1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር ያካሄዳቸው የጥር ወር ዋና ዋና የስራ እንቅስቃሴ በምስል ሲቃኝ:-…
See more
በከተማዉ እያጋጠሙ ያሉ አደጋዎችን ለመቀነስ በሚደረገዉ ጥረት የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎች ሚና የላቀ እንደሆነ ተገለፀ፡፡
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በከተማዉ እያጋጠሙ ያሉ አደጋዎችን ለመቀነስ እየተደረገ ያለዉን ጥረት ለማገዝ የሚያስችል ዉይይት ከሚዲያ ተቋማት ኃላፊዎችና ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በዛሬው እለት የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ዉይይት አካሂዷል ።
የዉይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሀመድ እንደተናገሩት በአዲስ አበባ እያጋጠሙ ካሉ አደጋዎች የአብዛኛዎቹ የአደጋ መንስዔ በጥንቃቄ ጉድለት የሚከሰቱ በመሆናቸው እነዚህ በሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት እያደረሱ ያሉትን አደጋዎች የህብረተሰቡን የጥንቃቄ ባህል በማሳደግ አስቀድሞ መከላከል እንደሚቻል ጠቅሰው ለዚህም የሚዲያ ተቋማትና ባለሞያዎች ሚና የማይተካ በመሆኑ ከኮሚሽን መ/ቤቱ ጋር በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በበኩላቸው እንደተናገሩት አደጋን አስቀድሞ በመከላከል ከተማዋን ሰላማዊና ከአደጋ የተጠበቀች ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን አስታዉሰዉ የሚዲያ ተቋማትና የሚዲያ ባለሞያዎች ድርብ ኃላፊነት ያለባቸዉ በመሆኑ የአደጋ መከላከልን ጉዳይ በዘገባዎቻቸዉ በማካተት የህብረተሰቡ የጥንቃቄ ባህል እንዲያሳድጉ አሳሰበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት መሠረተ ልማትና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ግዛቸው አይካ መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተዉ ባደረጉት ንግግር የአደጋ ስጋትን አስቀድሞ በመለየት ህብረተሰቡን ከማስተማርና ከማስገንዘብ አኳያ የዉይይት መድረኩ ወሳኝ እንደነበረ ጠቅሰዉ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የአደጋ ክስተትን መረጃ በሂደት ላይ እያለ እንዲሁም የአደጋዉን መነሻ ምክንያትን ከሚመለከተዉ አካል
አጣርቶ መዘገብ እንደሚገባቸዉም አስረድተዋል።
ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሁፍ በአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ ኃላፊ በም/ኮሚሽነር ደሳለኝ ፉፋ ቀርቦ ከተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት ቀርቦ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ከተማ አቀፉ ህዝባዊ ኮንፈረንስ በሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ እና ተግባቦት ፈጥሮ ተጠናቋል!
በብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና ም/ቤት አባላት የተመራው ሀገር አቀፍ የህዝብ ኮንፈረንስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ አባገዳዎች ፣ ወጣቶች ፣ ሴቶች ፣ የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በከተማ ደረጃ የተካሄደ ሲሆን በፓርቲያችን አቅጣጫዎች ዙሪያ የጋራ ተግባቦት መፍጠር አስችሏል።
የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ ለከተማ አቀፍ ውይይቱ የተዘጋጀውን መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን ከተሳታፊዎች በተነሱ ሀሳቦችም ዳብሯል።
የህዝባችን ተሳትፎ አጠናክረን ፣ ተግዳሮቶችን እየተሻገርን ፣ ፈተናን ወደ ድል እየቀየርን ወደ ፊት መራመድ ግድ ይለናል ያሉት ወ/ሮ አለሚቱ ፓርቲያችን በሁለተኛው መደበኛ ጉባዔው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች በቁርጠኝነት ለመፈፀም ቃልአችንን አድሰናል ብለዋል።
ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት የሀገረ መንግስት ግንባታውን ለማጠናከር ጥራት ያለው የአባል ምልመላን ጨምሮ የአመራሩንና የአባላትን የአመለካከትና የተግባር አንድነት በማጠናከር ፣ ጠንካራ ኢንስፔክሽን በማካሄድ ቃልን አልቆ ለመፈፀም ብርቱ ጥረት እንደሚደረግ አስገንዝበዋል።
ነፃ እና ገለልተኛ ተቋማትን ለመገንባት የተጀመሩ መሰረታዊ ስራዎችን በማፅነት የፍትህ ስርዓቱን ይበልጥ ለማሻሻልም ርብርብ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡
ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ስኬታማነት ፣ ለሽግግር ፍትህ ስርዓቱ ውጤታማነት ሁሉም የድርሻውን በማሳረፍ የሀገር ግንባታውን ማፋጠን እንደሚገባም ተጠቅሷል።
የኢኮኖሚ ዕድገቱን ማፋጠን በብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ ልዩ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን ያመላከቱት ርዕሰ መስተዳድሯ፣ ለጋራ ሀገራዊ ዕድገቱ የአጎራባች ክልሎች ቅንጅት ይበልጥ እንዲጠናክር ይሰራል ብለዋል።
የወጣቶችን እና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀናጀ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሯ በቀጣይ 9 ነጥብ 15 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።
ለሀገራችን መልማት ዕምቅ አቅም የሆነውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃት እንደ ሀገር የተጀመረው ውጤማ ርብርብ ይበልጥ እንደሚጠናከርም ተመላክቷል።
ከብልሹ አሰራር የተላቀቀ ስኬታማ ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ እመርታ ለማስመዝገብም በቴክኖሎጂ የታገዘ ብርቱ ጥረት ይደረጋል ተብሏል።
ለሀገር ግንባታ ፣ ገዥ ትርክትን ለማስረፅ ፣ የኢትዮጵያን እውነታ ለመግለፅ ውጤታማ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ ማከናወን የፓርቲያችንም አቅጣጫ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ማህበራዊ ሚዲያውን ለሀገር ግንባታ በማዋል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም ተገልጿል።
የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው በህዝባዊ ኮንፈረንሱ ላይ እንደተናገሩት ከቃል እስከ ባህል በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ምን አቅደን ምን አሳካን ፣ምን ገጠመን ፣ እንዴት ተሻገርነው የሚሉ ጉዳዮች በጥልቀት መገምገማቸውን ጠቅሰዋል።
ከጉባዔው ተሳታፊ አመራርና አባላት በተጨማሪ ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ፣ ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም በርካታ የውጭ ሀገር እህት ፓርቲ አመራሮችም ጭምር በተገኙበት የተካሄደው የፓርቲው ጉባዔ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የስራ አስፈፃሚ እና የምክር ቤት አባላት ምርጫ እንደተካሄደበትና ሀገራችንን እና ህዝባችንን ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ አቅጣጫ መቀመጣቸውንም አስገንዝበዋል።
የብልፅገና ፓርቲን የመጀመሪያ ጉባዔ አቅጣጫዎች ህዝብን ባሳተፈ የአባላትና የአመራሩ ርብርብ በተግባር መረጋገጣቸውን ያወሱት ዶ/ር እንዳሻው የዛሬው ህዝባዊ ውይይትም ለለሁለተኛው ጉባዔ አቅጣጫዎች ስኬት የህዝባችን ድጋፍና ተሳትፎ እንዲጠናከር እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡
ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የተጀመረውን አበረታች ርብርብ በማጠናከር የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል እንዲሁም የጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ጅማሮውን ለማጠናከር ለብልፅግና ጉባዔ ውሳኔዎች ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በከተማ አቀፍ ኮንፈረንሱ ላይ የተሳተፉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተመዘገበ ያለውን አጓጊ ልማት አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ህብረ ብሔራዊ አብሮነትን ለማዳበር የሚጠቅሙ ገንቢ ሀሳቦችን ያቀረቡ ሲሆን በጋራ ትብብር ሊታረሙ ይገባል ያሏቸውን የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችንም አንስተዋል።
ከፍተኛ አመራሩ ህዝብን ለማድመጥ በየጊዜው እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ክብር የሚገባው መልካም ተግባር ነው ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች ለመሪዎቻችንን ያለንን ክብር ይበልጥ በመትጋት ራዕያቸውን በማሳካት እናረጋግጣለን የሚል ይዘት ያላቸው ሀሳቦችን አንፀባርቀዋል።
የኑሮ ውድነቱ ቁልፉ መፍትሄ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ በመሆኑ ለግብርና እና ለኢንዱስትሪ ምርታማነት እንደ ከተማም እንደ ሀገርም የተጀማመሩ ጥረቶችን ማጠናከር እንደሚገባም ተገልጿል።
የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው የመሩት ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና ሌሎችም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ያስተባበሩት ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች የተሳተፉበት ከተማ አቀፍ የህዝብ ኮንፈረንስ በሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ እና ተግባቦት ፈጥሮ ተጠናቋል።
ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ኮንፈረንሱ በከተማችን በተለያዩ መርሀ ግብሮች መካሄዱን ቀጥሏል !
በብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና ም/ቤት አባላት የሚመራው ሀገር አቀፍ የህዝብ ኮንፈረንስ በከተማ ደረጃ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ የብልዕግና ተምሳሌት በሆችው ከተማች የኢትዮጵያን መፃኢ ጊዜ ከፍ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ መክሮ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን አውስተዋል።
ህዝባዊ ኮንፈረንሱ ብልፅግና ሀገር እየመራ ያለ ፓርቲ እንደመሆኑ ውሳኔዎቹን ህዝብ በማወያየት ተጨማሪ አቅም ለመፍጠር መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሞገስ ከዛሬው የማጠቃለያ ኮንፈረንስ በፊትም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ስኬታማ ውይይቶች መካሄዳቸውን ጠቅሰዋል።
እስካሁን በተደረጉ ህዝባዊ ውይይቶች የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮችንም እና ለመፍታት የተደረገውን ርብርብም አቶ ሞገስ ለከተማ አቀፍ ውይይቱ ታዳሚዎች አቅርበዋል።
ከሴቶችና ከወጣቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ፣ የመልካም አስተዳደር ፣ የልማት ጥያቄዎች ፣ የፅንፈኝነት አስተሳሰብና ተግባርን መታገል ላይ እና አስተማማኝ ዘላቂ ሰላም ለመገንባት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ምን እንደሚመስሉ በህዝባችን ጥያቄዎች ሲቀርቡ እንደነበር ተወስቷል።
የፌዴራል መንግስቱ የሚመልሳቸው በፌዴራል መንግስቱ እየተመለሱ መሆኑ ፤ በከተማ ደረጃ የሚመለሱ የህዝብ ጥያቄዎች ደግሞ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማቀናጀትና ህዝብን በማስተባበር እየተመለሱ መሆናቸው ተገልጿል።
በከተማችን ባለፉት ሶስት ዓመታት 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩ ከወጣቶችና ከሴቶች ተጠቃሚነት አንፃር ተጠቅሷል።
የከተማችን ገቢ 2011 ዓ/ም 30 ቢሊዮን ብር አካባቢ የነበረ ሲሆን በዚህ ዓመት 2030 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ በመልካም አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
ከከተማዋ በጀት 70 በመቶው የሚሆነውን ለካፒታል በጀት ማዋል በመቻሉ ተጨባጭ ስኬቶች መመዝገባቸው ተጠቅሷል።
በሌማት ቱሩፋት ፣ በከተማ ግብርና እና በአረንጓዴ ልማት እና በሜጋ ፕሮጀክቶችም አበረታች ስኬቶች ተመዝግበዋል።
በማህበራዊ ልማትም በተለይም የትምህርት እና የጤና ተደራሽነትን እና ጥራትን ለማረጋገጥ ሰፋፊ ስራዎች ተከናውነዋል።
ለወጣቶችና ለታዳጊዎች 1300 የስፖርት ማዘውተሪያዎች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማረምም በቴክኖሎጂ የታገዙ ሰፋፊ የሪፎርም ተግባራት እየተሰሩ ነው።
