uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Відкрити в Telegram

Показати більше
1 474
Підписники
Немає даних24 години
-37 днів
-2130 днів
Архів дописів
የየካ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽህፈት ቤት በ4ኛ ዙር የ90 ቀናት ዕቅድ ትግበራ ወረዳ 01 እና 04ን በፅዳትና ውበት ሙሉ በሙሉ ሞዴል በማድረግ አስመረቀ ፅህፈት ቤቱ በ4ተኛ ዙር የ90 ቀናት እቅድ ትግበራ ወረዳ አንድ እና አራትን በፅዳትና ውበት ሙሉ በሙሉ ሞዴል በማድረግ በዛሬው እለት አስመርቆ ለነዋሪዎች አስረክቧል። በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አማካሪ አቶ በላይ ታደሰ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳሪክተር አቶ ሳዲቅ ሽኩሪ፣የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ፣የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጫሊ ቤኛ፣የየካ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ከፋያለው ተሾመ፣የሁለቱም ወረዳ የስራ ሀላፊዎች፣የሀገር መከላከያ አባላት፣የፅዳት አንባሳደሮች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አማካሪ አቶ በላይ ታደሰ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ ለማድረግ ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በመግለፅ የካ ክፍለ ከተማ ለነዋሪዎች ምቹ እና ፅዱ አከባቢ በመፍጠር ሒደት ውስጥ ቀዳሚውን ቦታ እንደሚይዝ አንስተው ይህ እንዲሳካ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጫሊ ቤኛ በበኩላቸው በ3ኛ እና 4ኛ ዙር 90 ቀናት እቅድ ትግበራ ካሉት 12 ወረዳዎች 6 ወረዳዎችን በክፍለ ከተማው ስር ካሉ 407 ብሎኮት 334ቱን ሙሉ ለሙሉ ሞዴል ማድረግ መቻሉን በማንሳት በቀጣይም የቀሩ ብሎኮችን ሞዴል ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እና ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀው የአከባቢው ነዋሪዎች ፅዳቱን በማስቀጠል የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። በ2016 በጀት አመት በ4ኛ ዙር የ90 ቀናት እቅድ ትግበራ በወረዳ አንድ 38 ብሎኮች እና 18 የመንግስት እና የግል ተቋማት እንዲሁም በወረዳ አራት 31 ብሎኮች በፅዳት እና ውበት ሙሉ ለሙሉ ሞዴል በማድረግ ተመርቀው ለነዋሪዎች የማስረከብ ስነ ስርአት ተካሂዷል። በመርሀ ግብሩ ላይ የመልሶ መጠቀም አውደ ርዕይ የተካሄደ ሲሆን ወረዳዎችን ሞዴል በማድረግ ሒደት ውስጥ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም እውቅና ተሰጥቷል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ህብረተሰቡ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ አጋላጭ ነገሮች እንዲጠነቀቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መልእክት አስተላልፏል ። የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአቃቂ
+7
ህብረተሰቡ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ አጋላጭ ነገሮች እንዲጠነቀቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መልእክት አስተላልፏል ። የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከትንሳኤ በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንዳይከሰቱ ህብረተሰቡ አስፈላጊ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በመንገድ አደባባዮችና ጎዳናዎች ላይ የቅድመ ጥንቃቄ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ አካሂዷል። ከበዓሉ ጋር በተገናኘ ምግብ በማብሰል እና በሌሎች ክዋኔዎች የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባና አደጋ ሲያጋጥምም ለተቋሙ ፈጥኖ ማሳወቅ እንደሚገባም ተገልጿል ። ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከክ/ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤትና ከሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑም የተቋሙ ባለሙያዎች ተናግረዋል። እሳትና ድንገተኛ አደጋ ቢያጋጥም በነጻ የስልክ መስመር 939፤ በቀጥታ የስልክ መስመሮች 011 155 53 00 ወይም በ 011-4-34-00-96 ደውሎ ማሳወቅ እንደሚቻልም ተገልጿል ። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+4

