመጣል?
Показати все...
05:56
Відео недоступнеДивитись в Telegram
Repost from N/a
05:56
Відео недоступнеДивитись в Telegram
Показати все...
TikTok · 𝑖𝑏𝑟𝑎ℎ𝑖𝑚 إبراهيم

Check out 𝑖𝑏𝑟𝑎ℎ𝑖𝑚 إبراهيم’s video.

የክርስቶስ ስቅለት ዋንውኛ ተዋንያን እነማናቸው? 1.እግዚያብሄር እራሱን አጥፍቷል(እራሱን ያጠፋ አምላክ)። 2.እግዚያብሄር ልጁን ገድሏል (ልጁን የገደለ አምላክ)። 3.ሰይጣን በአስቆሮጡ በይሁዳ ገብቶ አስገደለው (ሰይጣን የክርስቲያኖች ባለውለታ ሆነ)። ከዚህ ውጪ አለ ምትሉትን ከታች ኮምቱ።
Показати все...
''የይሁዳ ጉዳይ'' ከአስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት መካከል አንዱ የነበረው አስቆርቱ ይሁዳ ኢየሱስን እንዲሰቀል ለካህናት አለቆች አሳልፎ የሰጠው ነው ይባላል። ነገሩን ስናስበው ይሁዳ ከካህናት አለቆቹ ከተቀበለው ሠላሳ ብር በስተቀር ሌላ ምንም ምክንያት ሳይኖረው የቅርብ ጓደኛውን ለዚያውም መምህሩንና ረዳቱን እንዲሰቀል አሳልፎ መስጠቱ ምክንያታዊነቱ ደካማ ነው። ቢሆንም የተፃፈው ይፈፀም ዘንድ የሚል የተለመደ ማስተባበያ ስላለ ለጊዜው እንስማማና ወደ ጉዳዩ እንግባ። ማቴዎስ እንደሚነግረን ኢየሱስ በሠላሳ ብር አሳልፎ እንደሚሰጥ አስቀድሞ በነቢያት አፍ ትንቢት ተነግሮለታል በማለት ቀጣዩን ማጣቀሻ ፅፏል፡- በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው። ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት። የሚል ተፈጸመ። ማቴ 27፡9-10 ይሁን እንጅ በኤርምያስ መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ የሚል ቃል የለም። ስህተቱ የተፈጠረው ማቴዎስ ማጣቀሻውን ሲፅፍ ከዘካርያስ መጽሐፍ ያገኘውን ኤርምያስ በማለት በመዘገቡ ነው። እኔም። ደስ ብሎአችሁ እንደ ሆነ ዋጋዬን ስጡኝ፤ ያለዚያ ግን ተዉት አልሁ። እነርሱም ለዋጋዬ ሠላሳ ብር መዘኑ። ዘካ 11፡12 ሁለተኛው ስህተት ደግሞ የካህናት አለቆቹ ለይሁዳ የሰጡት ‹‹ብር›› አሁን እኛ የምንጠቀምበት ገንዘብ (Currency) ሳይሆን የ‹‹ብር›› ማዕድን እንደሆነ ማሰቡ ነው። ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ? እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት። ማቴ 26፡15     ‹‹መዘኑለት›› የሚለው ቃል ብሩ የሚመዘን እንጅ አሁን የምንጠቀምበት አይነት የመገበያያ ገንዘብ እንዳልሆነ ይገልፃል። የእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስም ‹‹ሠላሳ ብር›› የሚለውን ቃል ‹‹thirty pieces of silver›› በማለት ገንዘቡ የብር ማዕድን እንደሆነ አብራርቶታል።   