ህዝባችን አዲስ አበባን እንደ ስሟ አበባ እያደረገ የኑሮ ደረጃውን ያሻሻለውን የመጀመሪያውን ዙር የኮሪደር ልማት ውጤት እያጣጣመ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሞገስ ሁለተኛው ዙር ደግሞ ሰፍቶ እየተተረጎመ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
የፓርቲውን የመጀመሪያ ጉባኤ ውሳኔዎች ለማሳካት በተደረጉ ጥረቶች ዘርፈ ብዙ ውጤቶች ተመዝግበዋል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባኤ ውሳኔዎችን ለማሳካት በተደረጉ ጥረቶች ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
"ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ሃሳብ በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ህዝባዊ ውይይት በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፥ በብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችን ለማሳካት በተደረጉ ሥራዎች ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።
ፓርቲው መላውን ህዝብ በማሳተፍ በሁለንተናዊ ልማት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ሥራዎችን ማከናወኑን ጠቅሰዋል።
የሃገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋት፣የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥና ዘላቂ ሰላምን መገንባት ረገድ መጠነ ሰፊ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
በገዢ ትርክት ግንባታና ብሔራዊ ጥቅምን በማረጋገጥ በኩልም አበረታች ለውጥ ተመዝግቧል ብለዋል።
የምግብ ሉዐላዊነትን ለማረጋገጥ በተደረጉ ጥረቶችም ሁኔታ ለውጥ መመዝገቡን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በጤና፣በትምህርትና በሰው ተኮር ልማቶች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
የአመራርና የአባላት ብቃትና ጥራትን በማረጋገጥ እንዲሁም ውጤታማ የምዘናና የግምገማ ስርዓትን በማበጀት ረገድ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ይሁን እንጂ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ አኳያ፣ ህዝብን የሚያረካ መንግስታዊ አገልግሎትን ከማቅረብና የድህረ እውነት ፈተናዎችን ከመሻገር አኳያ ውስንነቶች መኖራቸውን ገልጸዋል።
የመደመርን መንገድና ብልጽግናን ግብ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው ፓርቲው እነዚህና መሰል ክፍተቶችን ነቅሶ ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
በመድረኩ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣የሃይማኖት አባቶች፣ሴቶች፣ ወጣቶችና ሌሎች የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።
AMN
በብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና ም/ቤት አባላት የሚመራው ሀገር አቀፍ የህዝብ ኮንፈረንስ በከተማ ደረጃ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ተጀምሯል።
የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው ፣በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና ሌሎችም በየደረጃው የሚገኙ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ለከተማ አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ውይይቱ የሀይማኖት አባቶች ፣ አባገዳዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ሴቶች ፣ ወጣቶች እና ሌሎችም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ከሁሉም ክ / ከተሞች በመምጣት ህዝባዊ ኮንፈረንሱ በሚካሄድበት ቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ታድመዋል።
ሀገር አቀፍ የሕዝብ ኮንፈረንስ ከነገ ጀምሮ በ25 የኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች ይካሄዳል።
በብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና ም/ቤት አባላት የሚመራው ሀገር አቀፍ የህዝብ ኮንፍረንስ ከነገ ጀምሮ በ25 የኢትዮጵያ ከተሞች መካሄድ ይጀምራል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀገር አቀፍ የህዝብ ኮንፈረንስ ላይ ለመሳተፍ አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል።
ከንቲባ አዳነች እና ልዑካን ቡድናቸዉ አርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል ። በቆይታቸውም በከተማዋ የተሰሩ የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ ፤ የህዝብ የምክክር መድረክ ላይም ይሳተፉሉ ተብሎ ይጠበቃል።