መጪዉ የትንሣኤ በዓል በተሟላ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በድምቀት እንዲከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተድርጎ ወደ ስራ መገባቱን የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ በመላ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የትንሳኤ በዓል በተሟላ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እንዲከበር ለማስቻል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ተድርጎ ወደ ስራ መገባቱን የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከ3ት ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር በዛሬው እለት ሚያዝያ 24 ቀን 2016 አ.ም በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እንደገለፁት ጽ/ቤቱ ለትንሳኤ በአል የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች በተቻለ መጠን በተሟላ ሁኔታ እንዲቀርብ በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን: በኤሌክትሪክ አገልግሎነ እና : በጽዳት አስተዳደር እጀንሲ በኩል ከማእከል ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞችና እስከ ወረዳዎች ድረስ ባለው መዋቅር ተገቢው ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ ህብረተሰቡ ለመጪው የትንሣኤ በአል ከማንኛውም አደጋ ተጠብቆ በአሉን በሰላም እንዲያከብር አስፈላጊውን የቅድመ አደጋ መከላከልና የግንዛቤ ስራዎች መከናወኑን አስረድተዋል:: ህብረተሰቡም በአሉን ሲያከብር ራሱንና አካባቢውን ከእሳት እና መሰል አደጋዎች እንዲጠብቅ አሳስበው አደጋዎች ካጋጠሙ በአፋጣኝ አደጋውን ለመቆጣጠር ከቅርንጫፍ ጣቢያዎች ጀምሮ እስከ ማእከል ድረስ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መደረጉን አስገንዝበዋል። የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ እንደገለፁት መጪው በዓል ፅዱና ውብ በሆነች ከተማ እንዲከበር አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ መከናወኑን ገልጸው በዓሉ ሰፊ የሆነ የእንስሳት እርድ የሚከናውንበት እንደመሆኑ የእርድ ተረፈ ምርቱን በተገቢው በማስወገድ የከተማውን ጽዳት በዘላቂነት መጠበቅ እንደሚገባ ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ገበየሁ ሊካሳ በበኩላቸው የትንሣኤ በዓል ከዋዜማው ጀምሮ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ጥቅም ላይ የሚውልበት እንደመሆኑ ተቋሙ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀዉ የሚስተዋለዉን የሃይል መቆራረጥ ለመቀነስ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ መከናወኑንም አውስተዋል። አክለውም ህብረተሰቡ የሃይል አጠቃቀም ላይ ሁሉንም በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የምግብ ማብሰያና ሌሎች ቁሳቁሶች በተመሳሳይ ስአት በአንድ ጊዜ ጥቅም እንዲሰጥ ማድረግ አደጋ የሚፈጥር በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content