ነገር ግን የታሪክ ድርሳናት እንደሚነግሩን በኢየሱስ ዘመን የመገበያያ ገንዘብ (Currency) ነበር። በተለይም ስልጣኔ ቀድሞ የደረሰባቸው የመካከለኛው ምስራቅና የአካባቢው አገራት ከኢየሱስ ልደት ከሶስት መቶ ዓመታት በፊት ጀምሮ የመገበያያ ገንዘብ ነበራቸው። እናም ከታሪክ አንፃር በማቴዎስ ወንጌል ለይሁዳ ብር መዘኑለት መባሉ ስህተት ነው። ምናልባት ግን ዘካርያስ ከኢየሱስ ልደት ከ520 ዓመታት በፊት ይኖር እንደነበረ ስለሚታመን በእሱ ዘመን ብር መመዘኑ ትክክል ነው። በአንፃሩ ማቴዎስ ኢየሱስ የኖረበትን ዘመን በትክክል የተረዳው አይመስልም። ሶስተኛው ስህተት የይሁዳን አሟሟት ይመለከታል። ማቴዎስ እንደፃፈው ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ ከሰጠው በኋላ በሰራው ስራ ተፀፅቶ፡- ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ። ማቴ 27፡5 ይላል። ነገርግን ወንጌላዊው ሉቃስ እንደፃፈው በሚታመነው በሐዋርያት ስራ ውስጥ፡- ይህም ሰው (ይሁዳ) በዓመፅ ዋጋ መሬት ገዛ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ። ሐዋ 1፡18 የሚል ቃል የምናገኝ ሲሆን በግንባሩ ተደፍቶ ጭንቅላቱ በመሰንጠቁ ምክንያት እንደሞተ ይተርካል። አንዳንድ ሰዎች ታዲያ ሁለቱን ሃሳቦች ለማስታረቅ ይሁዳ ታንቆ ሳለ ገመዱ ተበጠሰና ወድቆ ሞተ ይላሉ ። ይሄ ጥሩ ልቦለድ መሆን ይችላል ። ማስረጃ ግን አይሆንም። ማቴዎስ እንደፃፈው ይሁዳ ታንቆ ሞቷል። በመታነቁ ባይሞት ኖሮ ታንቆ ሞተ ሊል አይችልም። በሐዋርያት ደግሞ ይሁዳ አልታነቀም። ይልቁንም ለማመን በሚያስቸግር ሁኔታ በግንባሩ ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀና አንጀቱም ተዘርግፎ ሞቷል። እናም መቀበል ያለብን ተጨባጩን እስከሆነ ድረስ ሁለቱ ሃሳቦች የተለያዩ ከመሆን አይወገዱም። ንቁ! በወንድም ሰልማን ገፅ 226-227 የተወሰደ https://t.me/muhammed6964 ወሠላሙ ዐለይኩም
Показати все...
ሙሐመድ የንፅፅር ማህደር

የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደኾነች ቃል ኑ፡፡(እርሷም) አሏህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፣በላቸው። እምቢ ቢሉም፦እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው።3:64 መልካም የማንበብና የማነፃፀር ጊዜ ይሁንሎ!

ክፍል 4 አርዮሳውያን (250-336 ዓ.ል) በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ፥ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡       የአስተምህሮቱ ዋና አራማጅ የእስክንድርያው ቄስ አርዮስ ሲሆኑ የተወለዱትም በሊቢያ ነው። አርዮስ ወደ ግብፅ በመሄድ በትክክለኛው የወንጌል ትምህርት ላይ ጥናትእንዳደረጉናበዋናነትም ከአንፆኪያው ሰማዕቱ ፃድቅ ሊሲያን ዘንድ እንደተማሩ ይነገራል። ፃድቁ ሉሲያን ከአርዮስ በፊት የነበሩ አርዮስ ይሏቸዋልም።       የካቶሊኩ የታሪክ ተመራማሪ ዋረን ካሮል ስለ አርዮስ በፃፈው ‹‹ቀጭንና ረጅም ሲሆኑ የሚማርክ ገፅታና የጠራ አነጋገር አላቸው። ሰዎች በስብዕናቸው ልቀትና በእውቀታቸው ምጥቀት ይማረኩላቸዋል።