1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
ስዋዊነት ፣የማህበራዊ ስብራት ተጐጂ የሆኑትን ሴቶች ህይወት ከመቀየር ይጀምራል::
እነሆ " ለነገዋ” የተሻለው ሁሉ ይገባታል!
Namummaan jireenya dubartoota cabinsa hawaasummaan miidhamoo ta'an jijjiiruu irraa eegala. Kunoo "Borii Isheef" waanti fooyya'aa hundi isheef mala!
ከአፍሪካ የንግድና ልማት ባንክ ግሩፕ ፕሬዘዳንት ከሆኑት አቶ አድማሱ ታደሰ ጋር በጋራ በምንሰራባቸው ጉዳዩች ዙሪያ ተወያይተናል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክፍል ሰማይ ላይ የታየው ክስተት በሰው ሰራሽ የስፔስ ቁስ ምክንያት የተከሰተ ሊሆን ይችላል፦ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦፓሻል ኢኒስቲትዩት
*************
በትናንትናው ምሽት በደቡብ ኢትዮጵያ ክፍል ሰማይ ላይ እየተቃጠለ ተቆራርጦ ወደ ምድር ሲጓዝ የታየው ቁስ በሰው ሰራሽ የስፔስ ቁስ ምክንያት የተከሰተ ሊሆን እንደሚችል የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦፓሻል ኢኒስቲትዩት ገለፀ፡፡
በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦፓሻል ኢኒስቲትዩት የከባቢ አየር ሳይንስ ተመራማሪ የሆኑት ገመቹ ፋንታ (ዶ/ር) ከኢቢሲ ዶት ስትሪም ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ጊዜ ያበቃላቸው ሳተላይት እንዲሁም ሳተላይቶችን የመጠቁባቸው የሮኬት ቁርጥራጮች ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡
በማንኛውም ሰው ሰራሽ መንገድ ህዋ ላይ የሚንቀሳቀሱ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ወደ ከባቢ አየር ውስጥ ሲገቡ የመቃጠል እና ተሰባብሮ የመውረድ ምልክቶችን እንደሚያሳዩ ገልጸዋል፡፡
ክስተቱ የተፈጠረው በተፈጥሮአዊ የህዋ አካላት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡
ከመሬት እና ከሶላር ሲስተም አፈጣጠር አንጻር አለቶች በመኖራቸው በማንኛውም ጊዜ እየተቆራረጡ ሊወርዱ እንደሚችሉ ነው ያነሱት፡፡
በዓለም ላይ እንደዚህ ያለ ሁነት እንደሚከሰቱ የሚናገሩት ተመራማሪው፤ አልፎ አልፎ ቁጥራቸው በርከት ያሉት ወደ ምድር እንደሚወርዱም ገልፀዋል፡፡
ሰው የሚኖርበት ቦታ ከ 4 እስከ 5 በመቶ እንደማይበልጥ የሚናገሩት ተመራማሪው፤ ተቆራርጠው የሚወርዱ ነገሮች ከሰው ዕይታ ውጪ የሚከሰቱበት ሁኔታው ስለመኖሩም ጠቅሰዋል። አልፎ አልፎ ግን ለሰው ዕይታ እንደሚጋለጡም ነው አያይዘው የገለጹት፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በዓመት እስከ 6 ሺህ ድረስ ተቆራርጠው ምድር የሚደርሱ እና አለፍ ሲልም የአሸዋ ቅንጣት በመሆን ወደ ምድር የሚወርዱ ስለመኖራቸው ነው ተመራማሪው የተናገሩት፡፡
የሚቃጠሉበት ምክንያት ደግሞ ወደ ከባቢ አየር ሲገቡ ከከባቢ አየር ጋር በሚያደርጉት ፍትጊያ የሚፈጠር ስለመሆኑም አያይዘዋል፡፡
"አሁን እንዳለን መረጃ በደቡባዊ ክፍል የታየው ምስል ሰማይ ላይ እየተቃጠለ ነው የሄደው፤ አርፏል አላረፈም የሚለውን እስካሁን ማወቅ አልቻልንም" ብለዋል፡፡
ምድር ሦስት አራተኛዋ ውኃ በመሆኑ በአብዛኛው ውኃ ውስጥ እንደሚወድቅ የሚናገሩት ተመራማሪው፤ ሰዎች የሚኖሩበት አካባቢ ካልወደቀ በስተቀር ጉዳት እንደሌለው ነው የተናገሩት፡፡
Ethiopian Broadcasting Corporation
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በቀን 30 ሚሊዮን ሊትር ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው የቦሌ አራብሳ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል::
ከለዉጡ ወዲህ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ጀምሮ የመጨረስ አንዱ ማሳያ የሆነዉ ይህ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የከተማችንን የፍሳሽ ማጣራት አቅም ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረበት በቀን 48 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ወደ በቀን233 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ከፍ ማድረግ አስችሎናል::