ማሳሰቢያ⚠️ ኤሌክትሪክ ሲቋረጥ መልሶ ለማገናኘት፣ ለቅድመ መከላከል ጥገናና አስቸኳይ ጥገና እንዲሁም ሌሎች ተቋሙ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች በተቋሙ አሰራር መሰረት ከፍያ መፈጸም ካለብዎ ከህጋዊ ደረሰኝ ውጭ የትኛውንም ያህል ገንዘብ ለማንኛውም አካል መክፈል አይጠበቅብዎትም! መሠል የክፍያ ጥያቄ ከመጣልዎም ህገወጥ መሆኑን በመገንዘብ ፈጽሞ ተባባሪ አይሁኑ፤ መሰል እኩይ ተግባር ሲያጋጥምዎ በ905 ነፃ የጥሪ ማዕከል፤ በአቅራቢያ ለሚገኝ ቢሮዋችን ወይም ለሚመለከታቸው የህግ አስከባሪ አካላት ጥቆማ በማድረግ ይተባበሩ! በተጨማሪ የአገልግሎታችን ደንበኛ ከሆኑ አምስት ዓመት ያለፋቸው ደንበኞች በሙሉ እስከ ሰኔ 30 ድረስ በየአገልግሎት መስጫ ማእከሎች በአካል በመቅረብ የውል እድሳት እያደረጉ ቢሆንም፤ ለወል እድሳቱ ተቋሙ ምንም አይነት ገንዘብ የማያስከፍል መሆኑንም እንገልጻለን፡፡ ውድ ደንበኞቻችን ተቋማችን ደንበኛ ተኮር የሆነ አገልግሎት በመስጠት እርካታዎን ከፍ ለማድረግ አልሞ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፤ በዚህ ሂደት ውስጥ አብዛኛው ሰራተኛ በቅንነትና በታማንኝት እያገለገለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ጥቂት የስነ ምግባር ግድፈት ያላቸው ሰራተኞች ከደላሎች ጋር በመመሳጠር ህብረተሰቡን በማደናገርና ገንዘብ በማሰባሰብ የግል ፍላጎታቸውን በህገ ወጥ መንገድ ለማሟላት የሚሯሯጡ እንዳሉም ይስተዋላልና ብልሹ አሰራርን በጋራ እንከላከል፡፡ ለኤሌክትሪክ አገልግሎታችን ጥራትና ፍትሀዊነት የእርስዎን እገዛ እንሻለንና ሀገራዊ ግዴታዎን እንዲወጡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

photo content
+4

ኤጀንሲው "ከተማዬን እወዳታለሁ፤ ፅዳቷን እጠብቃለሁ!" በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ ግንዛቤ ፈጠራ ስራ አካሄደ። የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የፊታችን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ "ከተማዬን እወዳታለሁ፤ ፅዳቷን እጠብቃለሁ!" በሚል መሪ ቃል ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ የሚያመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ እና የእርድ ተረፈ ምርት በአግባቡ እንዲያስወጎድ እንዲሁም በከተማዋ ፅዳት ዙሪያ የሚከሰት የደንብ ጥሰትን ለመከላከል የሚያስችል በሁሉም ክ/ከተሞች በመዘዋወር የጎዳና ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል። ከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ ፅዳት ዙሪያ የሚከሰት የደንብ ጥሰትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣ ደንብ ቁጥር 150/2015 መሠረት ማንኛውም ሰው በቤቱ ወይም በመንገድ ላይ የሚያመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ ካልያዘና በተገቢው መንገድ ካላስወገድ በህግ እንደሚያስቀጣው ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል። የመኖሪያ አካባቢውን በንፅህና ያልጠበቀ 500 ብር ያስቀጣል። የድርጅቱን ንፅህና ያልጠበቀ 3000 ብር ያስቀጣል።። ከኢንዱሰትሪ የሚመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ ያልያዘ 10,000 ብር ያስቀጣል። ከጤና ተቋማት የሚመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ ያልያዘ 15,000 ብር ያስቀጣል። በከተማዋ ፅዳት ዙሪያ የሚከሰት ህገወጥነትን በጋራ እንከላከል! ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ኤፍኤም 97.1 ጋር በመተባበር የከተማውን ጽዳትና የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎች ላይ ከማህበረሰቡ በቀረቡ ግልጽነት የሚፈልጉ ጥያቄዎችና ጥቆማዎች ዙሪያ የተሰጡ ማብራሪያና ምላሾችን በፌስቡክ ገፃችን እንዲከታተሉት እነሆ ብለናል :: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የልዑካን ቡድን አባላት በአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መ/ቤት ተገኝተዉ የልምድ ልዉዉጥ አካሄዱ ። የልዑካን ቡድኑ ከከተማዉ
+2
