1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
ትውልድን መገንባት ቀዳሚው ሥራችን ነው!
ዛሬ የመረቅናቸዉ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች በታማኝነት የማገልገል እና የትጋት ዉጤቶች ናቸዉ።
በእርጅና ብዛት የተጎሳቀሉ ፣ግብአት ያልተሟላላቸዉ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት እንቅፋት የፈጠሩ፣ በሂደትም በተማሪዎቻችን የ12ኛ ክፍል አጠቃላይ ውጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የፈጠሩ እና የትምህት ጥራት ያጓደሉ ችግሮችን ቀርፈን በአጭር ጊዜ 6ኛ እና 8ኛ ክፍልን ጨምሮ በ2ኛ ደረጃ የተማሪዎቻችን አበረታች ውጤት አስመዝግበናል ።
የተሻሻሉ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መፃህፍትና ቤተ ሙከራ፣ የህፃናት ማረፊያ፣ ፅዱና አረንጓዴ ቅጥር ጊቢ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ያላቸውን የትምህርት መሰረተ ልማቶች እያስፋፋን እንገኛለን።
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የከተማዋን የትምህርት ተደራሽነት ለማረጋገጥ እና የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል በያዘው እቅድ ባለፉት አምስት ዓመታት 110 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል። በነባር ትምህርት ቤቶች ውስጥ የማስፋፊያ ስራ በመስራትም ከ30 ሺህ በላይ የመማሪያ ክፍሎችን መገንባት እና 334 መመገቢያ አዳራሾች፣ 206 ቤተ ሙከራ እና ቤተመጽሐፍት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መገንባት ችለናል። እንዲሁም ትምህርት ቤቶች አካታች፣ ምቹ፣ ውብና ንፁህ፣ የደህንነትና የውበት ደረጃን የጠበቀ አጥር መገንባት ተችሏል፡፡
የተቀናጀና የተናበበ እቅድ በመንደፍ የስራ ባህላችንን በማሻሻል በሰራናቸው ስራዎች ውጤታማ ሆነናል።
በዚህ ስራ በመሳተፍ ትውልዱ ላይ መልካም ዘርን የዘራችሁትን ሁሉ ላመሰግን እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነቾ አቤቤ
ከሁሉም በላይ የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን !
በ2017 በጀት ዓመት ከ5.2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የገነባናቸዉን 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች መርቀን ለአገልግልሎት ክፍት አድርገናል።
ፕሮጀክቶቹ በጥራትና ደረጃቸዉን ጠብቀዉ የተሰሩ 14 አዳዲስ ትምህር ትቤቶች፣ 64 ነባር ትምህርት ቤቶች ላይ በማስፋፋያ ስራ የተገነቡ 1,655 የመማሪያ ክፍሎች፣ የአይሲቲ ክፍሎች፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የመመገቢያ አዳራሾች፣ ቤተ መፅሀፍቶች፣ የስፖርት ሜዳዎች፣ ምድረ ጊቢዎችን ፅዱና ዉብ የማድረግ ስራ፣ የመጸዳጃ ቤቶች እና የውሃ አገልግሎትን ጨምሮ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እና መምህራን ምቹ የማድረግ ስራዎችን ያካተቱ ናቸው።
ትውልድን ለማነጽ በተሰራው ስራ አብራችሁን የሰራችሁትን ሁሉ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም እያመሰገንኩ፣ እነዚህ ትምህርት ቤቶች የእናንተ እና የልጆቻችሁ ሀብት በመሆናቸው እንድትንከባከቧቸው አደራ እላለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከዊንጌት አደባባይ -ጎጃም በር የመንገድ መብራት ጥገና ስራ ተከናወነ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ወደ ስራ ከገባበት ኃላፊነትና ተግባር ውስጥ አንዱ የሆነውን የመንገድ መብራት ጥገና ስራ ርክክብ ባደረገባቸው ዋና መንገዶች ላይ አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ጨለማ የሆኑ መንገዶችን በጥናት በመለየትና አስፈላጊውን ጥገና ለማከናወን የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት በማድረግ መብራቶቹን የማብራት ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ጥገና ከተደገላቸው አካባቢዎች ውስጥ ከጎጃም በር- ዊንጌት የሚያዘልቀው የቀለበት መንገድ አንዱ ሲሆን ይህ መንገድ ከፍተኛ የትራፊክ እንቅስቃሴ ያለበት፣ በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች ቀለበት መንገዱን ተሻግረው በተለያየ አቅጣጫ የእግር ጉዞ የሚያደርጉበትና በአካባቢው የጉለሌ እፅዋት ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች ተቋማት የሚገኙበት መሆኑ ይታወቃል፡፡