››       በማለት ይገልፃቸዋል።(1)       አርዮስ ኢየሱስ እንደማንኛውም ሰው ፍፁም ፍጡር ሲሆን ለፈጠረውም ለአብ ተገዥ ነው በማለት አስተምረዋል። ኢየሱስ የአብ ልጅ መባሉ አምላክነቱን እንደማይገልፅ ‹‹አብ ከኔ ይበልጣል›› በማለት የመሰከረውን በማስረጃነት ይጠቅሳሉ። ‹‹አብ ወልድን እንደ ልጁ ከያዘው ወልድ ለልጅነቱ መነሻ አለው ማለት ነው፤ ይህም ወልድ ያልነበረበት ጊዜ መኖሩን ያሳያል። ስለዚህም ወልድ ከምንምነት የተገኘ ፍጡር ነው።››       በማለት የሥላሴ አስተምህሮት ስህተት መሆኑን ለአትናቴዎስና ለተከታዮቹ በማስረጃነት አቅርበዋል።(2)       ይህም በአብያተክርስቲያናት መካከል ያለው ሰፊ የአስተምህሮት ልዩነት ለኒቂያ ጉባዔ መጠራት ምክንያት ሆኗል። የባዛንታየኑ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ በጊዜው ክርስትናን የማይቀበል አረማዊ ቢሆንም በግዛቱ ውስጥ የተፈጠረውን የእምነት ክፍፍል ለፖለቲካ ትርፉ ሲል መቋጫ ሊያበጅለት ጉባዔው እንዲካሄድ አድርጓል። በጉባዔው ላይም ከፍተኛ ውግዘት የደረሰባቸው የእስክንድርያው ቄስ አርዮስ ‹‹ወደ ትክክለኛው የኢየሱስ ትምህርት እንመለስ። ኢየሱስ አንድም ቀን አምላክ ነኝ ሲል ያላስተማረም። በሥላሴ አራማጆች አምላክ መደረጉ ፍፁም ስህተት ነው። ኢየሱስ እንደማንኛውም ሰው የአምላክ ፍጡር ነው።››       በማለት ማስተማራቸውትችና ስድብ አሸልሟቸዋል። በስተመጨረሻ የአርዮስን አስተምህሮት የሚገልፁ መጽሐፍት እንዲቃጠሉና ይዟቸው የተገኘ ሰውም በሞት እንዲቀጣ ንጉሱ ውሳኔውን አሳልፏል።(3)       አርዮስም ከውግዘቱ በኋላ ጥገኝነት ወዳገኙበት የፍልስጤም ምድር ሄደው ማስተማራቸውን ቀጥለውበት እንደነበር ይነገራልም። በዚያም እያሉ በ327 ዓ.ል የእስክንድርያው ጳጳስ ‹‹እስክንድር›› በመሞቱ በምትኩ አትናቴዎስ ይሾማል። ንጉስ ቆስጠንጢኖስም በአርዮስና በአትናቴዎስ መካከል ያለው ልዩነት ለማርገብና በመካከላቸው የትብብር መንፈስ እንዲፈጠር አርዮስን ወደ ቤተመንግስቱ እንዲመጡ ይጋበዛሉ። አዛውንቱ አርዮስም ግብዣውን ተቀብለው በቁስጥንጥንያው ቤተመንግሥት በተገኙበት ሌሊት ድንገት በተፈጠረ ህመም በአፋቸው ብዙ ደም ከፈሰሳቸው በኋላ በ86 ዓመታቸው ህይወታቸው ልታልፍ ችላለች።       የአርዮስ አሟሟት በሥላሴ አራማጆች የአምላክ ቁጣ ነው ሲያሰኝ በአንድ አምላክ የሚያምኑት ተከታዮቻቸው ግን ያለጥርጥር በምግብ ተመርዘው ነው ይላሉ።(4)       አርዮስ በድንገት በመሞታቸው ክፉኛ ያዘነው ንጉስ ቆስጠንጢኖስም የአሟሟታቸውን ጉዳይ የሚያጠና ቡድን አቋቁሞ እንደነበረ ይጠቀሳል። በምርመራው የአትናቴዎስ እጅ እንዳለበት በመረጋገጡ ለውግዘት ተዳርጓልም። ከዓመት በኋላምንጉስ ቆስጠንጢኖስ የአርዮስን ትምህርት ተቀብሎ በኒቆዶሚያው ጳጳስ ኢዮሲበስ እጅ እንደተጠመቀና እምነቱን እንደያዘ መሞቱ በታሪክ ተዘግቧል።(5)       ከአርዮስ ሞት በኋላ የእምነቱ ተከታይ የነበሩት በአብዛህኛው የሰሜን አፍሪካና የሜድትራኒያን አካባቢ ሕዝቦች ኢስልምና ሲመጣ ተልዕኮውን በቀላሉ ሊቀበሉት ችለዋል። በዚህም የካቶሊክ ሊቃውንት ነቢዩ ሙሐመድን (ዐሰወ) ዳግማዊ አርዮስ ይሏቸዋል።       በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በአገረ እንግሊዝ የሚገኙ ‹‹የቅድስት ካቶሊክ እና የአርዮሳውያን ሐዋርያት ቤተክርስቲያን›› የአርዮስን አስተምህሮት እንደሚከተሉ ገልፀዋል። ነገር ግን አርዮስ የሚቀበሏቸውን የማርያምን በተዓምር መፀነሷንና የኢየሱስን በአካሉ ወደ ሰማይ ማረግ አይቀበሉም። ይልቁንም ኢየሱስ ከዮሴፍና ከማርያም የተገኘ የስጋ ልጅ መሆኑንና ወደ ሰማይ ያረገውም በመንፈስ ብቻ እንደሆነ ያስተምራሉ።       የይሆዋ ምስክር ተከታዮችም ‹‹የዘመኑ አርዮሳውያን›› የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ሲሆን ‹‹ወልድ አብን ፍፁም ያውቀዋል።››       የሚለው አስተምህሮታቸው ከአርዮስ የተለየ ያደርጋቸዋል። አርዮስ አብ ለሰዎች በፈቃዱ ካሳወቃቸው ውጭ እውቀቱም ይሁን ስራው በወልድም ቢሆን በሌላ አካል አይመረመርም ይላሉ። መንፈስ ቅዱሳን በተመለከተ ደግሞ የይሆዋ ምስክሮች ‹‹እግዚአብሔር ፈቃዱን የሚፈፅምበት ኃይል ነው›› ሲሉ አርዮስ ግን መንፈስ ቅዱስ ‹‹ሰው ወይም የተመረጠ መልዓክ›› ሊሆን በማለት አስተምረዋል።       በብዛት በአሜሪካን የሚገኙትና ጥንታዊ የአካባቢውን የእምነት ፍልስፍናዎች እንደያዘ የሚታመነውን የጆሴፍ ስሚዝ (1830) ‹‹ሞርሞን›› የተሰኘውን መጽሐፍ እንከተላለን የሚሉት ‹‹Church of Jesus Christ of Latter day Saints›› ተከታዮችም የአርዮስን አስተምህሮት እንደሚከተሉ ይነገራል። ይሁን እንጅ አብዛሃኛው የእምነታቸው መመሪያዎች ከአርዮስ እንደሚለይ ጥናት ያደረጉ ሰዎች ፅፈዋል።(6) __ (1) Warren H. Carroll (1987). “The Building of Christendom” (History of Christendom, Vol 2), pp.10 (2) John McClintock (1867). “Cyclopedia of Biblical, Theological and Ecclesiastical Literature”(Vol.7), p. 45. (3) Wisconsin Lutheran College (2010).“Fourth Century Christianity: Edict by Emperor Constantine against the Arians   (4) Edward Gibbon (2012). “The History of the Decline and fall of the Roman Empire” (Vol 8)   (5) Vasilief, Al (1928).“History of the Byzantine Empire: The Empire from Constantine the Great to Justinian” (6) Daniel S. Tuttle (1981). Mormons A Religious Encyclopedia: 1578 ------------------------------Ω-------------------------------------- https://t.me/muhammed6964 ወሠላሙ ዐለይኩም
Показати все...