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የልዑካን ቡድን አባላት በአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መ/ቤት ተገኝተዉ የልምድ ልዉዉጥ አካሄዱ ። የልዑካን ቡድኑ ከከተማዉ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የተወጣጡ የወረዳ አመራሮች ሲሆኑ አባላቱ በድሬዳዋ ሊያጋጥሙ የሚችሉ እሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አደረጃጀትና አሰራርን የተመለከተ የልምድ ልዉዉጥ ዛሬ ሚያዚያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም አድርገዋል። የልዑካን ቡድኑ አባላት አንጋፋ ከሆነዉ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራሮች ከተደረገላቸዉ ገለጻ ሰፊ ልምድ እንዳገኙ ጠቅሰዉ በቀጣይ በሚኖሩ ግንኙነቶች በትብብር እንደሚሰሩ አስታዉቀዋል። በመርሀ ግብሩ ላይ የኮሚሽን መ/ቤቱን አደረጃጀትና አሰራር ዙሪያ በኮሚሽኑ አመራሮችና ባለሞያዎች ለልዑካን ቡድኑ አባላት ገለጻ ተደርጎላቸዋል። ለእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት መጪዉ የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ዘርፍ የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች ተገመገሙ። ከቀናት በኋላ የሚከበረዉ የትንሳኤ በዓል ከማዘጋጃ
+5
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት መጪዉ የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ዘርፍ የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች ተገመገሙ። ከቀናት በኋላ የሚከበረዉ የትንሳኤ በዓል ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ጋር በተያየዘ የአገልግሎት መቋረጥና የአደጋ ክስተት እንዳያጋጥም በተጠሪ ተቋማቱ የተደረገ ቅድመ ዝግጅት ዛሬ ሚያዚያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ተገምግሟል። ተጠሪ ተቋማቱ በዓሉን አስመልክቶ ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ጋር ተያይዞ አደጋ እንዳይከሰትና የአገልግሎት መቋረጦች እንዳያጋጥም የጋራ ዕቅድ አዉጥተዉ ወደስራ መግባታቸዉን አብራርተዋል።… See more

ከአንድ ወር በፊት የኮሪደር ልማት ስራ ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አጠቃላይ ግምገማ አድርገን ነበር። ዛሬ እንደገና ከአዲስ አበባ አስተዳደር አመራሮች እና የኮሪደር ልማት ስራ መሪዎች ጋር በመ
+1
ከአንድ ወር በፊት የኮሪደር ልማት ስራ ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አጠቃላይ ግምገማ አድርገን ነበር። ዛሬ እንደገና ከአዲስ አበባ አስተዳደር አመራሮች እና የኮሪደር ልማት ስራ መሪዎች ጋር በመገናኘት በስራዎቻችን ርምጃ ዙሪያ ጥልቀት ያለው ውይይት አድርገናል። እነኚህ ስራዎቻችን የግንባታ ብቻ ጉዳዮች አይደሉም፤ ይልቁንም ከተማችንን ወደ ላቀ ምቹ፣ ንቁ እና ዘላቂ የመኖሪያ ከባቢ የመለወጥ ጥረቶች ናቸው። ሥነውበትን በማሳደግ፣ አረንጓዴነትን በማስፋት ብሎም መሰረተ ልማትን በማሻሻል የህዝባችንን ጤና መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የስራ ዕድሎችንም እየፈጠርን ነው። በጋራ እነዚህ ጥረቶቻችን የአዲስአበባን አጠቃላይ ይዞታ በማላቅ እውነትም ለሁሉም ነዋሪዎቿ ፍላጎቶች የተመቸች ያደርጓታል"። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድከአንድ ወር በፊት የኮሪደር ልማት ስራ ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አጠቃላይ ግምገማ አድርገን ነበር። ዛሬ እንደገና ከአዲስ አበባ አስተዳደር አመራሮች እና የኮሪደር ልማት ስራ መሪዎች ጋር በመገናኘት በስራዎቻችን ርምጃ ዙሪያ ጥልቀት ያለው ውይይት አድርገናል። እነኚህ ስራዎቻችን የግንባታ ብቻ ጉዳዮች አይደሉም፤ ይልቁንም ከተማችንን ወደ ላቀ ምቹ፣ ንቁ እና ዘላቂ የመኖሪያ ከባቢ የመለወጥ ጥረቶች ናቸው። ሥነውበትን በማሳደግ፣ አረንጓዴነትን በማስፋት ብሎም መሰረተ ልማትን በማሻሻል የህዝባችንን ጤና መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የስራ ዕድሎችንም እየፈጠርን ነው። በጋራ እነዚህ ጥረቶቻችን የአዲስአበባን አጠቃላይ ይዞታ በማላቅ እውነትም ለሁሉም ነዋሪዎቿ ፍላጎቶች የተመቸች ያደርጓታል"። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በመረጃ ማዕከሉ ላይ በገጠመ ድንገተኛ የቴክኒክ ብልሽት ሲስተማችን የተቋረጠ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል። በመሆኑም አሁን ጥገናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ አ