የመንገድ መብራቱ መሰራቱ በአካባቢው የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ቀድሞ ለመከላከል፤ ህብረተሰቡ በሰላም እንዲንቀሳቀስና የህብረተሰቡንም ደህንነት ምንጊዜም ከማስጠበቅ አኳያ ቀንና ማታ ለሚሰራው የከተማው የፀጥታ አካል የአካባቢውን ልማትና ሰላም ከመጠበቅ አኳያ ምሽቱን ያለምንም ስጋት እንዲንቀሳቀስ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ በመንገዱ ተቀብሮ የነበረው ኬብል ተደጋጋሚ ስርቆት ተፈፅሞበት አገልግሎት መስጠት ባለመቻሉ በምሰሶዎች አናት ላይ መስመሮቹን በአዲስ በመዘርጋት፤ በመንገዱ ውስጥ ከፍተኛ የእግረኞች እንቅስቃሴ በሚያደርጉበትና ለትራፊክ አደጋ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ቦታዎችን በመለየትና አስፈላጊውን ጥገና በማከናወን ወደ አገልግሎት ማስገባት ችሏል፡፡
የሚፈፀም ስርቆትን ከመከላከልና ከመጠበቅ አኳያ ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት፣ የክ/ከተማና ወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል፡፡
በመጨረሻም በመብራት መሰረተ-ልማት ላይ ህገወጥ ተግባር ሲፈፅም ያገኘ ማንኛውም ሰው በአካል በቅርብ ለሚገኝ የፀጥታ አካል እንዲሁም በባለስልጣኑ ነፃ የስልክ መስመር 9101 በመደወል ጥቆማ በመስጠት የጋራ ንብረት የሆነውን የመንገድ መብራት መሰረተ-ልማት በጋራ እንጠበቅ ሲል መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የ2017 አ.ም በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ምዘና በዛሬዉ እለት ተካሄዷል።
የጽ/ቤቱ የ2017 አ.ም በጀት አመት እቅድ የስራ ክንውን የተመዘነው በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና ስትራቴጂክ አመራሮች እንዲሁም የተቋሙ ዳይሬክተሮች በተገኙበት ከከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ተቋማት በተውጣጡ መዛኝ አካላት ነው።
በምዘናው ጽ/ቤቱ በአዋጅ በተሰጠው ተልእኮ፣ተግባርና ሃላፊነት መሠረት በእቅድ የተያዙና የተከናወኑ ተግባራትን ፤ ከአገልግሎት አሰጣጥ ፣ስራዎችን በስታንዳርድ ከመፈፀም፣ምቹ የስራ ከባቢን ከመፍጠር ፣የሰው ተኮር ስራዎች ከመተግበር፣ስራዎች በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ ከማድረግ አንፃር፣የ90 ቀናት የንቅናቄ ስራዎች እና በርካታ ዝርዝር ተግባራትን በዉይይት ቀርቦ የሰነድና የአካል ምልከታ ተደርጎባቸዋል።
የመዛኝ ቡድኑ አባላት በተቋሙ የተከናወኑ ጠንካራና አበረታች ስራዎች በበጀት አመቱ መመዝገባቸውን ገልፀው በስራ ሂደቱ የታዩ አንዳንድ መስተካከል ያለባቸዉን ቦታዎች አመልክተዉ በተከናወነው ስራዎች ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።
በዚሁ የምዘና መድረክ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በተቋሙ የተከናወኑ ተግባራት በተለይም ተቋሙ በተልእኮው ከተቀመጠው አገልግሎቶች በዘለለ ስራዎችን የቁጥር መለኪያን ከማሳካት ባለፈና ስትራቴጂካሊ የአመራር ሰጭነት ሚናን በሚገባ በመወጣት የነዋሪዎችን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ፍላጎት የማርካት ጉዳይን ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በበጀት አመቱ ውጤታማ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።
አክለዉም በጽ/ቤቱ በበጀት አመቱ በርካታና ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው የተመዘገበዉ ዉጤት በይበልጥ ለቀጣይ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የስማርት ሲቲ ሙሉ ትግበራ የሚያነሳሳ ወሳኝ ምእራፍ ነው ሲሉም አስገንዝበዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ በማጠቃለያቸውም ምዘናው ጽ/ቤቱ በቀጣይ በጀት አመት ፅዱ፣ ውብ፣ ወንዞቿ ከብክለት የፀዱ፣ ሙሉ በሙሉ ብርሃን የነገሰባት ከተማ መዲናችንን ለማድረግ እና የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት የቀነሰባት ውብና፣ ዘመናዊ ከተማ ለማድረግ በተቋሙ የተያዘውን እቅድ ወደ ሙሉ ትግበራ ለማስገባት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ነዉ ብለዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በክረምት ለ5 የአቅመ ደካማና የሀገር ባለውለታ ለሆኑ አካላት የቤት እድሳት አስጀመረ
ሀምሌ10/2017 ዓ.ም