ይህ የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ከ240 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአካባቢውን ነዋሪዎች የዘመናዊ ፍሳሽ ማጣሪያ ፣ስርዓት ተጠቃሚ የሚያደርግ ነዉ።
ለአንድ ከተማ ወሳኝ ከሆኑ መሰረተ ልማቶች መካከል የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓትን ማዘመን ትልቅ ስራ ሲሆን ጤንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ከመፍጠር አኳያ ያለው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡በመሆኑም ይህ የፍሳሽ ማጣሪያ ስራ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓታችንን የሚያዘምን፣ የከተማችን ነዋሪዎችን እና በአጎራባች አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎት የረዥም ጊዜ ቅሬታን ምላሽ የሚሰጥ ፣ከተማችንን ከብክለት የጸዳች፣ ውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ እዉንየሚያደርግ ነዉ።
ፕሮጀክቱ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዖ ያደረጋችሁ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ኮንትራክተርና አማካሪ ድርጅት ክፍለከተማው ከምንም በላይ በፈቃደኝነት ለልማት ከቦታው የተነሱ አርሶ አደሮችን በነዋሪው እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በተለያዩ አካባቢዎች በሰማይ ላይ የታየውን ተቀጣጣይ የሚመስል ቁስ ምንነት እያጣራሁ ነው”፦ የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ
**************************
በትናንትናው ዕለት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍሎች ምንነቱ በውል ያልታወቀ በሰማይ ላይ ሲምዘገዘግ የሚታይ ተቀጣጣይ ነገር መመልከታቸውን በርካቶች የአካባቢው ነዋሪዎች በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ላይ በተንቀሳቃሽ ምስል እና በፎቶ አስደግፈው ሲያጋሩ ተስተውሏል።
ይህንንም ተከትሎ ከምሽቱ 1፡30 ገደማ በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ ምንነት በማጣራት ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ አስታውቋል።
የክስተቱን ምንነት በእርግጠኝነት ለማብራራት ያስችል ዘንድ ሁኔታውን በቅርበት እያጣራሁ ነው ያለው ተቋሙ የተጣራ መረጃ ሲደርስም ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚደረግ እና የማጣራት ሥራው እንኪጠናቀቅ ሁሉም ሰው በተረጋጋ መንፈስ እንዲጠባበቅ አስታውቋል።
ተቋሙ በታዩት ተንቀሳቃሽ ምስሎች ለመመልከት እንደቻለውም የእነዚህ አካላት ስብስብ የጠፈር ፍርስራሾች አሊያም የሚቲዮር አለቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ መላምቱን አስቀምጧል።
Ethiopian Broadcasting Corporation
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በተለያዩ ተቋማት ውስጥ መፈጸም እና መሟላት የሚገባቸው የቅድመ አደጋ መከላከል የደህንነት ተግባሮች:-
1.በቂ የማምለጫ በሮች፣ /Emergency Exit/
በአንድ ድርጅት ዉስጥ የበሮች ብዛት ከሁለት በላይ ሆነዉ መዘጋጀት የሚኖርባቸዉ ሲሆን የበሮች ብዛት ሊወሰን የሚችለዉ የሚከተሉትን ነጥቦች መሠረት በማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡
የድርጅቱን ስፋት፣
የጥሬ ዕቃዎችና የምርት ዉጤት ብዛትና ዓይነት፣
የማምረቻ መሣሪያዎች ብዛት፣
በድርጅቱ ተቀጥረዉ ያሉና ለወደፊት ሊቀጠሩ የታሰቡ ሠራተኞች ብዛት፣
የተገልጋዮች /የጎብኝዎች/ ብዛትን ታሣቢ በማድረግ ነዉ፡፡
የማምለጫ በሮች አላማ፡-
• የተወሰኑ በሮች በአደጋ ወይም በቃጠሎ አደጋ ቢያዙ ቀሪዎቹ ፡-
1. ሰዎች ከአደጋዉ ስፍራ በቀላሉ ማምለጥ እንዲችሉ
/ሕይወትን ለመታደግ/
2. ንብረትን ከአደጋ ለማዳን፣
3. አደጋዉን በተለያዩ አቅጣጫዎች በመግባት በአፋጣኝ በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንዲቻል ነዉ፡፡
2.በቂ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎች፡-