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በመረጃ ማዕከሉ ላይ በገጠመ ድንገተኛ የቴክኒክ ብልሽት ሲስተማችን የተቋረጠ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል። በመሆኑም አሁን ጥገናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ አገልግሎቱ የተጀመረ መሆኑን እየገለጸ ተገልጋዩ በትዕግስት በመጠበቁ ከልብ ማመስገኑን ይገልጻል:: Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በመረጃ ማዕከሉ ላይ በገጠመ ድንገተኛ የቴክኒክ ብልሽት ሲስተም መቋረጡን አስታውቆ የኤጀንሲው የቴክኖሎጂ ቡድን ከከተማው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በመረጃ ማዕከሉ ላይ በገጠመ ድንገተኛ የቴክኒክ ብልሽት ሲስተም መቋረጡን አስታውቆ የኤጀንሲው የቴክኖሎጂ ቡድን ከከተማው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በጋራ ጥገና እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል:: በመሆኑም ኤጀንሲው በአጭር ሰዓታት ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጥገና እንደሚጠናቀቅ በመግለፅ በአገልግሎቱ መቋረጥ ተገልጋዩን ይቅርታ እንጠይቃለን ብሏል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!

በኮሪደር ልማት ምክንያት የተነሳውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕንጻ የመልሶ ግንባታ ስራን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ እና
+8
በኮሪደር ልማት ምክንያት የተነሳውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕንጻ የመልሶ ግንባታ ስራን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ እና ሌሎች የሀይማኖቱ አባቶች በተገኙበት ዛሬ አስጀምረናል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የከተማ ኘላን እና ልማት እንዲጠበቅ፣ ከተማችን እንድትለማ፣ እንድትዘምን እና የተሻለ ዲዛይን እንዲተገበር በርካታ ትብብር በማድረግ ላይ የምትገኝ ሲሆን ይህ ዛሬ መልሶ ግንባታ ስራውን ያስጀመርነው ህንጻ የዚህ አንዱ ማሳያ ነው። ይህ ህንጻ ባለ 4 ወለል የነበረ ሲሆን አዲሱ ግንባታ ለፓርኪንግ ግልጋሎት የሚውል አንድ ቤዝመንት የሚጨምር ዘመናዊ ባለ አራት ወለል ህንጻ ሆኖ ከአካባቢው ልማት፣ ፕላን፣ በዙሪያው ካሉ ሌሎች ቅርሶች እንዲሁም ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ጋር የሚናበብ ነው። ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቅቀን ለቤተክርሰቲያኗ የምናስረክብ ይሆናል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች የልማት ኮሪደር ስራውን በመደገፍ ከጎናችን ስለቆሙ ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአስተዳደራችንን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቅቀናል:: ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከፈተናዎቻችን ባሻገር አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ ለነዋሪዎችዋ ምቹ እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻ ዓለም አቀፍ
+3
የአስተዳደራችንን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቅቀናል:: ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከፈተናዎቻችን ባሻገር አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ ለነዋሪዎችዋ ምቹ እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ የሰነቅነውን ራዕይ ዕውን ማድረግ ያስቻሉ ፈጠራ የታከለባቸው አዳዲስ አሰራሮችን በመከተል ፣ ጠንካራ የስራ ባህል በመገንባት እና የአመራር ቁርጠኝነትን እና ቅንጅትን በማረጋገጥ የጀመርናቸው ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ጀምረን በመጨረስ ለህዝባችን አገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ አድርገናል:: የነዋሪውን የኑሮ ጫና አቅልለው ተስፋ ያለመለሙ የሰው ተኮር ስራዎቻችንም የበርካቶችን ሸክም ያቀለሉ የአቅመ ደካሞችንና የሀገር ባለውለታዎችን እምባ አብሰው ማህበራዊ ፍትህን ያነገሱ የመሬት ዲጂታላይዜሽን እና የገቢ አሰባሰብ ስራችን ውጤት ካገኘንባቸው