*****************
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎፍቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ጋር በመተባበር የ90 ቀን እቅድ የክረምት በጎ ፍቃድ ልዩ ልዩ ተግባራት አንዱ አካል የሆነውን የአቅመ ደካማ ቤት ዕድሳት መርሃ ግብር ዛሬ በይፋ አስጀምሯል፡፡
በዕለቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደሲሳን ጨምሮ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።
በበጎ ፈቃድ መርሀግብሩ ላይም 5 ቤቶች እድሳት የሚደረግላቸው ሲሆን ሙሉ ወጪዬቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማስተባበርና በማሳተፍ የሚሸፍን መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ተጠሪ በሆኑ ተቋማት ለሚሰጡ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች የሚከተሉትን አድራሻዎች ይጠቀሙ!
1.የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ
ዋና ቢሮ አድራሻ፡- በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ፒያሳ እሪ በከንቱ ዮናታን ቢቲ ህንጻ ከ7ኛ ፎቅ ጀምሮ
ነጻ የስልክ መስመር - 6199
ቴሌግራም፡- https://t.me/CGAACMA
ዩቲዩብ ፡- https://www.youtube.com/@aacma-bu4zt
ዌብሳይት፡- www.aacma.gov.et
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100064800963883
2.የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
ዋና ቢሮ አድራሻ :- አዲሱ ገበያ ቱኒዝያ መንገድ ሸገር መናፈሻ ግቢ ውስጥ
ነጻ የስልክ መስመር - 7533
ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et
የፌስቡክ (facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686
ቴሌግራም (telegram): https://t.me/addisvaitalpress
ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320
3. የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
ዋና ቢሮ አድራሻ ;-አራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 10 አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊትለፊት
ነጻ የስልክ መስመር :- 939
fdrmc1926@addisfire.gov.et
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/AADRMC1
4. የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን
➠ ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AAESA.Official
➠ ኢንስታግራም፦ Instagram as @esaa_2017. https://www.instagram.com/esaa_2017
➠ ቴሌግራም፡ https://t.me/AACA_ESAA
➠ ዩቲዩብ፡-https://www.youtube.com/@AACA-ESAA
➠ ቲክ ቶክ፡- https://www.tiktok.com/@aaca.esaa
➠ ሊንክድ ኢን፡- https://www.linkedin.com/.../esaa-electric-service.../
➠ ለማንኛውም ጥቆማ ፡- ነፃ የስልክ ቁጥር 9101 ወይም በቀጥታ ስልክ መስመር +251-11-1127775
➠ በአካል፡- አራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ዋስትና የንግድ ማዕከል 15ኛ እና 17 ኛ ወለል ላይ እንገኛለን፤
ስ.ቁ 0111127775
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ባለፉት ሁለት እና ሶስት አመታት እየተከልናቸው ያሉ ችግኞች በአብዛኞቹ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የከተማችን የጎርፍ ተጋላጭነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ናቸው።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በተጠናቀቀው የ2017 በጀት አመት 233 ቢሊዬን ብር ገቢ በመሰብሰብ የከተማችንን የልማት ስራዎች በላቀ ደረጃ እንድንፈፅም ላስቻሉን የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች የእዉቅና እና የምስጋና መርሃግብር አካሄደናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት አመራሮች፣ ሠራተኞች እና ባለድርሻ አካላት የዛሬው እለት የ7ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ማኖር መርሐግብር በምስል ሲቃኝ:-
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