• እንደ ድርጅቱ የሥራ ባሕሪይና ባሉት የሥራ ክፍሎች ብዛት አኳያ በቂና ተገቢ የሆኑ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎ ሊዘጋጁ ይገባል፡፡
እነሱም፡-
• በቋሚነት /Fixed Installation/
• በተንቀሳቃሽ /Mobile/
• በቀላሉ በእጅ የሚያዙ /Portable/ የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎችን እንዲሟሉ በማድረግ እይታን ከሚከለከሉና መሰናክል ከሚሆኑ ነገሮች ነፃ ሆነዉ በስድስት ወር አንድ ጊዜ ፍተሻ እየተደረገላቸዉ ደህንነታቸዉን በማረጋገጥ ከመሬት በ1.50 ሜትር ከፍታ በግድግዳ ላይ ማዘጋጅት ያስፈልጋል፡፡
3.በእሳት አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ሙያ የሰለጠነ የሠው ሀይል ማዘጋጀት
4. ዓለም አቀፍ የድህንነት ምልክቶችን ማዘጋጀት
• በድርጅቱ ውስጥ ባለው የጥሬ ዕቃ፣ የምርት ውጤት ዓይነት፣ እንደተቁዋሙ አይነትና የአገልግሎት አሰጣጥ፣ እንዲሁም የአንድን የሥራ አካባቢ ምንነት የሚገልፁ ምልክቶችን በቅድሚያ ማዘጋጀት ተገቢ ሲሆን ይህም በሰውም ሆነ በንብረት ላይ አደጋን ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን በቅድሚያ በማስገንዘብ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ያስቀራሉ /ይከላከላሉ/፡፡
5. በቂ መተላለፊያዎች፡-
በድርጅቱ ዉስጥ የሚከሰቱ የእሳት ቃጠሎና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎችን በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠር፣ እንዲሁም በህይወትም ሆነ በንብረት ላይ ሊደርስ የሚችለዉን አደጋ ለማስቀረት፣ የጉዳቱን መጠን ለመቀነስ እንዲሁም ተገቢዉን ዕርዳታ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመስጠት ያመች ዘንድ መተላለፊያ መንገዶች ከማናቸዉም አደናቃፊ ነገሮች ነጻ ሆነዉ እና ከመዉጫ በሮች ጋር ትይዩ ሆነዉ ሊዘጋጁ ይገባል፡፡
6. የማንቂያ ደወል / Fire Alarm/፡-
• ከሥራ መግቢያና መዉጫ ሰዓት ከሚሰማዉ የደወል ድምጽ የተለየ ሆኖ የእሳት ቃጠሎ አደጋ መከሰቱን የሚያስገንዘብ ሲሆን እያንዳንዱ ሠራተኛ የሣይረኑን ድምጽ በሚስማበት ወቅት አደጋ መፈጠሩን ተገንዘቦ አደጋዉ ከተፈጠረበት አካባቢ እራሱን ነፃ በማድረግ በአደጋ ጊዜ መገናኛ ወይም መሰብሲቢያ ሥፍራ እንዲገኝና በአቅራቢያዉ የሚያገኘዉን የማጥፊያ መሣሪያ ይዞ በመሄድ እሳቱን ለማጥፋት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ ያስችላል፡፡
7የአደጋ ማሳወቂያ መሳሪያዎች /Detectors/
• የእሳት ቃጠሎ አደጋን ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን የሚያሳዉቁ ማለትም ከሚቀጣጠልዉ ነገር በሚወጣዉ ጭስ፡- ሙቅትና ነበልባል በቀላሉ ሊቀጣጠሉ የሚችሉ ጋሶች ከመያዣ ዕቃዎች ዉስጥ አምልጠዉ በመዉጣት ከፍተኛ ቃጠሎን በመፍጠር ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከመፈጠሩ አስቀድሞ ለመቆጣጠር እንዲቻልና በተለይም በሰዉ ላይ ጉዳት ለያደርሱ የሚችሉ ሁኔታዎችን ጭምር የሚጠቁሙ መሣሪያዎች ሰለሆኑ እንደየሥራ ባህሪዉ በተገቢዉ ቦታ ላይ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡
8.የዕቃዎች አደራደር፡-
በማናቸዉም ድርጅቶች ዉስጥ በተለያዩ መጋዘኖች ዉስጥ ንብረቶች ሲቀመጡ በዓይነታቸዉና እንደየመቀጣጠል ባህሪያቸዉ ተለይተዉ በየድርድሩ መካከል በቂ መተላለፊያ በማስቀረት ከግድግዳዉ የተወሰነ ክፍተት በመተዉና በመጋዘኑ ዉስጥ በቂ የአየር ምልልስ እንዲኖር በማድረግ የንብረት አያያዝ ወይም የእቃዎች አደራደርን ከቃጠሎ አደጋ ሊጠበቁ በሚችሉበት ሁኔታ ማከማቸት ይገባል፡፡ ይህም በእሳት ቃጠሎ አደጋ ወቅት ንብረትን ከአደጋ ሥፍራ ለማዳን፣ ቃጠሎዉን በቀላሉ ለመቆጣጠርና እሳቱ እንዳይስፋፋ ይረዳል፡፡
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለሴተኛ አዳሪነት እና ለተለያዩ የማህበራዊ ችግሮች ተጋልጠዉ የነበሩ 400 እህቶቻችንን እና ሴት ልጆቻችንን ለሁለተኛ ዙር ስልጠና እንኳን ደህና መጣችሁ ብለናል።
በመጀመሪያ ዙር ስልጠና የወሰዱ ከ300 በላይ የሚሆኑ እህቶቻችን በ17 አይነት ዘርፎች የክህሎት እና ተሃድሶ ስልጠና ወስደዉ የሞያ ባለቤት ሆነዉ የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ።