ስራዎች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው:: ከተማችንን ውብ፣ ጽዱ እና ለመኖር ምቹ ለማድረግ የጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራችን ለነዋሪዎቻችን መልካም እድል የፈጠረ ሲሆን ግምገማችን በቀሪ ወራት ጥንካሬዎቻችንን በማጽናት ድክመቶቻችን ከነመንስዔዎቻቸው ተነቅሰው እንዲወጡ እና ለላቀ ውጤታማ ስራ የሚያተጉ እንዲሁም የነዋሪዎች ቅሬታ ምንጭ የሆኑትን ቀልጣፋና ከተማዋን የሚመጥን የአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ሌብነት እና ጉቦኝነት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የምንሰራ ይሆናል:: እየፈጠርን ፈጥነን በመተግበር ቃል በገባነው ልክ አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እኔ የአንድ ወር ደሞዜን አስተዋፅኦ በማድረግ “ፅዱ ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴሌቶን ላይ ተሳትፌያለሁ :: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮችም የ"ፅዱ ጎዳና -ኑሮ በጤና" ንቅናቄ በፍጥነት ጥሪውን
+3
እኔ የአንድ ወር ደሞዜን አስተዋፅኦ በማድረግ “ፅዱ ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴሌቶን ላይ ተሳትፌያለሁ :: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮችም የ"ፅዱ ጎዳና -ኑሮ በጤና" ንቅናቄ በፍጥነት ጥሪውን ስለተቀላቀላችሁ በከተማ አስተዳደሩ ስም እያመሰገንኩ ያልተቀላቀላችሁ አመራሮችም ካምፔኑን እንድትቀላቀሉ ጥሪ አስተላልፋለሁ። ለአላማው መሳካትም ሁሉም ሰው ያገባኛል በሚል በንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 የ“ጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና” ንቅናቄን እንዲቀላቀል ጥሪ አቀርባለሁ:: ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"ዛሬ የ”ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” የዲጂታል ቴሌቶን ተሳትፎ ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ። ለጋራ ጥቅም በጋራ ስንቆም ድንቅ እንሆናለን። እስከአሁን በ #ጽዱኢትዮጵያ ቴሌቶኑ ያልተሳተፋችሁ
"ዛሬ የ”ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” የዲጂታል ቴሌቶን ተሳትፎ ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ። ለጋራ ጥቅም በጋራ ስንቆም ድንቅ እንሆናለን። እስከአሁን በ #ጽዱኢትዮጵያ ቴሌቶኑ ያልተሳተፋችሁ ዛሬ በቀሪዎቹ ሰዓታት፣ በመጪዎቹ ቀናት እና ሳምንታትም እንድትቀላቀሉ አበረታታችኋለሁ። በጋራ ትርጉም ያለው በጎ ተፅዕኖ መፍጠር እንችላለን"። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በገበታ ለሸገር እንዲሁም በተለያዩ የከተማችን የልማት ስራዎች ሃሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ፕሮጀክቶቹን ወርዶ በመምራት ከተማችንን እንደ ስሟ ውብ እና ፅዱ
+1
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በገበታ ለሸገር እንዲሁም በተለያዩ የከተማችን የልማት ስራዎች ሃሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ፕሮጀክቶቹን ወርዶ በመምራት ከተማችንን እንደ ስሟ ውብ እና ፅዱ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ከተማችንን ውብ፣ ፅዱና ለነዋርዎቿ ምቹ የማድረግ ራዕያቸው አካል የሆነ “ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” የሚል አዲስ ሃሳብ የአፍሪካዊያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ጀምረዋል። ይህ አዲስ ተግባር ነዋሪዎቻችንን በሚያሳፍር መልኩ በየመንገዱ ከመፀዳዳት ይልቅ፣ የከተማ ውበትን በሚጨምር መልኩ፣ ጤናማ አካባቢንም ለመፍጠር የሚያስችል ሲሆን ለነዋርዎቿ ምቹ ከተማ ለመፍጠር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በጀመሩት በዚህ ታላቅ ተግባር ላይ ከማንም በላይ መላው አመራራችን እና ተጠቃሚ የሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ማስተላለፍ እወዳለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

photo content
+6