በማህበረሰባችን ውስጥ ስር በሰደደ ኃላቀር አስተሳሰብ፣ ኢፍትሃዊነት ፣ ፆታዊ ጥቃት እና ተጋላጭነት ምክንያት በእህቶቻችን እና ሴት ልጆቻችን ላይ የሚደርስ ማህበራዊ ስብራትን በመጠገን ማህበራዊ ፍትህን ለማስፈን የጀመርነውን ስራ በመደገፍ ከጎናችን የቆማችሁ የከተማችን ልበ ቀና ባለሃብቶችን፣ የቦርድ አባላት፣በሞያችሁ እየደገፋችሁን ያላችሁትን እንዲሁም ራዕያችንን ወደ መሬት ለማውረድ የደከማችሁ የማዕከሉ አመራሮችንና፣ ሰራተኞች እና መምህራንን በእህቶቻችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
የሁለተኛ ዙር ሰልጣኝ የሆናችሁ እህቶቻችን የማዕከሉ ቆይታችሁ እራሳችሁን የምትለውጡበት፣ ለቤተሰቦቻችሁ እንዲሁም ለሌሎች መለወጥ አርአያ የምትሆኑበት እንዲሆን አደራ እያልኩ የሚሰጣችሁን ስልጠና በትጋት በመከታተል እንደ መጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ስኬታማ እንድትሆኑ ጥሪ አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
Giddugala Haaroomsaa fi Guddina Ogummaa Dubartoota Boriitti obboleewwan keenyaa dubartootaa fi ijoolee keenya dubartootaa rakkoolee adda addaatiif saaxilamanii turan 400 leenjii marsaa 2ffaatiif baga nagaan dhuftan jennee simanneerra.
Leenjii marsaa jalqabaa kan fudhatan obboleewwan keenya 300 ol ta'aniif ogummaa dameelee akaakuu 17 fi leenjii haaroomsaa fudhatanii ogummaa qabaatanii carraan hojii uumameefiira.
Sababa ilaalcha duubatti hafaa hawaasa keenya keessa tureen, haqa-malummaa miidhaa saalaa fi saaxilamummaatiin cabiinsi hawaasummaa obboleewwan keenyaa fi ijoolee keenya dubartootaa irra gahu suphuudhaan haqummaa hawaasummaa diriirsuuf hojii eegalle deeggaruun nu cinaa kan dhaabbattan abbootii qabeenyaa onnee garii magaalaa keenyaa, miseensoota boordii, ogummaa keessaniin nu gargaaraa kan jirtan akkasuma mul'ata keenya lafatti gadi buusuuf kanneen dadhabdan hooggantoonni fi barsiisotni giddu galichaa maqaa obboleewwan keenyaatiin isin galteeffachuun barbaada.
Obboleewwan keenya leenjitoota marsaa 2ffaa kan taatan turtiin keessan giddu galichaa kan itti of jijjiirtan, maatii keessaniif akkasumas jijjiiramuu kanneen birootiif fakkeenya kan itti taatan akka ta'u amaanaa isiniin jechaa leenjii isiniif kennamu ciminaan hordoftanii akka leenjitoota marsaa jalqabaa milkaa'ota akka taatan yaamicha dhiheessa.
Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሀገራዊ ፕሮጀክቶች በክልሎች ደረጃ ያለ አፈፃፀም ግምገማ ተደርጎ እንደነበር ይታወሳል። ይኽን ተከትሎ በክቡር አቶ አደም ፋራህ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት የተመራ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ ተካሂዷል።
በስብሰባው የመስክ ምልከታና ግምገማ ቡድኖች መሪዎች ግምገማዎቻቸውን እና ግኝቶቻቸውን አቅርበዋል። ይኽ የሱፐርቪዥን እና የግብረመልስ ሂደት ሰፋ ያለው ሥርዓትን የማጠናከር ተግባር አካል ሲሆን አፈፃፀሞችን በዞን እና ወረዳ ደረጃ በመመልከት ክፍተቶችን መለየትን አላማ አድርጓል።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን እና ለመድሃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ!
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
